ሐራ ጥቃ የሚባሉ ሰዎች ቀዳሚሁ ቃል ሥጋ ኾነ /በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም ሥጋ ኾነ/ የሚለውን ብቻ ይዘው አካላዊ ቃል ተለውጦ ሥጋ ኾኖ በማህፀነ ድንግል ማርያም አደረ ብለው ያምናሉ። የቃና ዘገሊላው ውኃ ተለውጦ ወይን እንደኾነ ፣ የሎጥ ሚስት ተለውጣ የጨው ሃውልት እንደኾነች ቃልም እንዲሁ ተለውጦ ሥጋ ኾነ አሉ። ይህ ግን የምንፍቅና ትምህርት ነው።
ሐራ ጥቃ በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም ሥጋ ኾነ የሚለውን ብቻ ሲያዩ ወኃደረ ላዕሌለ /በእኛም አደረ/ ያለውን አላዩም። ልብ በሉ! ወንጌላዊው ዮሐንስ ምዕራፍ 1 ቁጥር 1
በመጀመሪያ ቃል ነበረ
ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ
ቃልም እግዚአብሔር ነበረ
“ቃልም ሥጋ ኾነ”
ወንጌላዊው “ቃልም ሥጋ ኾነ” አለን እንጂ “ቃልም ወደ ሥጋ ተለወጠ” አላለንም። ቤተክርስቲያናችንም ይህንኑ አምና ቃል በተዋህዶ ከእመቤታችን ሥጋን ነሳ በድንግል ማርያም ማህጸንም አደረ ብላ ወንጌልን ታስተምራለች።
ንስጥሮስም ቀዳሚሁ ቃል /በመጀመሪያ ቃል ነበረ/ የሚለውን ሳይመለከት ወኃደረ ላዕሌነ /በእኛም አደረ/ የሚለውን ብቻ አየና ኃደረ በብእሲ /ከሴት ዘንድ አደረ/ ብሎ እመቤታችን ወላዲተ አምላክ አይደለችም አለ። ፊደል ይገላል እንዲሉ ፊደሉን በቁሙ ብቻ ካየነው ቆመን እንቀራለን። ቆመን ብንቀርስ በተሻለ ነበር ከዚህ የከፋው እንዳንነሳ ኾነን መውደቃችን ነው። ብዙዎች ፊደል ብቻ አይተው ወድቀዋልና። እለ አርዮስ እለ መቅደንዮስ እለ ንስጥሮስ እለ መርቅያን …… እነዚህ ኹሉ የቆመውን ፊደል አይተው ቆመው የቀሩ ናቸው።
በከመ ይቤ ቅዱስ ጳውሎስ “እስመ መፅሐፍ ይቀትል ወመንፈስ ያሐዩ” ፪ኛ ቆሮንጦስ [፫: ፯] እንዲል ፊደል እንደ አርዮስ ፣ እንደ ንስጥሮስ እንደ ሐራ ጥቃ ይገላል፤ መንፈስ ቅዱስም ሕይወትን ይሰጣል።
Visit this Blog! http://
·
·
You, Hiwi Mulatu, Kidest Lema, Sara Wondemagegnehuand 37 others like
this.
·
Zuriyash Aduna tmsegene
May
19 at 9:41am · · 1
Weldegebriel Adhanom egzabhier
kenante gara yhun endih adrgo yabzan!
May
19 at 4:32pm · · 1
Ejigayehu
Gebre tesga ybzalchu
May
20 at 11:18am · · 1
·
No comments:
Post a Comment