Monday, 20 August 2012

አገልግሎት!

አምራለሁ ብላ ተኩላ አይኗን አጠፋችው ቸኩላ!" ብሎ ሲተርባት እሷም ቀበል አድርጋመከራው ያላለቀለት በሬ ቆዳው ለነጋሪት ይጠፈራልብላ አፉን አስያዛቸው። ከእኛ ሰፈር ሁለት ፍቅረኛሞች ከሚጎሻሸሙበት የቅኔ አዝመራ በመነሳት ይህ ጽሁፍ ተጀመረ።

የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና የምነቅፍብህ ነገር አለኝ!” ራዕይ 2:4
አንድ ወዳጄ የልብ የልቡን ሊያወጋኝ ነበር እንዲህ ብሎ ያጫወተኝ፤ እኔም የልብ የልቤን ስለነገረኝ የልብ የልቡን ሰማሁት፤
እህህህ ……. አያያያያያ…..
እያለ መጣና ንግግሩን ቀጠለ፤ አገልግሎት ቀላል አይደለችም ለካ ጃል! ታንገዳግዳለች ለካ! አለ እራሱን እያንገዳገደ። ኧረ እንዲያውም ታጎብጣለች አለና እራሱ እንደ መጉበጥ አለ፤ ሆዴ በጀርባዬ ቢሆን ገፍቶ ገደል በጣለኝ ነበር ሲል አነጋገሩ አሳቀኝ። ይህ ወዳጄ ወትረ ነገረ ስራው ሁሉ ያስቃል፤ ቀልድ አሳምሮ ስለሚችልበት በንግግሩ ሁሌ እንደሳቅን ነው፤ ካሳቀን በኋላ ወዲያው ቁም ነገር ጣል ያደርጋል፤ ዛሬም እንደለመደው ትንሽ ቀልዶቹን ከለቀቀ በኋላ ወዳጄ የልቡን ቀጠለ፤

እኔ የምልህ እኔ ብቻ ነኝ እንዲህ የሚሰማኝ ወይስ ሁላችሁም ይሰማችኋል? ለምን? እንዴት? እያለ ጥያቄውን አንጎደጎደው። የልቡን ለሚነግርህ ልብህን ስጠው! የሚለውን አባባል ለመጠቀም ልቤን ሰጥቼው ሰማሁት። ወዳጄ ይህ በአንተ የተጀመረ አይደለም፤ ሁሉም የሚሰማው ነውና ብዙ ራስህን አትረብሽ ብዬ ለማረጋጋትም ሞከርኩ። 


መኑ ይኅድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ? 
በእርግጥ አገልግሎት ታንገዳግዳለች፤ እንደ ወዳጄ እኔም እየተንገዳገድኩ እንዳላሳያችሁ ለጊዜው መተያየት አንችልም! የሆነው ይሁንና የፈለገ ብንንገዳገድ የት እንሄዳለን? መኑ ይኅድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ? ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? ርሃብ ነውን? ስደት ነውን? ግርፋት ነውን? እያለ ታላቁ ሐዋርያ የደረሰበትን ሁሉ እያነሳ ያስብና ይህ ሁሉ ግን ከክርስቶስ ፍቅር፣ ከአገልግሎት ፍቅር እንደማይለየው ይነግረናል።እናቱ የሞተችበትና ውሀ ልትቀዳ የወረደችበት እኩል ያለቅሳሉእንዲል እኛ ይህን ያህል ባንፈተንም እንደ ሐዋርያው የተፈተነ ያህል እንሆናለን።እንስራዋን ጥላ ወንዝ ወረደችአሉ፤ አንዘንጋ ይህ እኮ መንፈሳዊ አገልግሎት ነው! ታዲያ እንዴት ያለ ፈተና አገልግሎትን እንጠብቃለን? “የሰይጣንን አመጣት የማያውቅ አይመንኩስእንዲል አገልግሎትን ያልተረዳም እንዲሁ ነው። 


ብልጥ የሆነ ሰው ግን በዚህ መረበሽ የለበትም።ለላም ቀንዷ አይከብዳትምይባላል እኮ ሰዎች! ኧረ አይክበደን። እስቲ እራሳችንን እንጠይቅ፤ 

ከአገልግሎት ፍቅር የሚለየን ማን ነው?

ይህ መልስ የሌለው ጥያቄ ነው። በቃ መልስ የለውማ። ለምን ታስባላችሁ? አልኳችሁ እኮ መልስ የለውም። ከአገልግሎት ፍቅር የሚለየን ማንም የለማ። 



ማን ነው ደስ ደስ እያለው አንዳች ሳይፈተን ያገለገለው?
ሐዋርያት ናቸውን? ካህናት ናቸውን? ሐዋርያውመልካም ገድል ተጋድያለሁ ሩጫዬን ፈጽሜያለሁ ሐይማኖቴን ጠብቄያለሁ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛልብሎናል፤ በመንፈሳዊ ህይወት ለጽድቅ አክሊል መጋደል ያስፈልጋል፣ በአለማዊ ህይወት የጀግንነት ጎፈሬ ለማግኘት መጋደል ያስፈልጋል! አንድ አገልጋይ ያለፈተና የአገልግሎት የጽድቅ አክሊልን ማግኘት ፈለገ ማለትሳይዋጉ ጎፈሬእንደ ማለት ይሆንበታል! 

እርሻው ሲያምር ዳቦው ያምርአለች ሴትዮዋ እውነቷን እኮ ነው፤ ይህን አባባሏን ስታስረዳምእርሻ የተባልነው እኛ ነን፤ ይህ እርሻ ሲያምር ለአገልግሎት የሚጋገረው ዳቦም ያምራልብላ አስረድታለች።አንድነት ያገባል ገነትይባላል እኮ ሰዎች! “አንድ ጣት ቁንጫ አይገድልምይላል የሀገራችን ገበሬ! ኧረ ምን የመሳሰሉ ምርጥ ምርጥ የአንድነት ተረቶች አሉን መሰላችሁ፤እርስ በእርሱ ያልተደጋገፈ ግድግዳ አይቆምምይልሃል የሀገርህ አባባል። በአንድ ወቅት ጀግናው ቀነኒሳብቻውን የሚሮጥ አይቀድምምብሏል። እውነት ነው ብቻውን የሚሮጥ አይቀድምምና እስኪ ከሰው ጋር አብረን እንሩጥ፤ እናንተዬዋ ነገር ነገርን ይወልዳል፤ ሩጫ ሲባል በቅርቡ በከተማችን ለንደን የሚጀመረው ኦሎንፒክ ትዝ አለኝ። ሁሉም ይለማመድና እስኪ ሁሉም ይሩጥ፤ ሁሉም መንፈሳዊ ሩጫን ይሩጥ። ሩጫዬን ፈጽሜያለሁ አለ ሐዋርያው! ይህች ሩጫ በእርግጥ ታደክማለች! ሩጠህ ሩጠህ ሩጠህ መጨረሻ ላይ የምታገኛት የድካም ውጤት ግን እንዴት ትጥማለች መሰለህ! እንዴት የመንፈስ ደስታ ትሰጣለች መሰለህ! “ከባለቤቱ እጅ የዋለ እንቁላል አይሰበርምእንዲል በጥንቃቄ የያዙት አገልግሎት ብዙዎች አጣጥመውታል፤በጅብ ችኩልነት ከምግብ ጣፋጭነት ሳይተዋወቁ ይኖራሉእንዲል የምንመገበውን እያጣጣምን ከሆነ በእርግጥ መጣፈጡ አይቀርም። ችግሩ በችኩልነታችን ሳንቀምሰው መቅረታችን ነው፤ እስኪ እንቅመሰው፣ እስኪ በአገልግሎትም እንበርታ።
ጌታን ለማገልገል በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ እንጂ ከዚህ ትጋታችሁ ወደ ኋላ አትበሉ [ሮሜ 12:11]

አገልግሎታችን ለብ ያለ መሆኑን /ጳውሎስ አይቷል መሰል 
ጌታን ለማገልገል በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ እንጂ ከዚህ ትጋታችሁ ወደ ኋላ አትበሉይለናል። ጌታችንም ለብ ያለውን አገልግሎታችንን አይቷል እኮ፤ ለብ ስላልን እንዲህ ብሎናልበራድ ወይም ትኩስ እንዳልሆንክ አውቃለሁ፤ በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም ነበር። እንዲሁ ለብ ስላልህ ከአፌ ልተፋህ ነውራዕ [3:13] ይህ ራዕይ ከጅምሩ እንዲህ ነበር፦ ሎዶቂያ የምትባል አንዲት ከተማ ከነበረባት የውሀ አቅርቦት ችግር የተነሳ ከአካባቢዋ ከሚገኙ ፍል ውሀዎች በቦይ ተስበው ለከተማዋ አገልግሎት ይሰጡ ነበር። ውሀው ወደ ከተማው ሲደርስ ለብ ይላል፤ ይህ ውሀ በብዙ ሚኒራሎች የተሞላ contaminated ስለሆነ ለመጠጣት በጣም አስቸጋሪ ነበር። ለቤተክርስቲያኑ መሪ እንደ ከተማው የውሀ ባህርይ እንዲህ የሚል መልዕክት ተጻፈለት፦በራድ ወይም ትኩስ እንዳልሆንክ አውቃለሁ፤ በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም ነበር። እንዲሁ ለብ ስላልህ ከአፌ ልተፋህ ነውበአገልግሎታችን ለብ ያልን ሳይሆን ጌታን ለማገልገል በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ! ተብለናል።

እሳት መጣብህ ቢሉት እሳር ውስጥ ገብቻለሁ አለ ሞኙ!” ፈተና ሲመጣ ወደ ኋላ ማለት የለብንም፤ ይህ እራስን ለፈተናው ማመቻቸት ነውና።

ወጣት የነብር ጣትነውና ነገሩ ወደ ኋላ ያላችሁ ሁሉ እንደ ቀደመው እንደ መጀመሪያው በርቱ እንደ በፊቱ በፍቅር አገልግሉ ይለናል ታላቁ ሐዋርያ! “የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና የምነቅፍብህ ነገር አለኝ!” ራዕይ 2:4 ይህ መልዕክትም ታላቅ ነው፤

ሲበላ ለሚከሳ ሲነግሩት ለሚረሳ ለዚያም ምግብ ለዚህም ነገር ንሳእንዲል እስኪ ልብ ብለን እንስማ፤መናገር መልካም ነው ማዳመጥ ይበልጣልእንዲል እስኪ እኛም ሐዋርያቱ የሚሉትን እናዳምጥ። አበው የዝሆን ጆሮ ይስጥ ይላሉ።
የአገልግሎት መሰረት የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች ምንድን ናቸው?

አንድ አገልጋይ ይህን ካላወቀ በእውኑ በአገልግሎቱ ሲናወጥ ይኖራል! ይህ የአንድ አገልጋይ የባንኩ የምስጢር ኮድ እንደ ማለት ነው፤ እነዚህም ፍቅር፣ ትዕግስት፣ ትህትና ናቸው። 

አገልግሎት ያለ ፍቅር ከንቱ ነው! 

አገልግሎት ያለ ትዕግስት ከቶ አይቻልም!

አገልግሎት ያለ ትህትና ፍሬ ቢስ ነው!

አገልግሎቱን የሚወድ ጆሮ ያለው ይስማ! 
የቀደሙት አባቶች በአገልግሎት ያለፉበትን የአገልግሎት ሚስጢር በነጻ ይግዛ! /ጳውሎስ ለዚህ ነው የአገልግሎት መሰረት የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎችን ፍቅርን፣ ትዕግስትን፣ ትህትናን እንድንገዛ የሚነግረን። ገላትያ 5:21 

አገልግሎት ጨለም ሲል ማማረር የለብንም፤ጨለማውን ከምታማርር ሻማውን አብራይባላልና ሻማውን ግዛና አብራ! የፍቅርን ሻማ! የትዕግስትን ሻማ! የትህትናን ሻማ ግዛና አብራ፤ ይህን ግዜ ጨለማው ብርኃን ይሆናል።

የፍቅር ሻማ! ፍቅር ማለት የሚወዱንን ብቻ መውደድ ማለት ሳይሆን የሚጠሉንንም መውደድ ማለት ነው!

የትዕግስት ሻማ! የካህናቱ ልብሰ ተክህኖ ሰፊና የተንዠረገገ የሚሆነው ትዕግስታቸው እንደ ልብሳቸው ሰፊ መሆኑን ለማመልከት ነው፤ የመዘምራን ልብስ ግን እንደምናውቀው ጠባብ ነው፤ ትዕግስታችን ሰፊ ሲሆን ምን አልባት ልብሱም ሰፊ ይሆን ይሆናል!

የትህትና ሻማ! ያለ ትህትናማ ማንን ልናገለግል ነው? ታላላቅ አገልጋይ የሚባሉትን እስቲ እንያቸው፤ ከሁሉ ዝቅ ዝቅ ይላሉ። እውቀት ጥበብ ችሎታ ወዘተዎች ለእነሱ አይታሰባቸውም። ሰዎች ከፍ ሲያደርጓቸው ከልባቸው ይጠሉታል ዝቅ ሲሉ ደስ ይላቸዋል። 
አገልግሎት በዲያቢሎስ ጥቁር መነጽር 

የበጎ ነገር ሁሉ ጠላት የሆነው ዲያቢሎስ እነሆ በየዕለቱ ሐሜትንና ወሬዎችን ሊያቀርብላችሁ ዝግጁ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ጥሎችንና ችግሮችን መከራዎችን ያቀርብላችኋል፤ ኧረ ጆሮ ከሰጣችሁትማ ምርጥ ምርጥ ወሬ ሊያዋራችሁ ሁሌ ዝግጁ ነው! የሰዎችን ሚስጢርና አስተሳሰብ ሳይበርድ በትኩሱ ያቀርብላችኋል። በልባችሁ ቦታ ስትሰጡትም ትበሳጫላችሁ ትጨናነቃላችሁ። ብልጥ የሆነ ግን የጆሮውን በር ከእነዚህ ከንቱ ነገሮች ሁሉ ይዘጋል! ይገርማል! የማይጠቅም ነገር ሰምቶ የውስጥ ሠላምን ማጣት ምንኛ ያላስተዋልነው ነገር ነው! 

ቢቻላችሁ ከሰው ሁሉ ጋር በሠላም ኑሩ! የምትለዋን የሐዋርያውን መልዕክት እወዳታለሁ፤ ሮሜ 12:18
ዮሐንስ አፈወር ምን አለ መሰላችሁ፤አስተዋይ በየቀኑ ጠላቱን ወዳጁ ሲያደርግ ሌላው ግን በየቀኑ የልብ ወዳጁን ያጣል!” ብሏል። እነዚህ ሁሉ ቢደመሩ ግን ፍቅር ትዕግስት ትህትና ናቸው! 

አንድ አገልጋይ በአገልግሎት እያደገ ሲሄድ ተካፋይ የሚሆንባቸው ነገሮች እያደጉ ስለሚሄዱ ስህተቶችም እያደጉ ይሄዳሉ። ኃላፊነቱ እየጨመሩ ሲመጡ ሙሉ ግዜው ይዋጣል፤ ራሱንም ይረሳል። ለነፍሱ የሚያስፈልጋትን ምግብ ስለማያቀርብላት ቁልቁል ይወድቃል። እንደዚህ አይነቱ ሰው እሱ ራሱ ሳይሻገር ሌሎች ሰዎችን ከአንዱ ወደብ ወደ ሌላኛው ወደብ የሚያሻግር ድልድይን ይመስላል፤ ወይም ደግሞ እሱ ወደ ቤተ መቅደስ ሳይገባ ሰዎች እንዲገቡ የሚጣራ ደወልን ይመስላል! ለዚህ እኮ ነው ሐዋርያውለሌሎች ከሰበኩ በኋላ ራሴ የተጣልኩ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምኩ አስገዛዋለሁያለው። [1 ቆሮ 9:27]
አገልጋይየሚለው ስም ለመላዕክት የተሰጠ ድንቅ ስም እንደሆነ ታውቃላችሁ! መላዕክት ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ የሚያገለግሉ መናፍስት አይደሉምን? መላዕክቱን መንፈስ የሚያደርግ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል፤
ዕብ 1:14 መዝ 103:4 ይህን ድንቅ ስም በድንቅ አያያዝ ያዘው። 

በአገልግሎት ማንኛውም አይነት ፈተና ሲገጥመን እግዚአብሔር ከፍ ላለ ተልዕኮ እያዘጋጀን እንደሆነ ታውቃላችሁ!? /ጴጥሮስን ያዘጋጀው ሥጋዊ ድካሙን እንዲያውቅና ከሌሎች ሐዋርያት በላይ ራሱን ከፍ አድርጎ እንዳያይ ነበር። ዮሴፍን በታላቅ ፈተና ውስጥ ለታላቅ ተልዕኮ አዘጋጀው፤ ነነዌን የሰበካት ነቢይን በማዕበል በወጀቡ ቢያልፍም ለካ ይህ ሁሉ ለተልዕኮ የሚያዘጋጁ ነበሩ! 

አንተ ዓሣ አጥማጅ አገልጋይ ሆይ!
ይህች ጽሁፍ ለአገልግሎትህ እንደምትጠቅምህ ይታመናል።

የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ!” 
ይህች ጽሁፍ በአገልግሎታችን የቆምን የመሰለን እንዳንወድቅ፣ የወደቅን እንድንቆም ታስባ የተጻፈች ናት።
1
ቆሮ [10:12]

በዐቢይ ጾም ገብር ኄር /ታማኝ አገልጋይ/ የሚላከው ኢሜልም እጅግ ይጠቅማልና ከወዲሁ አያምልጦ!

አንተ ዓሣ አጥማጅ አገልጋይ ሆይ!
መረቡን ወርውሮ በተገኘው ዘዴ ሁሉ የበዙ ዓሦችን የሚያወጣ ዓሣ አጥማጅ ምንኛ ብልኅ ነው! -//-



·                                  
·                                
·                                 35 shares
·                                  
o                                                       
This page is Prepared by one of London St Trinity Sunday school students yonas zekarias http://yonas-zekarias.blogspot.com/
Page: 1,144 like this
March 10 at 10:06am ·  · 1 · 
o                                                       
Hana Asfaw Kale hiwot yasemaln!!! hulachnem bagelgelotachen endenbereta egziyabher yerdan amen!!!
o                                                       
Agegnehu Bezabih Wondime getachinnena medhanitachin leul egzi'iabiher ejig yetewodede yamarena yetbareke yeagelgilot edmen ketena gar awahido yistelih. Kale hiywot yasemalen.
March 10 at 10:46am ·  · 1
o                                                       
Fasika Alem ቃለ ሕይወትን ያሰማልን እኛም ሰምቶ ለመፈጸም ያብቃን
March 10 at 11:10am ·  · 1
o                                                       
Azeb Ejigu Medanihalem batachenen ytsena
o                                                       
Sintayehu Sisay kalewet yasemalin
o                                                       
John Yohannes kale hewet yasemaln
o                                                       
Alemamenen Erdaw KALE HYWETEN YASEMALEN!TELIK TEMHERT SETOGNAL SEHUFU BEWERE TENEDECHE WEDAJOCHEN EYTELAHU BALHUBET SEAT NEW YTENAGERKEGN.EGZIABHER YSTELEN!!
o                                                       
Roman Wuebet Churchቃልህይውትይስማልንእኛምስምቶለመፈጰምያብቃን
o                                                       
o                                                       
Hagaranesh Wazama kale hiewot yasemalen
o                                                       
Sinework Teklewold Menigste semayn yawrisilin
March 23 at 6:17pm ·  · 2
·                                

No comments: