ዘና ብላችሁ ተቀመጡና አንድ ድንቅ ታሪክ ላውጋችሁ!
“ብዙ ውሸቶች አንድ እውነት አይወጣቸውም” ይሉ ነበር እቴጌ ጣይቱ። ኤፍራታ የምትባል የአምስተኛ ክፍል አስተማሪ ነበረች አሉ………… ኤፍራታ የአስተማሪነት ስራዋን የጀመረችው ለሕፃናቱ ውሸት በመናገር ነበር………… አስተማሪ በሆነችበት በመጀመሪያዋ ቀን ከተማሪዎቹ ፊት ለፊት ቆመችና ሁሉንም እኩል እንደምትወዳቸው ተናገረች………..
ይህ ግን እውነት አልነበረም ……….…… ምክንያቱም ዮናስ የሚባል ልጅ ፈዛዛና ከተማሪዎቹ ጋ በደንብ እንደማይጫወት ኤፍራታ ታውቅ ነበር………….. ዮናስ ልብስ አለባበሱ ጀልጋጋ ነው…………… ፊቱ በዝንብ ተወሮ………. ንፍጡ ተዝረክርኮ…………….. ጸጉሩ እንዳይፈታ ተቆጣጥሮ ኧረ ስንቱ ተዘርዝሮ! ……………..
ዮናስ እንደምንም ተንገዳግዶ ያቺን ዓመት ጨረሳት…………. በዓመቱ የመዝጊያ ወራት ኤፍራታ የልጆቹን ፋይል ማንበብ ጀመረች………….. የዮናስ ፋይል ተራ ደረሰ………… የፋይሉን በደንብ አለመያዝ አይታ "አይ እንደ ልጁ ፋይሉም ግራ የገባው ነው" አለች በልቧ……….. እንደምንም ጨክና ፋይሉን ገለጥ አደረገችው……….. ኤፍራታ በድንጋጤ ወላፈን ተመታች……….. የዮናስ አንደኛ ክፍል አስተማሪ እንዲህ ብለው ጽፈዋልና፦ "ዮናስ እጅግ ጎበዝ ተማሪና በፈገግታ የተሞላ ልጅ ነው። ስራውን በጥራት ይሰራል ካጠገቡ መሆንም ያዝናናል"

የሁለተኛ ክፍል አስተማሪው እንዲህ ብለው ጽፈዋል። "ዮናስ ጎበዝ ተማሪና በክፍል ጓደኞቹና በመምህራኑ የሚወደድ ተማሪ ነው። ይሁን እንጂ እናቱ በቅርቡ በከባድ ሕመም ስለታመሙ ተወዳጁ ልጃችን በከባድ ህይወት ውስጥ እንዳለ እናውቃለን"
የሦስተኛ ክፍል አስተማሪው እንዲህ ብለው ጽፈዋል። "የዮናስ እናት በቅርቡ በመሞታቸው ዮናስ ክፉኛ አዝኗል። አንድ X ሲያገኝ ያለቅስ ነበር። ዛሬ ግን ቀን ሙሉ የሚያስለቅሰው የእናቱ ሞት ነው። ብሩህ አእምሮ ቢኖረውም የእናት ሐዘን ነውና በጣም ተቸግሯል"
የአራተኛ ክፍል አስተማሪው እንዲህ ብለው ጽፈዋል። "ዮናስ ለትምህርቱ ትኩረት አይሰጥም። በክፍል ውስጥ ይተኛል። ጓደኛም የለውም። ብቸኝነት ያበዛል። ማንም ሳይነካው ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል። የዕንባው ብዛት የልጅነት ፊቱን እየጎዳው ነው"
የአምስተኛ ክፍል አስተማሪው ኤፍራታ ነበረች ይህንን ሁሉ ጉድ የምታነበው። በዮናስ ታሪክ እጅግ ተረበሸች። በአስተሳሰቧም አፈረች። በአንድ ወቅት የክፍል ተማሪዎቿ በሚያማምሩ የስጦታ መጠቅለያዎች የገና ስጦታ አመጡላት። ዮናስ ግን በካኪ ወረቀት አሽጎ ስጦታውን ለኤፍራታ ሰጠ። ኤፍራታ ስጦታዎቿን በተማሪዎቹ ፊት መክፈት ጀመረች። በመጀመሪያ ቸኩላ የተከፈተው የዮናስን ስጦታ ነበር። ስጦታውም የእጅ አምባርና ሽቱ ነበር። ኤፍራታ እጅግ ደስ ብሏት ለመጀመሪያ ጊዜ ለዮናስ ፈገግታ አሳየችው። የእጅ አምባሩን አድርጋ ሽቱውን ተቀባች።
ዮናስ በዛች ቀን ልቡን ያሳሰበውን አንድ ብርቱ ነገር ሊነግራት ፈልጎ ኤፍራታ ብቻዋን እስከምትሆን ጠበቃት። ብቻዋን ሲያገኛት " ዛሬ ፈገግታሽ የእናቴን ፈገግታ አስታወሰኝ" አለ ዮናስ ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ። "እናቴ በገና በዓል ላይ ሁል ጊዜ ይህንን ሽቱ ትቀባ ነበር። የእጅ አምባሩም በጣም ደስ ይላል ስላት ነው የገዛችው። መቼም ከእጇ ላይ አይለይም ነበር። አሁን ግን እኔንም ተለየችኝ" ብሎ ተንሰንቅስቆ አለቀሰ። ዕንባው እንደ ጅረት በሁለቱም የልጅነት ዓይኖቹ ፈሰሱ። ኤፍራታም ዮናስን አቅፋ አነባች። ዮናስን አፅናንታ ለግማሽ ሰአት ያህል ለብቻዋ አለቀሰች። ዮናስ ግን ግማሽ ሰዓት ሳይሆን ሕይወቱን ሙሉ ያነባል።
ኤፍራታ ከዛች ቀን ጀምሮ ለዮናስ የተለየ ትኩረት መስጠት ጀመረች። ዮናስ ድጋፍ ሲያገኝ የበፊቱ ማንነቱ እየተመለሰ መጣ። በዓመቱ መጨረሻ ዮናስ ከክፍሉ ምርጥ ተማሪ ሆኖ ተሸለመ። ኤፍራታ ሁላችሁንም እኩል እወዳችኋለሁ ስትል ዋሽታ ነበር። አሁን ከሁሉም ይልቅ ዮናስ ተወዳጅ ተማሪዋ ነውና!
ከዓመት በኋላ ኤፍራታ ከቤትዋ በር ስር አንድ ደብዳቤ አገኘች። ደብዳቤው "ምርጥ አስተማሪዬ ነሽ ከዮናስ" ይል ነበር። ከስድስት ዓመታት በኋላ ሌላ ደብዳቤ አገኘች። "ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ጨርሻለሁ። በደረጃም ሦስተኛ ወጥቻለሁ። አሁንም ግን ምርጥ አስተማሪዬ አንቺ ነሽ" ይላል።
ከአራት ዓመት በኋላ ኮሌጅ እንደሚጨርስና አሁንም ምርጥ አስተማሪው እንደሆነች አረጋገጠላት ……….…… ደብዳቤዎቹ መዝነባቸውን ቀጠሉ……….…… በመጨረሻም በባችለር ድግሪ እንደሚመረቅና አሁንም የማትተካ ምርጥ አስተማሪ መሆኗን አረጋገጠላት……….…… ዘመናት አለፉ……….…… ዮናስ በቅርቡ እንደሚያገባና ኤፍራታ በሠርጉ ላይ ተገኝታ በእናቱ ቦታ ላይ በክብር እንግድነት እንድትቀመጥ ጋበዛት……….…… የሠርጉ ቀን ፈጥኖ ደረሰ……….…… ኤፍራታ ዮናስ የሰጣትን ስጦታ የእጅ አንባሩን አድርጋ ሽቱውን ተቀብታ በሠርጉ ላይ ተገኘች……….…… ዮናስ ገና ከሩቅ ኤፍራታን እንዳያት ዕንባ ቀደመው……….…… ከክብር ቦታው ዝቅ ብሎ ወረደና ኤፍራታን ተጠምጥሞ አቀፋት……….…… እርስ በእርሳቸው ተለቃቀሱ……….…… ከዛሬ ስንት ዓመታት በፊት ተቃቅፈው አልቅሰው ነበር……….…… ዛሬ ግን የደስታ እንባ ተጋሩ! “ውድ እንግዶቼ በህይወቴ ታላቁን ቦታ የያዙ ውድ መምህሬ ናቸውና እጃችሁን ተውሼ ማመስገን እፈልጋለሁ” አለ። ወዲያው ጭብጨባውም እንደ ጉድ ቀለጠ!
በሠርጉ መሃል የዮናስ የእጅ አላርም ጮኸ………. ይህች ሰዓት ዮናስና ጓደኛው ሔርሜላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀጣጥረው የተገናኙባት ሰዓት ነበረች……….…… ዮናስ ለሔርሜላ በጆሮዋ የቀጠሯችን ሰዓት ደርሷል ብሎ በእጁ ተሸክሟት ከአዳራሹ ወጣ……….ሔርሜላ “ፍቅር ዓለም አቀፍ ቋንቋ ነው፤ የፍቅር ሀገሩ ልብ ነው” የሚል አባባል ነበራት።
ለመጀመሪያ ጊዜ ጓደኛውን ባገኘበት ውብ ፓርክ የግራ ጎን አጥንቱ ሔርሜላን በቀኝ እጁ እቅፍ ድግፍ አድርጎ የፍቅር ጉዟቸውን ቀጠሉ……….…… ይህች ፓርክ አብረው ትምህርታቸውን ያጠኑባት ፣ ሀ ሁ ብለው የፍቅርን ፊደል የቆጠሩባት፣ ሠርጋቸውን የደገሱባት ፓርክ ነበረች። ሔርሜላም በተራዋ ዮናስን አቅፋ የምነግርህ ሰፕራይዝ አለኝ አለችው።
ዮናስም በያ ይነገረን አለ……….
ሔርሜላ ፈገግ እያለች ዮናስን እንደ እናቱ የምትንከባከቢው አንቺ ነሽ ብላ የእናትህን የእጅ አምባር ኤፍራታ ሰጠችኝ አለችው አሁንም ፈገግ እያለች……….…… ይህ የሔርሜላ ፈገግታ እውነተኛው የእናቱ ፈገግታ ነበር………
ከጣፋጭ ቆይታ በኋላ በእጁ ተሸክሞ እናዳወጣት ተሸክሞ ወደ አዳራሹ መለሳት። እድምተኞቹ በደስታ ተቀበሏቸው……….…… ዮናስ በሠርጉ ላይ ንግግር ማድረግ ጀመረ……….…… ወላጅ የሞተባቸውን ሕጻናት አንርሳቸው እንርዳቸው! በግሌ በእናቴ ስም ወላጅ የሞተበትን ህጻን ለማሳደግ ቃል እገባለሁ አለ። ከእድምተኞቹ ብዙዎቹ ቃል ገቡ።
"ጨረቃ ሳለች እሩጥ እናት ሳለች አጊጥ"
ሠርጉም እንደ ታሪኩ በጥሩ አጨራረስ ~ // ~ ተፈፀመ!!~ // ~
~ // ~ ~ // ~ ~ // ~ ~ // ~ ~ // ~ ~ // ~
የልጅ ዮናስ ብሎግ አባል ይሁኑ!!