ስለ ዘመናችን ቤተክርስቲያን እጅግ የሚያዝኑ አንድ አባት አውቃለሁ። ዘወትር “አይ እናቴ” እያሉ ያዝኑ ነበር። ብዙ ሰዎች ስለ ሥጋ እናታቸው የሚያዝኑ ነበር የሚመስላቸው። እሳቸው ግን “እናቴ” የሚሉት ቤተክርስቲያንን ነበር።
ዛሬም እንደለመዱት አይ እናቴ ብለው ንግግራቸውን ጀመሩ። ይሁዳ ጌታን አሳልፎ የሰጠው በመሳም ነበር፤ ዛሬ ብዙዎች ቤተክርስቲያንን በመንከስ አሳልፈው ሰጥተዋል። ወደፊትም ይሰጣሉ። ወተት የምትመግበውን እናት ካደገ በኋላ ጡቷን የሚነክስ ልጅ ምንኛ የተረገመ ነው አሉ ክፉኛ እያዘኑ። ጥንታዊቷን ቤተክርስቲያን መጠበቅ ዓለምን ከመጠበቅ አያንስም ይል ነበር የቤተክርስቲያኑ በረኛ። ልጆቼ ሆይ የቤ
ተክርስቲያንን ወተት ተመገቡ እንጂ የእናት ጡት ነካሾች አትሁኑ አሉንና ስለ ጸሎት እንዲህ እያሉ አስተማሩ።
“ለምኑ ይሰጣችኋል በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል”
እናት አረቄ እየጠጣች ልጇን ወተት ታጠጣ ነበር። ልጁ አረቄ ካልተሰጠኝ ብሎ እሪሪሪሪ እያለ አለቀሰ። የፈለገ ቢያለቅስ እናት ለልጅዋ አረቄ አትሰጠውም። እንደሚጎዳው ታውቃለችና! እኛም እንዲሁ አንዳች ነገር ካልተሰጠን ብለን ስናለቅስ ጌታችን የሚጎዳንን ያውቃልና የሚጎዳንን አይሰጠንም። ለበሽተኛ መድሐኒት የሚያዘው ሐኪሙ እንጂ በሽተኛው አይደለምና!
ስናመሰግን ከምንጮኸው ጩኸት ይልቅ ትንሽ ስንቆነጥጥ የምንጮኸው ጩኸት ይበልጣል። እስኪ ለብዙ ዘመናት ጸልያችሁ ያልተሳካላችሁ ለአንድ አፍታ አስቡት። አሁን ደግሞ ለምን ይሆን ይህ ልመና ያልተፈጸመልኝ ብላችሁ ጠይቁ። እንዲህ የሚል አባባል አለ።
የለመንከው ወዲያው ቢሳካልህ እምነትህን ይጨምርልሃል።
አንዳች ነገር ለምነህ ባይሳካልህ ትዕግሥትን እያስተማረህ ነው።
ፈጽሞ ባይሳካልህ ግን ያቺ ልመናህ ለአንተ አትጠቅምምና እግዚአብሔር ለአንተ የሚጠቅምህን እያዘጋጀልህ ነውና በተስፋ ጠብቅ። በለሱን የጠበቀ ፍሬውን ይበላል አይደል የሚባለው።
በጸሎት ላይ ስንለምን ሦስት መሰረታዊ ነገሮች ያስፈልጋሉ። ሐዋርያው እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ እንዳለ
እምነት
ተሥፋ
ፍቅር
እምነት ሳይኖር አንዳች ልመናችን አትፈጸምም።
ተስፋም ያስፈልጋል። ለዚህ እኮ ነው ብዙዎች የለመኑት ሲዘገይ ተስፋ ቆርጠው ጠንቋይ ፍለጋ የሚባዝኑት።
ፍቅር ከሁሉ ይበልጣል። ፍቅር ሳይኖር የሚለመን ልመና ይፈጸማል ማለት እናት ለልጅዋ ምጥ አስተማረቻት እንደማለት ነው። ከቶ አይቻልምና!
በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል ለምኑ ይሰጣችኋል።
Visit this Blog! http:// yonas-zekarias.blogspot.com /

Visit this Blog! http://
— with Frhewot
Tesfaye, Tiemar
Gebretnsae,Alexander
Solomon, Robel
Hailemariam, Senai
Mehari, Andualem
Ferede, Senait
Yemane, Ephrem
Bekele and Eyob
Ghebrebrhan.
·
·
·
June
23 at 10:59am · · 1
June
23 at 3:07pm · · 1
June
23 at 3:37pm · · 1
Yoni khy
June
26 at 8:47pm · · 1
·
No comments:
Post a Comment