ኦሪት ማለት ሕግ ማለት ነው። አይሁድም ሕገ ወጥ ሕግ አስከባሪ ነበሩ። ራሳቸው ሕገ ወጥ ኾነው አሕዛብን ሕግ ጠብቁ ይሉ ነበር። በዘመናችንም ሕገ ወጥ ሕግ አስከባሪ ብዙ ናቸው!
ኦሪት!
ኦሪት እስክትሰራ ኃጢአት በዓለም ተደብቃ ትኖር ነበር። ኦሪት ከተሰራች በኋላ ግን ኃጢአት እንደ ሰኔ ሰርዶ ራሷን ብቅ ብቅ አደረገች። ኦሪት ዘመነ መልከ ጼዴቅ ሳይፈጸም ዘመነ ወንጌል ሳይጀመር እንደ ወተት ዝንብ ጥልቅ ብላ ገባች። ኦሪት በረከተ ምድርን ለኢያሱ በረከተ ሰማይን ለኤልያስ ታሰጣለች።
ጥንቱን ሰው ሲፈጠር እንደ መላዕክት በሕገ ልቡና ሊኖር ነበር። ይህ ባይኾን የኦርት ሕግ ተሰራለት።
ሕገ ልቡና እንደ ግእዝ
ኦሪት እንደ ንባብ
ወንጌል እንደ ትርጓሜ ይመሰላሉ።
ኦሪት ማለት ሕግ ማለት ነው። ኦሪት ዘፍጥረት ሲል የመፈጠር ሕግ ሲል ነው።
ፈራሽ በስባሽ በሚኾን በዚህ ሰውነታችሁ ላይ ኃጢአትን አታሰልጥኗት። እቴጌ እቴጌ አትበሏት። ሥጋችሁ የኃጢአት ጦር አድጋችሁ ነፍሳችኹን አትውጉበት። ነፍሳችሁን የጽድቅ ጦር አድርጋችሁ ሥጋችሁን ውጉበት እንጂ። ከእንግዲህ ወዲህ ኃጢአት አይሰለጥንባችኹም። ከኦሪት ወደ ወንጌል ተመልሳችኋልና።
Visit this Blog! http://
·
·
·
May
19 at 8:49am · · 1
May
19 at 8:57am · · 1
May
19 at 9:14am · · 2
May
19 at 9:39am · · 1
·
No comments:
Post a Comment