Monday, 20 August 2012

የዕንባ ዘለላ!




ዘና ብላችሁ ተቀመጡና አንድ ታሪክ ልንገራችሁ፤
በአህያ ቆዳ የተሰራ ቤት ይፈርሳል ጅብ የጮኸ እለትይላል የሀገሬ ሰው፤ ነገሩ ወዲህ ነው እነሆ በለንደን የምንኖር ሐበሾች በክራይ የምንገለገልበት ቤተክርስቲያን አለ፤ ቤተክርስቲያኑን ከነጮች ጋር በፈረቃ ነው የምንጠቀመው። እሁድ ጠዋት ለቅዳሴ እንገባና ከሰአት ነጮቹ ገብተው የራሳቸውን ፕሮግራም ያካሄዳሉ። ሲፈልጉ ስፖርት ይሰሩበታል ደስ ሲላቸውም ይደንሱበታል! እኛም በየሳምንቱ ለቅዳሴ እየተገለገልንበት እንዲህ እያለ ይቀጥላል። ይህ የእንግሊዝ አብያተክርስቲያናት ጸባይ ነው፤ ድሮ አባቶቻቸው ያወረሷቸው በእየ 7 እርምጃ የተሰሩ ቤተክርስቲያን ነበራቸው፤ አሁን 
በእየ 3 እርምጃ የተሰሩ የጭፈራ ናይት ክለብ አላቸው፤ ከቤተክርስቲያናቸው ስር /under ground/ የጭፈራ ቤት ተሰርተዋል፤ ዛሬ አውሮፓዊያኑ ከጥንት ነዋሪዎች በስተቀር ቤተክርስቲያን የሚመጣ ህዝብ የላቸውም፤ ስለዚህም ቤተክርስቲያኑ ይሸጥና የጭፈራ ቤት ይሆናል ማለት ነው። 


ጨረቃ ብትደምቅ አታሞቅ የሰው ቤት አያደምቅነውና ነገሩ ሰሞኑን በምንገለገልበት ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው ቤተ መቅደስ እንዲፈርስ ጠይቀዋል፤ሂድ አትበለው እንዲሄድ አድርገውእንደ ማለት ነው። ቢሯችንም ተዘግቶ አገልግሎቱ ቆሟል። ሰበካ ጉባኤው ሰሞኑን ተሰብስቦ ሌላ ቤተክርስቲያን ፍለጋ እየተሯሯጠ ነው።ሞት ቢዘገይ የቀረ ይመስላልአለች ሴትዮዋ እውነቷን እኮ ነው፤ እኛም ዝምታቸው ሲዘገይ የቀረ መሰለንና ቤተክርስቲያኑ የራሳችን መሰለን፤ በመጨረሻዋ ሰአት ላይም ተረባረብን፤ ይህን ያዩ የለንደን እማ ወራዎችምሞት ሲደርስ ቄስ ጦር ሲደርስ ፈረስብለው ተረቱ! 


በእርግጥ ነጮቹ እስከ ዛሬ ቤተክርስቲያኑን እንድንጠቀም ስለፈቀዱልን ማመስገን ይገባናል፤ ሲጀመር የራሳችን አያያዝ ጥንቃቄ የጎደለው ነበር። ምዕመናንም በንፅህናው ረገድ ችላ ያሉ ይመስላል፤ የሰ//ቤቱ ተማሪዎች በፅዳቱ ቢተጉም በአጠቃላይ አያያዛችን ላይ የጥንቃቄ ጉድለት ነበር፤ አንዳንድ እቃዎች ተሰበሩ፣ በካርፔንት እና በወንበሮች ላይም ሻማ ፈሰሰ፤ ይህን የመሰለ ወዘተ ተረፈዎች ሲደማመሩ ችግሩ ጎላና እነሱም መናገር ጀመሩ፤ 

*
እስከ ሁለት ወር ድረስ ግዜ ተሰጥቶናል፤ ከዛ በኋላስ እንወጣለን ማለት ነው? ወይስ ምን ይመጣ ይሆን? የትንሣኤውን በዓልስ የት ይሆን የምናከብረው? መልካሙን ያሰማን።

ለዚህ ነውየዕንባ ዘለላእናዋጣ የተባለው። ለጸሎት ስትቆሙ እስቲ ስለዚህ ጉዳይ አንዲት አባታችን ሆይ ድገሙ፤ እስቲ ሁላችንም ትንሽ የዕንባ ዘለላ እናዋጣ፤ እስቲ ተሳሉ; እስቲ የዕንባ ዘለላ አዋጡ፤ የእያንዳንዳችን የዕንባ ዘለላ ተጠራቅማ ምን አልባት ታላቅ ስራን ትሰራ ይሆናል ማን ያውቃል? እስቲ አብዝታችሁ ጭኹና ለምኑ፤ ከእልፍ አእላፋት የወፎች ጩኸት መካከል የልጇን ድምጽ ለይታ የምታውቅ ለየት ያለች የወፍ ዝርያ አለች፤ ከመካከላችንም እግዚአብሔር የመረጠው ጩኸቱ ይሰማ ይሆናል ማን ያውቃል?

ለጸሎት በቆማችሁ ግዜ ይህችን ጉዳይ በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ፤ እስቲ እንደ ነብያቱ በዕንባ ዘለላ ጭምር ልመናችንን እናቅርብ፤ የኢየሩሳሌም ቅጥር እና ቤተ መቅደሱ ሲፈርስ ነህምያና ኤርሚያስ ያደረጉት ትዝ እንደሚለን የታመነ ነው። ነህምያ የንጉሥ አስተናጋጅ ነበር፤ በቤተ መንግሥት እየኖረይህንንም በሰማሁ ግዜ ተቀምጬ አለቀስኩአለ፤የኢየሩሳሌም ቅጥር መፍረሱን፣ ቤተመቅደሱ መፍረሱን፣ሰው ከእግዚአብሔር መራቁን በሰማ ግዜ አለቀሰ፤ ብዙ ግዜም እፀልይና እጾም ነበር ነህምያ [1: 4] እንዲሁ ነብዩ ኤርሚያስም ቤተመቅደሱ መፍረሱን አይቶ አለቀሰ፤ ሰቆ. ኤር. [3: 44]

የሁለቱን እንባ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርብ ደገኛ የሆነ አንድ የከበረ መልአክ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፤ ይህ መልአክ እግዚአብሔርን ምን ብሎ ነበር የለመነው? እግዚአብሔርስ ለዚህ ደገኛ መልአክ ምን ብሎ ይሆን የመለሰለት? 
አቤቱ የሠራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ እነዚህን 70 አመት /እስራኤል በባቢሎን የተወረችበት 70 አመታት/ የተቆጣሃቸውን የኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ድረስ ነው፤ እያለ እግዚአብሔርን ለመነ፤ እግዚአብሔርም ደስ በሚያሰኝና በሚያጽናና ቃል ለመልአኩ መልሶለት ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ከተሞች ምህረትን አደረገ! የኢየሩሳሌም ቅጥር በእነ ነህምያ ተሰራ! ቤተ መቅደሱም በእነ ዘሩባቤል፣ ዘካርያስና ሐጌ አስተባባሪነት ተሰራ! በዚህ ታሪክ ውስጥ የመልአኩን ምልጃ ልብ ይበሉ፤ ትንቢተ ዘካርያስ [1: 12] 

የእምነት ጸሎት ኃይልን ታደርጋለችእንዳለ ሐዋርያው እነሆ የዕንባ ዘለላ ይህን የመሰለ ግዳጅን ትፈጽማለች! 

በስደት ሀገር መስኮቱን ወደ ኢየሩሳሌም ከፍቶ የሚጸልየው ሰው ማን ነበረ? በስደት ሀገርማ ብዙዎች እግዚአብሔርን ይዘው ድንቅ ስራውን አዩ፤ አብርሐም ሙሴ ዮሴፍ  
እግዚአብሔርን ይዘው ተሰደዱ፤ ነብዩ ዳንኤልም በስደት ሀገር መስኮቱን ወደ ቅድስት ሀገር ከፍቶ ይጸልይ ነበር። 


እኛም በስደት ያለን እንደ ነብዩ ዳንኤል መስኮታችንን ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጲያ ከፍተን የምንጸልይበት ብርቱ ጉዳይ አለ፤ ይህ ብርቱ ጉዳይየዕንባ ዘለላ የምናዋጣበት ብርቱ ጉዳይ ነውእነሆ እንደ ያዕቆብ ልጆች እንጀራን ፍለጋ በምድረ አውሮፓ ወደ ለንደን ተሰደድን፤ ስደትን ለስደተኛ ማን ያስረዳዋል? ወንጌሉማንም ከዛሬ ጀምሮ ጌታን እወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ምክንያቱም ከታናሽነት ጀምረው ሁሉም ያውቁኛልእንደሚል ስደትን ለሚያውቃት ማንም አያስረዳውም። 

ስለስደት እንነጋገር ከተባለ ግን ስደት 4 ልጆች አላት፤ ናፍቆት ብቸኝነት የሚፈራረቁ ሀዘንና ደስታ ናቸው።

የስደት ልጆችን የምታጽናና አንዲት እናት አለች፤ ይህችም ቤተክርስቲያን ናት።


በስደት ያዘነው ሁሉ በቤተክርስቲያን በርከክ ብሎ አንድ ሁለቴ የሰላም አየር በርጋታ ሲተነፍስ ያኔ የውስጥ ሰላምን ያገኛል! ይህች ቤተክርስቲያን በስደት ሀገር ለስንቱ መጠለያ ሆነች? ስንቱን አጽናናች? ስንቱን የነፍስ ረፍት ሰጠች? ይህን ሳስብ ሁሌ ይገርመኛል! አንድ ታላቅ ሰውቤተክርስቲያን ባትኖር ኖሮ ሐበሻ በስደት ሀገር ቆሞ መሄድ አይችልም ነበርብለዋል። ይህ በእርግጥ እውነት ነው፤ የእኛ ጸባይ በህብረት መኖር ነው፤ ከሌላው አለም ሲነጻጸርም እኛ ሀዘንን መቋቋም አንችልም። ለዚህ ነውቤተክርስቲያን ባትኖር መቆም አንችልምያለው። አሁን ግን ይህች መጠለያ ቤተክርስቲያናችን እኔ እንዳቆምኳችሁ እናንተም አቁሙኝ እያለች ነው፤

ይህች ጽሁፍም ዋና አላማዋ ለዚህ ጥሪ አንዳች መልስ እንሰጥ ዘንድ ነውና አንብበን ብቻ ዝም አንበል፤መንገድ በሀሳብ አይደረስምእንዲል ማሰብ ብቻ ሳይሆን አንዳች ነገር በተግባር እንስራ፤ስራ የሌለው እምነት ሙት ነውእንዳለ ሐዋርያው እምነታችን ሕያው እንዲሆን እስቲ አንዳች ነገር እንስራ፤ጫማ የለም ብለው የሚያጉረመርሙ እግር የሌላቸውን አይተው ይጽናኑእንደሚል እኛም ሳናጉረመርም አንዳች ስራን እንስራ፤ ሰው እናቱ ብትራብ ዝም አይልም ከአፉ ነጥቆ ይሰጣታል፤ ምንም የስደት ኑሮ ባይደላም እናት ናትና የሚወጣ ገንዘብ እንኳን እንደየ አቅማችን ብናደርግ ለታሪክ የሚሆን ትንሽ ስራ ሰራን ማለት ነው። 



ነህምያእኛ ባሪያዎቹ እንነሳለን የሰማይ አምላክ ያከናውንልናልእንዳለ እስቲ እግዚአብሔር እንዲያከናውንልን እኛ ባርያዎቹ እንነሳ፤ እስቲ እናንተም ያላችሁን ሀሳብ አቅርቡ፤

ከእንግሊዝ ውጪ የምትኖሩ ወገኖቻችንም እስቲ በጸሎት እርዱን፣ በሀሳብ አትርሱን፣ እናንተ ስትጸልዩ እኛ የዕንባ ዘለላን ስናዋጣ የነብያቱን እንባ ያሳረገ መልአክ የእኛንም ያሳርግ ይሆናል ማን ያውቃል? 


የዕንባ ዘለላን አዋጡ!

........................................


·                                  
·                                
·                                  
o                                                       
Gashaw Zemene Adise Amlak yasbachu endet yasaznal.
o                                                       
Sisay Wolde Ye semay amelak yaknwnlnal egna barywcu tensten enseraln 
ye tensaw geta ye betkrstan tensay yasyen Amen!
o                                                       
Sisay Wolde Ye semay amelak yaknwnlnal egna barywcu tensten enseraln 
ye tensaw geta ye betcihrstan tensay yasyen Amen!
o                                                       
Enane Ashagre Amlak yerdahue.
o                                                       
Selam Gebre Besewe zende yekebede be amelake zend kelale newena e/re maderyawen lenantem mesebasebyawen 
yazegajelachu amene
o                                                       
Addis Gebyhu Egezeabehar melekame newe bemekera kenem mesheshegeya newe.yeserawete geta egezeabehare yeredachu!
o                                                       
Marta Mekonnen Ayzowachew lena yekebeden le amlake emint natna
o                                                       
Dawit Setargachew E/r yamene manem afero ayakem isum ayasaferm yehennem yaregew mekenyat alew wendme ayezon tagesu becha geta hulun neger lebego yargilachuh bereketuna tebekaw ayeleyachuh..
o                                                       
Tsega Tesfaye Egziabher melkam new bemekera kenm mesheshegiya new awo amlakachin mesheshgiyachin newna enantem tesebasbachihu esun yemtamelkubetn yazegajlachihu amlake kidusan kenante gar yhun
o                                                       
Estifanos Belew hulu neger lebego new
o                                                       
Yayneabeba Teferi Ahunem behone egzeabehar yateme ayetelanem yanegan manyawokale basedatem behone esone yamenamlekbten bate yesatanal beto hulu yegezabehar nawona ayezochu egame basalot aberanchu nane enbachnen eyafasasen ensaleyanan esome zem ayelem
o                                                       
GOD ,the father of all saints is real and he will bless keep and protect you our brothers and sisters from all evil and he will too keep our mother saint church . This is fasting month so let's togther pray and pray to the LORD in the name...See More
o                                                       
Fekadu Girma E/R fetno yaregagachew zend silazenu ena siletekezu sewoch ENMALIDALEN!!!
o                                                       
Meron Fekru emabrhane terdacue!!!
o                                                       
Fasika Alem ስለ ስደትና ሰለ ቤተ ክርስትያን የማያስብና የማይጸልይ በስደት የሜኖር ኢትዬጵያዊ የለም ምክንያቱም መታቂያችን መለያችነ መከበርያችን ግርማ ሞገሳችን ናአትና እሷ ከሌለች እኛም የለንም ካለሷማ ሰደተ እንዴት ይዘለቃለ ሰለዚህ በውንድማችን ላይ አድሮ እግዛብሄር እየተጣራ ነውና ጆሮ እንስጠው በተለይ በስደት ያለን ሰዎች ለዚ መልክት የተለየ ትኩረት ሰጥተን ልንጸልይበት ይገባል ግዜውም የሱባዩ ስለሆነ አብዝተን እናልቅስ የነብያቱን ልመና የተቀበለ አምላክ ይርዳን አሜን::
February 29 at 5:19am ·  · 1
o                                                       
Melat Tadess Emberhan kene legua yetbkuachu!
o                                                       
Senait Kifle E/r yerdachu
o                                                       

o                                                       
Amelek Kassaye ፈጣሪ የራሱ የሆነውን ማደሪያ ይስጣችሁ፡፡
o                                                       
Eyerusalem Beshah E/y yerdachu dengle tamaledachu
o                                                       
Fre Abebe dengel blte kena tamaldachu
o                                                       
Yosi Man Be'ewnet tsihufu libn yemineka naw. Igna Binberta Egziabher lebetu qenae aydelemn?
o                                                       
Abay Gossaye ABATACHIN,YEALEM NIGUS,MEDHANIALEM yirdachu
o                                                       
ቅዱሱ ሐዋርያም ‹‹… በመጽናትም ጤናሞች እንዲሆኑ ምከራቸው›› /ቲቶ 22/ያለዉ ያለጽናትም ጤናማም ስለማንሆን ነዉ፡፡ እንግዲያዉስ ጤናሞች እንድንሆን፣ፍሬዋንም እንበላ ዘንድ ለበጎ ነገር እንጽና፡፡በዚህ እግዚአብሔርንም ወደ መምሰል ለመሸጋገር እንችላለንና /2 ጴጥ 16/.......ከአገልግሎት ፍቅር የሚለየን ማን ነው? ማንም::
o                                                       
Rahel Berahnu selebetekersteyane senesa enaem ulle yemechenekebet guday new. yanetenem tufe sanebeu embaye eyemeta new enam egezeyabhare bedemu mesreto yeseraten betekersetyan manem lenekate ayekebam enam egzeyabehere lulachenem lebona setone betekersetyanachene beselam endetekoyelen ullem beselotachen endenasebat esu yeredan.
o                                                       
Biruk Tesfaye Kale hywetn yasmalene. Ysesrael ngus betekrstiyann ytebk
May 12 at 9:49am · 
o                                                       

o                                                       

No comments: