የሕገ ኦሪቱ ሊቅ፦ ምን ማድረግ እንዳለበት ፥ መጽድቂያውን ጌታችን በነገረው ጊዜ፦ እርሱ ግን ራሱን ሊያጸድቅ ወድዶ፦ «ባልንጀራዬ ማን ነው?» አለ። «የሚመስለኝ ፥ የሚተካከለኝ ማነው?» ማለቱ ነው። ራሱን ከጉልላቱ ላይ ያስቀመጠ ሰው በመሆኑ የትዕቢት ንግግር ነው። ትዕቢት ደግሞ ዲያቢሎስ የተያዘበት አሸክላ ነው ፤ ኢሳ ፲፬፥፲፪። ቅዱስ ያዕቆብ እንደተናገረው፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ያዕ ፬፥፮። ጠቢቡ ሰሎሞንም፦ «ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤» ብሏል። ምሳ ፳፱፥፳፫።
ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ፤
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦ በሊቅነቱ ብቻ ተመክቶና ተመጻድቆ፦ «ባልንጀራዬ ማነው?» ያለውን ሰው ያስተማረው በምሳሌ ነው። ምሳሌውም፦ «አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ይወርድ ነበር፤ ሽፍቶችም አገኙት፤ ደበደቡት ፥ አቈሰሉት ፥ልብሱንም ገፍፈው በሕይወትና በሞት መካከል ጥለውት ሄዱ። አንድ ካህንም በዚያች መንገድ ሲወርድ ድንገት አገኘው፤ አይቶም አልፎት ሄደ። እንዲሁም አንድ ሌዋዊ በዚያ ቦታ አገኘውና አይቶ እንደፊተኛው አልፎት ሄደ። አንድ ሳምራዊ ግን በዚያች መንገድ ሲሄድ አገኘው፤ አይቶም አዘነለት። ወደ እርሱም ቀረበ፤ ቊስሉንም አጋጥሞ አሰረለት፤ በቊስሉ ላይም ወይንና ዘይት ጨመረለት፤ በአህያውም ላይ አስቀምጦ እንዲፈውሰው የእንግዶችን ቤት ወደ ሚጠብቀው ወሰደው፤ የሚድንበትንም ዐሰበ፤ በማግስቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለእንግዳ ቤት ጠባቂው ሰጠውና፦ በዚህ አስታምልኝ፤ ከዚህ የሚበልጥ ለእርሱ የምታወጣው ቢኖር እኔ በተመለስሁ ጊዜ እከፍልሃለሁ፥ አለው። እንግዲህ ሽፍቶች ለደበደቡት ሰው ከእነዚህ ከሦስቱ ባልንጀራ የሚሆነው ማንኛው ይመስልሃል? ሲል ጠየቀው ፤ እርሱም፦ ምሕረት ያደረገለት ነዋ አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም፦ እንኪያስ አንተም ሂድና እንዲሁ አድርግ አለው።»የሚል ነው። ሉቃ ፲፩፥፳፱-፴፯።
ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ መውረድ ማለት፦ ከፍ ካለ ሥፍራ ወደ ዝቅተኛው ሥፍራ መውረድ ማለት ነው። ትርጉሙም፦ ከብሮ መዋረድን ፥ተሹሞ መሻርን ፥አግኝቶ ማጣትን ያመለክታል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፦ «ገዢዎችን ከዙፋናቸው አዋርዷል፤ . . . ባለጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል፤» ያላችው እንዲህ ዓይነቱን ነው። ሉቃ ፩፥፶፪ ፣ መዝ ፻፵፮፥፮።
Visit this Blog! http://
·
·
You, Meraf Berhanu, Fms Bereket, Yeshi Abshero and43
others like this.
·
Biniyam Shiferaw qalihewat yasemalen ...!!!
May
12 at 8:44am · · 1
Tsehay Fantu kalehiwet yasemalen
May
12 at 9:29am · · 1
Tsega Tesfaye Kale hiwetn yasemaln bro.
May
12 at 9:33am · · 1
......ቅዱስ ጊዮርጊስ ይጠብቅልኝ + + +!
May
12 at 9:42am · · 1
Sisy Bahru Kalh hiewet yasamalen
May
12 at 9:51am · · 1
Yayneabeba Teferi Kale hiwoet yasameln!
May
12 at 10:28am · · 1
Sosina Sema yagalgelote zamnachwne yarezemelne !!!
May
12 at 11:40am · · 2
Meron Tesfaye KALE HIWET YASEMALEN.YEAGElEGELOT EDMEHN
YARZMLEN.
May
12 at 8:37pm · · 1
Rahel Berahnu thank you yone dese yemel picture new.
Ejigayehu
Gebre kal hiowt yismalen bewdaman betan ytebkaln
Melat Habte like this
No comments:
Post a Comment