Friday, 9 August 2013

ሚካኤል

ጌታዋን ያመነች በግ ላትዋ እውጭ ያድራል

እረኛቸውን ያመኑ በጎች ሁሉን ጥለው ተከተሉት። እስኪ ከበጎቹ አንዱ ጥያቄውን እንይ፦
ዛሬ እኔ ሳልሆን ቅ/ጳውሎስ ይጠይቃል

/1/ ወደ ዕብራውያን
1፥14 ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?

/2/ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አድኖናል። ታድያ መላዕክቱ ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ለምን ይረዳሉ?

/3/ ((መዳንን ይወርሱ ዘንድ)) ከምን ስለመዳን ነው የሚያወራው? ከእሳት ከገደል ወይስ ከምን ይሆን?

/4/ ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ያግዛሉ ማለት ምን ማለት ነው?


// ጾም //



ዝንቱ ዘመድ ኢይወጽዕ ዘእንበለ ጾም ወበ ጸሎት // አብሮ አደግ አጋንንት ያለጾምና ጸሎት አይወጣም፤ ማቴ 17፦21

// ጾም //

ጾምሰ እማ ለፀሎት
ወእህታ ለአርምሞ
ወነቃየ ለአንብዕ

ጾም የፀሎት እናት፣ የተመስጦ እህት ፣ ለንስኃ እንባ ምንጭ ናት!

መዝሙረ ዳዊት 6
1 አቤቱ፥ በቍጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመዓትህም አትገሥጸኝ።
2 ((ድውይ ነኝና አቤቱ፥ ማረኝ)) አጥንቶቼ ታውከዋልና ፈውሰኝ።
3 ነፍሴም እጅግ ታወከች አንተም አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?
4 አቤቱ፥ ተመለስ ነፍሴንም አድናት፥ ስለ ቸርነትህም አድነኝ።
5 በሞት የሚያስብህ የለምና፥ በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው?
6 በጭንቀቴ ደክሜያለሁ ((ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ))
7 ((ዓይኔ ከቍጡ ዕንባ የተነሣ ታወከች ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ አረጀሁ))

ዳዊት ሆይ የንስኃ እንባህ ክቡር ናት!!

የደጋጎቹ አለቃ ክቡር ጴጥሮስ ሆይ እንደ ጅረት ወንዝ ያነባኸው እንባ ክቡር ናት!

ሳናውቅ ከሰራነው በድፍረት የበደልንህ እጅጉን በልጧልና አቤቱ ሆይ ይቅር በለን።

መሥዋዕተ አበው ዕጣነ ዘካርያስ የተቀበልክ አምላክ
የኛንም ተቀበል ምስጋናና ፀሎት፤ አሜን።

http://yonas-zekarias.blogspot.com/

Tuesday, 6 August 2013

//ከልጅነት እስከ ሽምግልና//



አባታችን አዳም ከህቱም ድንግል መሬት ከተፈጠረባት ሰከንድ ጀምሮ አምላኩ እግዚአብሔር ነበር። አባታችን ያዕቆብ ከልጅነቴ ጀምሮ የመገበኝ እግዚአብሔር ብሎ እምነቱን መሰከረ። ዳዊት ተቀበለውና ከማህጸን ጀምሮ አምላኬ ነህ ብሎ ይበልጥ አጸናው! 

ዳዊት በበገናው ከማህጸን ጀምሮ አምላኬ ነህ እንዳለ ከማህጸን ጀምሮ እስከ ሽምግልና አምላካችን እግዚአብሔር ነው። 

ትንቢተ ኢሳይያስ 46
3 እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ የእስራኤልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከሆድ ያነሣኋችሁ ከማኅፀንም የተሸከምኋችሁ፥ ስሙኝ።
4 እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፥ እስከ ሽበትም ድረስ እሸከማችኋለሁ እኔ ሠርቻለሁ እኔም አነሣለሁ እኔ እሸከማለሁ እኔም አድናለሁ።

/1/ ዘመዶቻችን ሆይ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላኬ ነው ብላችሁ የምታምኑት ከስንት ዓመታችሁ ጀምሮ ነው?

2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
3፥15 ((ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ )) መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።

/2/ ጢሞቴዎስ ከልጅነት ጀምሮ ኢየሱስ ክርስቶስን ያምናል። እናንተስ ከልጅነት ጀምሮ ክርስቶስን ታምናላችሁን?

ወደ ዕብራውያን
8፥11 እያንዳንዱም ጐረቤቱን እያንዳንዱም ወንድሙን። ጌታን እወቅ ብሎ አያስተምርም (( ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና።))

/3/ ከታናሽነታችሁ ጀምሮ ክርስቶስን ታውቃላችሁን?

/4/ የያዕቆብ መልእክት 2፦19 አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።
አጋንንት ያምናሉ የእናንተ ልጆች ምን ያምናሉ?

http://yonas-zekarias.blogspot.com/

Monday, 5 August 2013

የሶስቱ ዛፎች ልመና



በአንድ ደን ውስጥ ተጠጋግተው የሚኖሩ ሶስት እድሜ ጠገብ ዛፎች ነበሩ፡፡ እኚ ዛፎች ሁሌም ሲነጋም ሲመሽ የሚደጋግሙት ልማና (ጸሎት) ነበር፡፡

የመጀመሪያው ዛፍ፡-
‹‹ጌታ ሆይ ሁሌ እንደምለምንህ ሁሉ አሁንም እለምንሀለው፡ ይህንን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሀለው፡፡ የታላቅና የተከበር ንጉስ መኖሪያ ቤት እና ያማረ የከበረ ዘወትርም የሚወለወል የንጉሱ ዙፋን ሆኜ እንድሰራ አደራ እልሀለው፡፡›› ይህን የዘወትር ጸሎቱ አድርጎ ሁሌም ይለምን ነበረ፡፡

ሁለተኛው ዛፍ፡-
‹‹አምላኬ ሆይ ይህው ዛሬም እንደወትሮዬ ይህን አንድ ነገር እለምንሀለሁኝ እርሱንም እንዳትነሳኝ እማጸንሀለው፡፡ ታላቅ መርከብና እጅግም ግዙፍ ሆኜ ማዕበልና ንፋስ የማይሰብረው ጠንካራ መርከብ እሆን ዘንድ፡፡ የሚያየኝም የሚገረምብኝ ብዙ ሰዎችንም የምሸከምና አስፈሪውን ማዕበል የሚሻገሩበት ውቂያኖሱኑም የሚያቋርጡበት ምርጥ መርከብ እሆን ዘንድ ነውና ይህን አትንሳኝ አደረህን›› ይል ነበር በነጋ በጠባ

ሶስተኛው ዛፍ፡-
‹‹ጌታዬ ሆይ አሁንም ልክ እንደ ቀነደመው ልመናዬ የተወቀ ነው አምላኬ ሆይ ከሁሉ ልቄ ከፍ ብዬ እንድታይና ብዙም ሕዝብ መጥቶ እኔን በመጎብኘት ከጥላዬም በታች ተቀምጦ አሩሩን ጸሐይና የዝናቡን ጠፈጠፍ እንዲያሳልፍ በስሪም በርካታ ሕዝብ ያርፍና ከፍ ብዬ ከሁሉም ልቄ እንድታይ ነው›› እያለ ይጸልይ ነበር ዘወትር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን አንድ ምስኪንና ደካማ ኑሮውን እንጨት በመሸጥ የሚተዳደር ሰው እነዚህ ዛፎች ወዳሉበት ጫካ ገባ፡፡ ከዚያም የሚቆርጠውን ዛፍ ሲፈልግ እነዚህን ሶስት ዛፎች ለዓይኑ ስላማሩት ሶስቱንም ዛፎች ለመቁረጥ ምልክት አደረገና ተራ በተራ ቆረጣቸው፡፡
ከዚያም የመጀመሪያውን የቆረጠውን ጣውላ ያደርገውና ለአንድ ገበሬ ይሸጥለታል፡፡ ይህም ገበሬ በጣም ቆንጆ ጣውላ በማግኘቱ ወደቤቱ ይዞት በመሄድ ከብቶቹ ይመገቡበት ዘንድ ለከብቶች መመገቢያ ሰራበት፡፡ ይህን ግዜም ጸሎቱ ያልሰመረለት ይህ ዛፍ እንዲህ ሲል ማማረር ጀመረ ጌታ ሆይ ይህን ያህል ዘመን ስለምን የነበረው ይህን ፈርቼ ለንጉስ መቀመጫ እሆን ዘንድ ነበር፡፡ አንተ ግን ጸሎቴን ቸል ብለህ ለከብቶች መመገቢያ አደረከኝ ብሎ ተማረረ፡፡

እንጨት ሻጩ ሁለተኛውንም ዛፍ ቆረጠና ጥሩ ጣውላ አውጥቶ አሁንም ይህን ጣውላ ለአንድ አሳ አጥማጅ ሸጠለት፡፡ አሳ አጥማጁም ጣውለው ቆንጆ መሆኑን ሲያይ አሳ ለማጥመጃ እንዲሆነው መለስተኛ ጀልባ ሰረበት፡፡ አሁንም ይህኛውም ዛፍ ጸሎቱ እንዳልሰመረለት ሲያውቅ ልክ እንደቀደመው ፈጣሪውን ማማረር ጀመረ፡፡ ጸሎቴ ለዚህ እንድበቃ አልነበርም አንተ ግን ተውከኝ ለብዙዎች ተሸካሚ እና አሻጋሪ መሆን ስሻ አንተ ግን በዚህች አነስተኛ የአሳ ማጥመጃ ላይ ጣልከኝ፡፡ ብሎ ተማረረ

ይህ እንጨት ፈላጭ ሶስተኛውንም ዛፍ ቆርጦ አምጥቶ ለአንድ አናጺ ሸጠው፡፡ አናጺውም በጣም ጠንካራና ቆንጆ ጣውላ መሆኑን ሲያስብ ወስዶ ምንም ሳይሰራበት ወደ መጋዘኑ አስገብቶ አስቀመጠው፡፡ ይሄኔ ይህም ዛፍ ጸሎቱ እንዳልሞላለት ሲሰማው በጣም በማዘንና በመተከዝ አሁንም እንደቀደሙት ዛፎች ሁሉ ማማርር ጀመረ፡፡ ጌታ ሆይ ለሁሉ መጠለያያ እና ከፍ ብዬ መታየትን ስመኝ እንዲህ ባለ ስፍራ ያለምንም አገልግሎት እንድቀመጥ ታደርገኛልህን ብሎ በጣም በማዘንና በመተከዝ ምሪቱን አሰማ፡፡

ከብዙ ጊዜያት በኋላ እግዚአብሔር የነገሩትን የማይረሳ የጠየቁትን የማይነሳ አምላክ ነውና፡፡ የእነዚህን ዛፎች ልመና ለመመለስ ወቅቱን ጠብቆ ተገለጠ፡፡ ዛፎቹም ከሚሽትና ከሚጠብቁት በላይ እጥፍ የሆነን ምላሽ ለመስጠት አምላክ በስጋ ተገለጠ፡፡
ከቅድስት ድንግል ማርያም ሲወለድ በገብቶች ማደሪያ ነውና የሁሉ ጌታና ንጉስ የመጀመሪያውን ዛፍ ጥያቄ ለመመለስ በከብቶች ግርግም ላይ ተኛ፡፡ ይህም ግርግም እስካሁን በዓለም ላይ ከተወለዱ ታላላቆች እንኳን ሊደርሱበት የማይችል ታላቁ የዓለም ፈጣሪ ተኛበትን ጥያቄው ተመለሰ

ቀጥሎ ጌታ ቀስ በቀስ በጥበብ ካደገ በኋላ በአንድ ባሕር አጠገብ በጣም ብዙ ሕዝብ ተሰብስቦ ስለነበር ጌታም ትንሽ ጀልባ ሲያይ የጀልባው ባለቤት የነበረውን አሳ አጥማጅ አስፈቅዶ ጀልባው ላይ ሆኖ ብዙ ሕዝብ ከሞት ወደ ሕይወት ይሻገር ዘንድ ጀልባው ላይ ሆነ ሕዝቡን አስተማረ በርካቶችም ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገሩ፡፡ ይህም ጀልባ እስከዛሪ ድረስ ወንጌል በተሰበከ ቁጥር ዝናው ይነጋራ፡፡ ጌታም በእርሱ ላይ የመዳንን ቃል ተናግሯልና ብዙዎችንም አጥምዶበታልና፡፡

ከዚያም በመቀጠል ሶስተኛውን ጥያቄ ለመመለስ ጌታ የሞት ፍርድ ተፈረደበት ሞቱም በተመሳቀለ እንጨት እንዲሆን ተወሰነ፡፡ በዚህም ሰዓት እሱን ለመስቀል የሚያስፈልገውን እንጨት ሲፈልጉ ከዚያ ከጠራቢው መጋዘን ስላገኙ ወስደው መስቀል ሰሩበትና በቀራኒዮ አደባባይ ከፍ አድርገው ሰቀሉት፡፡ ይህው እስካሁን ድረስ እርሱ የተሰቀለበት መስቀል በዓለም ላይ ከፍ ብሎ ይታያል ብዙዎችም በእርሱ እየተጠለሉ በደሙ በቀደስው ቅዱስ መስቀል ከመከራ አርፈዋል፡፡

እግዚአብሔር እኮ እጅግ በጣም ደግ ነው፡፡ እርሱ እየደከመ እየሞተና እየተሰቃዬ የልጆቹን ጥያቄ አንድም ሳያይቀር ይመልሳል፡፡ እግዚአብሔር በእውነት ታማኝ ነው የሰው ልጅ ግን ችኩል ነው ማስተዋልም የተለየው ነው፡፡

ወዳጄ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚሰራ አታውቅምና አትከራከር ብቻ አንተ ጸልይ እርሱ ቢያዘገይብህም ለተሻለ ነገር ትከሻህን እየሰፈረው ነውና አንተ ብቻ ጸልይ ጸልይ……. ተባርክልኝ ጌታዬ ክብርም ሁሉ ለአንተ ይሁን አሜን!!

አንብበው እንደጨረሱ ለወዳጆቹ አካፍሏቸው
http://yonas-zekarias.blogspot.co.uk/
284Unlike ·  ·