Monday, 20 August 2012

“በሐሳብሽ ድንግል ነሽ”





አባታችን ሆይ ብለን ስንጸልይ ‹‹በሐሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ›› እንላለን። ሰዎች ደግሞ ይጠይቃሉ። እንዲህ እያሉ። በሥጋ ድንግል ናት አላችሁ። መጽሐፉም መስክሯልና መከራከር ያስቸግራል። በነፍሷ በሕሊናዋ ድንግል ናት የምትሉት በምን አወቃችሁ? አሉን።

እኛም መለስን። እንዲህ እያልን። 

ጌታ መጽሐፍን ስለማትመረምሩ ትስታላችሁ ብሎ ነበርኮ። ሉቃስ ምን ነበር ያለው? ‹‹ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው ብላ አሰበች›› ይላል፡፡ (ሉቃ1.29) ‹‹አሰበች›› ማለቱን ልብ በሉ፡፡ ይህን አለች ቢል ሰምቶ ነው፤ ይህን ሠራች ቢል አይቶ ነው ይባላል፡፡ ‹‹አሰበች›› ሲል ምን እንላለን? የክርስቲያኖች መልስ አንድ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ምን እንዳሰበች ገልጾለት ነው እንላለን፡፡ ሰይጣንና መናፍቃን የሚሉት አያጡምና ምናልባት ገምቶ ነው ሊሉ ይችላሉ፡፡ መቼም በዚህ አይሳቅም!!! መጸለይ ነው እንጂ፡፡


አንድም ‹‹ይህን ሁሉ ነገር በልቧ እያሰበች ትጠብቀው ነበር፡፡›› ሲል መስክሯል፡፡ (ሉቃ2.19 ሉቃ2.51) መንፈስ ቅዱስ በልቧ ያለውን ካልገለጠለት ‹‹በልቧ እያሰበች ትጠብቀው ነበር›› እያለ ሊናገር እንዴት ደፈረ? በሰው ልብ ያለውን ከመንፈስ ቅዱስና ከሰውዬው በቀር ማንም ሊያውቅ እንደማይችል ቅዱስ ጳውሎስ ጽፎ የለምን? (1ቆሮ2.11)
ድንግል ማርያም በሕሊናዋ የዚህ ዓለም ምኞት አልነበራትም፡፡ እንኳን ኃጢአቱና ኃጢአት ያልሆነውም ሥጋዊ አኗኗር በልቧ አልነበረም፡፡ ይህም ማለት ‹‹አግብቼ ወልጄ መልካም እየሠራሁ ቤተሰቦቼን እየረዳሁ እኖራለሁ›› የሚለው አሳብና ምኞት በውስጧ አልነበረም፡፡ ይህም ፈጣራ ሳይሆን በቅዱስ ዳዊት የትንቢት ቃል ይታወቃል፡፡ ስለ እርሷ ‹‹ልጄ ሆይ ስሚ ጆሮሽን አዘንብዪ የእናትሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ›› ብሏል፡፡ ምእመናን! አባቷ ዳዊት እረ ስሚኝ፣ ጆሮ ስጪኝ እያለ ለምኖ ሲያመሰግናት ስሙ!!
‹‹
እርሺ›› ማለት ምን ማለት ነው? አታስቢ ማለት አይደለምን? የምትረሳውስ ምንድር ነው? የእናት የአባቷን ቤት ነው፡፡ ይህ ማለት የእናት የአባትሽን ቤት አትመኚ! እንደ እነርሱ አግብቼ፣ ወልጄ እኖራለሁ ብለሽ አታስቢ ማለት ነው፡፡ ልብ በሉ! ቅዱስ ዳዊት ነቢይ ነው፡፡ እርሷ ይህን ዓለም እንድትረሳ የመከራት እንዳይመስላችሁ፡፡ እንደምትረሳው አውቆ በፈሊጥ ትንቢት ተናገረ እንጂ፡፡ አነጋገሩ እኮ ‹‹አቤቱ ተነሥ›› እንደሚለው ዓይነት ትንቢት ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት ይህን ቃል ብዙ ጊዜ ደጋግሞ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ተናግሮታል፡፡ (መዝ131.8) ኢየሱስ ክርስቶስ ዳዊት ‹‹ተነሥ›› ስላለው የተነሣ ይመስላችኋል? እንደሚነሣ አውቆ ትንቢት መናገሩ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እንዲሁ ‹‹እርሺ›› ቢልም እንደምትረሳው አውቆ ትንቢት ተናገረ እንጂ ያስረሳት ዳዊት አይደለም፡፡

አንድም አብርሃም ማለት አበ ብዙሃን /የብዙሃን አባት/ ማለት እንደሆነ ማሪሃም ማለት እመ ብዙሃን /የብዙሃን እናት/ ማለት ነው። በዮሐንስ በኩል ለሁሉ እናት ትኾን ዘንድ ተሰጥታናለችና። አንድም መልአኩ በትንቢተ ነቢያት በመላእክት ደስ የተሰኘሽ ምልዕተ ክብርት ሆይ ደስ ይበልሽ አላት። አንድም የመላኩን የምስጋና ቃል ሰምታ ብትደነግጥ ኢትፍርሂ እሙ እያለ አረጋጋት። መላእክት የፈሩትን ማረጋጋት ልምዳቸው ነውና። ኢትፍራህ ዳንኤል ኢትፍራህ ዘካርያስ እያለ አረጋግቷቸዋልና። 

አንድም መልአኩ ትጸንሲ ዘእንበለ ዘርአ ብእሲ ባላት ጊዜ እመቤታችን ምድር ያለ ዘር ታፈራ ዘንድ ሴት ያለ ወንድ ትጸንስ ዘንድ እንዲህ ያለ የምስራች ከማን አገኘኸው አለችው። መልአኩም እስመ አልቦ ነገር ዘይሳኖ ለእግዚአብሔር /ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና/ አላት። ይኩንኒ በከመ ትቤልኒ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ አለችው። ይህን ቃልዋን ምክንያት አድርጎ አካላዊ ቃል በማሕጸንዋ ተቀረፀ። 

አንድም መልአኩ የኤልሳቤጥን መጸነስ ቢነግራት እመቤታችን ተደስታ ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ ገሠገሠች። ስለ ሦስት ነገር ሔዳለች። ዘካርያስ ዲዳ ሆኗል ብለዋታልና። ኤልሳቤጥ ጸንሳለች ብለዋታልና። ዮሐንስም በማህጸን እያለ ይሰግዳልና። ኤልሳቤጥ የእመቤታችንን የሰላምታ ድምጽ ሰማች። ያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ መላባትና ድምጿን ከፍ አድርጋ የጌታዬ ናት ወደኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይኾንልኛል ብላ አመሰገነች። ኤልሳቤጥ የቀድሞ አነጋገርዋ የቀዘቀዘ ነበር። የእመቤታችንን የሰላምታ ድምጽ ስትሰማ ግን ድምጿ ከፍ አለ። መንፈስ ቅዱስ ሞልቶባታልና። አንፈራጸ እጓል በውስጠ ከርስየ /ጽንሱ በማሕጸኔ በደስታ ዘሏል/ አለች። መንፈስ ቅዱስ ያደረባት ኤልሳቤጥ ስለ ጽንስ መንቀሳቀስ ተገርማ አይደለም ይህን ያለችው። የሰላምታሽ ድምጽ ጽንሱን አሰገደ ስትል ነው እንጂ! 

Visit this Blog! http://yonas-zekarias.blogspot.com/
 ·   ·  · Share · Edit
·                                  
·                                
·                                 88 shares
·                                  
o                                                       
Etnesh Lemma EGNA BEHASABUWAM BESEGAWAM DINGEL ENDAHONACH ENAM ANALEN KE SETOCH HULU TALAYITA NESIT KEBERET ENDA HONACE ENAMINALEN!!! LAMIKARAKARUT GIN EGZIHABER ASITAWAY LIBONA YISTACHEW AMEN,,,!!!
o                                                       
Negassi Hafte Kalehiwot yasemalin!!!
o                                                       
Alemtsehay Assefa kale hiwot yasemalin
o                                                       
Helen Hagos አሜን! ቃል ህይውትን ያሰማልን!!!
o                                                       
Atenasia Yohannes ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
o                                                       
Amen k.H.Y
o                                                       
Bitania Birhanu Bmahten kene lmariam tesma: bterarama hagr befram ketma: yohanes ynagr breha yadgw: dngel setnagr men endazelelw.
June 23 at 11:03am ·  · 2
o                                                       
Esayas Habte Haile Betame yamerale
o                                                       
Tsige Tena · Friends with Frehiwot Melese and3 others
ewnentah newe!!!!!!!
o                                                       
Addis Duga · Friends with Bewket Bush
Dengell hoy ynakush hulu wede egersh xama ysegedalu. Se'alilen kidest weladet amelak.
June 23 at 10:54pm ·  · 1

No comments: