ምንኩስና ከሌለ ጵጵስና የለም
ዘና ብላችሁ ተቀመጡና አንድ አሪፍ ታሪክ ላውጋችሁ!
በደማቅዋ የለንደን ከተማ ደማቅዋን የቅዳሜ ፀሐይ እየሞቅኩ ነበር። እቴጌ ጣይቱም የደላህ አንተማ ምን አለብህ እቴ፤ “ምንም ያህል ቢበርደው ቅቤ ፀሐይ አይሞቅም” አሉና አሳቁኝ። እኔም እቴጌ አልሰሙም እንዴ? “ኑሮ ካሉት ፍሪጅም ይሞቃል አለ እኮ ቅቤ” አልኳቸው። እቴጌ ጣይቱም ትንሽ ፍግግ ብለው የወርቅ ጥርሳቸውን ብልጭ አደረጉና እንደለመዱት የቅዳሜ ጨዋታቸውን እንዲህ ብለው ቀጠሉ።
የዘመኑ አብርሐም የተባለለት እጅግ ደግ ሰው ነበር አሉ። ይህ ሰው ያለውን ከድሆች ጋ ተካፍሎ መብላት ይወድ ነበር። ሰዎች ግን ቀኑበት። ሰይጣን ራሱን ገምሶ “አብርሐም ተቀይሯል” ብሎ እንደቀናበት በዚህ ሰውም ቀናበት። ሰዎች ሁሉ “የሰውን ሥጋ ይበላል” እያሉ ስሙን አጠፉ። ይህ ሰው እንደለመደው በአዲስ ዓመት በዓል ከበሬ ቅርጫ የተወሰነ ቀንሶ ለድሆች ሊሰጥ ቤቱ አስገባ። ይህን ያየ “መቻል" የተባለ ውሻ በጓሮ በር ቆርቆሮውን ገንጥሎ እየሮጠ ወደ ሰውየው ቤት ገሠገሠ። ያ ሰው ለሚስቱ ድምጹን ከፍ አድርጎ ኧረ ያንን “የሰው ሥጋ” ውሻው እንዳይበላ አላት። ሰዎች ሁሉ ክው አሉ። በቃ! የሰው ሥጋ ይበላል ተባባሉ። ሰውየውም መቻል የተባለውን ያንን ውሻ እያሻሸ እንዲህ ብሎ ገጠመ፦
ሁለት ውሾች አሉኝ የማሳድጋቸው
አንዱ ሰምቶ ማለፍ ሌላው መቻል ናቸው!!
በደማቅዋ የለንደን ከተማ ደማቅዋን የቅዳሜ ፀሐይ እየሞቅኩ ነበር። እቴጌ ጣይቱም የደላህ አንተማ ምን አለብህ እቴ፤ “ምንም ያህል ቢበርደው ቅቤ ፀሐይ አይሞቅም” አሉና አሳቁኝ። እኔም እቴጌ አልሰሙም እንዴ? “ኑሮ ካሉት ፍሪጅም ይሞቃል አለ እኮ ቅቤ” አልኳቸው። እቴጌ ጣይቱም ትንሽ ፍግግ ብለው የወርቅ ጥርሳቸውን ብልጭ አደረጉና እንደለመዱት የቅዳሜ ጨዋታቸውን እንዲህ ብለው ቀጠሉ።
የዘመኑ አብርሐም የተባለለት እጅግ ደግ ሰው ነበር አሉ። ይህ ሰው ያለውን ከድሆች ጋ ተካፍሎ መብላት ይወድ ነበር። ሰዎች ግን ቀኑበት። ሰይጣን ራሱን ገምሶ “አብርሐም ተቀይሯል” ብሎ እንደቀናበት በዚህ ሰውም ቀናበት። ሰዎች ሁሉ “የሰውን ሥጋ ይበላል” እያሉ ስሙን አጠፉ። ይህ ሰው እንደለመደው በአዲስ ዓመት በዓል ከበሬ ቅርጫ የተወሰነ ቀንሶ ለድሆች ሊሰጥ ቤቱ አስገባ። ይህን ያየ “መቻል" የተባለ ውሻ በጓሮ በር ቆርቆሮውን ገንጥሎ እየሮጠ ወደ ሰውየው ቤት ገሠገሠ። ያ ሰው ለሚስቱ ድምጹን ከፍ አድርጎ ኧረ ያንን “የሰው ሥጋ” ውሻው እንዳይበላ አላት። ሰዎች ሁሉ ክው አሉ። በቃ! የሰው ሥጋ ይበላል ተባባሉ። ሰውየውም መቻል የተባለውን ያንን ውሻ እያሻሸ እንዲህ ብሎ ገጠመ፦
ሁለት ውሾች አሉኝ የማሳድጋቸው
አንዱ ሰምቶ ማለፍ ሌላው መቻል ናቸው!!
ከላይ ስጀምር “ዘና ብላችሁ ተቀመጡ” እንዳልኩ አሁን ደግሞ “ኩርምት ብላችሁ ተቀመጡ”
ባልልም እስኪ አንድ ቁም ነገር እንጫወት።
እርሻ የተባሉ ገዳማትን
እንጠብቅ እንጂ
ገዳማትን እርሻ አናድርጋቸው!!”
ከወራት በፊት በአንድ ጉባኤ ላይ ያሳለፍኩትን አንድ ልብ የሚሰቅል ውሎ ላካፍላችሁ። ጉባኤው የተካሄደው በደማቅዋ በለንደን ከተማ ነበር። የጀር ቅ/ ሥላሴ ገዳምን ለመርዳት ታስቦ የተከናዋነ ነው። የጀር ቅ/ ሥላሴ ገዳም የተመሰረተው በ15ኛው መክዘ በዘመነ ኢያሱ ነበር። ይህ ገዳም እጅግ ክቡር ነው። 20 እና 40 ዓመታት የዘጉ ክቡር ባሕታዊያን የሚፈልቁበት ምንጭ ፣ የሚያድጉበት እርሻ የጀር ቅ/ሥላሴ ገዳም ነው። ቅ/ጳውሎስ በዕብራዊያን መልዕክቱ እንዳለው ዓለም ለእነሱ አልተገባቸውምና በዚህ ክቡር ገዳም ዳዋ ጥሰው ዋዕይ ቁሩንም ታግሰው ፣ ዳባ ታጥቀው ደንጊያ ተንተርሰው ፣ ድምፀ አራዊትን ፀበ አጋንንትን ታግሰው የሚኖሩ ባሕታዊያን አሉ። በሌላ ስፍራ ዘግተው የሚኖሩ ባሕታዊያን በጀር ቅ/ሥላሴ ገዳም ሲመጡ ቡዙ ቀን እንዃን መቆየት አይችሉም። ይህች ቦታ የተፈቀደችው ለተመረጡት ነውና። ለዚህ ነው ይህ ገዳም ክቡር ነው ያልኩት።
በዚህ ክቡር ገዳም ቅዳሴ እና ሰአታት ሲቆሙ ሁል ጊዜ ከአጠገባቸው የሚቆም አንድ ሐሳብ አለ። ለቅዳሴ የሚቆሙበት ጧፍ ያልቅብኝ ይሆን? የሚል ሐሳብ። ባሕታዊያኑ ጧፉ እንዳያልቅባቸው እፍ እያሉ ያስቀድሳሉ! እፍ ተብላ የጠፋችው የጧፍ ቁራጭ ለሚቀጥለው ቀን ትሆናለችና! ይህ የባህታዊያኑ ሕይወት ነው። የባህታዊያኑ እጅ ለስንቱ ይዘርጋ? እጃቸው መዘርጋት ያለበት ለጸሎት ነው ወይስ ለልመና? አሁን የሚያስፈልገው “የዛሉ እጆችን” መደገፍ ነው።
“የዛሉ እጆች!”
ወዳጄ ሆይ! ለእኔ ብለህ ስማ አልልህም ለቤተክርስቲያን ብለህ ስማ ልበልህ እንጂ። ሰሞኑን እናት ቤተክርስቲያን መልካም እረኛ ደግ ፓትርያርክ ለመምረጥ በጸሎት ተጠምዳለች። ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለተናዊ ዕድገት ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት የሚበጅ ተተኪ አባት (ፓትርያርክ) ለቤተ ክርስቲያኗ እግዚአብሔር ባወቀ መርጦ እንዲያስቀምጥ በመላዋ ኢትዮጵያና በውጭ ሀገር በሚገኙት አህጉረ ስብከት፣ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት ከጳጉሜን 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 10 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል። ሱባኤው የታወጀው በተሰበረ ልቡና፣ በሰቂለ ኅሊና ሆነን ጸሎታችንን ወደ አምላካችን እንድናደርስ ነው። መጪው አዲስ ዓመት እና ተያያዥ በዓላት መሆናቸው ግልጽ ከመሆኑ ጋ አንዳንዶቻችሁ እንደጠየቃችሁት “በዓሉን በጾም እንድናሳልፍ” የሚጠይቅ ውሳኔ ሳይሆን ለዚሁ ታላቅ ጉዳይ ብቻ በአንድ መንፈስ ጸሎታችንን እንድናደረግ ብቻ ነው። እናንተም ይህን ብርቱ ጉዳይ በጸሎታችሁ ቸል እንደማትሉት የታመነ ነው። ከእልፍ አእላፋት ከብዙ የወፎች ጩኸት መካከል የልጇን ድምጽ መስማት የምትችል በአፈጣጠሯ ለየት ያለች አዕዋፍ አለች። ማን ያውቃል ከኛ መካከል እንደ ጫጩቷ ድምፁ የሚሰማለት ይኖራል። እስኪ እንጩኽ። እስኪ ድምጻችሁ የሚሰማላችሁ ደግ እረኛ ለቤተክርስቲያን ደግ መሪ ለኢትዮጵያ ስጥ ብላችሁ አብዝታችሁ ጩኹ።
ዋልድባን የመሰሉ ገዳማት ከሌሉ አቡነ ተክለሃይማኖትን የመሰሉ መነኮሳት አይኖሩም። ዋልድባን የመሰሉ ገዳማት ከሌሉ አቡነ ጴጥሮስን ፣ አቡነ ሲኖዳን የመሰሉ ፓትርያርክ ለማግኘት እንደጎመጀን ይቀራል!! ጳጳሳቱ ፣ ፓትርያርኩ የሚገኙት ከገዳማት ነው። አቡነ ሲኖዳን የመሰሉ ኅሩይ የተመረጡ አባት የሚገኙትም ከገዳማት ነው። “እርሻው ሲያምር ዳቦው ያምር” አሉ እቴጌ ጣይቱ።
==> በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ገዳም አቡነ አረጋዊ የገደሙት ደብረ ዳሞ (ዙር አባ) ነው። በዚህ ገዳም አባታችን አቡነ አረጋዊ ለሠራዊቱ የሚሆን ውኃ እንዲፈልቅ በሚጸልዩበት ጊዜ 40 ምንጭ ፈልቋል።
==> በዓለም የመጀመሪያው ባህታዊ አባ ጳውሊ ሲሆን በዓለም የመጀመሪያውን ገዳም የገደመው ደግሞ አባ እንጦንስ ነው።
==> አባ ጳውሊ ከወንድሙ ጋር የአባታቸውን ንብረት በሚካፈሉበት ጊዜ ተጣሉ። በመንገድ ላይ ሲሄዱም ሰዎች አንድ የሬሳ ሳጥን ይዘው ሲጓዙ አዩ፤ አባ ጳውሊም የእኔም መጨረሻ ይኸው ነው! ወንድሜ ሆይ ከአንተ ጋር አልጣላም ብሎ ከኋላው ቀስ እያለ ተጓዘ፤ በመጨረሻም መንገዱን ቀይሶ ወደ በረሃ በመግባት በዓለም የመጀመሪያው ባህታዊ ሆኗል!
==> አባ እንጦንስም በቤተክርስቲያን ወንጌል ሲነበብ ሰማ፦ ፍጹም መሆን ብትፈልግ ያለህን ንብረት ሽጥና ተከተለኝ ማቴ [19: 22] የሚለውን ቃል ሰምቶ ያለውን ንብረት ሽጦ በዓለም የመጀመሪያ የሆነውን ገዳም በግብጽ ምድር መሰረተ!
==> እንደነ አብርሐም መርዓዊ ከጫጉላ ቤታቸው ወተው ገዳማዊ ህይወትን የኖሩ ታላላቅ አባቶች አሉ።
==> ገዳማዊ ህይወትን ለአባቶችችን ያስተማሩትም መድኃኒተ ዓለም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ነቢዩ ኤልያስና መጥምቁ ዮሐንስ ናቸው።
“ለገዳም የረዳ አይጎዳ” አሉ እቴጌ ጣይቱ! በውጪ ያላችሁ ታማኝ ልጆች እስቲ የቻላችሁትን አድርጉ። ሀገር ቤት ስትገቡ ገዳማትን መጎብኘት እንደ ዕቅዳችሁ ያዙና የቻላችሁትን ትንሿን ስራ ለመስራት አስቡ።
ትሰሙ እንደሆነ የወንጌል ቃል
አለመስጠት ያፀድቃል!
(ወንጌል መስጠት ያጸድቃል አለ)
መቼም እናንተ ሁሉን ታውቃላችሁና ለእናንተ ማስረዳት ቀባሪን ማርዳት ይሆንብኛል ብዬ እፈራለሁ። በለንደን በተካሄደው ጉባኤ ላይ ክርስቲያኑ የቻለውን ለማድረግ ሞክሯል። ጨረታ ተጫረትን፤ የገቢ ማሰባሰቢያም ተደረገና ወደ ፫ሺህ ፓውንድ ተሰበሰበ። ይህን በብር ዘርዝራችሁ እናንተው ድረሱበት። “ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም” አሉ እቴጌ። አንድ ልቤን የነካ ነገር ልንገራችሁና ሐሳቤን ልቋጭ። በመጀመሪያ ለጨረታው የተመረጠው የገዳሙ መስራች የአቡነ ኢያሱ ገድል ነበር። ይህን ገድል በ £10 ተጀምሮ እስከ £300 ፓውንድ ድረስ ቀጠለ። እንዲሁ ሌሎችም ጨረታዎች ተካሄዱ። በመጨረሻ ለጨረታው እድለኛ የሆኑ ሽልማታቸውን ሊወስዱ ወጡ። የራሳቸውንም ንግግር አደረጉ። ይህ አባባል ግን የሁላችንንም ልባችንን ሰበረ። አስለቀሰንም። አቶ አይናለም የተባሉ ምዕመን ይህን ጨረታ የተጫረትኩት የራሴ ምክንያት ስለነበረኝ ነው። ልጄ ገና ታናሽ ብላቴና ነው። ነገር ግን ምግብ መብላት ፈፅሞ አይችልም። ምግቡን የሚያገኘውም በሆዱ በጉሉኮስ ነው። [አቶ አይናለም ይህን ሲናገሩ ዕንባቸው ከንግግራቸው ይቀድም ነበር] እንደማንኛውም ወንድሞቹና እህቶቹ መመገብ እንዲችል ይህን ገድል ገዝቼ በእምነት ልጄን እዳብሰዋለሁ። እናንተም “ሰይፈ ሥላሴ” ብላችሁ ፀልዩለት አሉ እንባ እየተናነቃቸው።
በታሪኩ ልቤ ተነካ። የቅ/ጳውሎስ የልብሱ ቁጨት ሕሙማንን ፈውሷል። የጻድቁ ገድልም ልጁን ይፈውስ ይሆናል ማን ያውቃል? በእምነታቸው ፅናትም ተገረምኩ። ጌታ በወንጌል ላይ 2 ግዜ ብቻ ተደነቀ ተብሎ ተፅፏል። አንደኛው በቅፍረ ናሆም ነዋሪዎች በእምነታቸው መቀዝቀዝ ነበር። ከአስራ አንድ በላይ ታላላቅ ተዓምራትን በፊታቸው ቢያደርግላቸውም የናሆም ከተማ የቅፍረ ናሆም ነዋሪዎች ግን በእምነታቸው ቀዝቃዛ ነበሩ። ሌላው ጌታችን የተደነቀው በሮማዊው ወታደው በእምነቱ ፅናት ነበር። ሮማዊው ወታደር “ቃል ብቻ ተናገር ልጄም ይፈወሳል” ብሎ ታላቅ እምነቱን መሰከረ። ጌታም ልጁን ፈወሰለት። አቶ አይናለምም እንደ ሮማዊው ወታደው “ቃል ብቻ ተናገር ልጄም ይፈወሳል” አሉ። እንደ እምነታቸው ይደረግላቸው፤ አሜን።
ገዳም ከሌለ ምንኩስና የለም
ምንኩስና ከሌለ ጵጵስና የለም
ጵጵስና ከሌለ ፕትርክና የለም! ምንኩስና ከሌለ ጵጵስና የለም