Monday 20 August 2012

የዲያቢሎስ መንግሥት




ዲያቢሎስ በአምሳለ ንጉሥ ዘውዱን ደፍቶ ከዙፋኑ ሁኖ ኃያላኑን በቀኝ በግራ በፊት በኋላ አቁሞ ታየ።

አንዱ የሌጌዎን አለቃ መጣ።

ዲያቢሎስም ከየት መጣህ አለው።

ከአንዲት ሀገር አለው።

ምን አድርገህ መጣህ አለው።

ባልና ሚስቱን ነገር ካለቀ በኋላ ነገር ሰርቼ ሊጋቡ ሲሉ አጣላኋቸው አለው። 

በስንት ጊዜህ ነው አለው። 10 ቀኔ አለ።

ይህችማ ቀላል ስራ ናት በል አሁኑኑ ከባድዋን ስራ ሰርተህ ና፤ በል ውጣ! አለው። እየከነፈ ወጣ። 


ኹለተኛው ሌጌዎን መጣ። አንተስ ምን ሰራህ አለው።

ወንድማማቾችን አባልቼ አጣልቼ መጣሁ አለው። 

በስንት ጊዜህ ነው አለው። 30 ቀኔ አለ።

ይህችማ ቀላል ስራ ናት በል አሁኑኑ ከባድዋን ስራ ሰርተህ ና፤ በል ውጣ! አለው። እየከነፈ ወጣ።

ሦስተኛው ሌጌዎን መጣ። ምን ሰርተህ መጣህ አለው።

40
ዘመን የዘጋውን መነኩሴ አስቼ ዓለማዊ ስራ አሰርቼ መጣሁ አለው። 

በስንት ጊዜህ ነው አለው። በመነኩሴው እድሜ ልክ ዘመኑን ሙሉ ተዋግቼዋለሁ አለ።

አንተንስ ሊያነግሡህ ይገባል ብሎ ከዙፋኑ ወርዶ ዘውዱን ደፍቶ አነገሠው። 

ጌታችን በወንጌል እርስ በእርሱ የተለያየ መንግሥት አይጸናም እንዳለን የዲያቢሎስ ሠራዊት እንዲህ ዘመናቸውን በሙሉ የሚዋጉ አሉ። ቀላል ስራ ሰርታችኋል ጨምሩ እየተባሉ የሚላኩ አሉ። /ጴጥሮስ እንዲህ ብሏል።


ዲያቢሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ በዙሪያችሁ ይዞራል” /እስመ ጸላኢክሙ ጋንኤን ይህጥር ከመ አንበሳ ዘይኃስስ ዘይውኃጥ/ ሉቃስ ያዕቆብ [22:31] 1 ጴጥሮስ [5:8] 

ምንም እንኳን ዲያቢሎስ እንደ ሚያገሳ አንበሳ በዙሪያችን ቢዞርም በእምነት ሆነን ልንቃወመው ይገባል፤ዲያቢሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ በዙሪያችሁ ይዞራልካለ በኋላ ወረድ ብሎ ቁጥር 9 ላይበእምነት ሆናችሁ ተቃወሙትይላልና።

Visit this Blog! http://yonas-zekarias.blogspot.com/
 ·   ·  · Share · Edit
·                                  
·                                
·                                 5 shares
·                                  
o                                                       
Fitsum Zemichael ቃለ ሕይወት ያሰማልን ወንድም !!!!
June 16 at 9:42am ·  · 1
o                                                       
Genet Damesa YEHYWET KAL YASEMALN !!!!
June 16 at 9:44am ·  · 1
o                                                       
Abiti Love Q H Y...kedanemeheret ateleyeh
June 16 at 10:20am ·  · 1
o                                                       
Mieraf W Giorgis tebarek bro yonas.
o                                                       
Fikirte Getachew Edeme yestlen.

No comments: