Friday 31 August 2012

“የፍቅር ዓይነቶች”


ሽሮን ሲሸውዷት ፕሮቲን ነሽ አሏት!” አንዲት የሰፈር ጓደኛዬ ፀጉሯን ምን ውስጥ እንደምትነክረው አላውቅም ብቻ ዘመናዊ ነኝ ለማለት እንደ ቀስተደመና በየቀኑ የፀጉሯን ቀለም ትቀያይረዋለች፤ ሰኞን ስለማትወደው ጥቁር ቀለም፣ ማክሰኞን አረንጓዴ፣ እሑድን ሰማያዊ ቀለም እያለች ትዘምንብን ጀመር። ከፀጉር ቀለሟ የሚሄድ ጥብቅብቅ ያለ ሱሪ ትለብስና ጫማዋዋን ትጫማና ከላይ የልጅነቷ የሚመስለውን ጃኬት ጣል ታደርግና በቃ! ከተሜውን ታዳርሳለች! 

እቴጌ ጣይቱም የሰፈራችን የአቶቢስ ተራ እማ ወራዎችን ሰብስበው እንዲህ የሚል ግጥም ገጠሙላት፦

አየን አወራነው የፀጉርሽን ነገር
ትንሿን ኮትሽን ለትንሿ ልጄ ብትሰጪያት ትፀድቂ እኮ ነበር!
ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ
ይህች አንዲት ፍሬ ልጅ በፈረንጅ ተገዝታ ትዝናናብን ወይ
!

ከዚህች የልጅነት አብሮ አደጌ አፈር ፈጭተን ውኃ ተራጭተን ነውና ያደግነው የሆድ የሆዳችንን ሳንደባበቅ እንጨዋወት ነበር። እሺ…… ግጥም ተገጠመልሽ አሉ! አልኳት ነገር ፈልጌ። ይኹና! አለች አንገቷን ሰበቅ አድርጋ። ለምን እንዲህ እንደምሆን ታውቃላችሁ? አለች እያፈጠጠችብኝ። ኧረ አናውቅም አልኳት ወደ ኋላዬ እያፈገፈኩ። ለምን መሰለህ? እኔ ፍቅር ይዞኛል! በቃ ልሙት እንዴ? አለችና የፍቅር ዕንባዋን አወረደችው! አለቀሰች። ከቦርሳዋ ውስጥም ወደድኩት ያለችውን ሰው ፎቶውን አሳየችኝ። ወዲያው በአንድ መፅሐፍ ውስጥ የልጁን ፎቶ አድርጋ ሰጠችኝ። እኔም በጣም ከረጅም ጊዜ በኋላ ያንን መፅሐፍ ዛሬ ከልብሴ ሻንጣ ውስጥ አገኘሁትና በማስታወሻዬ ላይ ጻፍኩት! የልጅነት ጉደኛዬ የሰጠችኝ መፅሐፍ ርዕሱየፍቅር ዓይነቶችየሚል ነበር።

የፍቅር ዓይነቶች” (types of Love)

/1/ “
ሮማንቲክ ላቭ” /Romantic Love/

ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ሄሮድስ ነው። ሄሮድስ የወንድሙን የፊሊጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ያፈቀራት ስትደንስ አይቷትና ዳንሷም ስለማረከው ብቻ ነው። ይህ ዓይነቱ ፍቅርሄሮድሳዊ ፍቅርይባላል። ይሄኛው የፍቅር ዓይነት የሚይዛቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ የሰውነትን ቅርጽ ብቻ አይተው የሚያፈቅሩ ሰዎች ናቸው። ሌሎች መሰረታዊ ነገሮችን ለምሳሌ ሃይማኖት ባሕርይ አስተሳሰብ ወዘተ ተረፈዎችን ከቁም ነገር አይቆጥሩትም። ሮማንቲክ አፍቃሪዎች ብዙን ጊዜ ቀናተኛ ናቸው። ያፈቀሩት ሰው ከማንኛውም ሰው እንዲያዩት አይፈልጉም።

/2/ “
ፓሽኔት ላቭ” passionate Love

ስሜታዊ ፍቅር! ይህ ፍቅር ስሜታዊ ፍቅር ነው። ስሜታዊ ፍቅር passionate Love በጣም አስቸጋሪ የፍቅር አይነት ነው። ሕሊናን ረፍት ከመንሳቱ በላይ ሕይወትን የመመሰቃቀልና በጣም የማጨናነቅ ባህርይ አለው። ለምሳሌ ትምርትና ስራ መጥላት የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት ይገኙበታል። ስሜታዊ ፍቅር የሚቆየው ስሜቱ እስኪሳካ ሩካቤ ሥጋ እስኪፈፅም ድረስ ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ ግን መጀመሪያ ከወደደው ውድ ይልቅ በኋላ የሚጠላው ጥል ይበልጣል! ይህን የመሰለው ፍቅር በመፅሐፍ ቅዱስ የአምኖን ፍቅር /አምኖናዊ ፍቅር/ ይባላል።


/3/ “
ሎጂካል ላቭ” Logical Love

ይህ ፍቅር ጣራና መሰረቱመመሳሰልየሚለው ቃል ነው። እነዚህ ፍቅረኛሞች የሚመሩት በሎጂክ ነው። ለምሳሌ እሷ ድግሪ ካላት የምትመርጠው ድግሪ ያለውን ሰው ነው። ወንዱም እንደዚሁ። 

/
4/ “ፍሬንድ ሺፕ” /Casual friendship/ 

ይሄኛው ፍቅር ብዙም አያስቸግርም። ሁለቱ ፍቅረኛሞች ምስጢር ይለዋወጣሉ፣ የሚያስደስታቸውም ጥምረታቸው ብቻ ነው።

/5/ “
ፉሊሽ ላቭ” foolish Love

የጅል ፍቅርአንዳንዶች በሞኝነት ራሳቸውን የሚያታልሉበት የፍቅር ዓይነት ነው። ለምሳሌ ምንነቱን ሳታውቅ ፎቶውን ብቻ አይታ ከነፍኩ በረርኩ የምትል ሴት አጋጥሟችሁ አያውቅም? ፎቶውን ብቻ አይታ ወደደችው! በቃ! ቆረጠች። በእቴጌ ጣይቱ ጥናት መሰረት ብዙዎች በዚህ ፍቅር ከተያዙ ቆይተዋል ይባላል። እድሜና ጤና ለፌስ ቡክ ይሁንና የእቴጌ ጣይቱ ጥናት ፍንትው ብሎ ያሳየናል። ይህ አይነቱ ፍቅር በምሁራን አገላለፅየጅል ፍቅር” foolish Love ይባላል።

/6/ “
ፖሰሲቭ ላቭ” /possessive Love/

ይህ ዓይነቱ ደግሞ ዝነኛ ሰውን የራስ ለማድረግ የሚደረገው የፍቅር ግብግብ ነው። ወንድ ስለሆንክ ለራስህ አዳላህ አትበሉኝ እንጂ ጥናቱ እንደሚያሳየው ብዙውን ጊዜ ይህ አይነት ፍቅር የሚይዛቸው ሴቶች ናቸው። እንደዚህ ዓይነቶቹ የእገሌ ባል መባልን ይፈልጋሉ። 

/7/ “አንሰልፊሽ ላቭ” unselfish Love 
ይህ እሷ ከምትጎዳ እኔው ልቸገር ዓይነት ፍቅር ነው። ፍቅር ግን መዋደድ እንጂ ውለታ መዋዋል አይደለም።

/8/ “
ጌም ፕሌይንግ ላቭ” Game playing Love

ይህ ዓይነቱ ፍቅር የያዛቸው ዓላማቸው አንድ ብቻ ነው። የሩካቤ ሥጋ ጥማቸውን ማርካት ብቻ። ይህ ብዙውን ጊዜ በወንዶች የሚበረታ የፍቅር ዓይነት ነው።

/9/ “
ኢምፒቲ ላቭ” Empty Love
ባዶ ፍቅር! ይህ ዓይነቱ ፍቅር በአጋጣሚ ተገናይተው ወደድኩሽ ከነፍኩልሽ አበድኩልህ ክንፍንፍ አልኩልህ የሚያሰኘው ነው። 

/10/ “
ሰልፊሽ ላቭ” selfish Love

ራስ ወዳድ ፍቅር! እነዚህኞቹ ደግሞ ፍቅርንብለው የሚጀምሩት የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት ነው። ለዚህኛው ፍቅር መሰረቱ ገንዘብ ነው። ገንዘቡ እስካለ ድረስ ሆዴ! አንጀቴ! ሞትኩልህ! አበድኩልሽ! ይባባላሉ። ገንዘቡ የጠፋ ዕለትስ? ያኔማ ግንኙነታቸውን ለማቋረጥ ዓይናቸውንም አያሹም። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የምትሆነን የኢዮብ ሚስት ናት። ኢዮብ ሐብት ንብረቱ ሲያልቅ የሚስቱ ፍቅርም አለቀ፤ ኧረ እንዲያው ለመሆኑ ፍቅር በአንድ ጊዜ የሚለቅ የጥፍር ቀለም ነው እንዴ? ይህ ዓይነቱ ፍቅር ገንዘቡ ሲጠፋ ፍቅሩም ድርግም የሚልየኢዮባዊ ሚስት ፍቅርይባላል።

/11/ “
ኮምፓኒየን ላቭ” companion Love
ይህ እድሜያቸው ከትዳር ክልል ውጪ ወጣ ያለባቸው ሰዎች የሚጀምሩት ውጥን ነው። ከእድሜያቸው ጋር ግብግብ ስለሚይዙ ያገኙትን አጋጣሚ ተጠቅመው ያገባሉ። ምክንያቱም ፊታቸው ያለው የልጅ አምሮት ልጅ ማሳደግ አብሮ መኖር …… ነው። እንዲህ ዓይነቱ ጋብቻ ትዳራዊ ፍቅር companion Love ይባላል።


/12/ “
ኮንሲዮሜት ላቭ” consummate Love

እውነተኛ ፍቅር! ይህ ዘለቄታ ያለው የአባ ወራ እና የእማ ወራዎቻችን ፍቅር ነው። ይህእውነተኛ ፍቅር ነው!” ክቡር አዲስ አለማየው እንደደረሱትፍቅር እስከ መቃብርእንደ በዛብህና ሰብለ ወንጌል ያለ ፍቅር ነው። ይህ እቴጌ ጣይቱን የመሳሰሉ እማ ወራዎች ያለፉበት ፍቅር ነው። 

ፍቅርን ፍቅር ነው የሚያሰኙት 3 ነገሮች ሲሟሉ ነው።

ስሜት /passion/ 

ቅርበት /intimacy/

ቁርጠኝነት Commitment 

መግባባት ሳይኖር መጋባት ግራ መጋባት ነው!” እንዲሉ መግባባት ያስፈልጋል። ሁለቱ ፍቅረኛሞች በስሜትና በአስተሳሰብ መግባባት አለባቸው። በአስተሳሰብ መቀራረብ ያስፈልጋል። በችግርና በኀዘን ለመረዳዳት ቁርጠኝነትም ያስፈልጋል።ራስን መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ማንም ራሱን ፈልጎ ማግኘት አለበት! እኛ የቱ ነው ያለነው? 

ያለንበት ጊዜ ሠርግ በሠርግ ነው። 

ለጋብቻ የደረሳችሁ ለማግባት አስቡ ለመጋባት ያሰባችሁ በጋብቻ ላይ ያላችሁ ለተጋባችሁ ሁሉ መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ! ብለው እቴጌ ጣይቱ ተመኝተዋል!

በዚህች ቀን (25/8/2012) ቅዱስ ጋብቻውን ለሚፈጽመው ጓደኛዬለአቶ እስጢፋኖስ እና / ልድያመልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ በሠርጋችሁ ላይ ሳላረፍድ ያድርሰኝ ብለዋል እቴጌ ጣይቱ!

*********

ይህችን ፅሑፍ ከጨረስኩ በኋላ ወዲያው የልጅነቴን ጓደኛ ደወልኩላት። ሔርሜላዬ እንደምን አለሽ? አልኳት ተጣድፌ። ሰላም ነኝ አለች….. በቃ የሆድ የሆዳችንን ተጨዋወትን። የሰጠሽኝን መፅሐፍ በድጋሚ ሳነበው ትዝ ብለሽኝ ደወልኩልሽ፤ አሁንም ፍቅር እንደያዘሽ ነው? አልኳት ድሮ እንደምቀልድባት ፍግግ እያልኩ። 

የሰጠውህን ፎቶህንስ ጣልከው እንዴ?” አለችኝ።

ከላይ ሳልነግራችሁ፤ ለካ ወደዱኩት ብላ የሰጠችኝ የራሴን ፎቶ ነበር!

እንዴታ አለ አልጣልኩትምአልኳት። 

ሔርሜላዬ ከሁለት ወር በኋላ እንደምታገባና በሠርጓ ላይ መገኘት እንዳለብኝ ነገረችኝ። በደስታ እንደምገኝ ነገርኳት። ጓደኛዬን ይዜ መምጣት እችላለሁ? ስላትለጓደኛህ ቦታ የለንምአለች ድሮ እንደምትጫወትብኝ እየቀለደችብኝ። ጓደኛ ስለመያዜም ወተወተችኝ፤ ማን ናት ወዴት ናት ….. አይ አብሮ ማደግ! ታላቅ ነው ለካ! ፍቅር ዓለም አቀፍ ቋንቋ ነው፤ የፍቅር ሀገሩ ልብ ነው ትል ነበር ሔርሜላዬ።


…….
አይነጋ የለ ነጋ ጊዜውም ነጎደ……. ያለንበት ወቅት የሠርግ ጊዜ ነው……. ለታላቅዋ የልጅነት ጓደኛዬ ታላቅ ስጦታ መያዝ አለብኝ……. ግን ምን? ታላቁ ስጦታዬ የዛሬ 11 ዓመት ሔርሜላ የሰጠችኝየፍቅር ዓይነቶችየሚለው መጽሐፍ ነው። አሁን ይህችን ውድ ስጦታ ይዤ ወደ ሠርጉ መገሥገሥ አለብኝ።


    ==>“የፍቅር ዓይነቶች”<==
                   
               ~ // ~ 
Like ·  · Share · Tag Friends shared 155
·                                
·                                  
o                                                       
Sari Love kkkkkkkkkkk lol ere mud alew eko tadeya normal webat bayehonm hulum ke zamn ga naw yamehadaw
o                                                       
Wonde Love ‎10q
o                                                       
Behailu Zerihun · Friends with Sari Love
minlemaletfeligeshnew?
o                                                       
Kiddy Love Kebede Great history! Thnx for tag! N' melikam gabicha le hermela lol
August 24 at 10:21am · Unlike · 1
o                                                       
Eyerusalem Getachew yemegerem tareke new wedegewalwe
o                                                       
Temesgen Woldeyesus Somewhat interesting
August 24 at 10:55am · Like · 1
o                                                       
Minte Godoliyase Bochera በጣም አመሰግናለው!!!
o                                                       
Amanuel Mekonnen Mushraw ante bthons?
o                                                       
Lishan Gebisa · Friends with Fekadu Sahile
libe yalwe libe yble Amesgnalwe Memihere
o                                                       
Betam astemare new
o                                                       
Solyana Lili Queen Wow betam desyemil tmhrtawi tarik new yoni God bless u tnx so much!
August 24 at 2:03pm · Like · 2
o                                                       
Micky Tesfaye · Friends with Belay Melesie and 4 others
yemgermriyash new ende hager bet eyalesh lol
o                                                       
Tige Love betam betam desyelal kehulu belay temerthu betam astemare new.........betam amesegenalehu!!!
August 24 at 8:16pm · Edited · Like
o                                                       
Minleyunet Fikade Betam betam des yelal astemarim nw mastewalm yeteyekal amesegenalehu
o                                                       
Tizebtin Kebede · Friends with Love Meron
Talak sew.telek sew lemeba metinekre yasfelegal.tasflegalegh.bertah.abo yemchi.
o                                                       
Emnet Abreham YONI I LOVE YOU SO MUCH!!!!!!!!!!! 

Excellent story

With appropriate picture!

I love it !! Guys you have to read it!
Wednesday at 4:44pm · Edited · Like · 1