Monday 20 August 2012

የዘንድሮ ፍቅር ለምኔ 5 ቀን ናት እንደ ጳጉሜ!



ኤሳው ብኩርናዬን ወስደህብኛል ሲል ወንድሙ ያዕቆብን አሳደደው። አባታቸው ይሥሐቅም ልጄ ኤሳው ሆይ እነኾ ያዕቆብ ብኩርናህን ይመልስልሃል። እባክህ ከወንድምህ ጋር በፍቅር ኑር አለው። ኤሳውም በእጄ ብሎ ለጊዜው ታረቀ። ያዕቆብና ኤሳው በአባታቸው እግር ላይ ወድቀር እያለቀሱ ተታረቁ። ተቃቅፈው አለቀሱ። 
ኤሳው ወደ ልጆቹ ሔዶ ከወንድሜ ጋር ተታረኹኝ ቢላቸው ይኽ የጃጀ አባትህ የስቀድሞ ብኩርናህን አስወሰደ። አሁን አታለለህ። ትወስደን እንደሆነ ውሰደን። ያለዚያ ጠባችን ከአንተ ጋር ነው አሉ። ኤሳው ከነሱ ብሶ ጦሩን ስቦ ልጆቹን አስከትሎ ወንድሙን ሊወጋ ከነፈ።

ሀገረ እስራኤል ያዕቆብን ይወዱታልና ወንድምህ ሊገድልህ መጣ አሉት። አሁን ተጣርቀን እንዴት ይኾናል? ሚስቴ ልያ ስለሞተች ልቅሶ ሊደርስ ይኾናል አላቸው። የኤሳው አመጣጥ ግን የከፋ ነበር። 

ያዕቆብ ኤሳውን ከሩቅ አይቶ ወንድሜ ሆይ ዛሬ ተታርቀን ዛሬ ልትወጋኝ ነውን? 

የዘንድሮ ፍቅር ለምኔ
5
ቀን ናት እንደ ጳጉሜ

ተብሎ ተተረተብን አለው። 

ኤሳውም የኔና ያንተ ፍቅር
አህያ ቀንድ ቢያወጣ ቁራ ቢነጣ ነው አለው።
ያዕቆብም አሥራ ኹለቱን ነገድ 12 ከፍሎ ሰልፍ ገጠመው። ኤሳው ጦሩን ቢስብ ቀስቱ ልቡን ብሎ ገድሎታል። የጦር ነገር አውራው ከወደቀ አይቆምምና አውራ የሌለው ንብ አለቃ የሌለው ሕዝብ እንዲሉ ኹሉም ተበትነዋል።

ይህ ኹሉ ምሳሌ ነው። 

ያዕቆብ የጌታችን ምሳሌ ሲኾን ልጆቹ የምዕመናን ምሳሌ ናቸው።

ኤሳው የዲያቢሎስ ምሳሌ ሲኾን ልጆቹ የአጋንንት ምሳሌ ናቸው። 

Visit this Blog! http://yonas-zekarias.blogspot.com/
 ·   ·  · Share · Edit
·                                  
·                                
·                                 4 shares
·                                

No comments: