Friday 14 February 2014

አጫጭር ቀልዶች


ሰላም የምትባል ሚስቴ ሙያ እንደ ቁምጣ ያጥራታልና ገንፎ ቀለባችን ነው። “የገንፎ እናት” የሚል ምርጥ ስም አወጣሁላት። ሰላሜ ግን አኩርፋኝ ወር ሙሉ ዘጋችኝ። ገንፎ አይዝጋኝ እያልኩ ገንፎዬን መዋጥ ግን አላቆምኩም።

ዮናስ ............ሰላሜ እንዴት ነሽልኝ ሴት ወንድ ለተባለ መኪና ሞተሩ ናት ሰላሜ ዓለሜ ነሽ እኮ!

ሰላም .......... ወንድ ሴት የምትነዳው ጎማ ነው ብላኝ እርፍ!

ስላኮረፈችኝ ስቄ አለፍኳት። አዬ ሰላሜ አዬ ሞተሬ አዬ እኔ ጎማው አዬዬዬ አልኩ በልቤ። ሰላሜ ልቤን ሰማችና ቀልዴን እኮ ነው ጌታዬ ቆይ ግን ሙያዬን ነው ያገባከው ወይስ እኔን? ስንት ባል ሚስቴ ሙያ የላትም እያለ በሰው ፊት እንደሚያዋርዳት ታውቃለህ? ስንት ባል የገዛ ሚስቱን ሙያ የለሽም እያለ ያንገበግባት ይሆን? አለችና እንዲህ ስትል ግጥም ዘረፈችልኝ;

ካልተነጋገሩ ካልተወያዩበት
ትዳር ብርጭቆ ነው ይሰበራል ድንገት

ግንባርዋን ስሜ ወጣሁ።

.......

ባሎች ሆይ ሁሉን በፍቅር መነጋገር መወያየት መስማማት ልመዱ።

ሚስቶች ሆይ “የሴት ምክር የእሾህ አጥር” እንዲሉ ቤታችሁን በፍቅር እጠሩ። “እውነተኛ ሚስት ባልዋን ትወልዳለች” እንዲሉ እንዲሁ ሁኑ!