Saturday 31 August 2013

ክርስቶስ ስለ እኛ ይፈርዳል

"...ስለኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነውን???”

ኢየሱስ ፈራጅ ወይስ አማላጅ?


በ1938 ዓ.ም የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ፦ “ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሳ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ስለ እኛይፈርዳል”። በ1975

ዓ.ም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተተረጎመውም እንዲህ ይላል፦
“የሚፈርድ ማን ነው? ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሳ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛም ይፈርዳል።”
በአሁኑ ሰዐት ከኦርቶዶክሳውያን በቀር በአብዝሃኛው ሕዝብ ተሰራጭቶ የሚገኘው እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው:: የሚኮንንስ ማን ነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” በሮሜ 8:-34 ላይ በተለያዩ ዘመናት የተጻፉ መጽሐፍ ቅዱሶችን ተመልክተናል። ቀድሞ የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ
ክርስቶስ ስለኛ ይፈርዳል ብሎ ፈራጅ ሲያደርገው በብዙወቻችን እጅ አሁን
የሚገኘው አዲሱ ትርጉም አማ ላጅ አድርጎታል። ታዲያ ትክክለኛው የቅዱስ ጳውሎስ ቃል የትኛው ነው? ብለን ስንጠይቅ መረዳት የምንችለው አንድም ቀዳሚውን በመመልከት ካልሆነ ደግሞ
ከምንባቡ ሃሳብ በመነሳት ነው። ስለዚህ ቀጥለን በዝርዝር እንመልከተው። ቁጥር 33 ላይ እንዲህ ሲል ይጀምራል:-“እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?” ይህ ማለት እግዚአብሔር ተከተሉኝ ብሎ በመጥራት የመረጣቸውን አይ እነርሱ አያስፈልጉንም ፣ አንተን ሊከተሉ አይገባቸውም ብሎ የሚከሳቸው ማን ነው? በማለት ይጠይቃል በመቀጠልም “የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው።" በማለት የመረጣቸውን ሰዎች መንግሥቱን ለማውረስ እናንተ የአባቴ ብሩካን የሚያጸድቃቸው እግዚአብሔር ነው አለ፤ እንዲሁም የሚኮንን (የሚፈርድ) ማን ነው? በማለት ይጠይቃል። “መኮነን” ከግዕዙ ሳይተረጎም ቀጥታ የተወሰደ ቃል
ሲሆን “ መኮነን“ ማለት መፍረድ ማለት ነው። ምክንያቱም “ኮነነ” ከሚለው የግዕዝ ሥርዎ ቃል የወጣ ነው። “ኮነነ” ማለት ደግሞ ፈረደ ፣ ገዛ ማለት ነው።እንግዲህ ማጽደቅና መኮነን የተለያዩ ትርጉም እንዳላቸው ማስተዋል ያስፈልጋል። ካፈርኩ አይመልሰኝ ካልሆነ እውነታው ይህ ነው። ማጽደቅና መኮነን የአማላጅነት ሥራ ሳይሆን የፈራጅነት ሥራ እንደሆነ ልብ እንበል። በመቀጠልም የሚኮንንስ ማን ነው? ብሎ ለጠየቀው ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ቁጥር 34 የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው” በማለት አሁን ያለበትን ስፍራ ይገልጻል። የሞተውና ሞትን ድል አድርጎ በሥልጣኑ የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ ማለት ነው። መቼም
እግዚአብሔር ቀኝና ግራ ፊትና ኋላ እንደ ፍጡር የለውም እርሱ ስፍራ የማይወስነው ረቂቅ ነው። የነፋስን ቀኝና ግራ የሚያውቅ ማን ነው ከነፋስ ይልቅ ነፍስ ትረቃለች ከነፍስ ደግሞ መላእክት ይረቃሉ። ከመላእክት ደግሞ የበለጠ እግዚአብሔር ይረቃል ስለዚህ በሁሉም ቦታ ምሉዕ ነው። ታዲያ በእግዚአብሔር ቀኝ ሲል ምን ማለት ነው? ብለን ስንጠይቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ቀኝ የተለያየ ትርጉም ቢኖረውም በዚህ ምዕራፍ ላይ ግን ክብርን ፣ ስልጣንን ያመለክታል።በመዝሙር 117:-16 “የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች” ይላል። ይህ ማለት እግዚአብሔር በስልጣኑ ኃይልን እንዳደረገ የሚገልጽ ነው።ምክንያቱም እግዚአብሔር ኃይልን የሚያደርገው ሰዎችንም ከፍ ከፍ የሚያደርገው በሥልጣኑ በመለኮታዊ ኃይሉ መሆኑ ግልጽ ነው። በመሆኑም የእግዚአብሔር ቀኝ ሲል ሥልጣኑን \መለኮታዊ ክብሩን\ ያመለክታል።በዘፀ 15:-12 ላይ “ቀኝህን ዘረጋህ ምድርም ዋጠቻቸው” ይላል ከዚህ የምንረዳው ግብጻውያንን እግዚአብሔር በስልጣኑ ምድር እንድትውጣቸው ማድረጉን ነው። ስለዚህ “በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው” ማለቱ በስልጣንና በክብር በሰማያት ያለው ማለቱ ነው። ይህም ማለት ክርስቶስ ቀድሞ ሥጋ ከምልበሱ በፊት ክብር የሌለው ሆኖ በኋላ ክብር አገኘ ማለት አይደለም ክብርና ሥልጣኑ ቅድመ ተዋሕዶ ጊዜ ተዋሕዶ ድህረ ተዋሕዶ ከባህርይ አባቱ ከአብ ከባህርይ ህይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።በመቀጠል እንዲህ ይላል “በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለኛ
_______ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” በክፍት ቦታው ላይ ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረውን ሙሉ ብንባል ያለጥርጥር የሚፈርደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው የሚለውን ነው። ምክንያቱም ከላይ በዝርዝር እንዳየነው ጥቅሱ የሚያመለክተው ፈራጂነቱን እንጂ
አማላጅነቱን በፍጹም አይደለም። ማጽደቅና መኮነን ከቻለ እንዲሁም በእግዚአብሔር ቀኝ \ክብር\ ካለ እርሱ የክብር ባለቤት ፈራጅ እንጂ አማልጅ አይሆንም። ደግሞ “የሚኮንን ማንነው?” የሚለውና “ስለኛ የሚማልደው” የሚሉት ሁለት ቃላት \ሐሳቦች\ \ርስ በርሳቸው እንዳይጋጩ አስማምቶ መተርጎም ያስፈልጋል። ንባቡን ይዞ መሮጥ ግን ወደ ባሰ ጥፋት የሚያመራ መሆኑንም ሐዋርያው አስረጝቶ አስረድቷል ትርጉም ያድናል ንባብ ይገድላል በማለት። ስለዚህ ማስተዋል ግድ ይለናል!!! 

"ጸሎተ ፍትሐት"



#ፍትሐት ማለት ከኃጢአት እስራት መፍታት
ወይም መፈታት ማለት ነው፡፡ ስለዚህም
ለሞቱ ሰዎች የሚደረገው ጸሎት ጸሎተ
ፍትሐት ይባላል።
የሙታን ነፍሳት ከሥጋ እንደተለዩ እስከ እለተ
ምጽአት ድረስ በማረፊያ ቦታ ይቆያሉ እንጂ
በቀጥታ ወደ መንግስተ ሰማይ ወይም ወደ
ገሃነመ እሳት እንደማይላኩ ቤተ ክርስቲያን
የምታምነውና የምታስተምረው ትምህርት
ነው፤ እስከ ፍርድ ቀን ድረስ የሚቆዩበትም
ቦታ ለጻድቃን ገነት ሲሆን ለኃጢአተኞች
ደግሞ ሲኦል ነው። የጻድቃን ማረፊያ ቦታቸው
ገነት መሆኑን ለማመልከት ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በነበረ ጊዜ
ንስሐ ለገባው ወንበዴ፡ “በእውነት እልሃለው
ዛሬውኑ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ”
ብሎታል። ሉቃስ ፳፫፡ ፵፫። የኃጢአተኞች
መቆያ ደግሞ ሲኦል መሆኑን ለማመልከት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሀብታሙ ሰውና
በድኻው አልዓዛር ምሳሌ ትምህርቱ ሀብታሙ
ሰው በሲኦል ውስጥ እንደነበረ ገልጿል።
ሉቃስ ፲፮፡ ፳፫፡፡
በሙታን ትንሣኤ ጊዜ የምንነሳው በውርደት
ወይም ክብር በሌለው ሁናቴ በመሬት ውስጥ
እንደተቀበርነው ሳይሆን፣ ሐዋርያው ቅዱስ
ጳውሎስ እንዳለው በክብር፣ በኃይልና
በመንፈሳዊነት ነው። ፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፭፡ ፵፪-
፵፬። ከዚያም በኋላ ወደ ክርስቶስ የፍርድ ፊት
እንቀርባለን። ፪ኛ ቆሮንቶስ ፭፡ ፲፤ ራዕይ ፮፡
፱-፲፩፡፡
ይቅርታ በዚሁ ዓለምና በሚመጣውም ዓለም
መኖሩን ቅዱስ መጽሐፍ ያስረዳል። ማቴዎስ
፲፪፡ ፴፪፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከዚህ ዓለም
በሞት ተለይቶ ለነበረው ለኦኔሲፎር
“በመጨረሻው ቀን ምሕረትን ይስጠው”
ብሎ ጸልዮለታል። ፪ኛ ጢሞቴዎስ ፩፡ ፲፰።
ቤተ ክርስቲያንም ይህንኑ ጸሎት ለሞቱ ሁሉ
ትጸልያለች።
ለሞቱ ሰዎች መጸለይ ደግሞ በጥንት በዘመነ
ብሉይም ነበረ። ጀግናው ይሁዳ መቃብዮስ
በጦርነት ለሞቱ ወታደሮቹ የኃጢአት
መሥዋዕት ይደረግላቸው ዘንድ ሁለት ሺህ
የብር ድራህም አሰባስቦ ወደ ኢየሩሳሌም
ልኳል። ፪ኛ መቃብያን ፲፪፡ ፵፫፤ ዕዝራ
ሱቱኤል ፮: ፴፭። አይሁድ ለሙታን ሲጸልዩ
ዳዊት ይደግማሉ።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
በተላከው የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ
መልዕክት ላይ ባደረገው ስብከቱ እንዲህ
ብሏል “አንድ ሰው ኃጢአተኛ እንደሆነ ቢሞት
የምንችለውን ያኽል ልንረዳው ይገባል።
የምንረዳውም በለቅሶና በሐዘን ሳይሆን
በጸሎት፣ በምጽዋትና በቁርባን ነው።
የዓለምን ኃጢአት ወደ ተሸከመው
የእግዚአብሔር በግ ስለ ሙታን የምንጸልየው
እነርሱ መጽናናትንና እረፍትን እንዲያገኙ ብለን
ነው እንጂ በከንቱ አይደለም። ጻድቁ ኢዮብ
ስለልጆቹ ያቀርብ የነበረው ቁርባን ጠቀሜታ
ከነበረው ስለ ሙታን የምናቀርበው ቁርባን
ምንኛ የበለጠ ጠቀሜታ ይኖረው?

Thursday 29 August 2013

በእውነቱ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?



በዚያም ወራት ብዙዎች ክርስቶስን ብዙ ይሉት ነበር። ግማሹ ነቢይ ነው ይሉ ነበር። መጥፎ ወሬ ይበራል መልካሙ ይተኛል እንዲሉ እንዲህና እንዲያ የሚሉ ወሬዎች በከተማዋ ተሰራጨ። ግማሹም ኤልያስ ነው መጥምቁ ዮሐንስ ነው አሉ። 



ቅ/ጴስሮስ ግን እንዲህ አለ፦ አንተ ውእቱ ወልደ እግዚአጽሔር ሕያው /አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ /

በጴጥሮስ ፋንታ እኛ ብንጠየቅ መልሳችን ምን ይሆን? አንተማ ፍጡር ነህ እንል ይሆን ወይስ አምላክ ነህ እንላለን?


አስተውሉ! ሰዎች የአብን ልጅ ማን ይሉታል አልተባለም። ይልቁንም ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል? ተባለ። ሰዎች የድንግል ማርያምን ልጅ ማን ይሉታል? ተባለ። ጴጥሮስም መለሰ፥ አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ! የአብ ልጅ የሰው ልጅ አንድ ነው! እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። አንዳንዶች የአብ ልጅ አምላክ ነው ይሉና የድንግል ማርያም ልጅን አምላክ ነው ለማለት አንደበታቸው ይታሰራል። ልቡና ህሊናቸው ፈራ ተባ እያለ ይጠራጠራል።

ክቡራን ሆይ! የድንግል ማርያም ልጅ የአብ ልጅ እንደሆነ ወንጌሉን አንብቡና እመኑ፣ ቅ/ጴጥሮስን ጠይቁና ልባችሁን አሳምኑ።


አምላክ እንዴት ይወለዳል? በፍጹም አይወለድም ብለው የቁርሃን ጥቅስ የሚጠቅሱ ክርስቲያናች አሉ። ክርስቶስ አልፋና ዖሜጋ ነውና ከተወለደ መጀመርያ አልፋ አይባልም ፣አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ ነበርኩ ስላለ ከቶ አይወለድም ይላሉ። ክቡራን ሆይ ይህማ በመጀመርያ ቃል ነበረ ያለውን አለማወቅ ነውና አስተውሉ!


አንዳንዶች አምላክ አይወለድም ሲሉ ኢሳይያስ እንዲህ አላቸው፦ ((ሕጻን ተወልዶልናል)) ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና ስሙም ድንቅ መካር ((ኃያል አምላክ)) ይባላል፤ ኢሳ 9፦6



ፕሮቴስታንት እህት ወንድሞቼ! የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናንተ ማን ነው? አምላክ ነው ወይስ ምንድን ነው?

http://yonas-zekarias.blogspot.co.uk/


Like ·  ·