Monday 20 August 2012



የፍቅር አንድምታ!

“የመላእክትን ቋንቋ ብናገር ፍቅር ግን ከሌለን ባዶ ነን ከንቱ ነን” አለ ታላቁ ሐዋርያ። 1ኛ ቆሮ. [13-ፍ]

የመላእክትን ቋንቋ ባውቅ ሲል መላእክት ቋንቋቸው ምን ይኾን? ግዕዝ ፣ ዕብራይስጥ? ወይስ ግሪክ? ምን ይኾን የመላእክት ቋንቋ?

እነኾ የመላእክት ቋንቋ “ፊልሙንጢ” ይባላል። ይህችን የመላእክት ቋንቋ ብንናገር ፍቅር ግን ከሌለን ባዶ የከንቱ ከንቱ ነን።

ፍቅር ኹሉን አንድ ያደርጋል!

ፍቅር ያቻችላል!

ፍቅር ይታገሳል!

ፍቅር ያስተዛዝናል!

ፍቅር ይራራል!

ፍቅር አያቃናም!

ፍቅር አያቋጣም!

ፍቅር በውስጥም በአፍአም ያሥታግሳል!

ፍቅር በውስጥም በአፍአም ተስፋ ያደርጋል!

ፍቅር በአንድ ልብ አንድ ሐሳብ ያደርጋል!

ፍቅር ኹሉን ይገዛል!!
“The Passion of Love”
“የ ፍ ቅ ር - ታ ላ ቅ ነ ት”

ስለ ክርስቲያኖች ከፍተኛ ፍቅር
ሐዋርያው ጳውሎስ አብዝቶ ሲናገር
ለቆሮንቶስ ሰዎች እንዲህ ብሎ ነበር
ብንናገር በሰው በመላእክት ልሳናን
ትንቢት ተገልጦልን ብናውቅም ሚስጥርን
ተራራን የሚያፈርስ ታምራት ቢኖረን
ጥበብና እውቀት ቢሰጠን በዝቶልን
በእምነታችን ፀንተን ፍቅር ግን ከሌለን
እንድማይጠቅም እቃ ባዶ ነን ከንቱ ነን

ድሆችን ለመርዳት ሃብታችንን ከፍለን
ሥጋችንን በእምነት ወደ እሳት ብንጥል
በፆምና ፀሎት ዘወትር ብንጋደል
ፍቅር ግን ከሌለን የለንም በጎ እድል

በአለም ላይ ያለውን ሁሉን ለማሸነፍ
በህይወት መዝገብ ላይ በክብር ለመፃፍ
ሊኖረን ይገባል ፅኑ የፍቅር ደጃፍ።
ሰው በተስፋ ተሞልቶ በእምነቱ ቢተጋ
ከአምላክ ይሰጠዋል ከፍተኛ ዋጋ።


http://yonas-zekarias.blogspot.com/

No comments: