Saturday 18 August 2012

==> ምሥጢረ ደብረ ታቦር <==



==> ሊቀ ነቢያት ሙሴ እጅግ ታዛዥና የዋህ ስለነበር ሀገረ ከንዓንን ለማየት ወደ ናባው ተራራ በወጣ ጊዜ ሁለት መላእክት በአረጋውያን ተመስለው መቃብር ሲቆፍሩ ቢያይ ላግዛቹ ብሎ መቆፈሪያውን ተቀበላቸው። እነሱም በመጨረሻ “ሰውየው በአንተ ልክ ነውና እስቲ ገብተህ ለካልን አሉት  እሱም በየዋህነቱ ጉድጓዱ ውስጥ ገብቶ እንደተኛ እንደ እንቅልፍ አሸልቦት በዚያው ዐረፈመላእክትም ቀበሩት። እስራኤላዊያን ሙሴን እጅግ ስለሚወዱት የሙሴን መቃብር እንደ ጣዖት እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን መቃብር ሰወረው። ነገር ግን ጠላት ዲያቢሎስ ሊያሳያቸው በመነሳቱ ቅዱስ ሚካኤል ተቃወመው በመጨረሻም ቅዱስ ሚካኤል ዲያቢሎስን እግዚአብሔር ይገስጽህ ብሎ ከራሱም ሰወረበት።[የሐዋርያው ይሁዳ መልዕክት ቁጥር 8]

 ነቢያቱ የእግዚአብሔርን ፊት ሊያዩ ይመኙ ነበርና ፊትህን አሳየኝ እያሉ ይለምኑ ነበር። ከነዚህም ውስጥ ነቢዩ ሙሴ የመጀመሪያው ነው። ሙሴ እግዚአብሔርን ክብርህን አሳየኝ ብሎ ለመነ። እግዚአብሔርም ማንም ፊቴን አይቶ የሚፀና የለምና ይህ አይቻልህም; ፊቴን ሳይሆን ጀርባዬን ታያለህ አለው [ዘፀ33:17] ሙሴ ይህን ተስፋ በልቡ ሰንቆ ይጠባበቅ ጀመር። ከጊዜ ብዛት ግን እረሳው። እንዲያውም በናባው ተራራ ላይ ዐረፈና አንቀላፋ። እስኪ እዚህ ጋ ጥያቄ እናንሳ። እግዚአብሔር ለሙሴ የገባውን ተስፋ አስቀርቶ ቃሉን አጥፏል ማለት ነው? ሙሴ እንዴት የእግዚአብሔርን ጀርባ ሳያይ ሞተ? የለመኑትን የማይረሳ የወደቁትን የሚያነሳ እግዚአብሔር እንደሰው ቃሉን አይቀያይርም። ሰው ነው ጠዋት የተናገረውን ማታ የማይደግመው። ሰው ነው ትላንት ከጎንህ ነኝ ያለውን ዛሬ ዠርባውን የሚሰጠው።እግዚአብሔር ለሙሴ ዠርባዬን ታያለህ ብሎ በብሉይ ኪዳን የገባለትን ቃል ኪዳን በአዲስ ኪዳን ፈጽሞለታል።

እነሆ ታሪኩ እንዲህ ነው፦ ሊቀ ነብያት ሙሴ  ከፊት ሆኖ ሕዝበ እስራኤልን እየመራ ማርና ወተት የምትፈራውን ምድረ ርስት ከንዓን ኢየሩሳሌምን ሊያወርሳቸው መንገድ ይመራቸው ነበር። እስራኤላዊያን ለእረኛቸው እጅግ አስቸጋሪ ነበሩና በውኃ ጥም ልትገግለን ከግብፅ አወጣኸን እያሉ በሙሴ ላይ አጉረመረሙ ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እግዚአብሔርም ሰማው በትሩን አነሳና ዐለቱን መታ ከዐለቱም ውኃ ፈለቀ። ይህን ውኃ የመሪባ ውኃ አለው። ከዛም ሙሴ የመሪባን ውኃ ያፈለኩላቹ እኔ ነኝ አለ። ከዐለቱ ውኃ ያፈለቀው ማን ነበር? ከዐለቱ ውኃ ያፈለቀው እግዚአብሔር ነበር ምንም እንኳን ሙሴ ምክንያት ቢሆንም ከዐለቱ ውኃ ያፈለቀው ግን እግዚአብሔር ነው።

==> ሙሴ እኔ የመሪባን ውኃ አፈለኩ ስላለ ብቻ ኢየሩሳሌምን አያት እንጂ በአካለ ሥጋ አልገባባትም። በናባው ተራራ ላይ ሆኖ ኢየሩሳሌምን ከሩቅ ሆኖ አይቶ ተሳለማትና በናባው ተራራ ላይ ዐረፈ። ከሩቅ ሆነው ተሳለሟት” እንዲል [ዕብ 11:13]


ሙሴ በናባው ተራራ ላይ ቢያንቀላፋም የለመኑትን የማይረሳ ጌታ ሙሴን ከናባው መቃብር ቀሰቀሰውና በታቦር ተራራ” ላይ አስቀመጠው። ጌታችን ለኤልያስና ለሦስቱ አዕማደ ሐዋርያት [ጴጥሮስ ዮሐንስና ያዕቆብ] በታቦር ተራራ ላይ በተገለጠ ጊዜ ሙሴም ከብዙ ዘመናት በፊት የለመነውን ልመና እንዲያይ በታቦር ተራራ ላይ ተገኘ። ጌታችንም ሙሴ ሆይ እነሆ ዠርባዬን ታያለህ ብዬህ የገባውልህ ቀን ይህች ናት፤ ለምነህ ነበርና እይ አለው።ሙሴም አየና ተደሰተ! በአካለ ሥጋ ያልገባባትን ኢየሩሳሌምን በአካለ ነፍስ አያት። ዠርባዬን ታያለህ ማለቱም ትስዕብት ሆኜ [አምላክ ወሰብእ] ሆኜ ታየኛለህ ማለቱ ነበር።

የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጥኤም ተብሎ በሚጠራው ሀገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም የታቦር ተራራ ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደ ፀሐይ የበራበት ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡ ይህ ቦታ ጌታ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው። የማቴዎስ ወንገል ምዕራፍ ፲፯፦ ቁጥር  እስከ  ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።"
ዓቢይ መሠረቱ ይሄ ሲሆን፣ በአገራችን የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይቺ ዕለት 'ቡሄየሚለውን ስያሜ አገኘች። ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡
በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ (ሲያኖጉይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ እረኞችም ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጡ፡፡ ታዲያ ያንን ማስታወሻ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የምናከብረውም ከዚህ በመነሣት ነው፡፡

ቡሄ በሉ ! !
ቡሄ በሉ ! !
ያዳም ልጅ ሁሉ`! !
የኛማ ጌታ የአለም ፈጣሪ
የሰላም አምላክ፣ ትሁት መካሪ
ድምጽህን ሰማና በብሩህ ደመና
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣና
ያዕቆብ ዮሐንስ ! እንዲሁም ጴጥሮስ
አምላክን አዩት ! ሙሴ ኤልያስ
አባቱም አለ ! ልጄን ስሙት
ቃሌ ነውና ! የወለለድኩት
ድምጽህን ሰማና በብሩህ ደመና
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን።


==> ምሥጢረ መንግሥቱን ለምን በታቦር ተራራ ገለጸው ?

መድኃኔዓለም ሌሎች ተራሮች እያሉ ክብሩን ለመግለጥ ስለምን ደብረ ታቦርን መረጠ ቢሉ ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡

==> ትንቢት

“ ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ወይሰብሑ በስምከ ”

ታቦርና አርሞንኤም በስምህ አምነው በተደረገላቸው ነገር ደስ ይላቸዋል፣ ስምህን ያመሰግናሉ፣ ለስምህም ምስጋና ያቀርባሉ፡፡ “መዝ 88፡12


==> ምሳሌ

በዚህች በታቦር ተራራ ባርቅ ሲሳራን ድል አድርጎበታል መሳፍንት 4፡6 ይኸውም ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡‹… የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደገና ክፉ ሥራ ሠሩ፡፡ እግዚአብሔርም በአሶር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቡስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው የሠራዊቱም አለቃ በአሕዛብ አሪሶት የተመረጠው ሲሣራ ነበር… ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና የእስራኤልንም ልጆች ሃያ ዓመት ያስጨንቃቸው ነበር›/መሳ 4.1-3/

ሁሌም ቢሆን የሰውን በደል ዐይቶ እንደወጣችሁ ግቡት፣ እንደገባችኋት ውጧት የማይልና ‹… ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል› የተባለለት እግዚአብሔር ከዚህ ቀንበር የሚላቀቁበትን መላ ራሱ አመለከታቸው፡፡ /1ቆሮ. 10-13/፡፡

እስራኤላውያን ወደ ፈጣሪያቸው በጮኹ ጊዜ የለፊዶት ሚስት የሆነችውንና እስራኤልን በነቢይነትና ዳኝነት ታገለግል የነበረችው “ነቢይቱን ዲቦራን” ተጠቅሞ የማሸነፊያ መላውን አመለከታቸው፡፡ ነቢይቱ ዲቦራ ትንቢት ከመናገር አልፋ የእስራኤልን ንጉሥ ባርቅ ከእኔ ጋር ወደ ጦርነቱ ውጪ ብሎ ባስጨነቃት ጊዜ በጦር አዝማችነትም ተሳተፈች፡፡

እግዚአብሔር በነቢይቱ በዲቦራ በኩል ለእስራኤል ንጉሥ ‹ሔደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጡ…› ብሎ አዞት ነበርና ንጉሡ ዐሥር ሺሕ ብረት ለበስ ያልሆነ እግረኛ ሠራዊት ይዞ ደብረ ታቦርን ተማምኖ በተራራው ላይ መሸገ ጦርነቱ ሳይጀመር አለቀ፡፡ ምክንያቱም ‹እግዚአብሔርም ሲሣራን ሰረገሎቹንም ሁሉ ሠራዊቱንም ሁሉ ከባርቅ ፊት በሰይፍ ስለት አስደነገጣቸው፡፡ ሲሣራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ…› /መሳ. 4.15/

እስራኤል በእግዚአብሔር አጋዥነት በታቦር ተራራ ላይ የሃያ ዓመት የግፍና የሰቀቀን አገዛዝ ቀንበራቸውን ከትከሻቸው አሽቀንጥረው በምትኩ የድል ካባን ደረቡ ‹… በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ› ተብሎም ጀግንነታቸው ተጻፈላቸው፡፡ የታቦር ተራራ ያኔ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ባለውለታቸው ነበር፡፡ /ዕብ. 11.32-34/

ጌታም በልበ ሐዋርያት ያለ ሰይጣንን ድል ያደርግበታልና ማለትም በልባቸው ጥርጥርን እና ፍቅረ ሢመትን( የሥልጣን ፍቅር) ያሳደረ ዲያብሎስን ድል ነስቶላቸዋል ፡፡ ከዚህም በመነሳት ነው በዓለ ደብረታቦር የደቀመዛሙርት ተማሪዎች በዓል ነው የሚባለው ፡፡

ለምን 3ቱን ሐዋርያት (ጴጥሮስ ፤ዮሐንስ እና ያዕቆብን) ብቻ ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ወጣ?፡-

==> ለፍቅሩ ስለሚሳሱ ነው፡፡ ይህም በዕብራይስጡ ኬፋ ፤ በግሪኩ ጴጥሮስ ፤በግዕዙ ኰኲሕ( ዐለት) የተባለው የዮና ልጅ ስምዖን ጌታ   እሞታለሁ እያለ ጌታችን ሲናገር አይሁንብህ በማለቱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ እርሱን ስሙት የሚል መለኮታዊ ድምጽ ሰምቷል፡፡ዮሐንስና ያዕቆብ ጌታን ምድራዊ መሲህ አድርጎ በማሰብ ቀኝ ጌትነትን እና ግራ ጌትነትን በእናታቸው በኩል  የማይገባ ልመና አቀረቡ ዮሐንስና ያዕቆብ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ? ሲባሉ አዎ ብለው መለሱ በዚህም ከባሕርይ አባቱ እርሱን ስሙት የሚል ድምጽ ሰሙ፡፡

==> በይሁዳ ምክንያት ነው ኢሳ 26.13 ‹ኃጥእ ሰው የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ያርቁታል› እንዲል እርሱን ጥሎ አስራ አንዱን ወደ ተራራ ይዞ ቢወጣ ከምሥጢር ቢለየኝ በሞቱ ገባሁበት እንዳይል፡፡ ያም ባይሆን  ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ለምን ይከለከላሉ ቢሉ አልተከለከሉም በርዕሰ ደብር (በተራራው አናት) ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተገለጸው ምስጢር በእግረ ደብር (በተራራው ግርጌ) ለነበሩት ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህም በደብረሲና ለሰባው ሊቃናት የተገለጠ ምሥጢር በከተማ ለነበሩት ለኤልዳድና ሙዳድ እንደተገለጠ ማለት ነው፡፡ ዘኁልቊ 11፡26


==> ኤልያስና ሙሴን ለምን አመጣቸው?

ሀ- በአንድ ወቅት ነቢዩ ሙሴ እግዚአብሔርን ‹‹ወለእመሰ ረከብኩ ሞገሰ በኀቤከ አስተርእየኒ ገሐደ ሊተ ወአእምር ወእርአይከ ከመ ይኩነኒ ርኪበ ሞገሰ በቅድሜከ ዮም›› በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘቴ እውነት ከሆነስ ፊት ለፊት ተገልጸህልኝ ልይህና በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘቴን ልወቀው› ሲል ጠይቆት ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ‹… ትሬኢ ድኅሬየ ወገጽየሰ ኢያስተርኢ ለከ፣ ጀርባዬን ታያለህ ፊቴን ግን አታይም› ብሎት ነበር፡፡ /ዘጸ. 33.13 እና 23/ የዚህ ኃይለ ቃል ትርጓሜና ሐተታ በደብረ ታቦር ተፈጸመ፡፡ እንዲህ ማለቱ በአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን ሰው ሆኜ ሥጋ ለብሼ ኋላ በደብረ ታቦር እስክገለጽልህ ድረስ አንተ በመቃብር ተወስነህ ትኖራለህ ማለቱ ነበር፡፡ ይህን ማለቱ እንደሆነ የታወቀው ግን በደብረ ታቦር ሙሴን ከብሔረ ሙታን አምጥቶ ባቆመው ጊዜ ነበር

ለ- ልዑል እግዚአብሔር ነቢዩ ኤልያስን ‹አንተሰ ትከውነኒ ስምዓ በደኃሪ መዋዕል፣ አንተ በኋለኛው ዘመን ምስክር ትሆነኛለህ› ብሎት ነበርና ይኸውም ኃይለ ቃል ኤልያስ ከብሔረ ሕያዋን መጥቶ ‹የእኔን የኤልያስን ጌታ ማን ኤልያስ ነው ይልሃል እግዚአ ኤልያስ፤ አምላከ ኤልያስ ይበሉህ እንጂ› ሲል በደብረ ታቦር ተፈጸመ፡፡  

“ታያለህ የተባለው ሙሴም አየ፣ ትመሰክራለህ የተባለው ኤልያስም መሰከረ”

ሐ- በፊልጶስ ቂሳርያ ጌታ ሐዋርያትን ‹ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል?› ብሎ በጠየቃቸው ጥያቄ ሲመልሱ ሙሴ ነው ይሉሃል ፤ እንዲሁም የኃይል ስራህን ተመልክተው ኤልያስ ነህ ይሉሃል ብለው ነበርና ሙሴን ከመቃብር ፤ ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ እግዚአ ሙሴ ፤ አምላከ ሙሴ ፤ እግዚአ ኤልያስ ፤ አምላከ ኤልያስ መሆኑን ለማስመስከር፡፡

==> ታቦር ተራራ የወንጌል ምሳሌ

1.     ተራራ ሲወጡት ያደክማል፣ ከወጡት በኋላ ግን ጭንጫውን፣ ግጫውን ሲያሳይ ደስ ያሰኛል፡፡ ወንጌልም ሲማሯት ትከብዳለች በኋላ ግን ጽድቅን እና ኃጢአትን ለይታ ስታሳውቅ ደስ ታሰኛለች፡፡

==> ታቦር ተራራ የቤተክርስቲያን ምሳሌ

1.     በታቦር ተራራ ከመዓስባን (ባለትዳር) ሙሴን ከደናግል ደግሞ ኤልያስ እንደተገኙ በቤተክርስቲያን በድንግልና የሚኖሩ መናንያን መነኮሳትም፣ በሕግ በሥርዓት የሚኖሩ ባለትዳሮችም ይገኛሉና፡፡

2. በታቦር ተራራ ከብሉይ ኪዳን ነቢያት ኤልያስና ሙሴን፣ ከሐዲስ ኪዳን ሦስቱን ሐዋርያት እንደተገኙ በቤተክርስቲያን ብሉይ ከሐዲስ እንዲነገር ለማጠየቅ ፤ ሐዋርያት የሰበኩት ወንጌል አስቀድመው ነቢያት በምሳሌና በትንቢት የተናገሩት እንደሆነ ሲያስረዳ ነው ፡፡ ነቢያት በቀየሱ ሐዋርያት ገሰገሱ እንዲል ‹በሐዋርያት በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል›ኤፌ 2፣20
   
==> ታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ

1.  ተራራውን በችግር እንዲወጡት መንግሥተ ሰማያትንም በብዙ መከራ የምትገኝ ናትና ‹እስመ በብዙኅ ጻማ ወድካም ኀለወነ ንባአ ለመንግሥተ እግዚአብሔር› ‹ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል› ሐዋ 14፡22

2.    በታቦር ተራራ የብሉይ ኪዳን ነቢያት፣ ከሐዲስ ኪዳን ሐዋርያት እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም፣ ሐዋርያትም አንድ ሆነው እንደሚወርሷት ያጠይቃል፡፡

3.    በታቦር ተራራ ከመዓስባን ሙሴ፣ ከደናግል ደግሞ ኤልያስ እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም መዓስባንም በአንድ ላይ እንዲወርሷት ያጠይቃል፡፡

4.    በታቦር ተራራ ሞተው ከተቀበሩት መካከል ሙሴን አመጣ፣ በብሔረ ሕያዋን ካሉት ደግሞ ኤልያስን አመጣ መንግሥተ ሰማያትንም ሞተው የተቀበሩትም በብሔረ ሕያዋን ያሉትም በአንድነት እንደሚወርሷት ያጠይቃል፡፡
       

==> በአጠቃላይ ታቦር ተራራ፡-

1.     የክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት የተመሠከረበት፣
2.    የምስጢረ ሥላሴ ትምህርት የተሰጠበት
3.    ፈጣሪ ከቅዱሳን ሰዎቹ ጋር የተገኘበት
4.    በልበ ሐዋርያት የነበረ ሰይጣን ድል የተደረገበት
5.    የሐዋርያት በተለይም የሦስቱ ባለሟልነት የተገለጠበት፣
6.    አሉባልታና ተራ ወሬ የከሸፈበት፣
7.    የቅዱሳንን ክብር ለሚያናንቁ ተራራም እንኳን ‹ቅዱስ› እንደሚባል የተማሩበት፣
8.    የብሔረ ሕያዋን መኖር የተመሰከበረበት
9.    የትንሣኤ ሙታን ዋስትና የተገለጠበት የክብር ሰገነት፣ የምስጢረ መቅደስ፣ ታላቅ ትምህርት ቤትም ጭምር ነው፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታ ሆይ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው ማለቱ

1.     የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት በሚታመንበት፣ ወልድ ዋሕድ በምትለው ሃይማኖት መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡

2.    መድኃኔዓለም ከቅዱሳን ወዳጆቹ ጋር በምትገኝበት አንተ እያበላኸን እየፈወስከን፣ ሙሴ ደመና እየጋረደ መና እያወረደ ባሕር እየከፈለ፣ ኤልያስ ሰማይ እየለጐመ እሳት እያዘነመ ዝናም እያቆመ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡

3.    በልበ ሐዋርያት ያደረ ሰይጣን ድል በተደረገበት በታቦር ተራራ ምሳሌ አንድም በወንጌል ሕይወት፣ አንድም በቤተ ክርስቲያን መኖር ለእኛ መልካም ነው ሲለን ነው፡፡

ፈጣሪያችን እግዚአብሔር እስከመጨረሻዋ ሕቅታ (እስትንፋስ) በታቦር ተራራ በተመሰለች ቤተክርስቲያን በሃይማኖታችን ጸንተን የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች የስሙ ቀዳሾች እንድንሆን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፤ አሜን።

አሐደ ለከ

ወአሐደ ለሙሴ

አሐደ  ለኤልያስ ንግበር ማኅደረ

ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ

[የማቴዎስ ወንጌል 171-8]




Thursday 16 August 2012

==>ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ዛሬ ሌሊት ዐረፉ<==





ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ዐርፈዋል፡፡ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር።

የግብጹ ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ካረፉ በኋላ እሳቸውን የመሰሉ ደገኛ አባት ፍለጋ ግብጽ በጸሎት ተጠምዳለች። ዳዊት በትንቢቱኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለችእንዳለ ደገኛ አባት ስጠን ብለን እጃችንን ወደ እግዚአብሔር መዘርጋት ያለብን ዛሬ ነው። በአሜሪካና በሀገር ቤት የተራራቀችውን ቤተክርስቲያን በፍቅርና በብስለት አንድ የሚያደርጉ አባት ይሰጠን ዘንድ የጸሎት ጊዜው አሁን ነው። ሐዋርያውእለት እለት የሚያስጨንቀኝ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ነውእንዳለ እንደ /ጳውሎስ ያለ ለቤተክርስቲያን ቀናተኛ ለመንጋው መልካም እረኛ እግዚአብሔር ያዘጋጅልን



ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ “Apostolic Succession” 

ከሐዋርያት አለቃ ከቅ/ጴጥሮስ እስከ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ድረስ ኢትዮጵያ ያሳለፈችውን ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ እንዲህ እናገኘዋለን፦

የሐዋርያት አለቃ /ጴጥሮስ ነው።

ከቅዱስ ጴጥሮስ ቀጥሎ /ማርቆስ።

/ማርቆስ ግብጽ ሄዶ መንበሩን በግብጽ አደረገ።

ከቅ/ማርቆስ ቀጥሎ አንያኖስ ነው።

ከአንያኖስ ቀጥሎ 20 ፓትርያርክ አሉ። 20ኛው አትናቴዎስ ነው። 

ከአትናቴዎስ ቀጥሎ ከሳቴ ብርኅን አባ ሰላማ /ፍሬምናጦስ/ ይህን ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ወደ ሀገራችን አመጣልን።

ፍሬምናጦስ ኢትዮጲያዊ አይደለም። አንድ ነጋዴ ሲድራኮስና ፍሬምናጦስ የሚባሉ ሁለት ልጆቹን ይዞ አንድ ነጋዴ ቤት ገብቶ መኖር ጀመረ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነጋዴው ሞተ። ልጆቹም በገበሬው ቤት መኖር ጀመሩ። ፍሬምናጦስም የኢትዮጵያዊያንንn እምነትና ባህል አደንቃለሁ። ለምን ሥጋ ወደሙን አትቀበሉም? ብሎ ገበሬውን ጠየቀው። ገበሬውም ካህናት ስለሌሉን ነው አለው። ፍሬምናጦስም በኢዛና እና ሳይዛና ፈቃድ ግብጽ ሄዶ ፕትርክናን ከአትናቶዎስ ተቀበለ።


የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ፍሬምናጦስ ነው።

ከዚህ ጊዜ በኋላ ለብዙ ዘመናት ኢትዮጵያ በግብጽ ፓትርያርኮች ስትመራ ቆይታለች።

የመጀመሪያው አራቱ ኢትዮጲያዊያን ጳጳሳት 1921 ተሾሙ! 

አቡነ ሚካኤል
አቡነ ጴጥሮስ
አቡነ አብርሐም
አቡነ ይሥሐቅ ናቸው።

ከዚህ ጊዜ በኋላ በግብጽና በኢትዮጲያ መካከል ለሃያ አመታት ያክል ሀገራችን ኢትዮጵያዊ ጳጳስ ያስፈልጋታል አያስፈልጋትም በሚል ሽኩቻ ውስጥ ነበሩ። 

ይህ እልህ አስጨራሽ ሽኩቻ አለፈና 1940 ሌሎች አራት ጳጳሳት በግብጻዊው ፓትርያርክ በአቡነ ዮሳብ ተሾሙ።

አቡነ ሚካኤል
አቡነ ያዕቆብ
አቡነ ባስልዮስ
አቡነ ጢሞቴዎስ ናቸው።

ከእነዚህ ጳጳሳት አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ ሊቀ ጳጳስ ኾነው ተሾሙ!! በዚህች እለት 21 ጊዜ መድፍ ተተኮሰ! ታላቅ ደስታ ነበርና! ጊዜውም 1943 . ሲኾን ለአቡነ ባስልዮስ ሊቀ ጵጵስናውን የሰጡት የግብጹ ፓትርያርክ አቡነ ዮሳብ ነበሩ። 

1951-1963 ዓም ድረስ የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ ፓትርያር ኾኑ!!


በርግጥ ከአቡነ ባስልዮስ በፊት አቡነ አብርሐምና አቡነ ዮሐንስ የሚባሉ ሌሎች ሁለት ፓትርያርክ ነበሩ። ነገር ግን የኢጣልያው መንግስት ስለሾማቸው ቤተክርስቲያናችን ሕጋዊ ፓትርያርክ አድርጋ አትቀበላቸውም። የመጀመሪያው ሕጋዊ ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ናቸው።



ከአቡነ ባስልዮስ ቀጥሎ ፓትርያር አቡነ ቴዎፍሎስ ናቸው።

ከአቡነ ቴዎፍሎስ ቀጥሎ አቡነ ተክለሐይማኖት ናቸው። 

ከአቡነ ተክለሐይማኖት ቀጥሎ አቡነ መርቆርዮስ ናቸው።

ከአቡነ መርቆርዮስ ቀጥሎ አቡነ ጳውሎስ ናቸው።


ከአቡነ ጳውሎስ ቀጥሎ ማን ይሆን?

ለቤተክርስቲያን ቀናተኛ ለመንጋው መልካም እረኛ እግዚአብሔር ያዘጋጅልን።