Monday 20 August 2012

መክሊት




አንድ ወጣት ልጅ ከአባቱ ጋር ሆኖ በባቡር ተሳፍሮ ይጓዝ ነበር። በድንገት በባቡሩ መስኮት እያየ እየዘለለ እንዲህ እያለ ጮኸአባቴ እይ ዛፎቹ ወደ ኋላ እየሮጡ ነውአለ። አባትየው ፈገግ አሉ። ከአጠገቡ የተቀመጡ ሰዎች ግን በልጁ ጸባይ አልተደሰቱምና በሕብረት አፈጠጡበት። በልባቸውም ተነጫነጩ። ልጁ ከእንደገና እየዘለለአባቴ አይታይህም እንዴ ደመናዎቹ ከኛ ጋር እየሮጡ ነውአለ። ይህን ጊዜ ተሳፋሪዎቹ በጣም ተናደዱና ልጅህን ለምን ሆስፒታል አትወስደውም? ብለው አባትየው ላይ በሕብረት ጮኹ። 

አባትየውም ፈገግ እያሉ ሆስፒታልማ ወስጀዋለሁ። እንዲያውም አሁን እኮ ነው
ሆስፒታል የመጣነው። ልጄ ከልጅነቱ ጀምሮ ዓይነ ስውር ነበር። ዛሬ ገና ዓይኑ ስለበራለት ነው እጅግ የተደሰተው አሏቸው። 

ሁሉም ሰው በራሱ ዓለም የራሱ የሆነ ታሪክ አለው። ማንንም ሰው በሚገባ ሳናውቅ አንፍረድ። እውነታውን ስናውቅ ሊያስገርመን ይችላልና አሉ የልጁ አባት አሁንም ፍግግ እያሉ። ሰዎቹ በስራቸው ተሸማቀቁ። ልጁም ነገሩ ስለገባው እንዲህ አላቸው። ወገኖቼ ለብዙ ዘመናት ብርኃንኔን አጥቼ ነበር። እንደ መጻጉዕ ሰው የለኝም ብዬ ተስፋ ቆርጬ ነበር። ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ብሎ ይህን ሁሉ ሕዝብ ፈጥሮ ሰው የለንም ስንል ይገርመኛል። ይህን ማለታችን ግን አያስወቅሰንም። ታላቁ ነቢይ ነቢዩ ኤልያስም ሰው የለኝም ብሎ ነበርና። በአንድ ወቅት ኤልያስ ብቸኝነት ተሰምቶት ነበር። እንኳን እኛ ነቢያቱም ብቻዬን ነኝ ብለው ነበር። በተለይ በስደት ሀገር ብቸኝነት ይሰማናል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ያለው ሰው ብቻዬን ነኝ ሊል አይገባውም። 

ልጁ የዐይኑን ኳስ እያንከባለለ ንግግሩን ቀጠለ። 

በጨለማው ዘመን ብቸኝነት ቢሰማኝም ዓይኑ የበራለት የበጥለሚዮስን ታሪክ ስለማውቅ ተስፋ ነበረኝ። ብርኃንን የመሰለ ነገር ምን አለ! ብርኃን መክሊት ነው። ይህን መክሊታቸውን ያላከበሩ ብዙ አሉ። ይህች የዛሬ ብርኃኔ ብዙ መክሊትን ማትረፍ አለባት። በጨለማው ዘመኔ የዓይን ስፔሽሊስት ለመሆን ተምሬያለሁ። እውቀቱ አለኝ። የሚቀረኝ ልምድ ብቻ ነውና ለዓይን አልባ ወገኖቼ በነጻ ሕክምና መስጠት አለብኝ። ይህች የዛሬ ብርኃኔ ብዙ መክሊትን ማትረፍ አለባት አላቸው።

መክሊት!

አምስት መክሊት የተሰጠው አትርፎ አሥር አደረገ።

ሁለት መክሊት የተሰጠውም አትርፎ አራት አደረገ።

አንድ መክሊት የተሰጠው ግን መክሊቱን ቀበራት!


አምስት መክሊት ያለው ሙሴ ነው። አምስት መጻሕፍት አሉትና። ሁለት መክሊት ያለው የቅ/ጴጥሮስ ምሳሌ ነው። ብሉይና ሐዲስን አስተምሯልና። አንድ መክሊት የተሰጠው መክሊቱን ቀበረ። ይህም ይሁዳ ነው። 

አንድም አምስት መክሊት የተሰጣቸው አስተምረው መክረው ፍሬ አፍርተው ቀልጸው ልክ ራሳቸውን አስመስለው ደቀ መዛሙርትን ያሳደጉ የፍጹማን ምሳሌ ናቸው። ቅጳውሎስ ጢሞቴዎስን እንዳስተማረ፤ /ጴጥሮስ ቀሌምንጦስን እንዳስተማረ። አንድ መክሊት ተሰጥቶት መክሊቱን የቀበረው ግን ተምሮ ያላስተማረ ሰው ምሳሌ ነው።

አንድም አምስት መክሊት የፍጹም ፍቅር የፍጹም ትህትና የፍጹም ትዕግሥት ምሳሌ ነው። 

አንድም አምስት መክሊት ያላቸው ጳጳሳት ናቸው።

ሁለት መክሊት ያላቸው ካህናት ናቸው።

አንድ መክሊት ያለቻው ዲያቆናት ናቸው።

ከኛ መካከል መክሊታችንን የቀበርን ስንቶቻችን እንሆን? የበዛ ስጦታ እያለን ቤተክርስቲያንን አለማገልገል መክሊት መቅበር ነው። ምርጥ ዕቃ የተባለው ንዋየ ኅሩይ /ጳውሎስ የጸጋ ስጦታ ልዩ ልዩ ነው እንዳለው እያንዳንዳችን የተሰጠን ጸጋ አለን። ይህን ጸጋ አለማወቅና በተሰጠን ጸጋ አለመስራት መክሊትን መቅበር ነው። 

እስቲ የኔ መክሊት ምንድን ነው? ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ፤ አሁን ደግሞ መክሊቴ ያለው የት ነው? የመክሊቴ ትርፍ ስንት ነው? በሉ። 
ለብዙ ዘመናት መክሊታችንን ቀብረን ነበር። ዛሬ ሁሉም የራሱን መክሊት ይወቅና ያትርፍ።

መክሊቴን ቀብሬ ባሳዝንህ (ማቴ. 25÷14-30)
መብራቴንም ይዤ ባልጠብቅህ
በታላቅ ይቅርታ እንድትምረኝ
በፍቅርህ ጎብኝተህ ከሞት አውጣኝ
የኔን ስራ ተወው ምግባሬን
የመስቀሉን ነገር መርሳቴን (ገላትያ 3:1)
አዚሜን አንስተህ አንተን ልይህ 
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላኬ ነህ።

ቸርነትህ ነው ያደረሰኝ እስከ ዛሬ 
ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከ ዛሬ 
ላመስግንህ የኔ ጌታ በዝማሬ /2/

Visit this Blog! http://yonas-zekarias.blogspot.com/
Unlike ·  · Unfollow Post · Share · Edit
·                                  
·                                
You, Fasica Belay, Aresema Beza, Meklit Hailu and 80 others like this.
·                                 63 shares
·                                  
o                                                       
Azeeb Gabrue kal hiwot yasamalen manegsta samyaten yawerselen
o                                                       
Azeeb Gabrue yagalegelot zemanehen yarezemeleh
June 30 at 11:16am · Unlike · 2
o                                                       
Eyob Hailu Kale hiwot yasemalen rejem edemea mullu teneneten yadelelen
June 30 at 11:38am · Unlike · 2
o                                                       
Genet Damesa KALE HYWET YASEMAK WENDMI !!!
o                                                       
Balemual Getachew I DO NOT KNOW WHAT I SAY. BCHA BERTA
June 30 at 3:19pm · Unlike · 2
o                                                       
Meaza Mulatu Egziabher ysitilin wendimachin Yonas timhirtihin betam new yemiwedew weqitun tebikeh yemitastelalifew melikit des yilal tebarek!!
June 30 at 6:40pm · Unlike · 1
o                                                       
Merry Mesfin wendmacen yonas dingl maryam yagelglot edmehin tibarklin betam bizu negern temirenal kale hiwot yasemalin .
July 1 at 4:41pm · Unlike · 1
o                                                       
Yohens Yamer bexem des yilel echin aymenoot endat ende xebequu mewooq teleq belxenet new
July 1 at 4:47pm · Like · 1
o                                                       
touching story..luv it.tnx for sharing.
July 5 at 7:49pm · Like
o                                                       
Wondwosen Wubie ቃለ ህይወት ያሰማልን
July 6 at 1:53pm · Like
o                                                       
Tigest Gebre egziabhir yestlen yone gita yebarkeh
July 6 at 7:34pm · Like
o                                                       
Begosew Getaneh it doesn't any sense
o                                                       
yet new? seyamer betameeeeeeeee
o                                                       
Awol Assefa where is the whole poem?
o                                                       
is it around abiyadiy, endabohani?? i know this monastery it is some distance away from tembien abiady....
o                                                       
Tom Habtom · Friends with Edilam Eshetu and3 others
በጣም አስተማሪ ነው፣እናመሰግናለን!
o                                                       
qale hiwoten yasemalen

No comments: