የልጅ ዮናስ ቀልድ እና ቁም ነገር!

“ሁለት ቀን ለመኖር አራት ቀን አትጨነቅ” ..... "አሁን ገና በራልኝ አለች እብድ ቤትዋን አቃጥላ!!" ዘና ብላችሁ ተቀመጡና አንድ አሪፍ ታሪክ ላውጋችሁ! (ዘወትር ቅዳሜ ይጎብኙን)

Friday, 26 July 2013

ሚካኤል

‹ያዳናቸውን እግዚአብሔርን ረሱ፡፡ እንዳያጠፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ፡፡›› የተሰመረበትንና ደምቆ የተጻፈውን ኃይለ ቃል ልብ ብለህ ተመልከት፡፡ (መዝ015.23) ባይቆም ኖሮ ሲል ባያማልዳቸው፣ ባይለምንላቸው፣ ባይጸልይላቸው ኖሮ ማለቱ ነው፡፡ ስለዚህ መቆም የሚለው ቃል ማማለድ የሚል ትርጉም እንደሚኖረው እንረዳለን፡፡

ዳግመኛም መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች (መላእክት) በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ፡፡ ሰይጣንም ደግሞ በመካከላቸው መጣ›› ይለናል፡፡ ‹‹ለመቆም›› ሲል ለመለመን፣ ለማማለድ ማለት ነው፡፡ አብሮአቸውም ሰይጣን መምጣቱን ልብ በል፡፡ ሰይጣን የመጣው ለምን ነበር? ጻድቁ ኢዮብን ለመፈተን ፈቃድ ያገኝ ዘንድ ፈጣሪውን ለመለመን አልነበረምን? የመላእክትም አመጣጥ ፈጣሪቸውን ስለሰው ለመለመን እንጂ ለሌላ አልነበረም፡፡ ይህን ሲገልጥ ‹‹ለመቆም መጡ›› ይለናል፡፡ መቆም መለመን፣ ማማለድ ማለት ነውና፡፡ (ኢዮ1.6)

መቆም ማለት መጸለይ፣ ማማለድ የሚል ፍቺ እንዳለው ካስጨበጡ በኋላ ይህንን ቃል በመጠቀም የመላእክትን አማላጅነት ማስረዳት ቀላል ይሆናል፡፡

ቃላት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እኛ ከምናውቀው ውጭ አንዳንድ ጊዜ በተቃራኒ አቅጣጫም እንኳን ፍቺ ይዘው ይገኛሉ፡፡ አገባባቸውን እንደመጽሐፍ ቅዱስ ዘይቤና ምሥጢር መማር የሚያስፈልገው ከዚህ የተነሣ ነው፡፡ ለብዙ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ የተቀመጡ ቃላትን ትክክለኛ መንፈስ አለመረዳት የመላእክትን አማላጅነት እንዳይረዱ አድርጓቸዋልና፡፡

ለምሳሌ፡- ቅዱስ ገብርኤል ራሱ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መልአኩ ገብርኤል ነኝ፡፡›› በማለት ተናግሯል፡፡ ይህም በቅዱስ ወንጌል የተጻፈ ኃይለ ቃል ሲሆን አብዛኞቻንን እናውቀዋለን፡፡ ልዩ የሚሆነው ግን የቃሉን ትክክለኛ አገባባዊ ትርጉም ባለማወቃችን ምክንያት መልአኩ ይህን ባለ ጊዜ ‹‹እኔ አማላጅ ነኝ›› እንዳለን አድርገን አለመረዳታችን ነው፡፡ መቆም ማለት ማማለድ የሚል ትርጉም ካለው ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የምቆም›› ማለት ደግሞ ‹‹የማማልድ›› ማለት መሆኑ አይጠረጠርም፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ገብርኤል አማላጅነቱን ራሱ ግልጽ በሆነ መንገድ ነግሮናል ማለት ነው፡፡

እስኪ እናንተ ፍረዱ! በዚህ ስፍራ ቅዱስ ገብርኤል አማላጅ ነኝ ማለቱን ካላመንን ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው›› ማለቱን ምን ብለን እንረዳዋለን? የእግዚአብሔር ፊቱ ወደ ሁሉም አቅጣጫ ነው እንጂ እንደፍጡር ወደ አንድ ገጽ የተወሰነ አይደለም፡፡ መላእክት ደግሞ በተፍጥሯቸው እንደ ሰው ልጅ የሚታጠፍና የሚዘረጋ እግረ ሥጋ ስለሌላቸው አይቀመጡም፤ አይተኙምም፡፡ ታዲያ አማላጃችሁ ነኝ ማለቱ ካልሆነ በቀር መልአኩ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው›› ሲል ምን ማለቱ ነው? መልአኩ እግዚአብሔርን እንደ ምድራዊ ንጉሥ ራሱን ደግሞ እንደ ንጉሥ ወታደር ቆጥሮ በንጉሡ ፊት ቀጥ ብዬ የምውል ዘበኛ ነኝ ማለቱ ነውን? በፍጹም አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ቤት ደጅ አፍ መቆምና በእግዚአብሔር ፊት መቆም ሁለት የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ምሥጢራቸውም እንዲሁ የተለያየ ነው፡፡ (ራእ21.12፤ ዘፍ3.24) ይልቅ ሊሆን የሚችለው እኔ በፊቱ ባለሟልነት ያለኝ ሁሉ ጊዜ ስለ እናንተ የማማልድ ነኝ የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

መልአኩ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ለምንድን ነው? ለማመስገን ነው እንዳንል ይህንን ሐሳብ ለካህኑ ለዘካርያስ መንገር ለምን አስፈለገው? የሚል ጥያቄ ያስነሣል፡፡ ትርጉሙ እንዲህ ቢሆን ወደ ካህኑ ወደ ዘካርያስ ከመጣበት ጉዳይ ጋር ንግግሩ ምንም ግንኙነት አይኖረውምና ይህን መናገር አያስፈልገውም፡፡ ከዚህ ይልቅ እኔ ሰዎችን ሁሉ ለማማለድ በእግዚአብሔር የምቆም ባለሟልነት ያለኝ መልአክ በመሆኔ የለመንከው ልመና መድረሱን የምሥራች ልነግርህ ብመጣ ቃሌን እንዴት ትጠራጠራለህ? ለማለት ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መልአኩ ገብርኤል ነኝ›› በማለት መልአኩ ይህን ተናገረ ብንል ከሁሉ በላይ የሚያስኬድና ለአእምሮ የሚመች ትክክለኛ ትርጓሜ ነው፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ስለ ቅዱስ ሚካኤልም በትንቢተ ዳንኤል ላይ እንዲህ ተጽፏል፡፡ ‹‹በዚያ ወራት ስለ ሕዝብ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል›› ይላል፡፡ (ዳን12.1) በዚህ ጥቅስ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹ስለ ሕዝብ ልጆች የሚቆመው›› ተብሏል፡፡ እረ ለመሆኑ ቅዱስ ሚካኤል ስለ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ‹‹የሚቆመው›› ለምንድር ነው? ለማማለድ አይደለምን? ይህን ካልተቀበልን ቃሉን ምን ብለን እንተረጉመዋለን? ለማመስገን ይቆማል እንዳንል ቃሉ የሚለው ‹‹ስለ ሕዝብ ልጆች የሚቆመው›› ነው፡፡ ስለ እኛ ጥብቅና ይቆማል እንዳንል ወደ ባሰ ስሕተት ይወስደናል፡፡ ሚካኤል በእግዚአብሔር ፊት ጥብቅና አይቆምምና፡፡ እግዚአብሔርም በጠበቃ የሚሟገቱት አምላክ አይደለምና፡፡ ጥብቅና ይቆማል ከማለት ይልቅ ትክክለኛውና የሚስማማው ወደ ፈጣሪ ሊለምንልን ወይም እኛን ለማማለድ ይቆማል የሚለው ትርጓሜ ነው፡፡ አስቀድሞ እንደተመለከትነው ‹‹መቆም›› የሚለው ቃል ማማለድ የሚል ትርጉም አለውና፡፡
Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 04:49 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

ሕሊና እና ምክንያት





በጎ ሕሊና ያለው ሰው እንዴት የታደለ ነው? ብዙዎች ግን ሕሊናቸውን በምክንያት ያታልሉታል። ድሮ ድሮ ኢየሱስ ጾሞልኛል ብለው ለሕሊናቸው ምክንያት ነግረውት ነበር። ነበር ካልኩ ነገር አለ ማለት ነው፤ ዛሬ ግን መጾም ተጀምሯልና ተመስገን ነው። ግን ግን ምስጢር መደበቁ ነው? መጾማችሁን ሳትነግሩን ድንገት መጾም ጀመራችሁሳ፤ ሆኖም ሁል ጊዜ ወቀሳ ብቻ ሳይሆን ማበረታታትም ይገባልና በርቱ።

በጅብ ሆዳምነት በእህል ጣፋጭነት ሳይተዋወቁ ይኖራሉ አሉ! የሀገራችን ጅብ ቀን ሙሉ ጾሞ ማታ ያገኘውን ሁሉ ግጥም አድርጎ ይጠልፋል አሉ። ጅብ በእኛ ጊዜ ቀረ!! መቼስ የዘንድሮ ጅብ አይረባም ፤ ሲዖል ይዘጋላችሁና ጅቦቹ እንደ ድሮ ከመጥለፍ አፕታይታችን ተዘግቷል አሉ። መቼስ የመርካቶ አራዳ ምግብ ሲበላ እንደ ጉድ ጠለፍን ነው የሚለው አሉ። የዛሬ ዘመዶቻችን ጾማችን ከጅብ ጾም መለየት አለበት አትሉም? ዳንኤልና ሰልስቱ ደቂቅ ጮማ ቁረጡ ጠጁንም ገልብጡ ሲባሉ አትክልትና ውኃ ይበቃናል አሉ።

መዝሙረ ዳዊት

109፥24 ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ።

አሁን ማን ይሙት ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ቅቤ ጠፋ? ታድያ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ ለምን አለ?

እንግዲያውስ ምን እንላለን? ኢየሱስ አድኖኛልና ሁሉ ተፈጸመ ካላችሁ ጾም ለምን አስፈለጋችሁ? ይህን በእጅጉ አስቡበት። ሐዋርያው በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ አለን። ያለመከራ አይገኝም እንጀራ እንዲሉ በመከራችን ብዛት የዘላለም ሕይወትን ባንወርስም ዘላለማዊ ሕይወት በቀላሉ አትገኝም። በጠባብዋ በር ተመላለሱም የተባለው ለዚህ ነው። ጮማ መቁረጥ ቢራ መገልበት ሲቻል አባቶች በበረሃ አትክልት መብላታቸው ዳዊትና ዳንኤል የጾሙትን አይተው ነው። እናንተም ትጾማላችሁ ፤ ገዳማዊያኑም ከእናንተ አስበልጠው ይጾማሉ። ታድያ ከእናንተና ከአባቶች የተሻለውን ማን አደረገ?? በስራና ያለ ስራ መንግስተ ሰማይ አንገባም! በሌላ አነጋገር ስራ የግድ ያስፈልጋል።

አንዳንዶቹም ምክንያት ፍለጋ ይደክማሉ። በየአይነቱ እየበላችሁ ቢራ እየገጠማችሁ ለምን ትጾማላችሁ እያሉ ለሕሊናቸው ምቹ ምክንያት ይነግሩታል። ይህ ግን ምክንያት እንጂ ትክክለኛነትን አያስረዳም። ቢራ ለሚደረግመው ስጋን የሚተኩ ምርጣምርጥ ምግቦች ለሚበላው ጾም ይህ አይደለም ብለን እንነግረዋለን እንጂ ሕሊናዬ ሆይ ደስ ይበልህ ምክንያት አለልህና አትረበሽ አንለውም!

ሕሊና እና ምክንያት

አንድ ኦርቶዶክስ ወንድሜ እንዲህ ብሎ ጠየቀ፦ ሴቶች ራሳቸውን ሳይከናነቡ ለምን ይጸልያሉ? አንዱ ፕሮቴስታንት ደግሞ ተከናንቦ የሚጸልይ ወንድ ራሱን ያዋርዳል ይላልና ካህናቱ ለምን ይጠመጥማሉ ብሎ ጠየቀ። ወዲያው አንዷ እህቴ አሁንማ የነብርን ጭራ ያዝን ብላ እጅግ ስትደሰት አየሁና ተገረምኩ። ለዘመናት የሕሊናዋ ጥያቄ ነበር ማለት ነው። እንግዲያውስ ስለምን ከህሊናዋ ጋ ስትጣላ ኖረች? በመሰረቱ ካህናቱ ከተሳሳቱ እኛን አትናገሩን እንደፈለግን እንሁን እንዴት ይባላል? ሁለታችንም ወደ እውነት እንምጣ ይባላል እንጂ ለሕሊና ምክንያት መደርደር ሕሊና ራሱ ይታዘባል! የዳዊት በገና ይደረደራል እንጂ የሕሊና ምክንያት አይደረደርም!

ተከናንቦ የሚጸልይ ወንድ ራሱን ያዋርዳል ካህናቱ ለምን ይጠመጥማሉ? ካህኑ ኢያሱ በራሱ ላይ ይጠመጥም ነበር። እነሆ መልአኩም አዲስ ጥምጣም ጠመጠመለት እንዲል ካህናት የሚጠመጥሙት ለዚህ ነው።

ዘፀ28:40 ቆቦችንም ለክብር ታደርግላቸዋለሀ...41 በክሀነት እንዲያገለግሉ
ዘሌ8:9 እግዚአብሄርም ሙሴን እንዳዘዘው በራሱ ላይ መጠምጠሚያዉን አደረገ...የተቀደሰዉንም አክሊል
ዘካ6:11 አክሊሎችንም ስራ በታላቁም ካሀን ...ራስ ላይ ደፋ 1ነገ21...

እንግዲያውስ ምን እንላለን? ካህናቱ የሚጠመጥሙት በዚህ ምክንያት ከሆነ እህቶቻችን ፍሪዝ አድርገው የሚጸልዩት ለምን ይሆን? ዘመዶቼ ሆይ ለሥጋችሁ ምኞት ስለምን ምክንያት ፈለጋችሁ? እህቶች ሆይ ኢስላም እህቶች ሲከናነቡ ጌታን ተከታይ መንፈሳዊያኑ ምክንያት ከምትፈልጉ ሥጋዊ ምኞታችሁን መቆጣጠር እንዴት አቃታችሁ? ቅ/ጳውሎስ ሰውን ከማሰናከል ከቶ ሥጋ አልበላም አለ። አስቡት ስጋ መብላት ኃጢአት ባይሆንም ሰውን ላለማሰናከል ብቻ ስጋ አልበላም አለ። ዘመዶቼ ሰውን ላለማሰናከል ይህን ያህል ባታስቡ ትንሿን ነገር መፈጸም እንዴት ተሳናችሁ? በመላዕክት ምክንያት ሴት ራስዋን ትከናነብ ይላል። መላዕክት ሥርዓትን ነቅተው ስለሚጠብቁ በቅድስት ቤተክርስቲያን ሴቶች ራሳቸውን ተከናንበው እንዳማረባቸው ውብ ሆነው ያመሰግናሉ።

አንዳንዶቹም ቅ/ጳውሎስ የጻፈበት ባህል እንጂ ግዴታ አይደለም እያሉ በባህል እያማካኙ እንደተለመደው ለሕሊናቸው ምክንያት ይሰጣሉ። ሕሊና ምክንያት ካላገኘ ደጋግሞ ይጠይቃልና ምክንያት ማቅረባቸው የግድ ነው። ከዚህ ውጪ የሆኑ ብዙ ምክንያቶችም እንደሚደረደሩ እናውቃለንና ሰው በገና ይደረድራል እንጂ ምክንያት አይደረድርም እንላቸዋለን።

ሴቶች ፓስተር ለምን አይሆኑም የሚሉም አሉ። ክርስቶስ 12 ሐዋርያትን ሲመርጥ 6 ወንድ 6 ሴት አድርጎ መምረጥ ይችል ነበር። ከየት እንደመጣ አይታወቅም በድፍረት ይፈጽሙታል። ፕሮቴስታንት ዘመዶቻችንን የሚመሩ አውሮፓዊያን በድፍረት ሁሉን ያከናውናሉ። የሰውን ልጅ ፍቅር እግዚአብሔር ይወዳልና ወንድ ከወንድ ሴት ከሴት ቢጋቡ የፍቅር አምላክ ቅር አይለውም የሚል መፅሐፍ ቅዱስ በቅርቡ ይወጣልና ጠብቁ።

እንግዲህ ለዚህም ክፉ ነገር የሕሊና ምክንያት ይደረደር ይሆን? እንግዲያውስ ምን እንላለን? ለሁሉ ምክንያት ቀረበ፤ ለጾም ምክንያት ....ጅብ በጎቹን ጠብቅ ቢባል ይጠፉብኛል አለ አሉ! ምን አለ ምክንያት ከሚሰጥ እውነቱን ነግሮን ልበላቸው ፈልጌ ነው ቢል? ምክንያት ለሰው ብቻ ሳይሆን ለጅብም ይሰራል ለካ።
Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 02:05 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Thursday, 25 July 2013

ጥንተ አብሶ


በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ 
**የሰው ዘር ናት ማለት በራሱ ጥንተ አብሶ አለባት አያሰኝም፡፡
**ድንግል ማርያም የሞተችው ልጇ ጥንተ አብሶን ካስወገደ በኋላ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡ 
**እኛን እንዳዳነንና እንደቀደሰን ተሰቅሎ፣ ሞቶ፣ ደሙን አፍስሶ ሥጋውን ቆርሶ አዳናት ቢባል ካልዳነችና ካልነጻች ሴት ተወለደ ማለት ነውና ሁሉን ነገር ከንቱ ያሰኛል፡፡ አስቀድሞ ካነጻት በኋላ ከእርሷ ተወለደ የሚባል ከሆነ ደግሞ ያው ዓለሙ ሁሉ ከመዳኑ በፊት ድኅነት በልዩ መንገድ ለእርሷ እንደተደረገ ማመን ግድ ነው፡፡
**‹‹ይህማ ካቶሊኮች ትምህርት ነው›› ፖለቲከኛነት እንጂ መንፈሳዊነት አይደለም፡፡
**የክርስትና እምነታችን ከግብጽ እንዳልመጣልን የታመነ ነው፡፡ 
**‹‹አቡነ እገሌ እንዲህ ያምኑ ነበር፤ አባ እገሌ እንዲህ ብለው ጽፈዋል፤ እንዲህ አስተምረዋል›› ኢየሱስ ክርሰቶስ የመሠረታትን ቤተ ክርስቲያን ክብር የሚነካና በግለሰብእ የተመሠረች ሃይማኖት አድርጎ መቁጠር ነው፡፡ 

ከሁሉ አስቀድሞ ‹‹ጥንተ አብሶ›› ማለት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት ይኖርብናል፡፡ በአጭሩ ‹‹ጥንት›› ማለት መነሻ፣መጀመሪያ ማለት ሲሆን ‹‹አብሶ›› ማለት ደግሞ በደል ማለት ነው፡፡ ሁለቱ ቃላት ተናበው የሚፈጥሩት ሐረግ ‹‹ጥንተ አብሶ›› ሲሆን የበደል መጀመሪያ የሆነ በደልን ያመለክታል፡፡በነጻ ፈቃዳቸው አስበው መበደል የሚችሉ የፍጥረት ወገኖች ሰዎችና መላእክት ናቸው፡፡ በሰማይ በደል የተጀመረው በዓለመ መላእክት ሲሆን በደለኞቹም ሰይጣንና ሠራዊቱ ናቸው፡፡ የሰዎች ልጆች ስለፈጸሙት በደል የምንነጋገር ከሆነ ግን በመጀመሪያ የበደሉ አዳምና ሔዋን ናቸው፡፡ የአዳምንና የሔዋንን በደል የውርስ ኃጢአት ከማለት ይልቅ ጥንተ አብሶ ማለት የበለጠ ይገልጠዋል፡፡ ያ የቀደመ በደል ተወግዷል፡፡ የሰው ልጆች በሙሉ በወልደ ማርያም በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ቤዛነት
ከቀደመው በደል ነጻ ወጥተዋል፤፡፡ ይህን ማስተዋል ስለተሣነው ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ‹‹እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል።›› በጥቅሱ መሠረት ዓይነ ልቡናው የታወረ ካልሆነ በቀር ማንም ቢሆን ከቀደመው ኃጢአት የነጻ መሆኑን መዘንጋት የለበትም፡፡ ይህን መርሳት አምላካችን የከፈለልንን ዋጋ እንደ ከንቱ መቁጠር ነውና፡፡ (2ጴጥ 1፥9)

ጥንተ አብሶ አለባት የሚሉ ሰዎች የሚያቀርቧቸው መከራከሪያዎች 

1.ኛ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከኢያቄምና ከሃና በሩካቤ በዘር የተወለደች የባሕርያችን መመኪያ ፍጽምት ሰው ናት፡፡ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያን የቀደሙትን አበው ቃል እና መጽሐፍ ቅዱስን ዋቢ በማድረግ ‹‹ቅድስት ድንግል ሰማያዊት ናት/ የሰው ዘር አይደለችም/ የሚል ቢኖር ውጉዝ ይሁን›› እያለች አጥብቃ ታስተምራለች፡፡ (ሃይ.አበ 123፥8) ይሁን እንጂ የሰው ዘር ናት ማለት በራሱ ጥንተ አብሶ አለባት አያሰኝም፡፡ አንዳንዶች ሰው ከሆነች ጥንተ አብሶ እንዴት አልኖረባትም እያሉ ይሞግታሉ፡፡ ይህም የጥንተ አብሶን ምንነት ካለማወቅ የሚመጣ ሙግት ነው፡፡ ጥንተ አብሶ በደልና የበደል ውጤት እንጂ ራሱን የቻለ ፍጥረት አይደለም፡፡ ማለትም ሰው እንደተፈጠረባቸው እንደ አራቱ ባሕርያተ ሥጋ እንደ እሳት፣ ነፋስ፣ ውኃና አፈር አይደለም፡፡ አዳም ሳይበድል በፊት ሰው ነው፡፡ መተላለፍ ካገኘውም በኋላ ሰው ነው፡፡ ጥንተ አብሶ የሌለበት ሰው ሊኖር አይችልም አይባልም፡፡ ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ አልደረሰባትም ነገር ግን ሰው ናት፡፡ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስም ጥንተ አብሶን ያጠፋ ፍጹም ሰውና አምላክ ነው፡፡ እኛም ክርስቲያኖች ጥንተ አብሶ ጠፍቶልናል፡፡ ነገር ግን አሁንም ሰዎች ነን፡፡ ስለዚህ ድንግል ማርያም ሰው እስከሆነች ድረስ ግድ ጥንተ አብሶ ነበረባት ማለት ጥንተ አብሶን ተፈጥሮአዊ ማድረግ ነውና ስሕተት ነው፡፡ ጥንተ አብሶ በሰው አለመታዘዝ ምክንያት የመጣ በደል እንጂ ከሰው ልጆች ጋር አብሮ የተፈጠረ ተፈጥሮአዊ ባሕርይ አይደለም፡፡ አዳምም ራሱ በጥንተ አብሶ ከመገኘቱ በፊት ሰው መሆኑን መርሳት አይገባም፡፡

2.ኛ ድንግል ማርያም በ64 ዘመኗ ሞታ በልጇ ሥልጣን ተነሥታለች፡፡ በሦስተኛውም ቀን አሳርጓታል፡፡ ይኸውም ሲሰላ ሞትን ይገድል ዘንድ የሞተው ልጇ በሥልጣኑ ተነሥቶ ካረገ ከ15 ዓመታት በኋላ ይሆናል፡፡ የእርሷ ሞት ‹‹ሁሉን የሚያስደንቅና›› ምክንያት ያለው ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ እንደተናገረው ልጇ በፍርድ እንደማያዳላ የሚያስተምር እና እርሷ የሰው ዘር እንጂ የመላእክት ዘር አለመሆኗን የሚያረጋግጥ ክንውን ነው፡፡ መላእክት እንደ ሰው አይሞቱምና፡፡ ይሁን እንጂ በመሞቷ ምክንያት ብቻ ጥንተ አብሶ ስለነበረባት ነው እያሉ የሚጽፉ አሉ፡፡ ድንግል ማርያም መሞቷ ከላይ የጠቀስነውን እውነታ እንጂ ጥንተ አብሶ ነበረባት አያሰኝም፡፡ የሞተችው ልጇ ጥንተ አብሶን ካስወገደ በኋላ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡ በጥንተ አብሶ ምክንያት ሞተች ማለት ጥንተ አብሶ አልተወገደም ማለት ነውና ከባድ ክህደት ነው፡፡ መሞት ብቻውን ጥንተ አብሶ መኖሩን ያሳያል የሚባል ከሆነ ክብር ይግባውና ኢየሱስ ክርስቶስም ሞቶ ስለተነሣ ጥንተ አብሶ ነበረበት እንደማለት ይቆጠራል፡፡ ይህ ደግሞ አይሁድ ከፈጸሙት የሚከፋ ኃጢአት ነው፡፡ እንኳን ድንግል ማርያም እኛም የምንሞተው ሞት በጥንተ አብሶ ተይዘን አለመሆኑን መረዳት አለብን፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ ሞትን በሃይማኖተ አበው ወደ መንግሥተ ሰማያት እንገባበት ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ መርቆና ከፍቶ ያዘጋጀልን ‹‹አዲስ መንገድ›› ይለዋል፡፡ (ሃይ.አበ 80፥17) ቅዱስ ባስልዮስም በጸሎቱ ስለ ሞት ሲናገር ‹‹ለባሪያዎችህ ሞት የለባቸውም ፍልሰት እንጂ›› በማለት ሞትን ‹‹ፍልሰት›› ሲል ሰይሞታል፡፡ (እግዚአ ሕያዋን) ለሚያምኑ ሁሉ ‹‹ሞት ጥቅም›› ነው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ (ፊል፥121) ስለዚህ ድንግል ማርያም ሞታ መነሣቷ የታመነ ቢሆንም ይህን እየጠቀሱ ጥንተ አብሶ አግኝቷት ነበር ማለት ስሕተት ነው፡፡

3.ኛ እመቤታች በጸሎቷ መሃል ‹‹መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች›› ማለቷን ቅዱስ ሉቃስ በወንጌል መዝግቦልናል፡፡ (ሉቃ1፥47) ‹‹መድኃኒቴ›› ማለቷን በመጥቀስ እንደማንኛውም ሰው ከጥንተ አብሶ መዳን የሚያስፈልጋት ስለነበረችና ስላዳናት ‹‹መድኃኒቴ›› አለች በማለት የሚከራከሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ይህ ቃል እመቤታችን በሃይማኖት የተናገረችው ነው፡፡ አምላክ የሌለው የለምና ሁሉም አምላኬ ሊል ይችላል፡፡ ‹‹መድኃኔቴ›› የሚል ግን የወደደና ፈቅዶ የተቀበለ፤ የተደረገለትንም ያወቀ ሰው ነው፡፡ ስለዚህ እመቤታችን ጥበቃውን እና ያደረገላትን በማድነቅ ፈጣሪዋን ያመሰገነችበት የደስታ ቃል ነው፡፡ ጥንተ አብሶ ነበረባት ግን አያሰኝም፡፡

ምክንያቱም ሰው ዳነ የሚባለው ከደረሰበት ነገር ሲድን ብቻ አይደለም፡፡ ሊደርስበት ከነበረ ነገር የተሰወረ ሰው ተረፈ ወይም ዳነ ይባላል፡፡ መድኃኒትም መድኃኒት የሚባለው የታመመውን ሲፈውስ ብቻ አይደለም፡፡ ገና ያልታመሙ እንዳይታመሙ የሚከላከልም እንዲሁ መድኃኒት ይባላል፡፡ በዚህ ማብራሪያ መሠረት ድንግል ማርያም ‹‹መድኃኒቴ›› ያለችው ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ስለሰወራትና ስላዳናት እንጂ እንደማንኛውም የሰው ዘር ጥንተ አብሶ ካገኛት በኋላ አድኗት አይደለም፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ያለው ጥቅስ ከላይ ያብራራሁትን ሐሳብ የሚደግፍ ቃል ይገኝበታል፡፡ የግብጹ ፈርዖን የእስራኤል ሴቶች ሲወልዱ ወንዶች ከተወለዱ ወዲያው እንዲገድሏቸው አዋላጆችን ሁሉ አዝዞ ነበር፡፡ ነገር ግን አዋላጆቹ በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት ሳይገድሉ አንዳንድ ወንዶችን እንዲሁ ተውዋቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ንጉሡ የግብፅም ንጉሥ አዋላጆችን ጠርቶ። ለምን እንዲህ አደረጋችሁ? ‹‹ወንዶቹን ሕፃናትንስ ለምን አዳናችሁ? አላቸው።›› (ዘጸ1፥18) እነዚህ ሕጻናት በሌሎች ሕጻናት የተፈረደው ፍርድ ተፈጻሚ ስላለሆነባቸው ‹‹ዳኑ›› ተባለ፡፡ ልብ በሉ ‹‹ዳኑ›› የተባለው ከበሽታ ቢሆን ሕመም አግኝቷቸው ነበር ለማለት እንከጅል
ይሆናል፡፡ እነዚህ ሰዎች የዳኑት ፈርዖን አውጆት ከነበረው የሞት ፍርድ ነበር፡፡ ታዲያ እነዚህ ሕጻናት ከሞት ዳኑ ማለት ሞተው ተነሡ ማለት ነው ወይስ ሳይሞቱ ቀሩ?

በተመሳሳይ ሁኔታ እመቤታችንም መድኃኒቴ ማለቷ በዕደ እግዚአብሔር ከጥንተ አብሶና በአዳም ከተፈረደው ፍርድ ስለተጠበቀች እንጂ ረክሳ ስለተቀደሰች አይደለም፡፡ ሎቱ ስብሐት! እንዲሁ በዘሮቹ ሁሉ ላይ በአዳም ምክንያት ፍርድ የተፈረደባቸው ሆኖ ሳለ እርሷ ግን የአዳም ዘር ብትሆንም ቅሉ ያ ዕዳ አላገኛትምና ከዚያ ሁሉ የዳነች ናት፡፡ ያዳናትም አምላኳ ነውና ‹‹አምላኬ፣ መድኃኒቴ›› አለች፡፡ ሊደርስብን ካለ ወይም ከተቃጣ ነገር ወይም እንደሚደርስ ከሚገመት ነገር ነጻ መሆን ራሱ መዳን ይባላል፡፡ ለምሳሌ ሕጻናት ገደል እንዳይገቡ እሳት እንዳያቃጥላቸው ነጠቅ ብታደርጓቸው ዳኑ አይባልምን? ሐዋርያው ጴጥሮስ የሞት ፍርድ ሳይፈረድበት ከእስር ቤት መልአኩን ልኮ ስላዳነው ‹‹አዳነኝ›› ማለቱ ተጽፎአል፡፡(የሐዋ12፥11)

ድንግል ማርያምን ዓለም በዳነበት መንገድ ዳነች፣ ነጻች እያሉ መናገር እናትነቷን መካድ ነው፡፡ እኛን እንዳዳነንና እንደቀደሰን ተሰቅሎ፣ ሞቶ፣ ደሙን አፍስሶ ሥጋውን ቆርሶ አዳናት ቢባል ካልዳነችና ካልነጻች ሴት ተወለደ ማለት ነውና ሁሉን ነገር ከንቱ ያሰኛል፡፡ አስቀድሞ ካነጻት በኋላ ከእርሷ ተወለደ የሚባል ከሆነ ደግሞ ያው ዓለሙ ሁሉ ከመዳኑ በፊት ድኅነት በልዩ መንገድ ለእርሷ እንደተደረገ ማመን ግድ ነው፡፡ እዚህ ድረስ መምጣት ግድ ከሆነ እንደ ኦርቶዶክሳዊያኑ አስቀድሞ ጠበቃት ማለት ክፋቱ ምን ላይ ነው? የበለጠ ፍጹምና መንፈሳዊው የእምነት መንገድ ይልቅ እንዲህ ማመን ነው፡፡ ምክንያቱም ሊወለድባት ሲልም ቢሆን ለብቻዋ ማንጻቱ ላይቀር ከእርሷ ለመጸነስ እስኪመጣ ድረስ ሁሉን እያወቀ ከጥንተ አብሶ ጋር እንድትቆይ አደረገ ከማለት አስቀድሞ በንጽሕና ጠብቆ አኖራት ማለት የበለጠ የቀና ነውና፡፡ ሰው እንኳን ቆይቶ የሚመገብበትን ቁስ ወድቆ ቢያይ ልበላበት ስል አጥበዋለሁና እስከዚያ ይንከባለል ብሎ ችላ እንደማይል የታመነ ነው፡፡ አምላክ እስክወለድባት በጥንተ አብሶ አድፋ ትቆይ ብሎ እናቱን ተዋት ማለት የማይመስል ነገር ነው፡፡

4.ኛ አንዳንዶች ‹‹ድንግል ማርያምን ጥንተ አብሶ ከቶ አላገኛትም›› የሚለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲሰሙ ‹‹ይህማ ካቶሊኮች ትምህርት ነው›› በማለት ለማስተባበል ይሞክራሉ፡፡ ይህንኑ ሐሳብ በጽሑፍ ያቀረቡ ሰዎች አሉ፡፡ ካቶሊኮች ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም ስላሉ ከእነርሱ ለመለየት ስንል እኛ የሌለባትን ጥንተ አብሶ አለባት ብንል ተገቢ አይደለም፡፡ ልዩነቶቻችን እንደተጠበቁ ሆነው ከካቶሊኮች ጋር የምንጋራቸው በርካታ ሃይማኖታዊ ጽንሰ ሐሳቦች አሉ፡፡ እነርሱን ላለመምሰል የምንመሳሰልባቸውን ሐሳቦች ሁሉ የኛ አይደሉም የምንል ከሆነ በዚህ መንገድ ስንቱን ልንጥል ነው? እውነትን መያዝ እንጂ እነ እገሌ ስለያዙት ብሎ መጣል ምክንያታዊ አያሰኝም፡፡ ከእነርሱ ጋር ለመመሳሰል ብለን እንዳልያዝነው ሁሉ ላለመመሳሰል ብለንም እውነቱን አንጥልም፡፡ በሌላ ስውር አላማ፣ ወይም መጠን አልባ የካቶሊክ ግላዊ ጥላቻ ይዞ፣ ወይም ደግሞ እነርሱን የሚቃወም ሁሉ ሐሳቤን ይቀበልልኛል በሚል ይህን የመሰለውን ሁሉ ምክንያት እያደረጉ ማቅረብ ፖለቲከኛነት እንጂ መንፈሳዊነት አይደለም፡፡

5.ኛ ሌላው ነጥብ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያት ከእኅት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ ናት፡፡ ለበርካታ መቶ አመታት ለቡራኬና ለክህነት አባቶችን ከግብጽ ስናገኝ ኖረናል፡፡ ይሁን እንጂ የክርስትና እምነታችን ከግብጽ እንዳልመጣልን የታመነ ነው፡፡ ስለሃይማኖት ትምህርት የራሳችን ሊቃውንት ነበሩን፤ አሉንም፡፡ በረጅም ታሪኳ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን በርካታ ሀብቷን የሚያሳጣና የሚለውጥ ፈተና አጋጥሟታል፡፡ ዋና ዋናዎቹ ተግዳሮቶቿ በፕሮቴስታን አገር ለበርካታ ዘመናት ቅኝ መገዛቷ፣ እስካለንበት ዘመን በሙስሊሞች የበላይነት መመራቷ፣ እና አዎንታዊውን ትተን በራሷ ልጆች የተደረጉ አሉታዊ ለውጦች ናቸው፡፡ ከዚህ ሁሉ ፈተና በኋላ የቤተ ክርስቲያኒቱ እስካሁን መኖር በራሱ በጎ ዕድል ነው፡፡ ስለዚህ አሁን ያሉት የሃይማኖት ተወካዮቿ እንደ ቀድሞዎቹ እንደ አትናቴዎስና እንደ ቄርሎስ ያለ አቋም ባይኖራቸው መደነቅ የለብንም፡፡ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን የወደደችውን ማመንና ማምለክ መብቷ መሆኑን መርሳት የለብም፡፡ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያላት እኅትማማችነት በጠና ቢታመምም ሞተ የሚባል አለመሆኑም እጅግ በጣም መልካም ነው፡፡ በአንድ ርእሰ ጉዳይ ዙሪያ የሁለቱን
እኅት አብያተ ክርስቲያናት አቋም ስንተነትን እነዚህን ሁሉ ጉዳዮች ከግምት ሳናስገባ ከሆነ የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ እንደርሳልን፡፡ ጥንተ አብሶን በተመለከተ ሁለቱን አኀት አብያተ ክርስቲያናት በማስተያየት ወደተሳሳተ መደምደሚያ የሚደርሱ ሰዎችም ይህንን ማስተዋል ያልቻሉ ናቸው፡፡

6.ኛ ‹‹አቡነ እገሌ እንዲህ ያምኑ ነበር፤ አባ እገሌ እንዲህ ብለው ጽፈዋል፤ እንዲህ አስተምረዋል›› እያሉ የግለሰቦችን ቃልና ጽሑፍ ለሃይማኖታዊ ጉዳይ በማስረጃነት የሚያቀርቡ አሉ፡፡ ይህ አካሄድ በራሱ የግለሰብእ ተጠቂ መሆንን ያሳያል፡፡ በተቃራኒዉም ተመሳሳይ ማስረጃ ማቅረብ ቢቻልም ሁለቱም መንገድ ከንቱነት ያለበት በመሆኑ ከዋና ዋና ምንጮች በመነሣት ሐሳብን መግለጥ የበለጠ መልካም ነው፡፡ የራሳቸውን ገድል ያልፈጸሙ መዋቲያንን ዋቢ ማድረግ ኢየሱስ ክርሰቶስ የመሠረታትን ቤተ ክርስቲያን ክብር የሚነካና በግለሰብእ የተመሠረች ሃይማኖት አድርጎ መቁጠር ነው፡፡ ሰው ከዚህ ቀደም የተናገረውን ዛሬ የማይደግም ተለዋዋጭ መሆኑንም መርሳት አይገባም፡፡ ስለዚህ ይህን መሰሉን ምክንያት በቁሙ ውድቅ ማድረግ እንጂ ምላሽ መስጠት አያስፈልገውም፡፡

ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ ነበረባት የሚሉ ሰዎች ሁሉ ከላይ የተጠቀሱትን ክብደት የሌላቸው ምክንያቶች ሁሉ እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ከተነሡበት አጀንዳ ጋር የሚያቀርቡት መከራከሪያ ዝምድና እንደሌለው ሳይረዱ ቀርተው ብቻ አይደለም፡፡ እንዲያው በግምት ብዙ ብንወረውር አንዱ ሳይመታልን አይቀርም ብለው እንጂ፡፡ በተጨማሪም ማስተላለፍ ለፈለጉት መልእክት ድጋፍ የሚሆን ሌላ አሳማኝ ማስረጃ ማቅረብ እንደተቸገሩም ያሳያል፡፡ ሌሎች ይመኑላቸው እንጂ ስለሚናገሩት ነገር እውነትነት ስላቀረቡትም ማስረጃ ተአማኒነት ደንታ የሌላቸው ሰዎች ከዚህ የተለየ መንገድ የላቸውምና አቀራረባቸው ድንቅ አይደለም፡፡
Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 04:40 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

እናት ለልጅዋ ነቢይ ናት!


የነቢዩ ዮናስ እናት ያቺ ሱናማዊት የኤልሳዕን በረከት አግኝታለች። ያልሰማ ካለ ይሂድና እንስራዋን ይይ። በዘይት መሞላቱን ይይ። ዕዳዋ መከፈሉን ይይ። ነቢዩ ኤልሳዕ ምን ላድርግልሽ አላት። ልጅ አልነበራትምና ልጅ እንድትወልድ አበሰራት። ልጇ ሲሞት አስነሳላት። እንግዲያውስ ይህን ህይወት እኛም ብንኖር እንዴት መታደል ነበር? ዕዳ እየከፈሉልን የሞተብንን እያስነሱ መኖር አይ መታደል ነበር!!

ቆይ ግን ሱናማዊቷ እግዚአብሔርን አታውቅም እንዴ?? ደግሞ ኤልሳዕን አገልጋይህ ነኝ ትላለች። የሰው አገልጋይ ነን እንዴ? ይህ ሁሉ አምልኮት ሲደረግ እግዚአብሔርስ እንዴት ዝም አለ?

ሱናማዊቷ ኤልሳዕን ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው ብላ ጠርታዋለች። እግዚአብሔር ማን ኤልሳዕም ማን እንደሆነ በሚገባ ታውቃለች። እነሆ የኤልሳዕን በረከት አፍሳለች፤ አምላክዋ እግዚአብሔርም ማድጋዋን ሞልቶ ልጅ አግኝታ ኖራለች። ደም ከደም ስር ጋ እንደማይጋጭ ሁሉ የእግዚአብሔር ስራ ከቅዱሳኑ ስራ ጋ አይጋጭምና!

የነቢያት ማህበር ለነቢዩ ኤልሳዕ ሰገዱ 2ኛ ነገሥት 2 ፦15 እነዚህ ነቢያት ሁል ጊዜ ይገርሙኛል። እኔ ብሆን ግን እኔም ነቢይ ኤልሳዕም ነቢይ ብዬ የማልሰግድለት ይመስለኛል። ግን ግን እኛም ነቢይ ኤልያስም ነቢይ ምን ያመጣል ብለው እንዴት አልተከራከሩም? ደግሞ እኮ ነቢይ ስለሆኑ ያለፈውንና የሚመጣውን ያውቃሉ። ታድያ ለጌታ ብቻ እንሰግዳለን ለምን አላሉም? የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ ላይ ሆኗል ብለው ነቢያቱ ሰገዱ። ለሰው ሲሰገድ ይህ ሁሉ ባዕድ አምልኮ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ እንዴት ተጻፈ? ይባስ ብለው ነቢያቱ ለኤልሳዕ "እነሆ እኛ አገልጋዮችህ ነን" አሉ። አሁን ማን ይሙት ሁሉም ነቢይ ከሆኑ ለምን አገልጋዩ ሆኑ? ደግሞ የሰው አገልጋይ አለ? ለማየት የሚፈልግ አይኑን ይገልጣል አሉ!

በዮሴፍ ምክንያት ግብጽ ጠገበች። በሙሴ ባህር ተከፈለ ፤ በኢያሱ ፀሐይ ቆመ፣ በኤልያስ ሰማይ ተለጎመ፣ በዳንኤል ምስጢር ተፈታ፤ ስለ ማን እንጨምር ? ለመተረክ ጊዜ የለንም ። እነዚህ ሁሉ እንደ ደመና በዙሪያችን ከበውን አይደለምን? እንግዲያውስ ካላየሁ አላምንም ማለት ዳግማዊ ቶማስ መሆን አይደለምን? ቶማስማ አምኖ አምላኬ ብሏል። ሁሉም ነቢይ አይደለም ሁሉም ጻድቅ አይደለም፤ ሁሉም ካህን ሁሉም ሐዋርያ አይደለም። እንግዲያውስ ሐዋርያቱን ለምን መረጣቸው? አስቀድሞ የወሰናቸውን ጠራቸው። ሁሉን ጥለው ተከተሉት። የጠራቸውን አጸደቃቸው አከበራቸውም። ወደ ቀደመው እንመለስ ፦ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ማለት ምን ማለት ነው? ጌታችን ይህን ቃል ለምን ተናገረ? ትርጉም የሌለው ቃል ነው?

Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 02:29 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Wednesday, 24 July 2013

የኢየሱስ ክርስቶስ ደም የአምላክ ነው ወይስ የሰው?


//ቃል ሥጋ ሆነ//


ቃል እንደ ረጅም ፈትል ከሰማየ ሰማያት ወረደ። ከድልግል ማርያም ተወለደ። ቃልም ሥጋ ሆነ። 

ስለ ፍቅር ብሎ እጆቹን በችንካር ተመታ። በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ አብዝቶ ዝም አለ! በእርሱ ቁስል ጉልበታችን ፀናች ነፍሳችን ተማረች ፤ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን። ስለ ፍጹም ፍቅር እጆቹን ዘረጋ። ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ አዳነን!

የኢየሱስ ክርስቶስ ደም የአምላክ ነው ወይስ የሰው?

የአምላክ ደም እንዳንል መለኮት ደም የለውም። የሰው ደም እንዳንል የሰው ደም ዓለምን እንዴት አዳነ? ሲዖልን እንዴት ከፈተ እንላለን። ፕሮቴስታንት ዘመዶቻችን ሆይ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም የአምላክ ነው ወይስ የሰው?
Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 04:05 5 comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

//ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ//


ማርያም ርኩስ ነበረች የምትል ምላስ ክርስቶስን ለማርከስ የምትቅለበለብ ምላስ ትመስላለች። የክርስቶስ ሥጋና ደም ማን አረከሰው? የእናቱን ሥጋ ተዋህዶ ተወለደ። ታድያ ክርስቶስ የለበሰው ሥጋ ርኩስ ነው የሚል እርሱ ማን ነው?

የሉቃስ ወንጌል 2

22-24 እንደ ሙሴም ሕግ የ((መንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ፥ በጌታ ሕግ።)) የእናቱን ማኅፀን የሚከፍት ወንድ ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይባላል ((ተብሎ እንደ ተጻፈ በጌታ ፊት ሊያቆሙት፥ በጌታም ሕግ።)) ሁለት ዋሊያ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ((እንደ ተባለ))፥ መሥዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት። // ሉቃስ የሚያወራው ሕጉን ስለመፈጸማቸው ነው። ኢይምስልክሙ ዘመጻእኩ እስአሮሙ ለኦሪት /ሕግን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ እንዳለ ሕጉን ፈጽመዋል/ ለዚህ ነው ወንጌላዊው ሕጉ እንደተጻፈና እንደተፈፀመ የሚነግረን። ስለ ሕጉ እየነገረን እንደሆነ ቃላቱን ይመልከቱ፦ ((መንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ፥)) ((እንደ ተባለ))፥ ((ተብሎ እንደ ተጻፈ በጌታ ፊት ሊያቆሙት፥ በጌታም ሕግ።))

ሉቃስ ለኃጢአት መስዋዕት አቀረበች ሊላ አልደፈረም አላማው  ከመንፈስ ቅዱስ ነውና የነገረን ሕጉ ስለመፈጸሙ ነው። የኦሪቱ ሕግ ግን መስዋዕቱ ለኃጢአት መሆኑን በግልጽ ይናገራል፦
ኦሪት ዘሌዋውያን 12

6 የመንጻትዋ ወራትም በተፈጸመ ጊዜ፥ ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአንድ ዓመት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ የርግብም ግልገል ወይም ዋኖስ ((ለኃጢአት መሥዋዕት)) ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታምጣለት።

8 ጠቦት ለማምጣት ገንዘብዋ ያልበቃት እንደ ሆነ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ሌላውንም ((ለኃጢአት መሥዋዕት ታቀርባለች)) ካህኑም ያስተሰርይላታል፥ እርስዋም ትነጻለች።

በዚህ አጋጣሚ የኦሪቱ ሕግ ሴት በረከሰች ጊዜ ቅዱስ ነገር አትንካ ይላል። ይህን ይዘው የጸሎት መጽሐፍ መንካት መስቀል መሳለም የሚፈሩ ሴቶች አሉ። ይህ ግን ልክ አይደለም። ሴት ልጅ በወር ተፈጥሮዋ ጊዜ ቅዱሳን መጻህፍትን ይዛ መጸለይ ትችላለች። ሌላው ሴት ልጅ በወር ተፈጥሮዋ ጊዜ ቤተ መቅደስ አትገባም። ወንድ ሲነስረው እጁ ቢደማ ቤተመቅደስ አይገባም። ምክንያም ስለረከስን ሳይሆን በቤተመቅደስ የሚፈሰው የክርስቶስ ደም ብቻ ስለሆነ ነው።

//ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ//

ኦሪት ዘሌዋውያን 12
1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።
2 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። ((ሴት ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ፥ ሰባት ቀን ያህል የረከሰች ናት እንደ ሕመምዋ መርገም ወራት ትረክሳለች።)) // ማርያም ጌታን ስለወለደች ርኩስ ሆነች የሚል ከቶ ማን ነው? ቅ/ገብርኤል ፀጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ አላት እንጂ መርገመ ሥጋሽ ቀረልሽ እንኳን ደስ አለሽ አላላትም! ማርያም የረከሰች ከሆነች ይህ ሁሉ የመላኩ ምስጋና ስለረከሰች የተነገረ ነውን? ኢሳይያስን ጠይቁት ጽድቃችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው እያለ ያለቅሳልና! እዚህ ደግሞ ፀጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ሲላት ተገረምን! ሰው ሁሉ ጽድቅ በጎደለበት በጨለማ ዘመን ማርያም ግን ፀጋን የተመላሽ ሆይ ተባለች! እነሆ ኤልሳቤትም ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አለቻት! በኦሪቱ ሴት ሁሉ ወንድ ሲወልድ የረከሰ ነው ሲባል ማርያም ግን ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች ናት! መርገመ ሥጋ ወዴት ነበርክ? ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች ማርያምን ታረክሳት ዘንድ እንዴት አቅም አጣህ?

3 በስምንተኛውም ቀን ልጁ ከሥጋው ሸለፈት ይገረዝ።
4 ከደምዋም እስክትነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቀመጥ ((የመንጻትዋ ቀንም እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰን ነገር አትንካ)) ማርያምን ረከሰች የሚል ማን ነው? እስክትነጻ የተቀደሰን ነገር አትንካ እያለ ጌታን በማህፀንዋ ታቅፋ በደረትዋ አመቻችታ በጀርባዋ እንዴት አዘለች? እስኪ መልሱልን? የተቀደሰን ነገር አትንካ እያለ ልጅዋን ስታቅፍ ርኩስ ነበረን? እስኪ መልሳችሁ ይሰማ?

Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 04:01 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Tuesday, 23 July 2013

//የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ//



  • //የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ// ይህችን አባባል ያስቀደምነው ዛሬ ያነበቡትን ነገ ደግመው ለሚጠይቁ ሰዎች የሚስማማ በመሆኑ ነው። ጥያቄ፦ ለመላዕክት የክብር ስግደት ይገባል ?ይህስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?


    መልስ :- 
    ቆርኔሌዎስ "ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል። ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው።እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ።ጌታ ሆይ ምንድር ነው? አለ። መልአኩም አለው። ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።"ሐዋ.10፡3-4

    መላእክት ክብራቸዉ አንዳንዶች እንደሚያስቡት አይደለም።መላእክት ግርማቸዉ እጅግ ድንቅ እና የሚያስፈራ ነዉ።ምክንያቱም የአምላክን ስም ይዘዋልና አምላካቸዉን ለብሰዋልና።"በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ።በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።"ዘጸ.23:20 እንዲል መጽሃፍ።ነገር ግን ሁሌም ሲያረጋጉ አየዞዋችሁ አትፍሩ ነው፡፡እኛም የተዋህዶ ልጆች የአምላክነት ሳይሆን የጸጋ( ከእግዚአብሔር የተሰጠ) ክብር ስለምንሰጣቸው አይዞዋችሁ ይሉናል፡፡የጸጋም ስግደት መጽሃፍ ስለሚያዝ እንሰግድላቸዋልን።

    ሆኖም አንዳንዶች ስህተት ነዉ ይሉናል።ለመልአክ ይሰገዳል ወይስ አሰግደም? በእርግጥ ብዙ ቦታ እግዚአብሔር የመረጣቸዉ የቀደሙ አባቶች ለመላእክት ሰገዱ ተብሎ ተጽፋል። እንዚህ አባቶች ሲያመልኩ የነበረዉ እግዚአብሔርን ነዉ ነገር ግን ለመላእክት የአክብሮት የጸጋ ስግደት ሰግደዋል ታድያ እነዚህ አባቶች ተሳስተዋል? እግዚአብሔርን አላመለኩም? ያመለኩት መላእክትን ነዉ ይባል ይሆን?።አልተሳሳቱም ምክንያቱም መረጃዉ የተገኝዉ በመንፈስ ቅዱስ ከተደርሰዉ መጽሃፍ ቅዱስ ነዉና ሁሌም እዉነት ነዉ።ሰማይና ምድር ያልፋሉ እንጂ ቃሌ ግን አያልፍም ብሎናልና።ማቴ.24:35።ነገር ግን አንዳንዶች በራእይ 22:8 ያለዉን የእግዚአብሄር ቃል በመያዝ ትከከለኛ ሚስጥሩን ባለማዎቅ ለመላእክት አይሰገድም ይሉናል።ግልጽ ለማድረግ እስቲ ለእያሱ የተገለጠ መልአክ እና ለዮሃንስ የተገለጠዉን መልአክ በማነጸጸር አብረን እንመልከት።

    ኢያ. 5 ፡14 “ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ” ለመልአኩ።ራእ.22:8 “በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ” እርሱም፦ እንዳታደርገው አለዉ።ካንተ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ አለዉ ::ለምን? አንዳንድ ወንድሞች ራእ.22:8ን ይዘው ለመልአክት አይሰግደም ይሉናል።ምስጥሩ ምንድን ነው? ለኢያሱ የተገለጠ መልአክ ስህተተኛ ነበር? ለምን አትስገድልኝ አላለውም? ለዮሐንስ የተገለጠውስ ለምን አትስገድልኝ አለ? ሁለቱም ጋ መላዕክት ናቸው ሁለቱም ሰዎች ሰግደዋል አንዱ መልአክ ኢያሱ ሲሰግድለት ምንም አላለም ሌላኛው መልአክ ግን ዮሐንስ ሲሰግድለት አትስገድልኝ አለው።

    እስኪ ይህን ተቃዋሚ ወንድሞች በምን ያስማሙታል? የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ 
    አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ ማለት ይህ ነው። ለመሆኑ ቅዱስ ዮሐንስ እና ኢያሱ ዛሬ እኛ ካለን እውቀት ያነሰ እውቀት ስላላቸው ነው የሰገዱት? እዉነት ለመናገር ኢያሱ እና ቅዱስ ዮሐንስ በዚያን ጊዜም ቢሆን ለማን መስገድ እንዳለባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ።”እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን"።ኢያ.24:15 ያለ ኢያሱ ሆነ ፍቁረ እግዚእ (የጌታ ወዳጅ የተባለ) የስላሴ ሚስጥ አስፋፍቶ የጽፈ(ዮሐ.1:1) ሰማያዊዉን ህይዎት በራእይ መልእክቱ ይሳየን።ምድራዊ ሞትን ያልሞተ።ክብሩ እጅግ የበዛ ዮሐንስ ፈጽሞ የአምላክን ክብር ለመልአክ አሳልፈዉ አይሰጡም።ዮሐንስስ መልአክ መሆኑ ጠፍቶት ነው? እንዲህ እንዳንል ከፍ ብሎ ባሳየኝ በመልአኩ እግር.. ይላል።ዮሐንስ አንድ ግዜ ብቻ አይደለም ለመልአኩ የሰገደለት ቀደም ብሎ በራእ.19:10 ሰግዶለታል።እንዴት ሁለት ገዜ ተሳስቱአል ይባላል? ለነገሩ አልኩ እንጂ ሶስተኛም ቢያገኝዉ ይስግድለታል ምክንያቱም ዮሐንስ ክርስትያናዊ ግዴታዉን እየተዎጣ ነዉና።ዕብ.13:7 "የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው"።የቀደሙት እነማን ናቸው?? ዳዊት ሎጥ ዳንኤል ጌዲዮን ወዘተ...የእነዚህን ፍሬ መመልከት መልካም ነው ፍሬያቸው ያማረ ነው።ዮሐንስ እነሱን መስሎ ሰገደ።ምክንያቱም ቅዱስ ዮሐንስ ለመላእክት እንደሚሰገድ ያውቃል ከቀደሙት አባቶች ተምራልና [ኢያ.5:13_15... ዳን.8:15_17....ዘኁ.22:31]።መልአኩም የጌታን ምሳሌ ተከትሎ እራሱን ዝቅ አደረገ።ዕብ.2:9 ።

    ትምህቱ ይህ ነው እራስን ዚቅ ማድረግ እንጂ ስግደት ይፈቀዳል ወይም አይፈቀድም ለሚል መልስ አይደለም።ለምሳሌ አንድ ትልቅ ሰው ቤታችን ሲመጣ ከወንበር ብድግ ስንል አይገባም ተቀመጡ ቢለን ሌላ ጊዜ ቢመጡ አይገባም ብለውናል ብለን ከወንበራችን አንነሳም? ዮሐንስም ያደረገዉ ይህንኑ ነዉ።ስለዚህ ለመልአክ የሚሰገደው የአክብሮት ስግደት መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል።ነገር ግን ዮሐንስ በክብሩ ታላቅ ስለሆነ መልአኩ እኔም እኮ ባርያ ነኝ አትስገድልኝ ብሏል።እንደዉ ለማስረዳት ያህል እንጅ ስግደት እንኳን ለመልአክ ለሰውም ይሰገዳል።ዘፍ.23፡12 “አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ ...”ዘፍ.23፡ 7 “አብርሃምም ተነሣ፥ ለምድሩ ሕዝብም ለኬጢ ልጆች ሰገደ።”ዘጸ.18፡7 “ሙሴም አማቱን ሊገናኝ ወጣ ሰገደም ሳመውም...”ይልብሃል። አብርሃም ለኬጢ ልጆች የአክብሮት ለእግዚአብሔር የአምልኮ ስግደት እንደሚያስፈልግ ጠንቅቆ ያዉቃልና ።አብርሃም የአምላክን ክብር ለሰው አሳልፎ የሚሰጥ አይነት ደካማ ሰው አይደለም(እነደዚህም ዓይነት ስህተት አይሰራም)።እነደዚህስ ተብሎ አልተጽፈም “ራእይ.3:9 እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ”።በዚህ ጥቅስ አምልኩ ነው ያላቸው ወይም አክብሩት ???

    እንዲሁም 1ኛ.ዜና መዋ.29:20 "ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ።አምላካችሁን እግዚአብሔርን ባርኩ አላቸው።ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔርና ለንጉሡ ሰገዱ"።ለእግዚአብሄር የአምልኮ ለንጉሱ የአክብሮት ስግደት እንደሚገባ ዳዊት አበክሮ ይናገራል።ታዲያ የዘመኑ ሰዎች ምን ነካቸዉ ትህትና ምነዉ ከንሱ ጠፋ??? እንግዲህ ምን እንላልን በመንፈስ ቅዱስ የተደርሰዉ የእግዚአብሄር ቃል መጽሃፍ ቅዱስ ለቅዱሳኑ ስግደት እንደሚገባ ስላስተማረን እንሰግድላቸዋለን።የአምልኮ ስግድት ግን አልፋና ኦሜጋ ለሚባል ይህን አለም ካለመኖር ወደ መኖር ላመጣ በፍጥርት ሁሉ ላይ ስልጣን ላለዉ የዘለአለም ንጉስ የጌቶች ጌታ የአማልክት አምላክ የነገስታት ንጉስ ለሚሆን ለአንድ እግዚአብሔር ብቻ!!!

    ==>የቅዱሳን መላእክት ምልጃ እና እረዳትነት አይለየን።
    ፍጥረታት ሲፈጠሩ የአምላክ ልጆች  መላዕክቱ እልል አሉ። ቃል ሥጋ ሆነ  አሁንም የአምላክ ልጆች መላዕክቱም በደስታ ዘመሩ። ቃል ሥጋ ሆነ ማለት ምን ማለት ይሆን? ፕሮቴስታንት ዘመዶቼ እስኪመልሱት እጠብቃለሁ። 

//የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ  አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ//

ይህችን አባባል ያስቀደምነው ዛሬ ያነበቡትን ነገ ደግመው ለሚጠይቁ ሰዎች የሚስማማ በመሆኑ ነው። ጥያቄ፦ ለመላዕክት የክብር ስግደት ይገባል ?ይህስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?

መልስ :- 
ቆርኔሌዎስ "ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል። ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው።እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ።ጌታ ሆይ ምንድር ነው? አለ። መልአኩም አለው። ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።"ሐዋ.10፡3-4

መላእክት ክብራቸዉ አንዳንዶች እንደሚያስቡት አይደለም።መላእክት ግርማቸዉ እጅግ ድንቅ እና የሚያስፈራ ነዉ።ምክንያቱም የአምላክን ስም ይዘዋልና አምላካቸዉን ለብሰዋልና።"በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ።በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።"ዘጸ.23:20 እንዲል መጽሃፍ።ነገር ግን ሁሌም ሲያረጋጉ አየዞዋችሁ አትፍሩ ነው፡፡እኛም የተዋህዶ ልጆች የአምላክነት ሳይሆን የጸጋ( ከእግዚአብሔር የተሰጠ) ክብር ስለምንሰጣቸው አይዞዋችሁ ይሉናል፡፡የጸጋም ስግደት መጽሃፍ ስለሚያዝ እንሰግድላቸዋልን።

ሆኖም አንዳንዶች ስህተት ነዉ ይሉናል።ለመልአክ ይሰገዳል ወይስ አሰግደም? በእርግጥ ብዙ ቦታ እግዚአብሔር የመረጣቸዉ የቀደሙ አባቶች ለመላእክት ሰገዱ ተብሎ ተጽፋል። እንዚህ አባቶች ሲያመልኩ የነበረዉ እግዚአብሔርን ነዉ ነገር ግን ለመላእክት የአክብሮት የጸጋ ስግደት ሰግደዋል ታድያ እነዚህ አባቶች ተሳስተዋል? እግዚአብሔርን አላመለኩም? ያመለኩት መላእክትን ነዉ ይባል ይሆን?።አልተሳሳቱም ምክንያቱም መረጃዉ የተገኝዉ በመንፈስ ቅዱስ ከተደርሰዉ መጽሃፍ ቅዱስ ነዉና ሁሌም እዉነት ነዉ።ሰማይና ምድር ያልፋሉ እንጂ ቃሌ ግን አያልፍም ብሎናልና።ማቴ.24:35።ነገር ግን አንዳንዶች በራእይ 22:8 ያለዉን የእግዚአብሄር ቃል በመያዝ ትከከለኛ ሚስጥሩን ባለማዎቅ ለመላእክት አይሰገድም ይሉናል።ግልጽ ለማድረግ እስቲ ለእያሱ የተገለጠ መልአክ እና ለዮሃንስ የተገለጠዉን መልአክ በማነጸጸር አብረን እንመልከት።

ኢያ. 5 ፡14 “ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ” ለመልአኩ።ራእ.22:8 “በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ” እርሱም፦ እንዳታደርገው አለዉ።ካንተ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ አለዉ ::ለምን? አንዳንድ ወንድሞች ራእ.22:8ን ይዘው ለመልአክት አይሰግደም ይሉናል።ምስጥሩ ምንድን ነው? ለኢያሱ የተገለጠ መልአክ ስህተተኛ ነበር? ለምን አትስገድልኝ አላለውም? ለዮሐንስ የተገለጠውስ ለምን አትስገድልኝ አለ? ሁለቱም ጋ መላዕክት ናቸው ሁለቱም ሰዎች ሰግደዋል አንዱ መልአክ ኢያሱ ሲሰግድለት ምንም አላለም ሌላኛው መልአክ ግን ዮሐንስ ሲሰግድለት አትስገድልኝ አለው።

እስኪ ይህን ተቃዋሚ ወንድሞች በምን ያስማሙታል? የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ 
አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ ማለት ይህ ነው። ለመሆኑ ቅዱስ ዮሐንስ እና ኢያሱ ዛሬ እኛ ካለን እውቀት ያነሰ እውቀት ስላላቸው ነው የሰገዱት? እዉነት ለመናገር ኢያሱ እና ቅዱስ ዮሐንስ በዚያን ጊዜም ቢሆን ለማን መስገድ እንዳለባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ።”እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን"።ኢያ.24:15 ያለ ኢያሱ ሆነ ፍቁረ እግዚእ (የጌታ ወዳጅ የተባለ) የስላሴ ሚስጥ አስፋፍቶ የጽፈ(ዮሐ.1:1) ሰማያዊዉን ህይዎት በራእይ መልእክቱ ይሳየን።ምድራዊ ሞትን ያልሞተ።ክብሩ እጅግ የበዛ ዮሐንስ ፈጽሞ የአምላክን ክብር ለመልአክ አሳልፈዉ አይሰጡም።ዮሐንስስ መልአክ መሆኑ ጠፍቶት ነው? እንዲህ እንዳንል ከፍ ብሎ ባሳየኝ በመልአኩ እግር.. ይላል።ዮሐንስ አንድ ግዜ ብቻ አይደለም ለመልአኩ የሰገደለት ቀደም ብሎ በራእ.19:10 ሰግዶለታል።እንዴት ሁለት ገዜ ተሳስቱአል ይባላል? ለነገሩ አልኩ እንጂ ሶስተኛም ቢያገኝዉ ይስግድለታል ምክንያቱም ዮሐንስ ክርስትያናዊ ግዴታዉን እየተዎጣ ነዉና።ዕብ.13:7 "የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው"።የቀደሙት እነማን ናቸው?? ዳዊት ሎጥ ዳንኤል ጌዲዮን ወዘተ...የእነዚህን ፍሬ መመልከት መልካም ነው ፍሬያቸው ያማረ ነው።ዮሐንስ እነሱን መስሎ ሰገደ።ምክንያቱም ቅዱስ ዮሐንስ ለመላእክት እንደሚሰገድ ያውቃል ከቀደሙት አባቶች ተምራልና [ኢያ.5:13_15... ዳን.8:15_17....ዘኁ.22:31]።መልአኩም የጌታን ምሳሌ ተከትሎ እራሱን ዝቅ አደረገ።ዕብ.2:9 ።

ትምህቱ ይህ ነው እራስን ዚቅ ማድረግ እንጂ ስግደት ይፈቀዳል ወይም አይፈቀድም ለሚል መልስ አይደለም።ለምሳሌ አንድ ትልቅ ሰው ቤታችን ሲመጣ ከወንበር ብድግ ስንል አይገባም ተቀመጡ ቢለን ሌላ ጊዜ ቢመጡ አይገባም ብለውናል ብለን ከወንበራችን አንነሳም? ዮሐንስም ያደረገዉ ይህንኑ ነዉ።ስለዚህ ለመልአክ የሚሰገደው የአክብሮት ስግደት መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል።ነገር ግን ዮሐንስ በክብሩ ታላቅ ስለሆነ መልአኩ እኔም እኮ ባርያ ነኝ አትስገድልኝ ብሏል።እንደዉ ለማስረዳት ያህል እንጅ ስግደት እንኳን ለመልአክ ለሰውም ይሰገዳል።ዘፍ.23፡12 “አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ ...”ዘፍ.23፡ 7 “አብርሃምም ተነሣ፥ ለምድሩ ሕዝብም ለኬጢ ልጆች ሰገደ።”ዘጸ.18፡7 “ሙሴም አማቱን ሊገናኝ ወጣ ሰገደም ሳመውም...”ይልብሃል። አብርሃም ለኬጢ ልጆች የአክብሮት ለእግዚአብሔር የአምልኮ ስግደት እንደሚያስፈልግ ጠንቅቆ ያዉቃልና ።አብርሃም የአምላክን ክብር ለሰው አሳልፎ የሚሰጥ አይነት ደካማ ሰው አይደለም(እነደዚህም ዓይነት ስህተት አይሰራም)።እነደዚህስ ተብሎ አልተጽፈም “ራእይ.3:9 እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ”።በዚህ ጥቅስ አምልኩ ነው ያላቸው ወይም አክብሩት ???

እንዲሁም 1ኛ.ዜና መዋ.29:20 "ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ።አምላካችሁን እግዚአብሔርን ባርኩ አላቸው።ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔርና ለንጉሡ ሰገዱ"።ለእግዚአብሄር የአምልኮ ለንጉሱ የአክብሮት ስግደት እንደሚገባ ዳዊት አበክሮ ይናገራል።ታዲያ የዘመኑ ሰዎች ምን ነካቸዉ ትህትና ምነዉ ከንሱ ጠፋ??? እንግዲህ ምን እንላልን በመንፈስ ቅዱስ የተደርሰዉ የእግዚአብሄር ቃል መጽሃፍ ቅዱስ ለቅዱሳኑ ስግደት እንደሚገባ ስላስተማረን እንሰግድላቸዋለን።የአምልኮ ስግድት ግን አልፋና ኦሜጋ ለሚባል ይህን አለም ካለመኖር ወደ መኖር ላመጣ በፍጥርት ሁሉ ላይ ስልጣን ላለዉ የዘለአለም ንጉስ የጌቶች ጌታ የአማልክት አምላክ የነገስታት ንጉስ ለሚሆን ለአንድ እግዚአብሔር ብቻ!!!

==>የቅዱሳን መላእክት ምልጃ እና እረዳትነት አይለየን።
    Like ·  · Unfollow Post · 3 hours ago
    • Meazi Habeshawit, Moges Abeje, Bright Destiny and 9 others like this.
    • Biruk Feleke 3 amet geta bewalebet wilo baderebet adiro yekalun timihirt yadamete yohannes endet yisasatal? Raeyun yetsafew eko 96 ametemiret gedema new 60'win amet mimenanin min bilo astemare?
      3 hours ago via mobile · Unlike · 1
    • Mezgebe Alem Lisanework kalehiwot yasemalen
      2 hours ago · Like
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ 1ኛ.ዜና መዋ.29:20 "ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ።አምላካችሁን እግዚአብሔርን ባርኩ አላቸው።ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔርና ለንጉሡ ሰገዱ"።ለእግዚአብሄር የአምልኮ ለንጉሱ የአክብሮት ስግደት እንደሚገባ ዳዊት አበክሮ ይናገራል።
      2 hours ago · Like · 4
    • Feker Tsige dn yonas egziabihear abzito yibarkih betam yemifeligewin neger new yagegnehut.kalehiwet yasemalin
      41 minutes ago via mobile · Like
    Options

Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 05:13 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Monday, 22 July 2013

/ /የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንደ ነብር ፀጉር//



ፕሮቴስታንት ዘመዶቻችን ማርያም የሰው ሁሉ እናት አትባልም ይላሉ። ክቡራን ሆይ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንደ ነብር ፀጉር ሲባል አልሰማችሁም? እሺ፤ ሌላው ቢቀር የዳዊት በገናንስ አልሰማችሁም?

እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ // ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላታል።

እንግዲህ ምን እንበል? ሰው ሁሉ ጽዮን ይላታል፤ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይላታል። መቼስ ራስን ከፍ ማድረግ የተካነ ካለ እኛም ብጹዕ ነን ማለቱ አይቀርምና እናንተ ትውልድ ሁሉ ብጹዕ አይላችሁም። ማርያም ግን ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይላታል እንላለን።

እስኪ ፕሮቴስታንት ዘመዶቻችንን እንጠይቅ፦

እምነ ጽዮን ይብል ሰብዕ ወብዕሲ ተወልደ በውስቴታ // ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላታል፤ በውስጧም ሰው ተወለደ።

/1/ ጽዮን የተባለ ሁሉ ለዳዊት ከተማ የተነገረ ነው?

/2/ ማርያምን እናታችን ስንል አኩርፋችኋል፤ ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን የሚለው የዳዊት ከተማን ነው?

/3/ በውስጧም ሰው ተወለደ ማለት ከመሬት ውስጥ ሰው ተወለደ ማለት ነው?

/4/ ትንቢተ ኢሳይያስ 60
14 የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ ((እግርሽ ጫማ )) ((ይሰግዳሉ )) የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።

በዚህ ትንቢት ጽዮን የተባለችው የዳዊት ከተማ ከሆነች ተራራ እግርና ጫማ አለው? ለተራራ መስገድ ጣዖት አይደለም?

በተራ ቁጥር የተጻፈውን እንደ ጨዋ በየተራ እንደምትመልሱት ተስፋ አለን። ከመልሳችሁ በኋላ አስተያየትና ጥያቄ ማቅረብ መብታችሁ ነው።
...........//............

የማቴዎስ ወንጌል 26
31 እረኛውን እመታለሁ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ የሚል ተጽፎአልና እነሆ በጎቹ ተበተኑ። ቅ/ማርቆስ በእምነት ያልጠነከረ ወጣት ነበረና ራቁቱን ሮጠ። እረኛው መስቀል ላይ ሲውል በጎቹ ተበተኑ። ከበጎቹ መካከል አንዱ መስቀሉ ድረስ ተከተለው። የእረኛው እናትም ከመስቀሉ ስር ነበረች።
ይቤላ ለእሙ ብእሲቶ ነዋ ወልድኪ // በመስቀል የዋለው እረኛ እናቱን እነሆ ልጅሽ አላት።
ወይቤሎ ለውእቱ ነያ እምከ // እረኛው ለበጉ እነሆ እናትህ አለው።


ይህች እናት ድንቅ ናት አምላክን ወልዳለችና። ይህች እናት ግሩም ናት የሐዋርያው እናት ተብላለችና። እንዳንቺ አይነት እናት ከቶ ማን ነው? ስለወለድሽ የሕይወት ምግብን ማርያም ሆይ እንወድሻለን! የአምላክ እናት የሐዋርያው እናት የእኛም እናት እንልሻለን።
ማርያም ለዮሐንስ ብቻ እናት ተባለች ይላሉ። ጌታ ለጴጥሮስ በጎቼን አሰማራ ሲል ለጴጥሮስ ብቻ የተነገረ ነው? ብለን ጠየቅናቸው። መልስ ግን አላገኙም። ጌታ እነሆ ልጅህ ያለውን ልጃችን አድርገን እንቀበል ይላሉ። መልሱ አዎ ልጃችሁ አድርጋችሁ መቀበል መብታችሁ ነው የሚል ነው! ማንነቱ የማይታወቀውን ልጃችን ማለት መብታችሁ ነውና። እኛ ግን ከዘፍጥረት - ራዕይ የተጻፈላትን የአምላክ እናት ማርያምን እናታችን እንላለን።
የዘመናችን ሰዎች ማርያም የሰው ሁሉ እናት አትባልም ይላሉ። ወላጅ እንደሌላቸው አልተዋችሁም ብሏልና ጌታ ረስቶ ማርያም እንዴት እናታችን ሆነች? ወይስ ማርያም የእንጀራ እናታችን ናት ይላሉ።
እኛም እንዲህ ጠየቅናቸው፤ ክርስቶስ ለዮሐንስ እነሆ እናትህ ሲል ወላጅ እንደሌላቸው አልተዋችሁም ያለውን ቃል ረስቶ ነው ወይስ ማርያም የእንጀራ እናቱ ናት? መልስ ግን ከቶ የላቸውም። መልስ የለምና አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው ብለን ዝም አልን። ሞኝ ሲናገር ብልህ ያዳምጣል እንዲሉ መናገር መልካም ነው ማዳመጥ ይበልጣል።



  • Debourah Alemu, Nani Moges, Moges Abeje and 37 others like this.
  • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ የማቴዎስ ወንጌል 26
    31 እረኛውን እመታለሁ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ የሚል ተጽፎአልና እነሆ በጎቹ ተበተኑ። ቅ/ማርቆስ በእምነት ያልጠነከረ ወጣት ነበረና ራቁቱን ሮጠ። እረኛው መስቀል ላይ ሲውል በጎቹ ተበተኑ። ከበጎቹ መካከል አንዱ መስቀሉ ድረስ ተከተለው። የእረኛው እናትም ከመስቀሉ ስር ነበረች።
    ይቤላ ለእሙ ብእሲቶ ነዋ ወልድኪ // በመስቀል የዋለው እረኛ እናቱን እነሆ ልጅሽ አላት።
    ወይቤሎ ለውእቱ ነያ እምከ // እረኛው ለበጉ እነሆ እናትህ አለው።
    7 hours ago · Like · 3
  • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ Solomon Girmatsion Wond Wosen/Debora Amare//Abel Tesfaye//Heaven Heaven Nahom ክቡራን ሆይ እንዴት ልታስረዱ ይቻላችኋል? ትንቢተ ኢሳይያስ 60
    14 የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ ((እግርሽ ጫማ )) ((ይሰግዳሉ )) የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።

    በዚህ ትንቢት ጽዮን የተባለችው የዳዊት ከተማ ከሆነች ተራራ እግርና ጫማ አለው? ለተራራ መስገድ ጣዖት አይደለም?
    7 hours ago · Edited · Like · 2
  • Chirstian HaGer Nat Ethopia አሜን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን ተባረክ ወንድሜ።
    7 hours ago via mobile · Like
  • Chirstian HaGer Nat Ethopia ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት። እግዚአብሔር ለሕዝቡ፥ በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል። በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል [መዝሙር 87:1-7]
    7 hours ago via mobile · Like
  • Yared Ashagre ወዳጄ፡ እንዲህ አይነት የአንድምታ ትምህርት ውስጥ መሳተፍ ብዙ ጊዜ ባይቀናኝም ነገር ግን ጥያቄህን እንዲሁ እንድታየው ብቻ እጽፋለሁ፡፡
    የመጽሀፍ ቅዱስን ቃላት መቼም በመደዴ እንደማትወስዳቸው ይመስለኛል፡፡ የእግዚአብሄር የእጆቹ ስራዎች ነን ሲል ቃሉ እግዚአብሄር እጅ አለው ብለህ እንደማትተረጉመው ግልጥ ነው፤ ወይም የአፍንጫው እስትንፋስ ብሎ ስለአምላክ ሲናገር አፍንጫ ያለው የፍጥረት አምሳያ እንደማትስል ይገባኛል፡፡
    ስለዚህ አንተ የማታደርገውን ሌላው እንደሚያደርገው ስለምን ታስባለህ? ወይስ ለትምህርትህ እስከተመቸ ድረስ ቃሉን የማጣጠፍ ስልጣን ያለህ ይመስልሃልን?
    በዚህ መንገድ ጥያቄህ ውድቅ ስለሆነ ሌላ መከራከሪያ ነጥብ ብታነሳ መልካም ይመስለኛል፡፡
    7 hours ago · Like · 1
  • Wond Wosen በጣም ጥሩ ይህን ካልክ የሚከተለዉስ ስለ ድንግል ማረያም ነዉ ወይንስ አይደለም!! ወንድሜ መልስ በአጭሩ እፈልጋለሁ እንዴት ፂዮን ተራራ ወይንም ቦታ እንደሆነ አስፋሀለሁ ኢሳያስ 60
    10 በቍጣዬ ቀሥፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና መጻተኞች ቅጥርሽን ይሠራሉ፥ ነገሥታቶቻቸውም ያገለግሉሻል።
    15 ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ፤ ይህ ስለማርያም ነዉ የተባለዉ ወይንስ አይደለም? አጭር መልስ እፈልጋለሁ ነዉ ወይንም አይደለም ሌላ ዝባዝንኬ አልፈልግም
    7 hours ago · Like · 2
  • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ Yared Ashagre ክቡር ሆይ አሁን የሚያስከፋ ቃል መቼ ተናገርኩ? መሳተፍ ካልፈለክ ለሌሎቹ እድል መስጠት አንተም መተው መብትህ አይደለምን? ኢትዮጲያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች እጅ አላት እንዴ ብሎ መጠየቅም ይቻላል። ሆኖም ሙሉ መልስ አልሰጠህም። በዚህ ትንቢት ጽዮን የተባለችው የዳዊት ከተማ ከሆነች ለተራራ መስገድ ጣዖት አይደለም?
    7 hours ago · Like · 1
  • Wond Wosen ዮናስ መልስ ስጠኝ አትሽሽ .. በቍጣዬ ቀሥፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና የተባለዉ ለድንግል ነዉ
    7 hours ago · Like · 1
  • Tadesse Gebre Michael Wond Wesen,,,,,,,Zbaznke? ? ? ? Sle Maryam yemineger hulu lante " Zbaznkie" new aydel? Kkkkkkkk
    7 hours ago via mobile · Like
  • Mezgebe Alem Lisanework mejemeriya yetetekewen meles zibazinkyema atihun
    6 hours ago · Like
  • Tadesse Gebre Michael Le Terara weym le Ketema mesgeds Le Taot ende Mesged ayhonbnm?
    6 hours ago via mobile · Like
  • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ Wond Wosen ክቡር ሆይ ሰላም። በተራ ቁጥር የተጻፈውን እንደ ጨዋ በየተራ እንደምትመልሱት ተስፋ አለን። ከመልሳችሁ በኋላ አስተያየትና ጥያቄ ማቅረብ መብታችሁ ነው ያልኩትን ረሳህ? እንደ ተራህ እየመለስኩ ነው። በቍጣዬ ቀሥፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና ያልከው ለማርያም አይደለም። በአጭሩ መልስ ስላልክ ታዘዝኩልህ። አሁን ተራው ያንተ ነው፤ በዚህ ትንቢት ጽዮን የተባለችው የዳዊት ከተማ ከሆነች ለተራራ መስገድ ጣዖት አይደለም?
    6 hours ago · Like · 2
  • Teketel Demamu Dingay lay wuha mafises min yaderigal metewu yishalal...
    6 hours ago · Like
  • Wond Wosen በጣም ጥሩ ስለዚህ የናቁሽ ሁሉ የሚለ ለማረያም አይደለም ማለት ነዉ! እንዲያዉም ምዕራፍ 60 የተፃፈዉ ለ ከተማዋ እንደሆነ የተረዳህ ይመስለኛል!!!ለቦታ እንደሆነ ላስረዳህ መዝሙረ ዳዊት 132 ሙሉዉን አንብበዉ 
    5 ለእግዚአብሔር ስፍራ፥ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያ እስካገኝ ድረስ ብሎ። ይልና እ/ር ደግሞ እንዲህ ይላል
    13 እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ።
    14 ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።
    15 አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ።
    16 ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል።
    17 በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለቀባሁትም ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ።
    18 ጠላቶችንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ፤ በእርሱ ግን ቅድስናዬ ያብባል። ይህ ማለት የዳዊትን ከተማ ፂዮንን ስለመሆኑ አትጠራጠር!! ዳዊት የፀለየዉ ጸሎት እ/ርን ለማሳረፍ ስለነበረ ፀሎቱ ተሰምቶለት የዳትን ከተማ መረጸ በመካከላቸዉ አደረ!! ይህን ለድንግል ማርያም መስጠት ወደስህተት ይወስዳልና በደንብ አጢነዉ!! ልታዉቅ የሚገባህ በብሉይ ኪዳን አይሁድና ሳምራዊ የሚሰግዱበት ቦታ የተለያየ እንደሆነ የምትአነጋ አይመስለኝም ለዛም ነዉ ወደ ፂዮን ይመጣሉ ስግደትንም ይፈፅማሉ! ለማለተ ነዉ! ለተራራ መስገድ ሳይሆን በተራራዉ ላይ በከተማዉ ላይ ስግደት ለእ/ር ማቅረብ ማለት ነዉ!! ደግሞ ስግደት የሚያስፈልገዉ ለእ/ር ብቻ እንደሆነ መዘንጋት የለብህም!!
    6 hours ago · Like
  • Tadesse Gebre Michael @ Ol Pro's,,,,,,,,,,,,,,"Yenakushm wede Egrsh chama ysegdalu". Mn malet yhon ? Ewnet ye E/r kal le Terara weym le Ketema endnsegd ynageral? Bnsegds le Taot endemesged ayhonbnmn?kehone tadya lemanew yetetsafew?
    6 hours ago via mobile · Unlike · 1
  • Yared Ashagre ለተራራ መስገድ ጣኦት አምልኮ ነው፤ እንዲሁም ለፍጥረት መስገድ፡፡ ለጌታ ለአምላክህ ስገድ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ ብሎ ጌታ ሰይጣንን ያባረረው በዚህ እውነት ላይ ቆሞ ነው፡፡ አለቀ፡፡ 
    አንድ የመጽሀፍ ክፍል ቁጥርን ገንጥሎ በዚያ ላይ መነጋገር አውድን ማጥፋት በሚባል ወንጀል ውስጥ ይከትታል፡፡ ይህንንም ብዙ ጊዜ ጥራዝ ነጠቅ እያላችሁ ሌሎችን ለመሳደብ እንደመንደርደሪያ ስትጠቀሙ ይስተዋላል፡፡ ያንኑ ወንጀል ደግሞ እናንተው ስታደርጉት አይታያችሁም፡፡
    የኢሳይያስ 60 ከተማ የራእይ 21 አዲሲቷ ኢየሩሳሌም መሆኗን በንጽጽር ቃል በቃል ማየት ይቻላል፡፡
    ስለዚህ ያለምንም ሌላ ማብራሪያ ሁለቱን ክፍሎች ማንበብ በቂ ነው፡፡
    6 hours ago · Like
  • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ Wond Wosen ክቡር ሆይ ለከተማዋ መሆኑን ስላስረዳኸኝ አመሰግናለሁ። ሆኖም የጠየኩትን ከመለስክ በኋላ ብታስረዳን ደስ ይለን ነበር። /1/ ጽዮን የተባለ ሁሉ ለዳዊት ከተማ የተነገረ ነው? /2/ በዚህ ትንቢት ጽዮን የተባለችው የዳዊት ከተማ ከሆነች ለተራራ መስገድ ጣዖት አይደለም?
    6 hours ago · Edited · Like · 1
  • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ Yared Ashagre ክቡር ሆይ የመለስኩት በቂ ነው ብለሃልና አመሰግናለሁ።
    6 hours ago · Like
  • Chirstian HaGer Nat Ethopia ወንደሰን ለምን ትቆራርጠዋለህ ማደርያ እስካገኝ ብሎ ይላል አልክ በጣም ጥሩ አሁን ለምጠይቅ መልስ እፈልጋለው በመጀመርያ ሙሉውን ፖስት አድርገው?
    6 hours ago via mobile · Like
  • Chirstian HaGer Nat Ethopia ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል።[መዝ 50:2] በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ በአሕዛብም መካከል አደራረጉን ንገሩ::[መዝ 9:11] ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ፤ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል። [መዝ 84:7]
    6 hours ago via mobile · Unlike · 1
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ ክቡራን ፕሮቴስታንት ዘመዶቻችን ሆይ ምን ትላላችሁ? 
      1/ ጽዮን የተባለ ሁሉ ለዳዊት ከተማ የተነገረ ነው?

      /2/ ማርያምን እናታችን ስንል አኩርፋችኋል፤ ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን የሚለው የዳዊት ከተማን ነው?

      /3/ በውስጧም ሰው ተወለደ ማለት ከመሬት ውስጥ ሰው ተወለደ ማለት ነው?

      /4/ ትንቢተ ኢሳይያስ 60
      14 የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ ((እግርሽ ጫማ )) ((ይሰግዳሉ )) የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።
      6 hours ago · Like · 2
    • Wond Wosen ዮናስ.. ያልገባህ ነገር ያለ ይመስለኛል! በሐዋርያት ስራ ኢትዮጺያዊዊ ጃንደረባ ወደ ኢየሩሳሌም ሊሰግድ የሄደዉ ለምን ይመስልሀል! ለቦታዉ ነዉ ወይንስ የእ/ር ታቦት መገኛ ስለሆነ? ማንም ለተራራ አይሰግድም ነገር ግን የሚሰግዱበት ቦታ ፂዮን ይባላል ከተማ ወይንም ተራራ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ስግደት ለእ/ር ነዉ! አይሁድንም ብትጠይቃቸዉ የሚመልሱልህ መልስ ይህ ነዉ!!!
      6 hours ago · Like · 1
    • Tadesse Gebre Michael Yared,,,,,,,,,,,yetenadedk tmeslaleh. Manm yasgededeh akal ko yelem.
      6 hours ago via mobile · Like
    • Mezgebe Alem Lisanework hahahhahaha wond , i think you failed
      6 hours ago · Like
    • Chirstian HaGer Nat Ethopia እኔ ምለው ግን ባይብልን ገልብጣችሁ ነው ምታነቡት ግን?
      6 hours ago via mobile · Edited · Like
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ Wond Wosen ወንድሜ ወንደሰን ኢሳይያስ የሚያወራው ስለማን ነው? ስለ እግዚአብሔር ነው ወይስ ስለ ጽዮን? ትንቢተ ኢሳይያስ 60
      14 የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ ((እግርሽ ጫማ )) ((ይሰግዳሉ )) የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።
      6 hours ago · Like
    • Weyni Getachew mels ayisetuhm wegeyachew ki kidest dingel Maryam ga selehone,,,,,
      6 hours ago · Like
    • Yared Ashagre • አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ። . . . . . . ኢሳ 60
      አሕዛብም በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፥ የምድርም ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርስዋ ያመጣሉ፤. . . . ራእ 21፡24
      • በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንቺ ስለሚመለስ፥ የአሕዛብም ብልጥግና ወደ አንቺ ስለሚመጣ፥ አይተሽ ደስ ይልሻል፥ ልብሽም ይደነቃል ይሰፋማል። ኢሳ 60
      የአሕዛብንም ግርማና ክብር ወደ እርስዋ ያመጣሉ። ራእይ 21፡ 26
      • በሮችሽም ሁልጊዜ ይከፈታሉ ሰዎች የአሕዛብን ብልጥግና የተማረኩትንም ነገሥታቶቻቸውን ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድ ሌሊትና ቀን አይዘጉም። ኢሳ 60

      የምድርም ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርስዋ ያመጣሉ፤ በዚያም ሌሊት ስለሌለ ደጆችዋ በቀን ከቶ አይዘጉም፥ ራእይ 21፡ 24-25
      • ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆንልሽም፥ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አይበራልሽም። ኢሳ 60

      ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር። ራእ 21፡23
      እና የመሳሰሉትን አንድ አይነት አሳቦች ሁለቱም ስፍራዎች እናገኛለን፡፡ አዲሲቷ ኢየሩሳሌም፤ የንጉሱ ከተማ፤ የክርስቶስ ኢየሱስ አካል የሆነችው ቤተክርስቲያን እውነት በራእይ ላይም ሆነ በኢሳይያስ ትንቢት ላይ ቁልጭ ብላ ትታያለች፡፡
      6 hours ago · Like
    • Tadesse Gebre Michael Yared,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,," Ye nakushm Hulu wede Egrsh Chama ysegdalu" yemilewns alagegnehewm ende? Slemn tewkew?
      6 hours ago via mobile · Like · 1
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ ብዙ ማብራሪያ ተሰጥቶናልና ማመስገን ይገባናል። ሆኖም መልሱን የሚመልስ ማን ነው? 1/ ጽዮን የተባለ ሁሉ ለዳዊት ከተማ የተነገረ ነው?

      /4/ ትንቢተ ኢሳይያስ 60
      14 የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ ((እግርሽ ጫማ )) ((ይሰግዳሉ )) የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። በዚህ ትንቢት ጽዮን የተባለችው የዳዊት ከተማ ከሆነች ለተራራ መስገድ ጣዖት አይደለም?
      6 hours ago · Like · 3
    • Tadesse Gebre Michael Betekrstyan snsalem na le E/rs bihon snsegd enante aydelem ende, le Dingay mesalem mn malet new? Eyalachu Orthodoxawyann yemttechut? Endet zare sle Betekrstyan tekorekorachu?
      6 hours ago via mobile · Like
    • Chirstian HaGer Nat Ethopia በጣም እኮ ነው ሚገረመው ለተጠየቁት መልስ ሳይዙ አሰስ ገሰሱን ከየት ይጠይቃሉ ከየት እንደሚያመጡት ብቻ ነው ገርም ሚለኝ
      6 hours ago via mobile · Like
    • Yared Ashagre Tadesse Gebre Michael: No my friend; I didn't drop that:

      Isa 60:14 And the sons of them that afflicted thee shall come bending unto thee; and all they that despised thee shall bow themselves down at the soles of thy feet; and they shall call thee The city of Jehovah, The Zion of the Holy One of Israel. 

      Yeah, the Church is well afflicted by the Jews and the world, and I hope you read the history of Nero the burner who put ablaze many Christians in fire. These are some of the afflictions the Church passed through. Despised? Yes the Church was well despised by the Greeks and the intellectuals of the time, and even in our recent history, the Church has been labeled as irrelevant and improper to modernism. 
      And look at Hebrews 12: 

      ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥
      በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥
      የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።
      ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥
      በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥
      የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።
      6 hours ago · Like
    • Bright Destiny Yared Ashagre can you pls tell us why did you write the verse 60:14 in English and the rest in Amharic ?
      6 hours ago · Edited · Like
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ ለማብራሪያው በድጋሚ እናመሰግናለን። መልሱን የሚመልስ ግን ማን ነው?
      5 hours ago · Edited · Like
    • Tadesse Gebre Michael Lemamtatat newa!
      6 hours ago via mobile · Like
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ ልበ አምላክ ዳዊት በገናውን እየደረደረ እንዲህ አለ፦
      እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ /ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላታል፤ በውስጧም ሰው ተወለደ! / መዝ [86: 5]
      ከመሬት ውስጥ ሰው ይወለዳል እንዴ? አይወለድም ወደፊትም አይወለድም፤ መዝሙሩን ልብ ብለን ስናነበው ግን “ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላታል፤ በውስጧም ሰው ተወለደ!” ይላል፤ ስለዚህም ጽዮን የተባለችው እመቤታችን ናት። የዳዊት በገና ቀጠለ እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና፤ ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት፤/ዛቲ ይዕቲ ምዕራፍየ ለአለም/ መርጫታለሁና በእርሷም አድራለሁ። መዝ [131: 13]
      5 hours ago · Like · 4
    • Yared Ashagre በጣም አስቂኝ ድምዳሜ ነው፡፡ ባራክ ኦባማ አሜሪካ ውስጥ ተወለደ ማለት የአሜሪካ መሬት ወለደው ማለት ነውን? በፍጹም! ይህንን መቼም ማብራራት አያስፈልገውም ነበር፡፡
      5 hours ago · Like
    • Feker Tsige mekawem bicha lela min alachew protestantochi
      5 hours ago via mobile · Unlike · 1
    • እንዳለልኝ አበራ ቾንቤ YARED@ TERO KALEDAGNA NAHE MAZEMUR 86:5 SAWE HOLO EINATACHEN TEYONE YELATELE BAWESTA SAWE TAWELDALEN= YEHA TENEBETE NAWE MAJAMREYA YATENAGERAWE LA NEGOSE DAWETE NAWE FETAMEWE LA EIYASOSE KERESTOSE YATENAGER NAWE SELAZEHE TEYONE YETEBALCHAWE DENGELE MAREYAMENE SETEHONE SAWE YTEWELDAWE EIYASOSE KERESTOSE NAWE LAZEHE YAMEYAREGAGETELHE BA EISAYASE 59:20 YALAWEN KALE BADANEBE ANEBEBAWE
      5 hours ago via mobile · Edited · Unlike · 2
    • DM HI Yared Ashagre Anyone who tries to deal in a logical manner with an illogical person is on a fool's errand.
      5 hours ago · Like
    • Wond Wosen Mezgebe Alem Lisanework why i failed
      5 hours ago · Edited · Like
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ Yared Ashagre በዚህ ትንቢት ጽዮን የተባለችው የዳዊት ከተማ ከሆነች ለተራራ መስገድ ጣዖት አይደለም? መልሱ ይለፈኝ አላችሁ? // ባራክ ኦባማ አሜሪካ ውስጥ ተወለደ ማለት የአሜሪካ መሬት ወለደው ማለት ነውን? ብላችሁ መጠየቅ ያለባችሁ ራሳችሁን ነበር። /1/ /ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላታል፤ በውስጧም ሰው ተወለደ! / መዝ [86: 5] ማለት ምን ማለት ነው? /2/ እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና፤ ይህች ((ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት)) ማለትስ ምን ማለት ይሆን?
      5 hours ago · Like
    • Yared Ashagre Endalelign Abera: ለዳዊት የተነገረ ጊዜ የትንቢቱ የመጀመሪያ ፍጻሜ ነበር ብለሃል ወዳጄ፡፡ የክርስቶስ ጊዜ ማርያም ከሆነች የዳዊት ጊዜ ያኔ ታዲያ ጽዮን ማን ነበረች?
      5 hours ago · Like
    • Tadesse Gebre Michael Mezmur 86:5,,,,,,, Mann yhon ahuns Tsyon enatachn yemnlew? Dawit keteman? Tsyon Teraran? Weys Tsyon Maryam?
      5 hours ago via mobile · Unlike · 1
    • Yared Ashagre Yoni Ab: Yonas Zekariyas: ለአንተ አተረጓጎም የተሰጠ መልስ ነበር እኮ ወዳጄ፡፡ ሰው መሬት ውስጥ ይወለዳል ወይ ብለህ የወሰድከው ድምዳሜ መሬት ውስጥ ካልተወለደ እንግዲያውስ. . . .የሚል ነበር፡፡ እንግዲህ ሰው ስለአገሩ ተናግሮ በዚያ ተወለድኩ ሲል የአገሪቱ መሬት ውስጥ ተወለድኩ ማለቱ ነው ወይስ ደግሞ ስፍራን እያመላከተ ነው? ነበር ጥያቄያዊ ምላሼ፡፡ አንተ ደግሞ ወደእኔው አዞርከው፡፡
      5 hours ago · Like
    • እንዳለልኝ አበራ ቾንቤ MAJAMREYA SELAKTEMAWE SELA ANEBAYETO TEYONE YATENAGER nawe
      5 hours ago via mobile · Edited · Like
    • Yared Ashagre የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን ጢሮስም የኢትዮጵያም ሕዝብ፥ እነዚህ በዚያ ተወለዱ።
      ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።

      ከጽዮን ተጨማሪ ረዓብ፤ ባቢሎን፤ ፍልስጥኤም፤ ጢሮስና ኢትዮጵያ ተጠቅሰዋል፤ እነዚህስ እነማን ናቸው?
      5 hours ago · Like
    • Mati Mat ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ - የመናፍቃን ትልቁ ማሳሳቻ ግማሽ መጥቀስ ነው. ሰይጣን ጌታን ሲፈትነው የነበረው ግማሽ በመጥቀስ ነበር. ሙሉው ጥቅስ መዝ86-5 "ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት" "This and that man was born in her: and the highest himself shall establish her." ልኡል መሰረታት የተባለው በውስጧ ሰው የተወለደውን ወንድሜ ማሪያም ናት ያላትን ነው. ማሪያም ተፈጠረች ወይስ ተመሰረተች? እ/ር ሰውን በመልካችንና እንደምሳሌአችን እንመስርት አለ እንዴ ? የሚመሰረተው /establish ሰው ነው ወይስ ከተማ ?ሰው የሚወለደው ከውስጥ ወደ ውጭ ወይስ ከውስጥ ወደ ውስጥ ? ይህንን መልስልኝ
      5 hours ago · Like
    • Mati Mat ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ መዝ 86-6 "እግዚአብሔር ለሕዝቡ፥ በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል።"ለመሆኑ በመጽሃፍ የሚነግራቸው በውስጧ የተወለዱት አለቆች ስንት ናቸው?ማሪያም ብዙ አለቆችን ወልዳለችን?
      4 hours ago · Like
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ Mati Mat ሰላም ወንድም ዓለም። ሁል ጊዜ ከመልስ በኋላ ጥያቄና ማብራሪያ ብናስከትል መልካም ነበር። " ልኡል መሰረታት ማደሪያው ትሆን ዘንድ ቀደሳት ሰራት አመቻችቶ በንጽህና በቅድስና መሰረታት ማለት ነው። ልኡል ማደሪያውን ቀደሰ እንዲል። 1/ ጽዮን የተባለ ሁሉ ለዳዊት ከተማ የተነገረ ነው?

      /4/ ትንቢተ ኢሳይያስ 60
      14 የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ ((እግርሽ ጫማ )) ((ይሰግዳሉ )) የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። በዚህ ትንቢት ጽዮን የተባለችው የዳዊት ከተማ ከሆነች ለተራራ መስገድ ጣዖት አይደለም?
      about an hour ago · Like · 3
      4 hours ago · Like
    • Wond Wosen መልስ ተሰጠህ እኮ አንብበህ ችግር ያለበት ቦታ ያልገባህ ካለ ንገር ጽዮን የተራራ ስም ነዉ! አንተ ለማርያም ይሰግዳሉ ለማለት ፈልገህ ነዉ! እንዲያ ከሆነ በዕዉነት ሞኝ ነህ!! ብሉይን በደንብ አንብብ
      4 hours ago · Like
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ Wond Wosen ወንድም ዓለም ምክራችሁ በዛ፤ መልሱን ግን ማን ይመልስ ?በዚህ ትንቢት ጽዮን የተባለችው የዳዊት ከተማ ከሆነች ለተራራ መስገድ ጣዖት አይደለም?
      4 hours ago · Like · 1
    • Mati Mat ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ-1/ ጽዮን የተባለ ሁሉ ለዳዊት ከተማ የተነገረ ነው? ላልከው እያወራን ያለነው ስለ ኢሳ60-14 ስለሆነ እሱን ጨርሰን አንድ በአንድ ማየት ይቻላል. "ጌታ ኢየሱስ እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ደካሞች ወደእኔ ኑ ..." እንዲሁም " ...ህይወት እንዲሆንላችሁ ወደእኔ መምጣት አትወዱም" የሚሉት ተሰርዞ "ወደእናቴ ሂዱና ወደእግሯ ጫማ ስገዱላት" የሚል ጌታ የለንም. "ጽዮን የተባለችው የዳዊት ከተማ ከሆነች ለተራራ መስገድ ጣዖት አይደለም?" ላልከው ጌታ ለሳምራዊቷ ሴት " በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም የማትሰግዱበት ግዜ ይመጣል..." ሲል ለተራራውና ለከተማው የማትሰግዱበት ...ማለቱ አልነበረም. ይልቁንስ በእውነትና በመንፈስ ስለመስገድ ሲያስተምር እንጂ በኢየሩሳሌምም ሆነ በተራራው የሚሰግዱትና የሚሰውት ለእ/ር እንደሆነ ያውቃል.
      4 hours ago · Like · 1
    • Wond Wosen በዚያ የእ/ር ክብር አለ! አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ኢትዮጺያዊዉ ጃንደረባ ወደ ኢየሩሳሌም የሄደዉ ለምንድን ነዉ ሐዋ 8 
      27 ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤ ለኢየሩሳሌም መስገድ ጣኦት አየደለምን? በአንተ አባባል? የኔ ወንድም ጽዮን ተራራ ስለመሆኗ አትከራከር በዚያም ለመስገድ መሄድ የእ/ር ክብር ያለበት ቦታ ስለሆነ እንጂ አንተ እንደምታሰበዉ አይደለም! ዉስጥህ እያወቀዉ ነዉ!!!!!!
      4 hours ago · Like · 2
    • Yared Ashagre Isa 60
      14 The sons also of them that afflicted thee shall come bending unto thee; and all they that despised thee shall bow themselves down at the soles of thy feet; and they shall call thee, The city of the Lord, The Zion of the Holy One of Israel.

      ወዳጄ ዮናስ፡ አንተ ሙሉ አሳቡን በጥንቃቄ ብታነብበው መልስህንም እዚያው ስለምታገኘው አትጠይቅም ነበር፡፡ ያንተ ጥያቄ ያው ጽዮን ማርያም ናት ለማለት መንደርደሪያ እንደሆነ ግልጥ ነው፡፡ እኛ ደግሞ ስንመልስልህ ጽዮንን ማርያም እንዳይደለች ለማሳየት ከሚል ልብ ተነስተን ሳይሆን ቃሉን በትክክል ከመገንዘብ ተነስተን ነው፡፡
      ስለዚህም ለተራራም ሆነ ለፍጥረት መስገድ ትክክል አይደለም፤ ነገር ግን እዚህ ጋር እያወራ ያለው ስለጽዮን አገዛዝ ከሁሉ በላይ ሆና የእግዚአብሄር ከተማ ተብላ ከፍከፍ ስለማለቷ፤ ነገስታትንና ባለጠጎችን ሁሉ ስለማንበርከኳ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በራእይ 21 ላይ በግልጥ አዲሲቷ ኢየሩሳሌም የንጉሱ ከተማ እንደሆነች ማስተዋል እንችላለን፡፡
      ስለዚህ ለተራራ መስገድ ጣኦት ሆኖ ሳለ የጽዮን ገዢ ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ ሁሉ ለእርሷ መንበርከካቸው ግን አምልኮን ወይም ሌላን ነገር አያሳይም፤ ይልቁን የንጉሱን ታላቅነት እንጂ፡፡
      አሜሪካ ልእለ-ሀያል አገር ተብላ አገሮች ሁሉ ሰገዱላት ሲባል አመለኳት ማለት አይደለም፤ ይልቁን አስገበረች፤ አንበረከከች፤ ገዛች. . .ወ.ዘ.ተ ማለት ነው፡፡
      አድካሚ ዙር ለምን እንደምትሄድ አይገባኝም፡፡
      4 hours ago · Like · 2
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ Mati Mat ወንድም ዓለም አሁን ከሌሎቹ አንድም ከሌላው ቀንም የተሻለ መልሰሃልና አመሰግናለሁ። በኢየሩሳሌምም ሆነ በተራራው የሚሰግዱትና የሚሰውት ለእ/ር እንደሆነ ያውቃል. ብለኸናል። ትንቢተ ኢሳይያስ 60
      14 የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ ((እግርሽ ጫማ )) ((ይሰግዳሉ )) የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። ኢሳይያስ የሚያወራው ስለ ጽዮን ነው ወይስ ስለ እግዚአብሔር? ወደ ((እግርሽ ጫማ )) ((ይሰግዳሉ )) የተባለው ለእግዚአብሔር ነው?
      4 hours ago · Like · 3
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ ወንድም ዓለም Wond Wosen አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤ለኢየሩሳሌም መስገድ ጣኦት አየደለምን? ብለሃል። በኢየሩሳሌም መስገድና ለኢየሩሳሌም መስገድ በጣም ይለያያሉ።
      4 hours ago · Like
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና፤ ይህች ((ለዘለዓለም)) ማረፊያዬ ናት፤/ዛቲ ይዕቲ ምዕራፍየ ለአለም/ መርጫታለሁና በእርሷም አድራለሁ። መዝ [131: 13] በዚህ ጥቅስ ጽዮን የተባለችው ከተማ ናት የሚሉ አሉ። የዳዊት ከተማ ለዘለዓለም ማረፊያው ናት?
      4 hours ago · Like
    • Tadesse Gebre Michael Ol Pro's,,,,,,,,,,,,,,Le tsyon terara mesged yaltegeba aydelemn? Le Dawit ketemas mesged le Taot endemesged aydelemn? Tadya enezi hulu kentu dkam kehone"wede egrsh chama ysegdalu"yetebalew lemn yhonal? Meches sle Maryam sinegerachu yemaywat slemihonbachu enji Glts new.
      4 hours ago via mobile · Like
    • Tadesse Gebre Michael Ye Dawit ketemas zelealemawi nat? Le Zelalem marefyaye endthon merchatalehu ylal na?
      4 hours ago via mobile · Like
    • Tadesse Gebre Michael Yared & Mati,,,,,,,,,,,,and aquam meyaz alebachu. TSYON yemilew le Dawit ketema new weys le Semayawit Eyerusalem?
      4 hours ago via mobile · Like
    • Tadesse Gebre Michael Le Maryam yemilew legizew ykrbachu. Be huletum zurya new yalachut na.
      3 hours ago via mobile · Like
    • Mati Mat ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ/Tadesse Gebre Michael-ኢሳ52-1 " ምርኮኛይቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የአንገትሽን እስራት ፍቺ" ስለሚል ሰው እንጂ ተራራ አንገት ስለሌለው ማሪያም ምርኮኛ ሴት ልጅ አላት ማለት ነው? ስለዚህ ማሪያም ልጅ አላት የሚለውን ትደግፋላችሁ ማለት ነው.?
      3 hours ago · Like
    • Tadesse Gebre Michael Yhn r'es lela gizie wendme.
      3 hours ago via mobile · Like
    • Mati Mat Tadesse Gebre Michael -ምነው ከኢሳ60-14 ጋር የተያያዘ ነው እኮ
      3 hours ago · Like
    • Mati Mat መልሱን የሚመልስ ግን ማን ነው?
      3 hours ago · Like
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ Mati Mat Heaven Nahom አላዋቂ ሰው ብዙ እየተናገረ አለማወቄን እወቁልኝ ይላል። ኢትዮጲያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ማለት እጅ አላት ማለት ነው? አንተ የጠቀስከው ስለ ዳዊት ከተማ ነው። ከላይ የጠየኩህን ለመመለስ ሞክር፦ ትንቢተ ኢሳይያስ 60
      14 የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ ((እግርሽ ጫማ )) ((ይሰግዳሉ )) የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። ኢሳይያስ የሚያወራው ስለ ጽዮን ነው ወይስ ስለ እግዚአብሔር? ወደ ((እግርሽ ጫማ )) ((ይሰግዳሉ )) የተባለው ለእግዚአብሔር ነው?
      40 minutes ago · Like · 3
      3 hours ago · Edited · Like
    • Tadesse Gebre Michael Tyake be tyake memeles tejemere ende? Ante mn tlaleh? Eshi Ethiopia ej alat ltlen yhon? Mezmur 67
      3 hours ago via mobile · Edited · Like
    • Mati Mat ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ /Tadesse Gebre Michael. ሙሉው ጥቅስ መዝ86-5 "ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት" "This and that man was born in her: and the highest himself shall establish her." ልኡል መሰረታት የተባለው በውስጧ ሰው የተወለደውን ወንድሜ ማሪያም ናት ያላትን ነው. ማሪያም ተፈጠረች ወይስ ተመሰረተች? እ/ር ሰውን በመልካችንና እንደምሳሌአችን እንመስርት አለ እንዴ ? የሚመሰረተው /establish ሰው ነው ወይስ ከተማ ?ሰው የሚወለደው ከውስጥ ወደ ውጭ ወይስ ከውስጥ ወደ ውስጥ ? ይህንን መልሱልኝ
      3 hours ago · Like

    • 2 hours ago · Edited · Like · 2
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ Yegeta Meseker ከመልሱ አንድ ነገር እንድትረዱ ስለፈለኩ ነው። ፕሮቴስታንትም መልስ አላት ለማለት ሞክሩና ጥያቄውን ሞክሩት
      2 hours ago · Like
    • Tadesse Gebre Michael Tyake, weym lela asteyayet kalachu mels kesetachu bewhala endemitebeklachu Bemasaseb neber tyakewn post yetederegew.
      2 hours ago via mobile · Unlike · 1
    • Shimelis Mergia Mati Mat ወይስ ዘንዶው ከተቆጣባት ከሴቲቱ ና ከዘርዋ ከቀሩት የክርስቶስ ምስክርነት ካላቸው ወገን ነህን? ከዘርዋ ከክርስቶስ ወገን ከሆንክ የሴቲቱ ልጅ ነህ ማለት ነውና፡፡
      2 hours ago · Like · 3
    • Mati Mat Shimelis Mergia- አንድ ነገር ላስረዳህ."የክርስቶስ ምስክርነት ካላቸው " የሚለውን ስትሰማ ምን ታስታውሳለህ? "ስለእኔ በሰዎች ሁሉ ፊት የሚመሰክርልኝ እኔም በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ" ምን ብሎ የመሰከረ ?"ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር..." አይልም? ስለእናቱ ይላል? ስለመላእክት ይላል ?ስለቅዱሳን ይላል. ?አሁን የክርስቶስ ወገን ማን እንደሆነ ይገባሃል
      2 hours ago · Like
    • Shimelis Mergia Mati Mat ምንድን ነው ግን እንዲህ ዘንዶው በተቆጣበት “በሴቲቱ” ላይ እንዲህ በጠላትነት መነሣትህ? ይህቺ እኮ የክርስቶስ ምስክርነት ላላቸው ሁሉ እናት ናት ምንክያቱም በክርስቶስ የእርሱዋ ዘሮች ተብለዋልና፡፡
      2 hours ago · Edited · Like · 4
    • እንዳለልኝ አበራ ቾንቤ MATI@ KA ZANEDWE GARE TELE YALETE SETETO NATE SATETO DAGEM DENGELE MARYAMENE NATE = KA MALEKTO GARE YATETALAWE ZANDWE NAWE TADEYA YASO AGAFERE NAHE ? WAYES KA WEDEYETEGNAWE WAGANE NAHE
      2 hours ago via mobile · Like · 1
    • Shimelis Mergia Mati Mat “ስለክርስቶስ በመመስከር” ሴቲቱን ትቀድማት ይሆን? ነፍሴ ጌታ ታከብራለች መንፈሴም በአምላኬና በመድኀኒቴ ሐሴትን ታደርጋለች …. በእኔ ታላቅ ሥራን አድረጋጓልና ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል" ያለች የአምላክ እናት ናት፡፡ እንደ እርሱዋ ከነፍሳቸው ጥግ ክርስቶስን የሚያመልኩ ሁሉ ስለክርስቶስ የሚመሰክሩ ናቸው፡፡ እነርሱም የእርሱዋ ዘሮች ይባላሉ፡፡ መጽሐፍ ይህን አረጋግጦልናል፡፡
      2 hours ago · Like · 3
    • Tadesse Gebre Michael Mati,,,,,,,,,,,,Tifozo neh?
      2 hours ago via mobile · Like
    • Tadesse Gebre Michael Mati,,,,,,,,,,,,Tifozo neh?
      2 hours ago via mobile · Like
    • Wond Wosen Tadesse Gebre Michael yeman tifozo.. ye arsenal woynis ye chealse??
      2 hours ago · Like
    • Tadesse Gebre Michael Wond wosen,,,,,,,,,,,,Ye tnte telatachn
      2 hours ago via mobile · Like · 1
    • እንዳለልኝ አበራ ቾንቤ WAND WANSNE@ ANETASE YA ZANDAWE TABABRE NAHE? MIKENEYATOME ZANEDOWE YATETALWE KA SETETO GARE EINA KA MALEKETO GARE NAWE ANETE KAYATEGNAWE WAGANE NAHE ?
      2 hours ago via mobile · Like · 1
    • Dereje Shibru ***** kale hiwot yasemalin yagelgilot zemenih yetebareke yhun amen.
      about an hour ago via mobile · Like · 1
Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 09:16 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest
Newer Posts Older Posts Home
Subscribe to: Posts (Atom)

እነሆ የአንባቢዎች ቁጥር 115,762 ደረሰ! /አሜሪካ እንግሊዝና ኢትዮጲያ ከ1ኛ - 3ኛ ያለውን ቦታ ይዘዋል/

ከልብ ለምወዳት ሰ/ት/ቤቴ

Promote Your Page Too

ተጨማሪ ማንበብ ይቻላል!

  • ►  2014 (4)
    • ►  03/30 - 04/06 (1)
    • ►  03/02 - 03/09 (1)
    • ►  02/09 - 02/16 (1)
    • ►  02/02 - 02/09 (1)
  • ▼  2013 (57)
    • ►  12/29 - 01/05 (1)
    • ►  12/22 - 12/29 (1)
    • ►  11/10 - 11/17 (1)
    • ►  09/01 - 09/08 (1)
    • ►  08/25 - 09/01 (5)
    • ►  08/18 - 08/25 (3)
    • ►  08/11 - 08/18 (3)
    • ►  08/04 - 08/11 (4)
    • ►  07/28 - 08/04 (8)
    • ▼  07/21 - 07/28 (9)
      • ሚካኤል
      • ሕሊና እና ምክንያት
      • ጥንተ አብሶ
      • እናት ለልጅዋ ነቢይ ናት!
      • የኢየሱስ ክርስቶስ ደም የአምላክ ነው ወይስ የሰው?
      • //ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ//
      • //የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ//
      • / /የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንደ ነብር ፀጉር//
      • ምስጢረ ተዋህዶ
    • ►  07/14 - 07/21 (3)
    • ►  07/07 - 07/14 (14)
    • ►  04/07 - 04/14 (1)
    • ►  03/10 - 03/17 (1)
    • ►  03/03 - 03/10 (1)
    • ►  01/06 - 01/13 (1)
  • ►  2012 (89)
    • ►  12/23 - 12/30 (2)
    • ►  12/16 - 12/23 (1)
    • ►  12/09 - 12/16 (1)
    • ►  11/25 - 12/02 (1)
    • ►  09/16 - 09/23 (1)
    • ►  09/09 - 09/16 (1)
    • ►  09/02 - 09/09 (2)
    • ►  08/26 - 09/02 (2)
    • ►  08/19 - 08/26 (37)
    • ►  08/12 - 08/19 (2)
    • ►  08/05 - 08/12 (1)
    • ►  07/29 - 08/05 (2)
    • ►  07/22 - 07/29 (1)
    • ►  07/08 - 07/15 (1)
    • ►  07/01 - 07/08 (2)
    • ►  06/24 - 07/01 (1)
    • ►  06/17 - 06/24 (2)
    • ►  06/10 - 06/17 (1)
    • ►  06/03 - 06/10 (1)
    • ►  05/27 - 06/03 (2)
    • ►  05/20 - 05/27 (1)
    • ►  05/13 - 05/20 (1)
    • ►  05/06 - 05/13 (2)
    • ►  04/22 - 04/29 (1)
    • ►  04/15 - 04/22 (1)
    • ►  04/08 - 04/15 (2)
    • ►  04/01 - 04/08 (1)
    • ►  03/25 - 04/01 (2)
    • ►  03/18 - 03/25 (1)
    • ►  03/11 - 03/18 (1)
    • ►  03/04 - 03/11 (1)
    • ►  02/26 - 03/04 (2)
    • ►  02/19 - 02/26 (1)
    • ►  02/12 - 02/19 (1)
    • ►  02/05 - 02/12 (1)
    • ►  01/29 - 02/05 (1)
    • ►  01/22 - 01/29 (1)
    • ►  01/15 - 01/22 (2)
    • ►  01/08 - 01/15 (1)
    • ►  01/01 - 01/08 (1)
  • ►  2011 (27)
    • ►  12/25 - 01/01 (2)
    • ►  12/18 - 12/25 (3)
    • ►  12/11 - 12/18 (2)
    • ►  12/04 - 12/11 (2)
    • ►  11/27 - 12/04 (7)
    • ►  11/20 - 11/27 (11)

የልጅ ዮናስ ብሎግ አባል ይሁኑ!

በባህላችን ምግብ ለብቻ አይበላምና ይህን ምግበ ነፍስ ለጓደኛዎ ያስተዋውቁ!. Ethereal theme. Theme images by MichaelJay. Powered by Blogger.