Friday 16 December 2011

"መቆምና ማየት"

አንድ የተከበሩ አባት እንዲህ ብለው ጠየቁ፤

መላእክት እንደ ሰው የሚታጠፍ እና የሚዘረጋ እግረ ሥጋ የላቸውም፤ ታዲያ መላኩ ቅ/ገብርኤል እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ ሲል ምን ማለቱ ነው?? ሉቃስ [1: 19]  

በእርግጥ ግሩም ጥያቄ ነው፤ መላእክት መንፈስ ናቸውና እግረ ሥጋ የላቸውም፤ አይቀመጡም አይነሱም አይቆሙምም!  
ሊቀ መላእክት ቅ/ገብርኤል እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ ማለቱ ምህረትን ጠያቂ አማላጅ ነኝ ሲል ነው። እንዴት ማለት ጥሩ ነውና እንዴት? እንበል

ይህን እንድንረዳ ልበ አምላክ ዳዊት የዘመረውን አብረን እንይ፤  የተመረጠው ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ባይቆም” ኖሮ ሕዝበ እሥራኤላዊያን በቅጽበት በጠፉ ነበር ይለናል መዝ. [105:23] ሙሴ ቀጥ ብሎ ስለ ቆመ አይደለም እስራኤላዊያን የተማሩት፤ ሕዝቡን ከምታጠፋ ሥሜን ከሕይወት መጽሐፍ ላይ ደምስስ!!! እያለ የለመነው ልመና ነው እስራኤላዊያንን ያስማራቸው ፀአት[32:32]

ስለዚህም መቆም” ማለት ቀጥ ብሎ መቆም ብቻ ሳይሆን  መለመን ፣ ማማለድ እንደሆነ ባህረ ጥበብ የሆነች ቤተክርስቲያናችን እንዲህ ከመጽሐፍ ቅዱስ እየያበሰለች ትመግበናለች!
እስኪ በአንድምት እንምጣ፤ አንድም ስለ ሕዝቡ የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል ዳንኤል [12:1] ቅ/ሚካኤል እግረ ሥጋ የለውም፤ ስለ እኛ ምህረትን ይለምናል እንጂ። አንድም መላዕክትም በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ፤ ሰይጣንም በመካከላቸው ነበር። ኢዮብ [1:6] ሰይጣን ከሳሽ ስለሆነ ቆመ አልተባለም መላዕክቱም ቆሙ የተባሉት ቀጥ ብለው ቆሙ ለማለት አይደለም፤ ሊለምኑ መጡ ለማለት ነው እንጂ።  አንድም እግርህ በድንጋይ እንዳይመታ በእጆቻቸው ያነሱሃል ይላል፤ መዝ. [90: 11] መላዕክት እንደ ሰው እጅ የላቸውም መንፈስ ናቸውና፤ ነገር ግን ሎጥን ከሰዶም እሣት እጁን ይዘው እንደወጡ ፈጥነው ደራሽ መሆናቸውን ሲያስረዳን ነው። አንድም መላዕክት እንደ ሰው የሚያዩበት ዓይነ ሥጋ የላቸውም፤ መንፈስ ናቸውና፤ በወንጌል ግን ጌታችን እንዲህ አለ፦ ከታናናሾቻችሁ ማንንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ ጠባቂ መላእክቶቻቸው ዘወትር የአባቴን ፊት ያያሉና ማቴ. [18:10] ያያሉና ማለት ዓይንን ገልጦ ማየት ማለት አይደለም፤ መላዕክት ዓይነ ሥጋ የላቸውም ተብሏልና። ያያሉ ማለት ይለምናሉ ማለት እንደሆነ አየህን?

አንድም “ጠባቂ መላእክቶቻቸው” የሚለውን ስንመለከት ጠባቂ የሚለቅ ቃል መላዕክት ጠባቂ እንደሆኑ አይነግረንምን? አንድም መላእክቶቻቸው የሚለው ቃል እያንዳንዱ ሰው ፪ ዑቃቢ መልአክ /ጠባቂ መልአክ/ እንዳሉት አይነግርህምን? ፩ዱ በቀን ሲጠብቅህ ፩ዱ በለሊት እንደሚጠብቅህ አታውቅምን?

የጥቅስ ጥናት ዘዴ
የቅ/ሚካኤል በዓል የሚውለው በ 12 ነው ስለዚህ ዳንኤል [12:1]
የቅ/ገብርኤል በዓል የሚውለው በ 19 ነው ስለዚህ ሉቃስ [1: 19]

·       ቁልፍ ቃላት መቆም ፣ “በእጆችቸው ያነሱሃል”፣ “ማየት”



Monday 12 December 2011

«ያለ ግብረ ሰዶም ርዳታ የለም»

ዛሬ የወጣው የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኦባማ ለግብረ ሰዶማውያን የሰጧቸውን ልገሳ ይዞ ወጥቷል፡፡ አሜሪካ ለሌሎች ተቋማትም ሆነ ሀገራት በምትሰጠው ርዳታ ተቋማቱም ሆኑ ሀገራቱ ለግብረ ሰዶማውያን መብቶች መጠበቅ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ከግምት ውስጥ እንደምታስገባ፣ የግብረ ሰዶማውያንን መብት እንዲከበር ለማድገረግ የውጭ ርዳታዋን እንደምትጠቀም መግለጣቸውን ጋዜጣው አትቷል፡፡
ይህንን ተከትሎም የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ሂላሪ ክሊንተን ለዲፕሎማቶቻቸው የግብረ ሰዶማውያንን መብቶች እንዲያስጠብቁ እና የመብት ጥሰቶችንም ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡
 አሜሪካ ፍላጎቶቿን ከምትጭንባቸው መሣርያዎች አንዱ የምትሰጠው ርዳታ ነው፡፡ ራሳቸው አሜሪካኖቸ$ there is no free lunch እንደሚሉት ርዳታ ብቻ የሆነ ርዳታ የለም፡፡ ርዳታ ከሚለው በጎ ቃል ጀርባ ግዴታ የሚባል ውስጠ ወይራ አለ፡፡
ሊቁ አንድን ሰነፍ ተማሪ ሁልጊዜ ሲያነብብ ንባብ ያርሙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ጓደኞቹ እየናቁት ሄዱ፡፡ እርሱም ንባቡን ከማሻሻል ይልቅ መምህሩን ዝም የሚያሰኝበትን ሌላ መንገድ አሰበ፡፡
አንድ ቀን በጋቢው ውስጥ አናት ውኃ የሚያደርግ የወይራ ዱላ ይዞ ወደ ንባቡ ቀረበ፡፡ ከዚያም ተጣዩን እያነሣ፣ ተነሹንም እየጣለ መዘንጠል ጀመረ፡፡ ተማሪዎቹ መምህራቸው ካሁን ካሁን ያርሙታል ብለው ቢጠብቁ እርሳቸው ዝም ብለዋል፡፡ ከዚያም አንዱ ደቀ መዝሙር ምነው የኔታ ለምን አያርሙትም? ይላቸዋል፡፡ የኔታም «ተወው ውስጠ ወይራ ነው» አሉት ይባላል፡፡
ብዙ ርዳታዎች እንደ ሰነፉ ተማሪ ውስጠ ወይራ ናቸው፡፡ እኛ የምናየው በሚዲያም የሚነገረን ከጋቢው በላይ ያለውን ነገር ነው፡፡ ከጋቢው ውስጥ ግን ወይራው አለ፡፡
በተለይም በዕድገት ወደ ኋላ የቀሩ ሀገሮች አድገዋል ከሚባሉት ሀገሮች ርዳታ እና ብድር ለማግኘት ሲሉ የአበዳሪዎቻቸውን እና የረጅዎቻቸውን ግዴታዎች ይቀበላሉ፡፡ ይህ የአደጉት ሀገሮች የርዳታ ጀርባ ጫና ከፖለቲካዊው እስከ ማኅበራዊ ግዴታዎች ይደርሳል፡፡ አሁን የኦባማ አስተዳደር ይፋ ያደረገውም ይሄንኑ ነው፡፡
እንግዲህ አማራጫችን ምንድን ነው?
ርዳታን ያለ ምንም ተጽዕኖ ማግኘት አይቻልም፡፡ ነገር ግን የተጽዕኖዎቹን መጠን መቀነስ ይቻላል፡፡ ልንቀበላቸው የምንችላቸውን፣ በከፊል ልንቀበላቸው የምንችላቸውን እና ፈጽሞ የማንቀበላቸውን ተጽዕኖዎች የለየ የመንግሥት ፖሊሲ በዚህ ረገድ ወሳኝ ነው፡፡
የሀገርን እና የሕዝብን ማንነት የሚቀይሩ፣ ብሔራዊ መብቶችን እና የሀገርን ጥቅሞች አሳልፈው የሚሰጡ፣ ሕዝብን ዘመናዊ ባርያ የሚያደርጉ ዓይነት ተጽዕኖዎች ሲመጡ «አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር» ማለት ያስፈልጋል፡፡
ሌላው መንገድ ደግሞ በዚህም በዚያም ብሎ ተጽዕኖን ለመቀነስ ብሎም ከናካቴው ለማስቀረት በሚያ ስችል የዕድገት ደረጃ ላይ መድረስ ነው፡፡ ድህነት እና ርዳታ አብረው የሚጓዙ ናቸው፡፡ «እምነ ርሃብ ይኼይስናት» ከረሃብ ጦር ይሻላል እንዳሉት ሐዋርያት ርሃብ ጦርነትን ያስመርጣል፡፡ ምክንያቱም ባለበት ቦታ ሁሉ ተጽዕኖዎች እንደፈለጉ ይንሸራሸራሉና፡፡
በሌላም በኩል ከሌሎች የምንወስዳቸው ነገሮች ሁሉ በመገልበጥ መወሰድ የለባቸውም፡፡ የማጥመቅ ሥራ መሠራት አለበት፡፡ አንድ ነገር ወደ ሀገሪቱ ሲመጣ ከሀገሪቱ ሕጎች፣ ባህሎች፣ እምነቶች፣ ሥሪቶች እና ማንነቶች ጋር ያለው ዝምድና መለካት ይገባዋል፡፡ ለአሜሪካ ወይንም ለእንግሊዝ መልካም የሆነ ሁሉ ለኢትዮጵያም መልካም ነው ማለት አይደለም፡፡
የሶማሌ ተራ ሰዎች ለመኪና የሚሆን መገጣጠሚያ ሲጠፋ ከተመሳዩ ሞደፊክ ይሠሩለታል፡፡ ለመኪናው በሚመጥን እና በሚገጥም መንገድ ማለት ነው፡፡ እኛም ከውጭ የምናመጣቸውን ነገሮች ሞደፊክ ብንሠራላቸው መልካም ነው፡፡
እኛ ትክክል ወይንም ስሕተት የምንሆነው በራሳችን መመዘኛዎች እንጂ አውሮፓ እና አሜሪካ ባወጧቸው መመዘኛዎች መሆን የለበትም፡፡ በመሠልጠን እና በመሠይጠን መካከል ልዩነት አለ፡፡ እኛ ማከክ ያለብን እኛን የበላንን እንጂ አሜሪካውያንን ወይንም እንግሊዛውያንን የበላቸውን አይደለም፡፡ እነርሱም የበላቸውን እኛም የበላንን እንከክ፡፡ እነርሱ በሸተታቸው ቁጥር እኛ ማስነጠስ የለብንም፡፡ እኛ ራሳችን የሚያስነጥስ ሞልቶን የለ እንዴ!
እንደዚህ ዓይነት ተጽዕኖዎችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለመወጣት ማኅበረሰባዊ ውይይቶች መኖር አለባቸው፡፡ ለመሆኑ ግብረ ሰዶምን ኢትዮጵያውያን እንዴት ያዩታል? ይህንን ተንተርሰው የሚመጡ ተጽዕኖዎችን እንዴት መቋቋም ይቻላል? ብንቀበላቸው ወይንም ባንቀበላቸው ምን ይከሰታል? በየአጋጣ ሚዎቹ መወያየት ያስፈልጋል፡፡
እነዚህ የግብረ ሰዶማዊነት አቀናኞች በግልጽ ሊሄዱባቸው የሚችሉ መንገዶች የተዘጉ ከመሰሏቸው ውስጣዊ መንገዶችን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ መገመት አለብን፡፡ በኢንተርኔት፣ በፌስቡክ፣ በፊልሞች፣ ውስጥ ለውስጥ በሚደራጁ ቡድኖች፣ ከልዩ ልዩ ሀገሮች በሚሰጡ የውጭ ዕድሎች ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡
በአንዳንድ የአውሮፓ ሀገሮች በግብረ ሰዶም ምክንያት የሚጠየቁ የጥገኛነት ጥያቄዎች ፈጣን ተቀባይነትን ያስገኛሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ለጥገኛነት ሲሉ ወደዚህ ተግባር የገቡ ወገኖቼን አይቻለሁ፡፡ እነዚህ ወገኖች አንድ ጊዜ በዚህ መስክ የጥገኛነት ጥያቄ ካቀረቡ በየሀገራቱ በሚገኙ የግብረ ሰዶማውያን ተቋማት በኩል ተመዝግበው በርግጠኛነት ግብረ ሰዶማዊ መሆናቸው እንዲረጋገጥ ያደርጋሉ፡፡ እናም ከማይወጡበት አዘቅት ውስጥ ይገባሉ፡፡
እጅግ የሚያስፈራው ደግሞ በማኅበረሰባችን ውስጥ ያለውን ወንድማዊ እና እኅታዊ ቀረቤታ ወደ ግብረ ሰዶማዊ ቀረቤታ የሚለውጡ ሰዎች ብቅ ካሉ ነው፡፡ በኛ ባህል በወንዶች እና በወንዶች፣ በሴቶች እና በሴቶች መካከል ከወንድምነት እና ከእኅትነት ያለፈ ቀረቤታ አይታወቅም፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት እየተስፋፋ ከመጣ ግን ሴት ልጆቻችንን ከሴቶች፣ ወንድ ልጆቻችንንም ከወንዶች ለመጠበቅ ልንገደድ ነው ማለት ነው፡፡ እጅግ ከባዱ ደግሞ ይህንን ጉዳይ ለልጆቻችን ምን ብለን እንደምናስረዳቸው ነው፡፡
በልዩ ልዩ ተጽዕኖዎች ምክንያት ወደ ችግሩ ውስጥ ለገቡ ወገኖቻችንስ መፍትሔው ምንድን ነው? ማኅበረሰቡ የሚያወግዘው፣ ሕግም የሚከለክለው ጉዳይ መሆኑ ስለሚታወቅ እነዚህ ሰዎች ነገሮችን የሚፈጽሙት በድብቅ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ነገሩ እንደ ፍግ እሳት ውስጥ ለውስጥ እየተፋፋመ እንዲሄድ ያደርገዋል፡፡ የችግሩ ሰለባዎችም ከመወገዝ ያለፈ መፍትሔ አናገኝም ብለው በማመን የጀመረ ይጨርሰኝ ወደሚል ተስፋ መቁረጥ ይደርሳሉ፡፡
እናም እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ እንደሚባለው እንኳንስ አሜሪካ ግብረ ሰዶምን ካልደገ ፋችሁ አልረዳም ብላ ቀርቶ እንዲሁም ቢሆን ችግሩ ሥር እየሰደደ ነውና ከሁላችንም ሁሉን ዐቀፍ የሆነ መፍትሔ የሚሻ ነገር ነው፡፡







መላእክት ሎጥን ከከተማው ካወጡ በኋላ እግዚአብሔር
ሰዶምና ገሞራን በእሳትና በዲን አጠፋ የሎጥ ሚስት
የጨው ሀውልት ሆነች



ግብረ ሰዶማዊነት ስያሜውን ያገኘው ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ድርጊቱን በፈጸሙ ሕዝቦች አገር ስም ነው፡፡ ይህ ኃጢአት በተለይ በሰዶም ይበዛ ስለነበር ግብረ ሰዶም ተብሏል፡፡ ሰዶምና ጐረቤቷ ገሞራ በዮርዳኖስ ሸለቆ አካባቢ የተቆረቆሩ ከተሞች ነበሩ፡፡ በእነዚህ ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ተግባር ከሞራልና ከተፈጥሮ ሕግ የወጣ አስጸያፊ ስለነበረ እግዚአብሔር የቁጣ በትሩን አሳርፎባቸዋል፡፡ /ዘፍ. 18-20/ ሁለት መላእክት ሎጥን ከከተማው ካወጡ በኋላ እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን በእሳትና በዲን አጠፋ፡፡ ዘፍ.12-10-26፡፡ በነዋሪዎቿ ጥፋት በእሳትና በዲን የተለበለበችው ሰዶም ዛሬ ሕይወት አልባ በሆነው ሙት ባሕር ተሸፍና እንደቀረች ይነገራል፡፡




የቀድሞዋ ሰዶምና ገሞራ ከተማ የአሁኑ ሙት
(ጨው) ባህር -
The Dead Sea



በዘመነ ኦሪት ይህን ኃጢአት ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ የተገኙ ያለ ምንም ርኅራኄ እንዲገደሉ ታዟል፡፡ «ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋልና ፈጽመው ይገደሉ ደማቸው በላያቸው ነው» /ዘሌ.20-13/ ግብረ ሰዶማዊነት የተጠቀሰውን ዓይነት የከፋ ቅጣት ቢያስከትልም ሰዎች ድርጊቱን ከመፈጸም አልተቆጠቡም፡፡ እስራኤላውያን በተደጋጋሚ ከላይ የተጠቀሰው አምላካዊ ትዕዛዝ ቢነገራቸውም አጸያፊው ተግባር ግን በእነርሱ ዘንድ የተለመደ ነበር /መሳ. 19-22/ 
ይህ በቅዱስ መጽሐፍ የተግባሩ እኩይነት የቅጣቱ አስከፊነት በተጨባጭ የተነገረለት ግብረ ሰዶማዊነት ሳይቋረጥ የዘመናትን ድንበር ተሻግሮ ነውርነቱ እንደ መልካም ተግባር ተቆጥሮ በአራቱ መአዘነ ዓለም እየተፈጸመ ይገኛል፡፡ በተለይም በሥልጣኔ ወደፊት ተራምደዋል የሚባሉት ምዕራባውያን ድርጊቱን ከ1980ዎቹ አጋማሽ ጀምረው በምስጢርና በድብቅ መፈጸማቸውን ትተው ወደ አደባባይ ካወጡት ሰነባብቷል፡፡ የድርጊቱም ፈጻሚዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እጅግ እያሻቀበ መጥቷል፡፡ አንዳንድ ምዕራባውያን አገሮች በሕጋቸው ያጸደቁት ግብረ ሰዶማዊነትን እኩያን የሆኑ አንዳንድ የኪነ ጥበብ ሰዎች የኪነ ጥበብን ሙያ ለወሲብ ንግድ ማስፋፊያ በማዋል በፊልም በሲኒማ እየተወኑ በእርስ በእርስ ጦርነት፣ በረሐብ፣ በኤች አይ ቪ/ኤድስ ቁምስቅላቸውን ለሚያዩ አፍሪካውያን ጭምር እንካችሁ እያሉ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ምዕራባውያኑ ፈሪሐ እግዚአብሔርን አሽቀንጥረው ጥለው ሕጋዊ ዕውቅና በመስጠት ጭምር ገቢራዊ ያደረጉት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በእኛይቱ አፍሪካዊ አገር ደቡብ አፍሪካም ገቢራዊ እየተደረገ ነው፡፡ 
ግብረ ሰዶማዊነት ወደ አገራችን የገባው ለተለያየ ጉዳይ ወደ አገራችን በሚመጡ የወጭ አገር ዜጐች እና ለብዙ ዓመታት በምዕራቡ ዓለም ኑረው በተመለሱና በሚመለሱ አንዳንድ ኢትዮጵያውን ጭምር መሆኑን ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች የዚህ አጸያፊ ድርጊት ሰለባ የሆኑትና ሰለባ የሚያደርጉት ቀደም ሲል በእነርሱ ላይ ካለፈቃዳቸው በግብረ ሰዶማውያን ተገደው በመደፈራቸው በመሆኑ ይነገራል፡፡ በተለያዩ ጥቅማጥቅም በመታለል በተፈጸመባቸው ወሲባዊ ጥቃት የእነርሱን የሕይወት መስመር ለመከተል እንዳበቃቸው ከግብረ ሰዶማውያኑ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙ በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ ግብረ ሰዶማውያኑ ዛሬ በመዲናችን በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች ኅቡዕ ድርጅት በማቋቋም፣ በካፌዎች እና በተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች ድርጊቱን እያስፋፉ ይገኛሉ፡፡ 
ወደ ሀገራችን በእነዚህ ወገኖች ታዝሎ በገባው የግብረ ሰዶም ተግባር በተለይም ዕድሜያቸው ከ10-14 በሚደርሱ የጐዳና ተዳዳሪዎች፣ በአንዳንድ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እገዛ በሕፃናት ማሳደጊያ ማዕከል በሚኖሩ አዳጊዎች ላይ ሳይቀር ድርጊቱ እየተፈጸመባቸው ነው፡፡ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ሕፃናትንና ወጣቶችን ለማማለል የተለያዩ አደንዛዥ ዕፆችን፣ ከረሜላ፣ ቸኮላት መሳይ ማደንዘዣ፣ ጫት፣ አልኮል እና የሚጤስ ነገር በመጠቀም ካደነዘዙአቸው በኋላ ድርጊቱን ይፈጽሙባቸዋል፡፡ እንዲሁም ጐልማሶችን በተለያዩ መሣሪያዎች በማስፈራራት እንደሚደፍሯቸው አንድ የጥናት ወረቀት ያስረዳል፡፡ /በላይ ሐጎስ፣«ስeuቷለ Aue ቷነደ Eአፐለoፀተቷተፀo o ምቷለe ችሀፀለደረe ፀነ Aደደፀሰ Aበቷበቷ» 2007/
ዓለም በቴክኖሎጂ ምጥቀት ወደ አንድ መንደር እየተለወጠች በመምጣቷ በዓለም ላይ የሚከሰት ሠናይም ሆነ እኩይ ለሆነ ነገር ሁሉ አገራት ተጋለጭ ናቸው፡፡ ከአንድ አገር ወደሌላ በሚደረግ ዝውውር፣ የቴክኖሎጂ የኢንፎርሜሽን እና ከዚሁ ጋር አብሮ በተለያዩ መንገዶች በሚደረጉ የእኩይ ልማድ ልውውጥ ምክንያት የምዕራባውያንን ፈለግ ለመከተል ደፋ ቀና የሚሉ አንዳንድ ወገኖች በአገራችን ብቅ ማለታቸው እየተሰማ ነው፡፡ በመንፈሳዊ ሥነ ምግባር በፈሪሐ እግዚአብሔር እየተጓዘች በኖረችው አገራችን እንደዚህ ዓይነት ድርጊት ለመፈጸም የሚንቀሳቀሱ ሰዎች መነሳታቸው እጅግ ያሳዝናል፤ ያሳስባልም፡፡ በቅድስት አገር ኢትዮጵያ የድርጊቱ ፈጻሚዎች እንቅስቃሴ ከተሰማበት ወዲህ ድርጊቱ ያሳሰባት እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 13 ቀን 2001 ዓ.ም «ጋነፀተeደ ፈoረ ልፀፈe Eተሀፀoፐፀቷ» በተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት አስተባባሪነት «ግብረሰዶማዊነት መብት ወይስ የዝሙት ከፍታ ጫፍ» በሚል ርዕስ ከሃይማኖት ከባሕል፣ ከታሪክ እና ከሳይንስ አኳያ በአፍሪካ ኅብረት በመከረበት ወቅት ድርጊቱን በማውገዝ አቋሟን ገልጻለች፡፡ ከተላለፈው የአቋም መግለጫ የሚከተለው ይጠቀሳል፡፡ «በሀገራችን ሕገ መንግሥት ውስጥ እንደተመለከተው ጋብቻ ክቡር መሆኑን ለቤተሰብም ጥበቃ የሚደረግለት መሆኑን እና በሀገራችን ካሉ የሃይማኖት እሴቶች ተቃራኒ የሆኑ ጉዳዮች በማንኛውም መስፈርት ግብረሰዶማዊነት መብት ተደርጎ ተቀባይነት ማግኘት የማይገባው በመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ይህንን አውቆ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን፡፡» ይላል፡፡
በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 629 ግብረ ሰዶምና ለንጽሕና ክብር ተቃራኒ የሆኑ ሌሎች ድርጊቶች ድንጋጌዎች አሉት፡፡ ማንም ሰው ከእርሱ ጋር አንድ ዓይነት ጾታ ካለው ከሌላው ሰው ጋር ግብረ ሰዶም ወይም ለንጽሕና ክብር ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነውን ሌላ ድርጊት የፈጸመ እንደሆነ በቀላል እስራት ይቀጣል፡፡ ይኸውም በ630-631 ወንጀሉን የሚያከብዱ ሁኔታዎች ተዘርዝረዋል፡፡ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግም አንቀጽ 13 መሠረት ይህ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕግ የተከለከለ መሆኑ ተደንግጓል፡፡ ከሕግና ከሃይማኖት ከባሕል ከታሪክ አኳያ ድርጊቱ አስጸያፊ በመሆኑ መንግሥትም ቤተ ክርስቲያንም በጋራ ድርጊቱን መከላከል ይጠበ ቅባቸዋል፡፡



ግብረ ሰዶማዊነት ፈሪሐ እግዚአብሔር ተዘንግቶ ከሞራልና ከመንፈሳዊ ሥነ ምግባር ዝቅጠት የሚመነጭ እኩይ ተግባር በመሆኑ ምእመናንም ይህን ሕገ እግዚአብሔርን የጣሰ፣ ከሕዝቡ መልካም ባሕል፣ ማኅበራዊ ትስስር፣ መልካም ሥነ ምግባራዊ አመለካከትና እምነትን የሚቃረን ድርጊትና የድርጊቱን ተዋናዮችን አጥብቀው ሊኮንኑ፣ ራሳቸውንም ሆነ ልጆቻቸውን ጠብቀው በሕገ እግዚአብሔር ጸንተው ሊኖሩ ይገባል፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት የሥነ ምግባርና የሃይማኖት ሕግ ከመጣስም በላይ ከኢትዮጵያዊው ማኅበረሰብ ባሕልና አመለካከት ጋር በተቃርኖ የሚጋጭና ያልተለመደ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም ከጥንት ጀምሮ በሃይማኖት የምትታወቀው የሀገራችን ቀጣይ ትውልድ እና ሁኔታ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ግብረ ሰዶማዊነት በአገራችን እንዳይስፋፋ የበኩላቸውን ይወጡ እንላለን፡፡

የአኩሪ ባሕል ባለቤት እየተባለች የምትጠራው አገራችን በመልካም ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በፈሪሐ እግዚአብሔር የሚታወቀው ስሟ እንደተከበረ እንዲቀጥል፤ በምዕራባውያን እየተፈበረከ የሚላከው የእኩይ ባሕል ልውውጥ ቁጥጥር በማድረግ መንግሥትም የበኩሉን መወጣት አለበት፡፡ የነገይቷን ኢትዮጵያ እና ቤተ ክርስቲያንን ሊረከብ የሚችል ብቁ ዜጋ በአገራችን እንዲኖር መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሥነ ምግባር መምህራን፣ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ወገባቸውን ታጥቀው ማስተማር አለባቸው፡፡
መንፈሳዊ መነቃቃትን እያጐለበቱ የመጡ ወጣቶችም በዘንድሮ የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ እንደታየው ለሃይማኖታቸው ለመንፈሳዊ ሥነ ምግባር ቅድሚያ በመስጠት መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ማሳደግና ከእኩይ ተግባራት ራሳቸውን ማራቅ ይጠበ ቅባቸዋል፡፡ የምእመናንን ሕይወት በመንፈሳዊ ሥነ ምግባር ለመቅረጽ «በጐቼን ጠብቅ» የሚለውን የአደራ ቃል ከአምላክ የተቀበሉ አባቶች ካህናት ለንስሐ ልጆቻቸው ግብረ ሰዶማዊነት ሊያስከትል ስለሚችለው መንፈሳዊና ሞራላዊ ክስረት አበክረው ቢያስተምሩ ግብረ ሰዶማዊነትን ሳይርቅ ከቅርቡ ሳይደርቅ በእርጥቡ መከላከል ይቻላል፡፡
በአንዲት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ታቅፈው የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፤ በመንፈሳዊ መርሐ ግብራቸው ላይ «ግብረ ሰዶማዊነት» ከጥንት ጀምሮ እስከ ዛሬ እያስከተለ ያለውን የሞራልና የመንፈሳዊ ሕይወት ዝቅጠት በተመለከተ ትኩረት ሰጥተው ማስተማር አለባቸው፡፡
ሠልጥነናል የሚሉት ምዕራባውያን «ግብረ ሰዶማዊነትን» የሰብአዊ መብት ጥያቄ አድርገው ስላቀረቡ የእነርሱን ድምፅ እንደ ገደል ማሚቱ በሀገራችንም እንዳያስተጋባ ከእያንዳንዱ ቤተሰብ ጀምሮ የሚመለከተው አካል ሁሉ ከወዲሁ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል እንላለን፡፡ ለነገው ትውልድ የምትጨነቅ እናት ቤተ ክርስቲያንም ግብረ ሰዶማዊነትን፣ በአጠቃላይም የመንፈሳዊ ሥነ ምግባር መርሆዎችን የሚፈታተኑ ተግባራትን የማውገዝና የማስተማር ተግባሯን አጠናክራ መቀጠል አለባት፡፡





የእኛ ድርሻ ምንድን ነው ?  ?  ?


ሃገር በሰዶም እሣት እንዳትቃጠል  ግዜው ጾም በመሆኑ እስኪ እንጸልይ እስኪ ይህን እያሰብን እንጹም!    

ነብዩ ኤርሚያስ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል የተባለው ነብዩ ኤርሚያስ የእየሩሳሌምን ቅጥር መፍረስ አይቶ እንዲህ አለ፦

ጸሎታችን ወደ አንተ እንዳያርግ አንተ ራስህን
በደመና ሸፈንክ!
                የእንባ ጉርፍ በዐይኔ ፈሰሰ፤  ሰቆ.ኤር. 3:44

ነብዩ ኤርሚያስ ጸሎታችን ወደ አንተ እንዳያርግ አንተ ራስህን በደመና ሸፈንክ ሲል እግዚአብሔርን ደመና የሚሸፍነው ሆኖ ሳይሆን ጸሎታችን እንዳያርግ ደመና የሆኑትን ፍቅር ማጣትን ፣ መለያየትን ፣ ኀጢአትንና ሌሎች ብዙ ደመናዎችን ሲነግረን ነው።  ከነዚህ ደመናት ፩ዱ ይህ ግብረ ሰዶም ነው።

ነብዩ ነህምያ በስደት ሃገር የንጉስ አስተናጋጅ ሆኖ በቤተመንግስት የሚኖረውና የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ያጽናናል የተባለው ነብዩ ነህምያም እንዲሁ የእየሩሳሌም ቅጥር መውደም ፣ ቤተመቅደሱ መፍረሱን ሕዝቡ መማረኩን በሰማ ግዜ እንዲህ አለ ይህንንም ነገር በሰማሁ ግዜ ተቀምጬ አለቀስኩ”፤ በሰማይም አምላክ ፊት አያሌ ቀናት ዐዘንኩ
ጾምሁ ጸለይኩ ነህምያ. ፩:፬
የ፪ቱን ነብያት እንባ በእግዚአብሔር ፊት ሊያሳርግ ፩ድ መልአክ በእግዚአብሔር ፊት ቆመና እንዲህ አለ፦ የሰራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ እነዚህን 70 ዓመት የተቆጣሃቸውን የኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ድረስ ነው” ብሎ ለመነ፤ እግዚአብሔርም የመልአኩን ምልጃ ሰማና በሚያጽናና ቃል መለሰለት፦ በምሕረት ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ ቤተ መቅደሴም ከንደገና ያሰራል፤ የሰላምን ገመድ በኢየሩሳሌም አደርጋለሁ”።  ዘካርያስ 1:12-14።
ጾም ጸሎታችን ደመና የምታልፍና የምትሰማ ያድርግልን አሜን።


የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጎብኘን ፤ በምህረቱ ይማረን አሜን ፡፡





 [የዲያቆን ዳንኤል ክብረት  እይታዎች + የአንድ ታናሽ ሰው እይታ]