Monday 20 August 2012

==> “የዛሬ አበባዎች የነገ ጥሬዎች”<==



ዘና ብላችሁ ተቀመጡና አንድ ታሪክ ላጫውታችሁ!



ከራሴ ጋር አጠር ያለች ስብሰባ አደረኩና አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ። ሰው በሞተ ቁጥር የሰፈሩ ሰው እትዬ ጣይቱን እድር ይግቡ እንጂ ብለው ሲመክሯቸውእዲያ በሕይወት እያሉ ሳይረዳዱ ቀባሪን ለሚያበላ እድር ምን አስጨነቀኝይሉ ነበር። የእድሩ ዳኛምጉድ መጣ ገንፎ ዛፍ ላይ ወጣ! የኛ
 ፈረንጅ!!” ብለው ሰዎች እንዲያግዟቸው በረጅሙ ሳቁ። እትዬ ጣይቱም ፈረንጅ እድር አለው እንዴ? ብለው ጠየቁ። የሚመልስ ሰው ግን አልተገኘም።እናንተን ማስረዳት ቀባሪን ማርዳት እንዳይሆንብኝ እፈራለሁአሉ እትዬ ጣይቱ የእድር ዳኛውን በቆረጣ እያዩ። በአባባላቸው ሰው ሁሉ ሳቀ።ማረኝ እንጂ አትመመኝ አይባልምይሉ ነበር እትዬ ጣይቱ። እውነታቸውን ነውኮ።ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ ነው መጨነቅአሉ እትዬ ጣይቱ! 

መቼስ የእትዬ ጣይቱ ጨዋታ አይጠገብም። በጨዋታቸውና በሙያቸው የተመሰከረላቸው ናቸው። እንዲያውም የእትዬ ጣይቱን ምግብ በልቶ ማን እጁን ይታጠባል ይባልላቸዋል። ዛሬም ምርጥ ምርጡ በየዓይነቱ ጠረጴዛው ላይ ተደርድሯል። እትዬ ጣይቱ አንድያ ልጃቸውን ኤፍራታን ጠሩና እኔ በልቻለው አቅርቡና አብራችሁ ብሉ አሏት። ኤፍራታም ኧረ አልራበንም በኋላ እንበላለን አለች። ጉድ እኮ ነው የሱን ሆድ መች አየሽው? አሉ እትዬ ጣይቱ። አባባላቸው አሳቀኝ።ከአንድ ብርቱ ሁለት ገልቱእስኪ አንድ ላይ ብሉ ብለው በየዓይነቱን አቀረቡልን። እትዬ ጣይቱ ምሳሌያዊ ንግግራቸውን አገለባብጠውት እያዝናኑ ስለሚያስተምሩ እወዳቸዋለሁ።ነገር በብርሌ ጠጅ በምሳሌአሉ እትዬ ጣይቱ! ዛሬ እትዬ ጣይቱ የነገሩኝ ታሪክ ይህ ነው፦

በአንድ ወቅት የእትዬ ጣይቱ ባለቤት አቶ ይድነቃቸው ገበሬዎች ከሚዘሩት ከአፈር ጋር የተቀላቀሉትን ጤፍ ሰበሰቡና ወቀጡት። ይህን ጊዜ ንጹህ ጤፍ ከአፈሩ ተለየ። አቶ ይድነቃቸው ይህን ጤፍ በሁለት ብር ሸጡና ዶሮ ገዙ። ዶሮውን አስታቅፈው ብዙ ጫጩቶችን አገኙ። ሲቀጥልም ዶሮውን በአምስት ብር ሸጡና በግ ገዙ። አቶ ይድነቃቸው ሰው ሁሉ እስኪደንቀው ድረስ በጉን አደለቡት አሰቡት። የሰባውን በግ ሸጡና አነስተኛ የእርሻ መሬት ገዙ። ሰው ሁሉ በአቶ ይድነቃቸው ተደነቀ። ከዛማ የእርሻ ምርቱ እንደ ጉድ ተስፋፋ። አቶ ይድነቃቸው የብዙ በጎች የብዙ ዶሮዎች የብዙ እንስሳት ባለቤት ባለሀብት ሆኑ! ሰው ሁሉ ስለተደነቀባቸውአቶ ይድነቃቸውየሚል ስም ወጣላቸው። ከጤፍ ፍርፋሪ የተከበሩ ባለሀብትም ሆኑ። አቶ ይድነቃቸው ድል ያለ ሠርግ ደግሠው እትዬ ጣይቱን አገቡ። አንድያ ልጃቸውን ኤፍራታንም ወለዱ።


በአቶ ይድነቃቸው የእርሻ ካምፓኒ ብዙ ገበሬዎች ተቀጠሩ። ከገበሬዎቹ መካከል አንዱ በጎቹን እየተንከባከበ ያደልባቸው ነበር። በጎቹ ቢታዩ ለዓይን የሚማርኩ ቢበሉ ለምላስ የሚጣፍጡ ሆኑ። አቶ ይድነቃቸው እጅግ ተደነቁና ይህን ገበሬ አስጠሩት። ገበሬውም ለጥ ብሎ እጅ ነሳናመጥቻለሁ ጌታዬአለ። አቶ ይድነቃቸውም ታታሪው ገበሬ ሆይ ስራህ ድንቅ ነው! በጎቹን በሚገባ ተንከባክበሃልና! በጣም የሚገርመኝ ግን በጎቹን ትቀልባቸዋለህ ታደልባቸዋለህ እንጂ ምን አወቁ? ሃይማኖታቸው ምንድን ነው? አትልም። ዛሬም ወላጆች ለልጆቻቸው ወተት ብቻ ምግብ ብቻ መግበው ስለ ሃይማኖታቸው ስለ አስተሳሰባቸው ካልተጨነቁ በግ አደለብን እንጂ ልጅ አሳደግን ማለት ከቶ አይችሉም! ልጆች ምን አወቁ? ምን ያስባሉ? ብለው ካልጠየቁ እውነትም በግ እያደለቡ ነው! አሉ እትዬ ጣይቱ ገና በጠዋቱ። እኔና ኤፍራታም በአባባላቸው ሳቅን።

እትዬ ጣይቱ አያችሁት ያን ልጅ? አሉ ድንገት ወደ ጓሯቸው እየተመለከቱ። በግ ለልጅዋ ወተት ስትመግብ አንድ ትንሽ ልጅ በጉልበቱ ተንበርክኮ ጎንበስ ብሎ አተኩሮ ይመለከት ነበር። ለሚያየው ሰውእኔም ወተቱን ባገኘሁትየሚል ይመስል ነበር። ኤፍራታ ቶሎ ብላ በያዘችው ሞባይል ፎቶ አነሳችው። ኤፍራታ በሳይንስ የተማረችውን አስታወሰችናእናት ለልጅዋ በመጀመሪያ የምታጠባው ወተት ማለትም እንገር /colostrums/ የሚባለው ለሕጻኑ ጤንነትና እድገት እጅግ ወሳኝ ነውአለችን። ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች ሳይሆንየዛሬ አበባዎች የነገ ጥሬዎችእንዳይሆኑ ማሰብ ያስፈልጋል አሉ እትዬ ጣይቱ አንድያ ልጃቸውን ኤፍራታን በስስት እያዩ። 

No comments: