Monday 20 August 2012

“ፕሮፌሽናል ለማኝ”




አንዱ ከተሜ አዲስ አበባ ለጉዳይ ይመጣል፡፡ ሲዘዋወር ቆይቶ ይደክመውና ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዐረፍ ለማለት ይገባል፡፡ በጣም ደክሞት ስለነበር አንዱ ዛፍ ሥር ጥቅልል ብሎ ይተኛል፡፡ ሲነሣ የሆነው ነገር የሕይወቱን መሥመር አስቀየረው፡፡

ከዕንቅልፉ ሲነሣ በዙርያው ብዙ ብሮችና ሳንቲሞች ተዘርግተዋል፡፡ እየገረመው ዘወር ዘወር ብሎም እያየ ቆጠራቸው፡፡ አሥራ ስምንት ብሮች ተሰባስበዋል፡፡ እርሱ በወር የሚያገኘው ሦስት መቶ ብር ነው፡፡ አሁን ምንም ሳይለፋ አሥራ ስምንት ብር አገኘ፡፡ ታድያ ለምን ጥቂት ጊዜ አልሠራም አለና ጀመረው፡፡ «ይኼው ዓመት ሆነኝ፡፡ አሁን አዋሳ ቤት እየሠራሁ ነው» አለና
ገረኝ፡፡ እንደዚህ ልጅ ልመናን ቀላል የገንዘብ ማግኛ መንገድ እድርገውት የተሠማሩ «ፕሮፌሽናል ለማኞች» ሞልተዋል፡፡

ፕሮፌሽናል ለማኞች እንዳሉ ኹሉ መረዳት ያለባቸውም ድኾች አሉ።

አንድ ሸረፌ የሚባል ባለጸጋ ነበር። ሹሙን ጠርቶ በቀን በቀን ፩ድ ወቄት ዱቄት ለድኾች ሳትሰጥ አትዋል አለው። ቢሰጥ እየበዛ ሔደ። ከበዛስ ብሎ ከታዘዘው አብልጦ ወቄት ዱቄት ይሰጥ ዠመር። ባለጸጋው ከቤተ መዛግብቱ ቢገባ ንብረቱ በዝቶ አገኘው። ሹሙንም ያዘዝኹህን ትተሃል እንዴ? ሲል ጠየቀው። ሹሙም እንዲያውም አብልጬ ሠጠኹ አለው። እንግዲያው አትገምግም እጅህ እንዳነሳ ስጥ ብሎታል። 

የተቸገረ ብታይ ከንፈር ከመምጠጥ የቻልካትን ትንሿን አድርግለት! ሐዋርያውበሥራና በምግባር እንጂ በቃል ብቻ አንዋደድእንዲል ለድኾች የቻልነውን እንስጥ! በየበዓላቱ ዶሮ በማይጮኽበት ጢስ በማይጤስበት ቤት ያለችንን አካፍለን እንብላ! ትዝ ይለኛል ልጅ እያለኹ ዓመት በዓል በኾነ ጊዜ ከክፍል ጓደኞቼ ጋር ዶሮ እያሰራን ለድኾች እናበላ ነበር።

Visit this Blog! http://yonas-zekarias.blogspot.com/
— with Beza Worku and Teshager Ayalneh.
 ·   ·  · Share · Edit
·                                  
·                                
·                                 72 shares
·                                  
o                                                       
Sintayehu Demoz YONAS ! Meliakitih Des Sil Tikikil Neh Meredadat Kenifer Bememetei Sayhon Betegibar Bemasayet Enije . EGIZIABIHER Yibarikih.
May 26 at 9:30am ·  · 3
o                                                       
Lilly Guthaun Kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk
o                                                       
Alemu Enyew kkkkkkkkkkkkkk
May 26 at 11:26am ·  · 1
o                                                       
Tina Taye EGZIABEHIR ybarikih
May 26 at 10:09pm ·  · 1
o                                                       
Atenasia Yohannes መረዳት የሚገባውን በቻልነው መጠን እንጐብኝ፡፡
·                                

No comments: