Tuesday 30 July 2013

//ኦርቶዶክስ ተዋህዶ//



ሐዋርያው ደም ሳይፈስ ስርየት የለም ይላል! የክርስቶስ ደም የአምላክ ብቻ ነው ከቶ አንልም። ከእመቤታችን የነሳው እንደሆነ እናውቃለንና መለኮትም ደም የለውምና። ድህረ ተዋህዶ የክርስቶስ ደም የሰው ብቻ ደም ነው አንልም። ይህ የከበደ ክህደት ነውና! የሰው ደም አዳነኝ ማለት ነውና፣ የሰው ደም ሲዖልን ከፍቶ ፍጥረት ሁሉ የዘላለም ሕይወት አገኘ የሚል ማን ነው? በአጭሩ ቃል ሥጋ ሆነ ማለት ቃል ወደ ስጋ ተለወጠ ማለት ነውን? በተዋህዶ ቃል ሥጋ ሆነ ! እንግዲያውስ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም የአምላክ ነው ወይስ የሰው? ብዙዎች መመለስ አልቻሉም። ተዋህዶን ስለማይቀበሉ በእርግጥ መልስ የላቸውም። በተዋህዶ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ደም አዳነን!

ፕሮቴስታንት ዘመዶቻችን ቃልና ሥጋ አልተዋሃደም ብለው ያምናሉ። ቃል ራሱን ጠብቆ ቃል ነው፣ ሥጋም ራሱን ጠብቆ ሥጋ ነው ይላሉ። ከክርስቶስ ልደት በፊት ቃል ነበረ፣ ክርስቶስ ሲወለድ ቃል ነው እንጂ ሥጋን አልተዋሃደም ይላሉ፣ ከክርስቶስ ዕርገት በኋላም ቃል ነው ብለው ያምናሉ። ታድያ ቃል ሥጋ የሆነው መቼ ነው?

No comments: