Wednesday 31 July 2013

ሞኝና ውኃ እንደወሰዱት ይሄዳል አሉ!



በመጽሐፍ ቅዱስ ልቤን የሚነካ አንድ ታሪክ አለ። በሉቃስ ወንጌል የጠፋው ልጅ ታሪክ ደስ ይላል። ሞኝና ውኃ እንደወሰዱት ይሄዳል እንዲሉ ጓደኞቹን ሰምቶ ከአባቱ ቤት ወጣ። ጠፍቶ አልቀረም አባቱ ቤት ገባ! ጠፍተን ያገኘን በቤቱም ያስገባን ቸር አባታችን ክብር ለእርሱ ይሁን! 

ወደ ጥያቄ እንግባ፦

ሉቃስ ወንጌል 15

4 መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?
5 ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፤
6 ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ። የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል።
7 እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።
8 ወይም አሥር ድሪም ያላት አንድ ድሪም ቢጠፋባት፥ መብራት አብርታ ቤትዋንም ጠርጋ እስክታገኘው ድረስ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት?
9 ባገኘችውም ጊዜ ወዳጆችዋንና ጐረቤቶችዋን በአንድነት ጠርታ። የጠፋውን ድሪሜን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ትላቸዋለች።
10 እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።

ፕሮቴስታንት ዘመዶቻችንን ጥያቄ እንጠይቅ፦

/1/ ኢየሱስ ክርስቶስ ((ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን)) ንስሐ በሚገባ ((በአንድ ኃጢአተኛ)) በሰማይ ደስታ ይሆናል ብሏል። ፕሮቴስታንት ዘመዶቻችን ደግሞ ሁላችንም ጻድቃን ነን ትላላችሁ፤ ጌታ እንዳለው ከመካከላችሁ ንስሐ የማያስፈልገው ጻድቅ ማን ነው?

/2/ ሁላችንም ጻድቃን ከሆንን ((ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ)) ንስሐ በሚገባ ((በአንድ ኃጢአተኛ)) በሰማይ ደስታ ይሆናል ማለት ምን ማለት ነው?

/3/ ክርስቶስ እንዳለው ንስሐ የማያስፈልጋቸው 99 ጻድቃን እነማን ናቸው? ንስኃ የማያስፈልጋቸው ለምንድን ነው? ንስኃ የሚያስፈልገው አንድ ኃጥዕ ማን ነው?

No comments: