Sunday 7 July 2013

ይድረስ ለፕሮቴስታንት ዘመዶቻችን ፬



ሰላም ለሁላችን ይሁን! ከመልስ በኋላ ማብራሪያና ጥያቄ የመጠየቅ መብታችሁ እጅግ የተጠበቀች ናት!! እነሆ ጥያቄው ተጀመረ፦ 

/1/ ኃጢአትን ይቅር የሚል እግዚአብሔር አይደለምን? 

አንድ ወጣት በዝሙት ቢወድቅ አባቶች ጋ ሄዶ ንስኃ ይገባል። ካህናቱ ጸልየው ኃጢአቱ ትሰረዛለች! ካህናት ይጸልዩለት ኃጢአት ሰርቶም ከሆነ ይሰረይለታል እንዲል ያዕቆብ 5 ፦13 የሰው ልጅ ኃጢአትን ለማስተሰረይ ሥልጣን እንዳለው ታወቀ ማርቆስ 2 ፦10 አሁን እስኪ ጥያቄ እናስከትል፦ የሰዎችን ኃጢአት ይቅር ብትሉ ኃጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል፤ ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ ግን ይቅር አይባልላቸውም! ማለት ምን ማለትነው? ሉቃስ 20፦23

/2/ አንዷ እህቴ //አቡነ አረጋዊ ባርኩን// የሚል ፖስት ስትለጥፍ ሰከንድ ባልሞላው ጊዜ ከአንድ እህታችን እንዲህ የሚል ተቃውሞ መጣ፦ ማን ናቸውና? በረከት ከእግዚአብሔር ብቻ ነው ተማሪ እሺ ተባረኪ። ብላ መለሰችላት። ራስዋ ባራኪ ሆና ጻድቁ ግን ባራኪ አይደለም ማለትዋ ገረመኝ። ሁል ጊዜ ተባረኩ ትሉናላችሁ ። አንዱን ቅዱስ ባርከን ብንል ስህተት ነው? መፅሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

/3/ ከእኔ አብ ይበልጣልና፡፡ ዮሃ14፡28 አብ ከክርስቶስ ይበልጣል ማለት ነው? ካልተበላለጡ ከእኔ አብ ይበልጣል ለምን ተባለ?

/4/ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያቱ ወረደ ማለት ምን ማለት ነው? በአካል ለሐዋርያቱ ወረደ ማለት ነው?

No comments: