Sunday 7 July 2013

ይድረስ ለፕሮቴስታንት ዘመዶቻችን ፫

/1/ 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፦1 ልመና ጸሎትና ምልጃ ለነገሥታትና ለባለስልጣናት እንዲደረግ አሳስባለሁ እንዲል ባህረ ጥበብ ቤተክ በቅዳሴ ላይ ለነገሥታቱ ለባለስልጣኑ ወዘተ እንማልዳለን ትላለች። እናንተስ ምልጃ ታቀርባላችሁ? እናንተ ምልጃ ካቀረባችሁ /ካማለዳችሁ/ ወዲያው ክርስቶስም ካማለደ ልዩነቱ ምን ይሆን? አቤሜሌክ ሲበድል ወደ አብርሐም ሂድ ተባለ ! የኢዮብ ጓደኞች ሲበድሉ ወደ ኢዮብ ሂዱ ተባሉ! ይህ በአዲስ ኪዳንም ተላልፏል። ኤልሳዕ ግያዝን እንዳየ ጴጥሮስም ሐናንያን እንዳየ ሁሉ ይህ በአዲስ ኪዳንም ያለ ነውና! የማስታረቅንም ቃል በእኛ ላይ አኖረ እንዲል 2ኛ ቆሮ 5፦20 በዘመነ ሐዋርያት ቅ/ጳውሎስ ካስታረቀ ወዲያውም ኢየሱስም ካስታረቀ ልዩነቱ ምንድን ነው?
/2/ እንዲጸለይላችሁ የምትፈልጉ ኑ እንጸልያለን ትላላችሁ። አንዱ ላንዱ መጸለይ ልክነውና አንቃወምም። ሆኖም ከእናንተ አንዱ ፓስተር አጋንንት እንዲወጣለት ጸልዮ ካማለደ ወዲያውም ክርስቶስ ካማለደው ልዩነቱ ምንድን ነው? /የሞኝ ጥያቄ ቢሆንም ምስጢር አለውና ለመመለስ ሞክሩ/
/3/ አንዳንዶች እንደሚሉን ወልድ በብሉይ ጊዜ መልአክ ነበር! እስራኤላዊያንን በበረሃ የመራው መልአክ ክርስቶስ ነበር ብላችሁ ልባችንን አስደንግጣችኋል። ክርስቶስ መልአክ ነበር? ካልሆነ ራዕይ 8 ላይ መልአኩ ፀሎት አሳርጓልና መላዕክት ፀሎታችሁን እንደሚያሳርጉ ታምናላችሁ?
/4/ እስራኤላዊያን ከግብፅ ባርነት የወጡት ለአብርሐም ለይስሐቅ ለያዕቆብ በገባላቸው ቃል ኪዳን ነው ብዬ አስባለሁ። ደጋጎቹ አባቶች ቢሞቱም ለነሱ በገባው ቃል ኪዳን ምክንያት ሕዝቡን ጠላታቸውን ድል አደረገላቸውም ብዬ አምናለሁ። በሐሳቤ ትስማማላችሁ ወይስ የሚቃወም አለ? ዘዳግም 77* ፱
/5/ ስለ ቅዱሳን በትጋት ለምኑ ይላል ኤፌሶን 6 ፦18 ፓትርያርክ መሆን ከባድ ፈተና ነው የጴጥሮስ ሥልጣን ነውና። ዲያቆን መሆን ከባድ ናት የቅ/እስጢፋኖስ ሥልጣን ነውና! ስለነሱ የፈረደ ሳይሆን ልመና ያቀረበ ማን ነው? ስለ ቅዱሳን በትጋት ለምኑ ይላልና ለቅዱሳን ትለምናላችሁ? እናንተ ከለመናችሁ ክርስቶስም ከለመነ ልዩነቱ ምንድን ነው? /በተደጋጋሚ እንደተተጠየቀው ለአንዱ መጸለይ እንዲማር መለመን ይቅር እንዲባል ነውና ማማለድ እንደሆነ መታወቅ አለበት። ኢዮብ ጸልዮ ሦስቱን ጓደኞቹን ካስማረ አማለደ ማለት ግልጽ ነውና!/

No comments: