Sunday 7 July 2013

ይድረስ ለፕሮቴስታንት ዘመዶቻችን! ፭



ሰላም ለሁላችን ይሁን! ((ከመልስ በኋላ)) ማብራሪያና ጥያቄ የመጠየቅ መብታችሁ እጅግ የተጠበቀች ናት!! እነሆ ጥያቄው ተጀመረ፦

/1/ አንዳንዶቹ "አንድም እንኳን ጻድቅ የለም ሁሉም በድሏል" ይላሉ። "ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ያገኛል" ስንላቸው ደግሞ እዚህች ጋ ቀልድ የለም እኛም ጻድቅ ነን ይላሉ። ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ብለን ለሕሊናቸው አሳልፈን እንስጥ። መልካም "ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ያገኛል" ማለት ምን ማለት ነው? እንዳላችሁን እኔም ጻድቅ ስለሆንኩ እኔን ብትቀበሉ የኔን ዋጋ ታገኛላችሁ ማለት ነው?

/2/ ለደቀመዝሙሬ ቀዝቃዛ ውኃ የሚያጠጣ ዋጋው አይጠፋበትም!

ሁላችንም ደቀ መዝሙር ነንና ለዚህ ሁሉ ሰው ቀዝቃዛ ውኃ ላጠጣ ነው ሞኝ መሰልኳችሁ ትላላችሁ። መልካም ። ይህን መጠየቅ ያለባችሁ እኛን ሳይሆን የቃሉ ባለቤት ክርስቶስን ነበር። ልብ አላላችሁም እንጂ ራሳችሁ መልሳችሁት ነበር። በዮናስ ስም ቀዝቃዛ ውኃ እናጠጣ ማለት ነው? በሰውነት ቢሻው በኃይሌ ገ/ሥላሴ በጌታነህ ከበደ ስም ቀዝቃዛ ውኃ እናጠጣ ማለት ነው? የመፅሐፍ ቃልን ማጣመም አይገባምና እንግዲያውስ ምን ይሻለናል? ሁላችንም ደቀመዝሙር ከሆንን እርስ በእርስ ቀዝቃዛ ውኃ እንገባበዝ? ወይስ መፍትሄው ምንድን ነው?

/3/ የመፅሐፉን ቃል የምትፈጽሙት መቼ ነው? ደቀ መዝሙር የምትሉት ማንም ይሁን ማን ለደቀ መዝሙር ቀዝቃዛ ውኃ የምትሰጡት መቼ ነው?

/4/ ለደቀ መዝሙር የተባለውን ለመላዕክት ለምን ታደርጋላችሁ ብላችሁ አኩርፋችኋል። መላዕክት ደቀ መዝሙር ናቸው? ወዘተ ተረፈ ብላችሁ ጠይቃችኋል። ማኑሄ ለመላዕኩ ያልከው ቃል ሲፈጸም እንድናከብርህ ስምህ ማን ይባላል ማለቱን ልብ በሉ! በደቀ መዝሙር ስም ቀዝቃዛ ውኃ ከተሰጠ በመላዕክቱ ስም ቀዝቃዛ ውኃ መስጠት ችግሩ ምንድን ነው? ዋናው ሐሳቡ ትክክል ነው ወይ? ብሎ መጠየቅ ነበር። ነቢያትንና ደቀ መዝሙሬን አክብሩ መላዕክቱን ናቁ የሚል አምላክ አለ?

/5/ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢዩን ዋጋ ያገኛል ማለት ምን ማለት ነው? ሁላችንም ነቢይ ነን?

No comments: