Saturday 26 November 2011

“The Honour & the Gifts of Righteous in the Bible” // “ክብረ ቅዱሳን በመፅሐፍ ቅዱስ”

“The Honour & the Gifts of Righteous in the Bible”

ክብረ ቅዱሳን በመፅሐፍ ቅዱስ”



በመፅሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ስለ ፃድቃን እየደጋገመ ይመሰክራል እነሆ ለበረከት፦

v   ነብዩ ኤልያስና ኤልሳዕ፦  ታላቁ ነብይ ኤልያስና
    ደቀመዝሙሩ ኤልሳዕ እግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ሰቷቸው ታላቅ ተዓምራትን ይሰሩ ነበር ፤ ኤልያስ የሰራብታዋን ልጅ ከሞት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ደግሞ የሱናማዊቷን ልጅ ከሞት አስነሳ       በመፅሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ግዜ የሞተን ያስነሳው ታላቁ ነብይ ኤልያስ ነው። ነብዩ ኤልሳዕ ደግሞ በህይወት እያለ የሱናማዊቷን ልጅ ከሞት አስነሳ; ከሞተ በሗላ ዓፅሙ የሞተውን ቢነካው የሞተው ተነሳ! 2ኛ ነገስት 13:21 
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ; በአካለ ሥጋና በአካለ ነፍስ ያሉ; ከፈጣሪ አማልደው ምህረት ያሰጣሉ”



v   ደጉ አብርሐምና ፃድቃን፦ ደጉ አብርሐም ሰዶም እንድትማር ለመነ፤ 50
ጻድቃን በፊትህ ቢገኙ ስለፃድቃን ስትል ለከተማይቱ ምህረት ታደርጋለህን? ብሎ ተማጸነ; ጌታም ምህረት እንደሚያደርግ ነገረው፤ ከተማይቱ በጻድቃን ደህይታ እንዃን 50 ቀርቶ 5 ጻድቅ ታጣ። የጻድቃን ደሃ ሃገርም አገኛታ መከራ። ዘፍ 18:22
* ስለ አብርሐም የሠራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ እኔ የማደርገውን ነገር ከአብርሐም እሰውራለሁን?” ዘፍ. 18:17
* ንጉስ አቤሜሌክ የአብርሐምን ሚስት ሲወስድ ከጥፋትህ ተመለስ እኔም እምርሃለሁ ማለት ሲችል ለአቤሜሌክ እግዚአብሔር እንዲህ አለው ነብይ ነውና ይጸልይልሃል አንተም ትድናለህ ዘፍ20:7; ኢዮብን ጓደኞቹ ቢያሳዝኑት እግዚአብሔር ለኢዮብ ጓደኞች /በልዳር ሳፎርና ኤልፋዝ ለተባሉት ጓደኞቹ / እንዲህ አላቸው ነብይ ነውና ይጸልያል እኔም ጸሎቱን እቀበላለሁ ኢዮብ42:7። ባለቤቱ እግዚአብሔር ጸሎቱን እቀበላለሁ እያለ መናፍቃኑ አትቀበልም ካሉ ከሰው ጋር ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር መከራከር ይሆንባቸዋል።  

v   ነብዩ ሙሴና ጻድቃን፦ ነብዩ ሙሴ ከሲና ተራራ ላይ የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዞ
ሲወርድ እስራኤላዊያን ጣኦትን ያመልኩ ነበር; እስራኤል ዘሥጋ ፍቁረ ጣኦት ብዙ ግዜ ስላሸነፋቸው እግዚአብሔር ለሙሴ ይህ ህዝብ አንገተ ደንዳና ነውና አንተን በሌላ ሕዝብ ላይ እሾምሃለሁ አለው; ሙሴ ምን አለ ሕዝቡን ከምታጠፋ ስሜን ከህይወት መጽሐፍ ደምስስ” [ዘፀ 32:32] ዳዊትም በመዝሙሩ “የተመረጠው ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ባይቆም ኖሮ እስራኤላዊያንን ባጠፈቸው ነበር አለ” መዝ 105:23። በፊቱ ባይቆም ኖሮ ማለቱ ቀጥ ብሎ መቆም ሳይሆን የሙሴን ታላቅ ልመና ለመግለጽ ነው። እግዚአብሔርም ለህዝቡ ምህረት አድርጎ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈበት ታቦት ለሙሴ በድጋሚ ተሰጠው።
* ሙሴንና አሮንን ተቃወመው ራሳቸውን እንደካህን የቆጠሩ ቆሬና 250 ሰዎች በአንድ ቀን በእሳት ተቃጥለው ሞቱ; እነሱን የተባበሩ ዳታንና አቤሮን ደግሞ ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው። ዘሁልቅ 16:31-36 ፤ ሲነጋም እስራኤላዊያን ህዝቡን አስገደላቹ ብለው በድንጋይ ሊወግሯቸው ተነሱ; ሙሴና አሮን ወደ ደብተራ ኦሪት ሸሹ። እግዚአብሔርም አምደ ብርሐን ከልሎ አዳናቸውና ሁለቱን ወንድማማቾች ከእስራኤላዊያን ማህበር ፈቀቅ በሉ; በቅስፈት አጠፋቸዋለሁ ብሎ በአንድ ቀን 14ሺ 700 ሰዎች ሞቱ። አሮን ልብሰ ተክህኖ ለብሶ ማዕጠንተ ወርቁን ይዞ ቢጸልያላቸው መቅሰፍቱ ተወገደ ዘሁ.16:41
*የተመረጠው ሙሴ በፊቱ ባይቆም ኖሮ በመቅሰፍቱ ባጠፋቸው ነበር ይላል; መዝ 105:23።
(ማክበር ለበረከት አለማክበርም ለመቅሰፍት ነውና)
/ቀጣዩን ገጽ ይመልከቱ/
*ነብዩ ኤልያስን አላከብር ያሉት ሁለት የ50 አለቆች በነብዩ ጸሎት ከሰማይ በወረደች እሳት ተቃጥለው ሞቱ። 2ኛ ነገ. 1:9

* የሙሴ ወንድም አሮንና እህቱ ማርያም ሙሴን ሲቃወሙ ማርያም በለምጽ ተመታች ሙሴ ቢጸልይ ዳነች። ዘሁ. 12:10

+++ ክቡር ዳዊትና ጻድቃን፦ ዳዊት በገናውን እየደረደረ እንዲህ አለ፦ የእግዚአብሔር አይኖቹ ወደ ጻድቃን ጆሮዎቹም ወደ ልመናቸው ናቸው። ዳዊት እንዲህ ብሎ የዘመረውን እኛ ባንሰማ እንዃን ዳዊት የዘመረባት በገናም ትታዘበናለች; የሠራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከመረጥኩት ጋር ኪዳን ገብቻለሁ ፤ ኪዳኔን አላፈርስም ከአፌ የወጣውንም አላጥፍም መዝ88:3 ፤ 88:34 ፤ ስለ ራሴና ስለባሪያዬ ስለዳዊት ስል ይህችን ከተማ እጋርዳታለሁ 2ኛ ነገስት 19:34 ፣ 20:6

+++ ጠቢቡ ሰለሞንና ፃድቃን ፦ አባት የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል” ሲል ልጅ ደግሞ በረከት በፃድቅ ራስ ላይ ነው” እያሉ አባትና ልጅ መሰከሩ ፤ ጌታችንም ቀዝቃዛ ውሃ በፃድቅ ስም የሚያጠጣ ቢኖር ዋጋው አይጠፋበትም እንዳለ
መዝ 111 ፣ ምሳሌ 10:6 ማቴ 10:40

+++ ነብዩ ኢሳያስና ፃድቃን፦ ኢሳያስ ከ700 መቶ አመት በፊት ድንግል በድንግልና ትጸንሳለች ብሎ ቢተነብይ የዘመኑ ሰዎች ሥጋውን በመጋዝ ለሁለት ሰንጥቀው ሰማዕትነትን ተቀበለ ፤ ስለ ጻድቃን በታላቁ ነብይ ትንቢት እንዲህ ይላል፦    ቃልኪዳኔን ለሚጠብቁ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከሴቶችና ከወንዶች የሚበልጥ
ዘላለማዊ ስም እሰጣቸዋለሁ; ኢሳ. 56:4 ቤተክርስቲያን በጻድቃን ስም የምትሰየመውም በዚሁ ምክንያት ነው።   
+++ ሐዋርያው ጴጥሮስና ጻድቃን ፦ እግዚአብሔር የፀጋ ስጦታ ለቅዱሳኑ ሰቷቸው ድንቅ ተዓምራትን ይሰሩ ነበር። ቅ/ጴጥሮስ ጥላው ድውያንን ሲፈውስ ቅ/ጳውሎስ ደግሞ የልብሱ ቁጨት አጋንንትን አወጣ የሐዋ.5:15 ፤ 19:12
የጌታ አይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉ ጆሮዎቹም ወደ ልመናቸው ናቸው። 1ኛ ጴጥ 3:12

በሐዋርያት ሥራ 19:14 ያለውን ግሩም ታሪክ እንዴት ይገርማል!”

+++ ሐዋርያው ዩሐንስና ጻድቃን፦ የሮማ ወታደሮች ፖሊካርፐስ የተባለ የሐዋርያው ዩሐንስ ደቀመዝሙርን አምላኩንና ሐይማኖቱን እንዲክድ አስገደዱት; ይህን የሰሙ ክርስቲያኖች በአፍህ ብቻ ካድ እኛ ለምን እንደዚህ እንደምትል እናውቃለን ብለው ፖሊካርፐስን መከሩት፤ ፖሊካርፐስ ግን ጌታዬ አንድም ቀን አልካደኝም እኔስ ለምን እክደዋለሁ ብሎ መለሰላቸው; የሮማ ወታደሮችም ፖሊካርፐስን በእሳት አቃጥለው ሰማዕትነትን ተቀበለ።
በእስያ የመጀመሪያው ሰማዕት የሆነው አንቲጳስ ደጎሞ በነድምጥያኖስ ዘመነ መንግስ በነሃስ መጥበሻ ተጠብሶ ሰማዕትነትን ተቀበለ። ራዕ 2:13 

+++ ሐዋርያው ያዕቆብና ፃድቃን፦ ያዘነ ቢያር ይጸልይ; ደስም ያለው ይዘምር ፤ የታመመ ቢኖር የቤተክርስቲያንን ቀሳውስት ይጥራና ዘይት
 /ቀንዲል; ቅብዐ ፈውስ/ ቀብተው ይጸልዩለት የእምነት ጸሎት ድውዩን ይፈውሳል
የፃድቅ ሰው ጸሎት ሐይልን ታደርጋለች ግዳጅንም ትፈጽማለችና” ያዕቆብ 5: 13-16
/ቀጣዩን ገጽ ይመልከቱ/
+++ ሐዋርያው ጳውሎስና ጻድቃን፦ ስለ ፃድቃን ሰማእታት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በእብራዊያን መልእክቱ በተከታታይ ምዕራፍ ላይ ይናገራል። /እብራዊያን ምዕራፍ 11; 12 እና 13/

+++ እብራዊያን 11:34 አለም ለነሱ አልተገባቸውምና በየበረሀው በየዋሻው ተንከራተቱ።

ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ ጻድቃን በየበረሃው ተንከራተው እንዳለፉ ነገረን; አሁንም በሀገራችን በየገዳሙና በበረሐው ጤዛ ልሰው ዳዋ ጥሰ ዋእይ ቁሩንም ታግሰው ለሃገር ለህዝብ የሚፀልዩ አበው አሉን። ሃገራችን ብትታረስ ብዙ ጻድቃን የሚበቅሉባት ቅድስት ሃገር ናትና። መናፍቃን ግን ገዳማዊ ህይወትን ይቃወማሉ; ታላቁ ሐዋርያ ግን በመልክቱ አለም ለፃዳቃን እንዳልሆነች ነግሮናል።
+++ እብራዊያን 12:1፦ ብዙ ምስክሮች በዙሪያችን አሉን።
ሐዋርያው ሰማእታትን ምስክሮች አላቸው; ሰማ መሰከረ ሰማእትነት ምስክርነት ማለት ነው።
በእብራዊያን 11:37 ላይ እነ ነብዩ ኢሳያስ በመጋዝ ለሁለት ተሰንጥቀው ሰማእትነት እንደተቀበሉ ገለጸና እነዚህ ሁሉ ምስክሮች /ሰማእታት/ በዙሪያችን አሉ አለን።
በነፍሳቹ ዝላቹ እንዳትወድቁ የጸናውን አስቡ; እብራዊያን 12:3; ሐዋርያው የጸኑትን ሰማእታትን እንድናስብ ይመክረናል።

የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፤
   የእምነታቸውንም ፍሬ እየተመለከታቹ በሕይወትቸው ምሰሏቸው። እብራዊያን 13:7
                                   
 ብዙ ግዜ የወደቀውን ነው የምንመስለው ነገር ግን የጸኑትን እነ ነብዩ ኢሳያስን እነ
አባ ተክለ ሐይማኖትን; አቡነ አረጋዊንና ሰማእቱን ቅዱስ ጊዮርጊስን እያሰብን በተጋድሎዋቸው መምሰል ቢሳነን የእምነታቸው ፍሬ እየተመለከትን የጸኑትን መምሰል እንዳለብን ይመክረናል።
አስቀድሞ የመረጣቸውን ጠራቸው የጠራቸውንም አከበራቸው” ሮሜ 8:30 ፤
 እኛም ያከበራቸውን ክብር ሰጠናቸው። እግዚአብሔር የመረጣቸውን የሚከስ ማን ነው? ሮሜ 8:33

የዚህን ዓለም ተውና መላዕክትን እንኳን እንድንገዛ አታውቁምን?”[1ኛ ቆሮ. 6:3]

ተክለሐይማኖት ፀሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስሌነ ለዓለም ዓለም አሜን”


+++ ብርሐንና ጻድቃን፦

እኔ የአለም ብርሐን ነኝ ያለው ጌታ ጻድቃንንም አንትሙ ብርሐኑ ለዓለም/እናንተ የአለም ብርሐን ናችሁ አላቸው/ እስቲ ጥያቄ እናንሳ በሳይንሱ ጨራቃ የራሱ የሆነ ብርሃን አለው እንዴ? የለውም ነገር ግን ከፀሐይ reflect ወይም አንጸባርቆ በለሊት ያበራልናል፤ ፃድቃንም ፀሐይ ከሆነው ጌታ ለጨለማዋ አለም ያበራሉ ማለት ነው። በጨለማ ክፍል ያለን ሻማ ብርሃን እንደሚሰጠን እያወቅን ግን ብናጠፋው ጨለማ የሚበረታብን በኛ ላይ ነው ፤ መናፍቃንም ጻድቃንን ቢቃወሙ ጨለማው የሚበረታው ባጠፉት በራሳቸው ላይ ይሆናል ማለት ነው። 

/ቀጣዩን ገጽ ይመልከቱ/
9ኙ ቅዱሳን”


አባ አረጋዊ                 አባ አፍፂ
   አባ አሌፍ                  አባ ሊቃኖስ
አባ ፅህማ                  አባ ገሪማ
               አባ ይምዓት               አባ ጰንጠሌዎን ናቸው።
                    አባ ጉባ



+++ የመናፍቃኑ ጥያቄ ስለ ፃድቃን፦ መናፍቃኑ ጻድቃን በአካለ ሥጋ እያሉ ያማልዳሉ መፅሐፍ ቅዱስ መስክሯልና ለመካድም አይመችም ነገር ግን እንዴት በአካለ ነፍስ ሆነው ያማልዳሉ ብለው ይጠይቃሉ፤ የኤላሳዕ ዐጽም የሞተን እንዳስነሳ አይተናል ይህ ብቻ በቂ ነበር፤ ለሚጠይቁን ግን ቤተክርስቲያን ሃገረ ጥበብ ናትና ብዙ መልስ አላት። ጌታችን ለፈያታዊ ዘየማን እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህአለው [ሉቃስ 23:43] በገነት ትኖራለህ የሚለው ቃል ፃድቃን በገነት ሕያው ሆነው ዓለምንና እኛን ስለሚመለከቱ ነው፤ ለምኑልን ስንላቸውም ስለ እኛ ይለምናሉ። እንዴት እንደሚለምኑ ማየት ትፈልጋለህ?  በጣም ይገርምሃል መፅሐፍ ቅዱስ ላይ በገነት ያሉት ፃድቃን ቀርተው በሲኦል ያለ የሃጥዕ ነፍስ እንዃን በምድር ላሉት ወንድሞቹ ሲለምን እናገኛለን። በሲኦል ያለው ሃጥኡ ነዌ በምድር 5 ወንድሞች አሉኝና እባክህን ወደዚህ እንዳይመጡ አላዛርን ላክልኝ እያለ ለመነ [ሉቃስ 16:19] በሲኦል ያለው ሃጥኡ ነዌ ስለወንድሞቹ ከለመነ በገነት ያሉት ፃድቃንማ እንዴት ስለእኛ አብልጠው አይለምኑ? እኛስ በወንጌሉ የተፃፈውን አምነን እናነባለን እንጂ አንብበን አንክድም። 

መላዕክትን በአርያም; ሐዋርያትን በአጽናፈ ዓለም  

ጻድቃንን በገዳም; ሰማዕታትን በደም ያጸና

 እኛንም በቀናችው በተዋሕዶ ኦሮቶዶክስ እምነታችን ያጽናን

                                   

ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፤ አሜን
የእግዚአብሔር ቸርነት
 ከሃገራችን ከኢትዮጲያና - ኤርትራ” አይለይ አሜን!
[ተክለ መድህን]



















No comments: