Saturday 26 November 2011

የጠፋው ልጅ (ሉቃስ 15:11)





የጠፋው ልጅ  (ሉቃስ 15:11)



አባቴ ሆይ መጥቻለሁ
ይቅር በለኝ በድያለሁ
ይቅር ባይ ነህና የበደሉህን
ቂም እንዳቲዝብኝ በደሌን ቆጥረህ
ስለማይገባኝ ለመባል ልጅህ
ቁጠረኝ እንዳንዱ ከአገልጋዮችህ

አባቴ ሲቆጣኝ አልመለስ ብዬ
ስትመክረኝ እናቴ አልሰማሽም ብዬ
ከወንድሜ ጋራ ሀብቴን ተካፍዬ
ከሰው ሃገር ሄድኩኝ ከአባቴ ተለይቼ

የማይጎዳ መስሎኝ የሃጥያት መከራ
ኮብልዬ ነበረ ወደ ሃጥያት ተራ
አሁንግን ተመለስኩ ጥፋቴን አውቄ
የሰማይ አባት ሆይ ይቅር በለኝ

በአባቴ ቤት ሞልቶ ማርና ወለላ
በአባቴ ቤት ሞልቶ የቅኔው አዝመራ
ሄድኩኝና መንገድ በሰፊው ጎዳና
ናፍቆቱ በዛብኝ ያሬዳዊው ዜማ

እኔም ልብ ስገዛ ስመለስ ከቤቴ
ገና ከሩቅ አይቶኝ ይቅር ባይ አባቴ
ወደኔ ሮጦ አቀፈና ሳመኝ
በልቤ እየገረመኝ ወዲያው መታቀፌ
ትንሽ ሊወቅሰኝ ነው ብዬ ስጠባበቅ
መች እሱ ሊያስታውስ የትላንቱን ዛሬ
ደገመና አዘዘ አዲስ ልብስ ለእራሴ
ደግሞም ቀለበት ለጣቴ ; ጫማንም ለእግሬ

ይቅር ባይ ነህና የበደሉህን
ቂም እንዳቲዝብኝ በደሌን ቆጥረህ
ስለማይገባኝ ለመባል ልጅህ
ቁጠረኝ እንደ አንዱ ከአገልጋዮችህ

የግጥሙ ትርጉም ፦ የጠፋው ልጅ” በመባል የሚታወቀው ታሪክ በሉቃስ ወንጌል
ምዕራፍ 15:11 ላይ ሲገኝ በጣም ልብ የሚነካ ታሪክ አዘል የመፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ ነው።
+++ ልጁ ከአባቱ ኮበለለ ብዙ ካሳለፈ በሗላ ወደ አባቱ ተመለሰ። ልጁ በልቡ እንደ ልጅ ሳይሆን እንደ አገልጋይ ለመቆጠር አስቦ ነበር እናም ወደ ቤቱ ተመለሰ; አባቱም ገና ከሩቅ አይቶት ወደሱ ሮጦ አቀፈውና ሳመው። በጣም የሚገርመው አንድም የወቀሳ ቃል አለማንሳቱ ነው! ይልቁንም አዲስ ልብስ ቀለበትና ጫማ እንዲያመጡለት አዘዘ!!!
                                    
ከጌታ ባርያ ከአንዱ /ተክለ መድህን/

No comments: