Saturday 26 November 2011

እንተዋወቅ // ስም፦ ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ እባላለሁ



















 
                        እንተዋወቅ

                            ስም፦ ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ እባላለሁ
                            ሀገር፦ መንግስተ ሰማያት
                            ዜግነት ፦ ክርስቲያን
                            ስራ፦ እግዚአብሔርን አመልካለሁ










+++ ቤተክርስቲያንና ቅ/ጳውሎስ፦ ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ ለቤተክርስቲያን እጅግ ይቀና የነበረ ሐዋርያ ነው። ቅ/ጳውሎስና ቤተክርስቲያን የአንድ ዕርግብ ሁለት ክንፍ እንደማለት ናቸው!! ሁለቱም አይለያዩምና; በቀዝቃዛ እስር ቤት እያለ ቅ/ጳውሎስ ያስብ የነበረው ለቤታክርስቲያን ነበር። አብዛኛውን መልዕክታቱንም የፃፈው ከምድር በታች ባለች ቀዛቃዛ እስር ቤት ውስጥ ነበር።  2ኛው የጢሞቴዎስ መልዕክት የተፃፈውም በቀዛቃዛዋ እስር ቤት ነበር!!!









ቅዱስ ጳውሎስ መልእክታቱን የጻፈባቸው ቀዝቃዛ እስር ቤት ይህን ይመስላል;
 ልእ እንደ ለንደን ባቡር መሄጃ / /under ground/ ሆን ካታኮምቦ /ግበበ ምድር/ ይባላል።







+++ ሐዋርያዊ ስራዎቹ፦ ይህ ታላቅ ሐዋርያ ከሐዋርያት ሁሉ ብዙ መንገድ በእግሩና በባህር በመጓዝ የደከመና በጉዞው ህይወቱን ለአደጋ ያጋለጠ ሲሆን ለአህዛብ ወንጌልን ለመስበክ በመመረጡ 16 መልዕክታትን ጽፋል፤ ሁለቱ ጠፍተው በመጽሐፍ ቅዱስ ያለው 14ቱ መልዕክታቱ ናቸው።

ታላቁ ሐዋርያ መልዕክታቱን እየፃፈ

+++   ዕውቀትን ከትህትና ጋር ደርቦ የያዘ ነበር፦ በእየሩሳሌም በሚገኘው በታላቁ የአይሁድ ት/ቤት ከሊቁ ከገማልያል እግር ስር ቁጭ ብሎ ብሉይን የተማረና አዲስ ኪዳንን አበጥሮ የሚያቃት ቢሆንም በእውቀቱ አልተመካም፤ እኔ ጭንጋፍ ነኝ እስከማለትም ደርሶ ነበር። 
1ቆሮ. 15:8

+++ ሥራ ወዳድ ነበር፦ ሌት ተቀን በወንጌል ቢደክምም ለምዕመናን እንዳይከብዳቸው ድንኳን እየሰፋ እራሱን ይችል ነበር!!!

+++ እጅግ ትዕግስተኛ ነበር፦ ብዙ ግዜ ቢታሰርም በረሃብ ቢደክምም መልዕክቱን በትዕግስት ሆኖ  በደስታ ይጽፍ ነበር፤ በጌታ ደስ ይበላቹ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላቹ እያለ በመልዕክቱ ያጽናና ነበር። 

+++ ተግባቢ ነበር፦ ቅ/ጳውሎስ ሰውን እንዴት መቅረብ እንዳለበት ያውቅ ነበር። ከተራ ሰዎች እስከ ነገስታት በፍቅር እየሳበ ክርስቲያን አድርጓል። በመልዕክቱ መጨረሻ የቤተክርስቲያንን ልጆች ስም እየጠራ ሰላምታ ማቅረብ የዘወትር ተግባሩ ነበር።

+++ ጥበበኛ ነበር፦ የቤተክርስቲያን አበው ቅ/ጳውሎስን መዶሻ ይሉታል። መዶሻ ማዕድናቱን ቀጥቅጦ አንድ እንደሚያደርግ ሐዋርያውም አህዛብንና ሕዝብን/እስራኤል ዘሥጋን/ አንድ ስላደረገ ነው።  በጉዞው ቲቶንና በርናባስን አስከትሎ ነበር; ቲቶ ግሪካዊ አህዛብ ሲሆን በርናባስ ደግሞ አይሁዳዊ ነበር። 

+++ በመጀመሪያ የቤተክርስቲያን አሳዳጅ ነበር፦ ቅ/ጳውሎስ በ32 አመቱ ክርስቲያንን ለማጥፋት ከሊቀ ካህናቱ ቀርቦ የፍቃድ ደብዳቤ ከተቀበለ በሗላ የሶርያ ዋና ከተማ ወደሆነችው ወደ ደማስቆ ሊደርስ ጥቂት ሲቀረው ነበር ከሰማይ የወረደው ብርሃን አካባቢውን ሞላውና ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ የሚል ድምጽ የሰማው። በመቀጠልም ለሐዋርያነት ተጠራ።

     +++ ታላቅ ሰማዕትነትን ተቀብሏል፦ በዘመኑ የነበረው ጨካኙ ንጉስ ኔሮን በጥጋቡ የሮማ ከተማ ስትቃጠል ማየት እፈልጋለሁ ብሎ አቃጠላት; የሮም ሕዝብ በክርስቲያን ላይ አሳበቡ፤ በዚህም ክርስቲያኖች ሰማዕት መሆን ግድ ሆነባቸው። ቅ/ጳውሎስም ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር በጨለማ እስር ቤት ታስሮ ከቆየ በሗላ በ74 ዓመቱ በሮማ ከተማ በኦስትያ መንገድ አንገቱን ተሠይፎ ሐምሌ 5 67 ዓ.ም በሰማዕትነት ዐረፈ።
   

“ሩጫዬን ፈጽሜያለሁ ሐይማኖቴን ጠብቄያለሁ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል” 2ኛ ጢሞቴዎስ 3:4


የእግዚአብሔርን ቃል የተናገራችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ; የእምነታቸውንም ፍሬ እየተመለከታቹ በህይወታቸው ምሰሏቸው ዕብራዊያን 13:7። ታላቁ ሐዋርያ ቅ/ጳውሎስ እንዲህ እንዳለው መላው ህይወቱ ትምህርት ትሁነን፤ አሜን።

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሌላ ሐዋርያ በቅርቡ ሊተዋወቀን ይችላል!!  ማን ይሆን? ቅ/ ጴጥሮስ ወይስ ቅዱስ ዩሐንስ ወይስ ማን?  ይቆየን
                                   

/ተክለ መድህን/


No comments: