Tuesday 27 August 2013

ከመካከላችን በለምጽ የተመታ ማን ነው?



አሮንና ማርያም እኛ ከአንተ በምን እናንሳለን ብለው ሙሴን ተቆጡ። እግዚአብሔር ወዲያው ስለ ሙሴ ተቆጣ። እርሱ ፈቅዶ የመረጣቸውን ሰዎች ሲቃወሙበት አይወድምና እግዚአብሔር ይቆጣል። ሙሴ አሮንንና እህቱ ማርያምን አልተቆጣም። ስለ ሙሴ ግን እግዚአብሔር ይቆጣል።

ለነቢይ በህልም እገለጻለሁ ለሙሴ ግን ፊት ለፊት እገለጻለሁ አላቸውና ስለ ስንፍናቸው ገሰጻቸው። የሙሴ እህት ማርያም ሙሴን ተቃወመችው። ደመ ወዝዋ ተከፈላት፤ በለምጽም ተመታች። ዛሬ ቢሆን ስንቶቻችን በለምጽ እንመታ ይሆን?

ከመካከላችን በለምጽ የተመታ ማን ነው? 

No comments: