Tuesday 27 August 2013

እናት ቤተክርስቲያን ይህች ናት!





የይሁዳ መልእክት 1
3 ((ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት)) እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።

ሃይማኖት ቃሉ ግዕዝ ነው። እምነት ማለት ነው። ይህች እምነት የተሰጠችው ለቅዱሳን ነው። አንዳንዶች ሁላችንም ቅዱሳን ነን ይላሉ። ሐዋርያው ይሁዳ ግን መልዕክቱን የጻፈላቸውን ሰዎች ወንድሞች እያለ ይጠራቸዋል። እነዚህን ወንድሞች ለቅዱሳን ስለተሰጠችው ሃይማኖት እንዲጋደሉ ይመክራቸዋል! እስኪ መልዕክቱን አብረን እናንብበው፦
የይሁዳ መልእክት 1
2 ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ።
3 ((ወዳጆች ሆይ፥)) ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ((ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት)) እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።

እነሆ ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልና የሐዋርያት ሥራን ጻፈ። የሐዋርያት ሥራ /ገድለ ሐዋርያት/ ምን ማለት ይሆን? ሉቃስ ክርስቶስን መስበክ ትቶ ስለ ሐዋርያት ሰበከ እንል ይሆን?

መፅሐፈ ኢዮብ

ስለ ኢዮብ መከራ ይናገራል። ገድለ ጊዮርጊስ ስለ ጊዮርጊስ መከራ ይናገራል።

መጽሐፈ ሩት
ስለ ሩት ይተርካል፤ ስለ ክርስቶስ ሰምራ የሚናገር መጽሐፍም አለ!

መፅሐፈ አስቴር
ስለ አስቴር ይተርካል ፤ ስለ አርሴማ የሚተርክ መጽሐፍም አለ!

ዳዊት በበገና ዘመረ ፤ ቅዱስ ያሬድ በጸናጽል ድጓ ጾመ ድጓ እያለ ዘመረ!

ከመዝሙር ሁሉ ታላቁ መዝሙር ማሕልየ መሓልይ ነው፤ ያሬድ አንቀጸ ብርኃንን ዘመረ!

ኢየሱስ ጌታ ነው! የሚሉ አሉ። እኛም ይህን ደረጃ ካለፍን ዘመናት አለፈ። ኢየሱስ ክርስቶስ የጌቶች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ የአማልዕክት አምላክ እንላለን! ኢየሱስ ጌታ ነው ከማለትና ኢየሱስ ክርስቶስ የጌቶች ጌታ ነው ከማለት የቱ ይበልጣል? ከዚህ በላይ ወንጌል ከየት ይምጣ?

ፊታችንንና መላ ሰውነታችንን ማማተብ ወንጌል ነው!
ስናማትብ በእጃችን ከግንባር ወደ ልብ እንወርዳለን
ከሰማየ ሰማያት ወረደ
ከድንግል ማርያም ተወለደ
ቀጥሎ እጃችንን ከግራ ወደ ቀኝ እንመልሰዋለን!
ከግራ ሲዖል ወደ ቀኝ መንግሥተ ሰማይ መለሰን ማለት ነውና!
ከዚህ በላይ ወንጌል ከየት ይምጣ?

መፅሐፍ ቅዱስ ፦
በዓለም ጥንታዊው የመፅሐፍ ቅዱስ ቅጂ በኢትዮጲያ እንደሚገኝ ታውቃላችሁ?? ይህ ጥንታዊ ቅጂ በአባ ገሪማ ገዳም ይገኛል!

መፅሐፍ ቅዱስ ከሰማይ አልወረደም። እግዚአብሔር የመረጣቸው ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ጻፉት። አባቶቻችንም አቆዩልን። ዛሬ ዘመዶቻችን የሚሰብኩንን ወንጌል ማን ሰጣቸው??

እናት ቤተክርስቲያን ይህች ናት!

http://yonas-zekarias.blogspot.co.uk/

Like ·  · 

No comments: