Thursday 29 August 2013

በእውነቱ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?



በዚያም ወራት ብዙዎች ክርስቶስን ብዙ ይሉት ነበር። ግማሹ ነቢይ ነው ይሉ ነበር። መጥፎ ወሬ ይበራል መልካሙ ይተኛል እንዲሉ እንዲህና እንዲያ የሚሉ ወሬዎች በከተማዋ ተሰራጨ። ግማሹም ኤልያስ ነው መጥምቁ ዮሐንስ ነው አሉ። 



ቅ/ጴስሮስ ግን እንዲህ አለ፦ አንተ ውእቱ ወልደ እግዚአጽሔር ሕያው /አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ /

በጴጥሮስ ፋንታ እኛ ብንጠየቅ መልሳችን ምን ይሆን? አንተማ ፍጡር ነህ እንል ይሆን ወይስ አምላክ ነህ እንላለን?


አስተውሉ! ሰዎች የአብን ልጅ ማን ይሉታል አልተባለም። ይልቁንም ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል? ተባለ። ሰዎች የድንግል ማርያምን ልጅ ማን ይሉታል? ተባለ። ጴጥሮስም መለሰ፥ አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ! የአብ ልጅ የሰው ልጅ አንድ ነው! እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። አንዳንዶች የአብ ልጅ አምላክ ነው ይሉና የድንግል ማርያም ልጅን አምላክ ነው ለማለት አንደበታቸው ይታሰራል። ልቡና ህሊናቸው ፈራ ተባ እያለ ይጠራጠራል።

ክቡራን ሆይ! የድንግል ማርያም ልጅ የአብ ልጅ እንደሆነ ወንጌሉን አንብቡና እመኑ፣ ቅ/ጴጥሮስን ጠይቁና ልባችሁን አሳምኑ።


አምላክ እንዴት ይወለዳል? በፍጹም አይወለድም ብለው የቁርሃን ጥቅስ የሚጠቅሱ ክርስቲያናች አሉ። ክርስቶስ አልፋና ዖሜጋ ነውና ከተወለደ መጀመርያ አልፋ አይባልም ፣አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ ነበርኩ ስላለ ከቶ አይወለድም ይላሉ። ክቡራን ሆይ ይህማ በመጀመርያ ቃል ነበረ ያለውን አለማወቅ ነውና አስተውሉ!


አንዳንዶች አምላክ አይወለድም ሲሉ ኢሳይያስ እንዲህ አላቸው፦ ((ሕጻን ተወልዶልናል)) ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና ስሙም ድንቅ መካር ((ኃያል አምላክ)) ይባላል፤ ኢሳ 9፦6



ፕሮቴስታንት እህት ወንድሞቼ! የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናንተ ማን ነው? አምላክ ነው ወይስ ምንድን ነው?

http://yonas-zekarias.blogspot.co.uk/


Like ·  · 

No comments: