Saturday 3 December 2011

"ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላታል"



v    “እምነ ይብል ሰብ”


ልበ አምላክ ዳዊት በገናውን አነሳና አስሩን ቅኝት ቃኘውና ስለእመቤታችን እንዲህ ብሎ ዘመረ;
እምነ ፅዮን ይብል ሰብ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ
ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላታል ፤ በውስጧም ሰው ተወለደ። መዝ 86:5


v መናፍቃኑ ፅዮን የተባለችው የዳዊት ከተማ ኢየሩሳሌም ብቻ ናት ይላሉ፤ ከመሬት ውስጥ ሰው ይወለዳል እንዴ? አይወለድም ወደፊትም አይወለድም; ዳዊት በውስጧም ሰው ተወለደ ያለው አማናዊ ጽዮን የሆነችውን እመቤታችንን ነው። ዳዊት ለመናፍቃኑ ደገመና እንዲህ አላቸው፦ እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና፤ ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት /ዛቲ ይዕቲ ምዕራፍየ ለአለም/ መርጫታለሁና በእርሷም አድራለሁ መዝ 131:13።
ማለት አምባ መጠጊያ ማለት ነው፤ እመቤታችን ሀገረ ምስካይ /የመማጸኛ ከተማ/ ናትና። አንድም እመቤታችን ጽዮነ ሥጋ ዘነፍስ; ጽዮነ ሃጥአን ዘጻድቃን ናትና ፤ ጻድቃን እነ አባ ሕርያቆስ እነ አባ ኤፍሬም ተዓምሯን የጻፈው ቅ/ደቅስዮስ እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ዋጋችንን ታሰጠናለች ብለው። ሃጥዓን እነ ታውፋንያ፤ እነ በላዔ ሰብ ታስምረናለች ብለው ተጠግተውባታልና እመቤታችን ጽዮን በመባል ትጠራለች። አንድም ልበአምላክ ዳዊት ፅዮንን ክበቧት እንዳለ መዝ. [47:12] ሐዋርያቱ እመቤታችንን መሃላቸው አድርገው ከበዋት ለጸሎት ሲተጉ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያቱ ወረደ ይለናል [የሐዋ. 1.14] አንድም ነብዩ ኢሳያስ ስለ ጽዮን /ስለ ድንግል ማርያም/ ዝም አልልም እንዳለ ኢሳያስ[62:1]
እኛም ዓምርሽንም በዓይኔ አይቻለሁ ሆይ ስልሽ
ድንግል ሆይ እጠግባለሁ እያልን እንዘምራለን።




                                      


የእመቤታችን ፀጋ የፀጋ ልብስ ይሁንልን ፤አሜን [ተክለ መድህን]








7 comments:

Saba Gebre said...

GOD BLESS YOU!

Abel Nesibu said...

Thanks!u tell the better God give u good health n long life time.

Eyerusalem Jery said...

God blessyou!!Saturday at 4:18pm via mobile · UnlikeLike ·

Yosi Man said...

Kale hiowt yasemalen may God bless u.Saturday at 5:59pm via mobile · UnlikeLike · 1You like this.

Eyuel Solomon's Views said...

ቃለ ሕይወት ያሰማልን ! በጣም እናመሰግናለን !!!!!!!!!!!!!

ዮናስ ዘካርያስ said...
This comment has been removed by the author.
ዮናስ ዘካርያስ said...

የሕይወትን ቃል ለሁላችንም ያሰማን ፤ አሜን!