Sunday 18 August 2013

ታቦት

  • ትምህርት ሃይማኖት (የሃይማኖት ትምህርት) በሁለትይከፈላል፡፡ ይኸውም፦1ኛ፡- ዶግማ 2ኛ፡- ቀኖና በሚል ነው፡፡ዶግማ፡- ቃሉ የግሪክ ሲሆን ፍችውም እምነት ማለት ነው፡፡ቀኖና፡- ደግሞ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ሥርዓት ማለት ነው፡፡ከእነዚህ ከሁለቱ ዶግማ ወይም እምነት አይጨመርበትም፤አይቀነስበትም፤ አይሻሻልም፤ ችግርና ፈተናም ቢመጣ እስከሞት ድረስ አጥብቀን የምንይዘው ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ይህንዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረ፤ ቢመረምርእንጂ የማይመረመር ሁሉን ቻይ አምላክ፤ የሚሳነው ነገርየሌለ ፈጣሪ፤ የሰማይና የምድር ባለቤት የሠራዊት ጌታ ሕያውእግዚአብሔር ነው፡፡እግዚአብሔር (ፈጣሪ) የአካል ሦስትነት አለው፡፡ በመለኮት፣በመፍጠር፣ በሥልጣን፣ በአገዛዝ፣ በፈቃድ ግን አንድ ነው፡፡በሦስትነቱ አብ፤ ወልድ፤ መንፈስ ቅዱስ ሲባል በአንድነቱአንድ መለኮት አንድ እግዚአብሔር ይባላል፡፡ በአዳምምክንያት ከመጣው የዘለዓለም ሞትና ከዲያብሎስ ባርነት ነጻየወጣነው ከሦስቱ አካላት በአንደኛው አካል ማለትም በወልድበኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህ ዶግማ ወይም እምነትይባላል፡፡ቀኖና ግን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ያደጉክርስቲያኖች የሚመሩበት ሥርዓት ስለሆነ፤ በሃይማኖትአባቶች ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት እንደጊዜው ሁኔታየሚሻሻል በመሆኑ የሚጨመርበት፤ የሚቀነስለት ነው፡፡ለምሳሌ ያህል እኛ ኦርቶዶክሳውያን የምንጠመቀው ሴትበሰማንያ ወንድ በአርባ ቀናችን ነው፡፡ የተወለዱ ሕጻናት ሴቷሰማንያ ወንዱም አርባ ቀን ሳይሞላቸው ቢታመሙናበሽታው አስጊ ከሆነ በ10፣ በ20፣ በ30…ቀናቸው መጠመቅይችላሉ ቀኖና ነውና፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን የቀዳስያን ብዛትመነሻው አምስት ነው፡፡ ምናልባት ከአምስቱ አንዱ፤ ሁለቱ፤ሦስቱ ቢታጡና ሌላም ተፈልጎ እስከ መጨረሻ የማይገኝከሆነ ከአቅም በላይም የሆነ ችግር ከገጠመ ሁለቱ ወይምአንዱ ብቻ ቀድሰው ማቁረብ ይችላሉ፡፡ ቀኖና ነውና፡፡ በቤተክርስቲያናችን ታቦት ሲከብር ቤተ ክርስቲያኑን የሚዞረውሦስት ጊዜ ነው ችግር ካለ አንድ ጊዜ ብቻ ዑደት ተፈጽሞሊገባ ይችላል። ቀኖና ነውና፤ ስለቀኖና (ስለሥርዐት) ቅዱስጳውሎስ በመልእክቱ እንዲህ ሲል ጽፏል።1. ‹‹ነገር ግን ሁሉን በአግባብና በሥርዐት አድርጉ፡፡›› 1ኛቆሮ. 14፥40፡፡2. ‹‹ወንድሞች ሆይ በሠራንላቸው ሥርዐት ሳይሆን በተንኮልከሚሄዱት ወንድሞች ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስክርስቶስ ስም እናዝዛችኋለን፡፡ እኛን ልትመስሉእንደሚገባችሁ እኛም በእናንተ መካከል ያለ ሥራእንዳልኖርን ራሳችሁ ታውቃላችሁ›› 2ኛተሰ. 3፥6-7›› ቀኖና(ሥርዐት) የሚወሰነው በሃይማኖት አባቶች እንደሆነናወንጌልን የሚስተምር ሰው ለሚያስተምራቸው ክርስቲያኖችበሃይማኖት አባቶች የተወሰነ ቀኖና ማስተማርና መሰጠትእንዳለበት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ያስረዳል፡፡በየከተማውም ሲሄዱ፥ ሐዋርያትና ቀሳውስት በኢየሩሳሌምያዘዙትን /የወሰኑትን/ ሥርዐት አስተማሯቸው፡፡ አብያተክርስቲያናትም በሃይማኖት ጸኑ ዕለት ዕለትም ቁጥራቸውይበዛ ነበር፡፡›› ይላል የሐዋ. 16፥4-5፡፡ በዚህየእግዚአብሔር ቃል መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ ደርቤንናልስጥራን በተባሉ ቦታዎች ለነበሩ ክርስቲያኖች ወንጌልንከሰበከ በኋላ ሐዋርያት የወሰኑትን ቀኖና (ሥርዐት)እነደሰጣቸው እንረዳለን፡፡ ስለዚህ ቀኖና ወይም ሥርዐትቤተክርስቲያንን ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም፡፡ በመሆኑምዶግማንና ቀኖናን ወይም እምነትንና ሥርዓትን ጎን ለጎን ይዞመጓዝ ሐዋርያትን መከተል እንጂ ወደ ኋላ ተመልሶ አይሁድንመከተል አይደለም፡፡ እንግዲህ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንንየሚቃወሙ ሰዎች ሁሉ፤ የሚቃወሙት በቀኖና (በሥርዐት)የሚመሩትን ክርስቲያኖች ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል የሆነመጽሐፍ ቅዱስን በመሆኑ እንዳይሳሳቱ አደራ እንላለን፡፡አሁን እንግዲህ የዶግማንና የቀኖናን ልዩነት ከተረዳን በቀጥታወደ ታቦቱ ጥያቄ እንሄዳለን፡፡


     ጥያቄ፡-1 ዛሬ በእኛ ቤተክርስቲያን ያለው ታቦት ነው? ወይስ ጽላት በታቦትና በጽላት መካከል ልዩነት አለና፡፡ መልስ፡- ታቦት የጽላት ማደሪያ ነው፡፡ ዘዳ 40፥20፡፡ ጽላት ደግሞ ቅዱስ ቃሉ የተጻፈበት ሰሌዳ ማለት ነው፡፡ ዘዳ 34፥27-28፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሁለት ነገሮች ዛሬም በሐዲስ ኪዳን አሉ። ሆኖም ግን አሠራሩ ሙሉ በሙሉ በዘጸ 25፥10-18 ያለውን የሙሴን ሕግ የተከተለ አይደለም፡፡ ምክንያቱም፤ 1ኛ፡- ታቦት እንደሙሴ ሕግ የሚዘጋጀው ከግራር እንጨት ሆኖ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፤ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ቁመቱም አንድ ተኩል ይሁን ይልና በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አድርግለት ይላል፡፡ ደግሞም ታቦቱን የሚሸከሙት ከወርቅ በተሠሩ መሎጊያዎች አራት ሰዎች እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ በአጠቃላይ የብሉይ ኪዳን የታቦት አሠራር እጅግ ከባድ በመሆኑ በሁሉም ዘንድ አይቻልም ነበር፡፡ ምናልባት አንዳንድ የቤተክርስቲያን ፍቅር የነበራቸው ነገሥታትና ዛሬም ፍቅረ ቤተክርስቲያን ያላቸው አንዳንድ ምዕመናን ይችሉት እንደሆነ ነው እንጂ፡፡ 2ኛ፡- ጽላት፤ ጽላትም እንደሙሴ ሕግ ከሆነ መዘጋጀትና መጠረብ ያለበት ከከበረ ድንጋይ ነው፡፡ በአንድ ታቦት ውስጥም መቀመጥ ያለባቸው ሁለት ጽላቶች ናቸው፡፡ ዘዳ 34፥1፡፡ በአጠቃላይ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሕግና ሥርዐት ከባድ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ሥርዐትም ለሐዲስ ኪዳኑ ሥርዓት ጥላ ሆኖ አልፏል፡፡ 2ኛ ቆሮ 3፥7-11 ፤ ቆላ 2፥17፤ ዕብ 10፥1፡፡ እንግዲህ እዚህ ላይ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦትና ጽላት የብሉይ ኪዳኑን የታቦት አሰራርና ሥርዐት ጠንቅቆና ተከትሎ የማይሄድ ከሆነ፤ ይህ የብሉይ ኪዳኑን የታቦትና የጽላት አቀራረጽ ሥርዐት ጠንቅቆ ያልሄደ የሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ከየት መጣ የሚል ጥያቄም ሳይነሳ አይቀርም፡፡ አንባብያን ሆይ በቀጥታ ወደ ጥያቄው ከመግባታችን በፊት በዚህ ጽሑፍ ዶግማ ላይ ስለዶግማና ቀኖና ማብራሪያ የሰጠነው ይህን ለመሰለው ጥያቄ እንዲጠቅም ነው፡፡ አሁን ወደ ሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ስንሄድ ቁም ነገሩ እንደሚከተለው ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽም ሆነ አጠቃቀሙ የተወሰነውና የሚወሰነው በቀኖና ነው፡፡ ቀኖና ደግሞ እንደ ሁኔታው የሚሻሻል ነው፡፡ ሲቻል ይጨመርበታል ሳይቻል ደግሞ ይቀነስለታል፡፡ እንግዲህ በቤተክርስቲያናችን ቀኖና ካበረከታቸው ነገሮች አንዱ የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽንና አጠቃቀምን ነው፡፡ ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን ታቦትን ለመቅረጽ የግራር እንጨት ባይገኝ በዘፍ 1፥31 ላይ ‹‹ እግዚአብሔርም የፈጠረውን (ያደረገውን) ሁሉ እጅግ መልካም እንደሆነ አየ›› ስለሚልና እግዚአብሔር የፈጠረውን ስለማይንቅ ከግራር ሌላ ከማይነቅዝ እንጨት መቅረጽ እንችላለን፡፡ ቁመቱ ወርዱና ዙሪያውም እንደችሎታችን ይሆናል፡፡ በውስጥና በውጭ ስለሚሆነው የወርቅ ክብርም እንደችሎታችን ይወሰናል፡፡ ከሌለንም ወርቁ ይቀራል ቀኖና ነውና፡፡ ስለጽላቱም እንደዚሁ ነው ከቻልን ከከበረ ድንጋይ፣ ከዕብነ በረድ መቅረጽ እንችላለን፤ ካልቻልን ጽላቱን ከማይነቅዝ እንጨት መቅረጽ እንችላለን፡፡ በሌላ በኩልም ከቻልን እንደ ብሉይ ኪዳኑ በአንድ ታቦት ሁለት ጽላት ማስቀመጥ እንችላለን፤ ካልቻን በአንድ ታቦት አንድ ጽላት ብቻ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የጽላቱን ማስቀመጫ ታቦት ባይኖረን ጽላቱን ታቦት ብለን በመጥራት በጽላቱ ብቻ መጠቀም እችላለን ቀኖና ነውና፡፡ በተጨማሪም በኤር 31፥31፤ 2ኛ ቆሮ 3፥1-3፤ በዕብ 8፥8-13፡፡ የእኛ አካልና ልቡና የእርሱ ታቦትና ጽላት አልሆነም ወይ? በሐዲስ ኪዳን ለምን ታቦትና ጽላት አስፈለገ? ለምንስ ይህ ሁሉ ተፈጠረ የሚሉ አሉ፡፡ የክርስቲያኖች አካልና ልቡና በክርስቶስ ደም ታቦት፤ ጽላት፤ ቤተ መቅደስ መሆኑን እናምናለን፡፡ ቢሆንም በሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ያስፈለገበት ምክንያት ስለአምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነትና ክብር ሲባል ነው፡፡ ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ክብሩን የገለጠበት፤ ቃሉን ያሰማበት፣ ሙሴን እንደባልጀራ ያነጋገረበት፣ የክብሩ ዙፋን ሆኖ ጽላቱ በውስጡ ለታቦቱ ማደሪያ በመሆኑ፤ በሐዲስ ኪዳንም የሥጋውና የደሙ የክብር ዙፋን እንዲሆን ሲሆን ስለእኛ በዚህ ዓለም መከራ የተቀበለውን መድኅኔዓለም ክርስቶስን ለማክበር ሲባል ነው፡፡


  • ጥያቄ2፡- በዘዳ 31፣18፣32፣15፣134፣1-5፡፡2ኛዜና5፣10 ያሉትን ጥቅሶች በመጥቀስ እግዚአብሔር ለሙሴየሰጠው ሁለት ጽላቶችን ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እነዚህን እልፍ አእላፋትጽላቶች ከየት አመጣቻቸው? አራብታችሁ ቅረጹ የሚል አለወይ?መልስ፡- በዘዳ 32፥19፡፡ ስንመለከት እግዚአብሔር ራሱአዘጋጅቶ ለሙሴ የሰጠውን ሁለቱን ጽላቶች እሥራኤል ጣዖትሲያመልኩ ስላገኛቸው ሙሴ ተበሳጭቶ ሰብሯቸዋል፡፡ነገርግን ቸርነቱ ለዘለዓለም የሆነ እግዚአብሔር አምላክ ለሙሴየመጀመሪያዎቹን አስመስሎ እንዲሰራ ነገረው፤ ሙሴምአስመስሎ ሠራ፡፡ ዘዳ 34፥1-5 መሥራት ብቻ ሳይሆንዐሥሩን የቃል ኪዳን ቃላትም በጽላቶቹ ላይ እንዲጽፍ ሙሉሥልጣን ከእግዚአብሔር ተሰጠው፡፡ ሙሴም ተፈቅዶለታልናአሥሩን ቃላት በጽላቶቹ ላይ ጻፈ፡፡ ዘዳ 34፥27-28 ከዚህጊዜ ጀምሮ ጽላትንም ሆነ ታቦትን እያስመሰሉ ለመሥራትሙሉ ሥልጣንን አግኝተናል፡፡ ይህን በተመለከተ አንዳንድአባቶች እንዲህ ይላሉ፤‹‹አዳም እንኳን በደለ አዳም ባይበድል ኖሮ አምላክ ሰው ሆኖበቀራንዮ ስለእኛ የመሰቀሉን፤ ስለኛ የመሞቱን የፍቅርምስጢር አናውቀውም ነበር፡፡››እስራኤልም በጥጃ ምስል ጣኦት አምልከው እንኳን በደሉእሥራኤል ባይበድሉ ሙሴ በእግዚአብሔር የተዘጋጁት ሁለቱጽላቶች' የሰው ልጅም እግዚአብሔር የሠራቸውን የፊተኞቹንአስመስሎ ለመሥራት ስልጣን ባልኖረውም ቢሠራም ለምንሠራህ ለሚለው መረጃ ባላቀረበም ነበር›› ይላሉ፡፡ ያም ሆነይህ ጽላትን አስመስለን፤ አባዝተን፤ አራብተን ለመሥራትመሠረታችን ሥልጣኑ ለኛ ለልጆቹ የተላለፈልን ከአባታችንከሙሴ ነው፡፡››ሙሴ የተሰበሩትን አስመስለህ ሁለት ጽላቶች ቅረጽ ከሚልበቀር ጽላቶችን አብዝታችሁ፤ አራብታችሁ ተጠቀሙ የሚልቀጥተኛ ቃል አምጡ ለሚለው ግን ነገሩ እንዲህ ነው፡፡በብሉይ ኪዳን የጽላትም ሆነ የቤተ መቅደስ ሥርዐት፤የመስዋዕቱ የዕጣኑ አገልግሎት፤ በኢየሩሳሌም ብቻስለነበረና፤ የሌላውም አገር ሕዝብ የሚከተለው የጣዖትንሥርዓት እንጂ የሙሴን ሥርዐት ባለመሆኑ ጽላቱ ተባዝቶተራብቶ ለሌላው አገር ሕዝብ አልተሰጠም፡፡እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ውጭ አልፈቀደምየተቀደሰውን ጣዖታውያኑ አሕዛብ ያረክሱታልና ስለዚህስግደቱም የቤተመቅደስ ሥርዐቱም በኢየሩሰሳሌም ብቻነበር። /ዮሐ 4፥18-24/በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ አሕዝቦችም ሠሎሞን ያሠራውታላቁ ቤተ መቅደስና ሁለቱ ጽላቶች አንሰውናል፤ በርቀትየምንገኝ እኛ የመንገድ ድካም በዝቶብናልና፡፡ ስለዚህበያለንበት ቤተ መቅደስ ሠርተን ጽላቱን አክብረን መገልገልእንፈልጋለንና ይፈቀድልን ብለው ሙሴም ከሁለቱ ጽላቶችበቀር ሌላ አልተፈቀደም ብሎ መልስ የሰጠበት ቦታ የለም፡፡ያም ሆነ ይህ በሐዲስ ኪዳንም በአምላካችን በኢየሱስክርስቶስ አምነው በአብ፤ በወልድ፤ በመንፈስ ቅዱስ ስምተጠምቀው ፤ሁለተኛ የድኅነት ልደት ተወልደውየእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ሥልጣን ሰጣቸው።ለክርስቲያኖችም ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስእንደሚበዙና በአዲስ ኪዳን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስስም ንጹሕ የሆነውን ቁርባን ከኢየሩሳሌም ውጭ በየቦታውለእግዚአብሔር ማቅረብ እንደሚችሉ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህይላል፡፡



  • 1. ‹‹ ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜበአሕዛብ ዘንድ ይከበራልና፤ በየስፍራው ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፤ንጹሕንም ቁርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅይሆናልና ይላል ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር›› ሚል1፥11፡፡2. ‹‹ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎየለምን? እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎአስተማራቸው›› ማር11፥17፤ ኢሳ 56 ፥ 7፤ ኤር 7፥11 ፡፡ይህ ትንቢት በቀጥታ ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች መሆኑግልጥ ነው፡፡ ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ቤተ መቅደስም ሆነየዕጣን፤ የቁርባን አገልግሎት እንኳን ከፀሐይ መውጫ እስከፀሐይ መግቢያ ድረስ ላሉ አሕዛብ በኢየሩሳሌም ከሚኖሩየእግዚአብሔር ሕዝቦች በቀር ለእስራኤል ጎረቤት አገሮችእንኳ አልተፈቀደምና፡፡ ነቢዩ ሚልክያስ ንጹሕ ዕጣን ያለውበማቴ 2፥11፡፡ ወንጌል እንደተናገረው ከአሕዛብ ወገን የሆኑሰብአ ሰገል በቤተልሔም ዋሻ ለክርስቶስ ካቀረቡት ጀምሮእስከ ዛሬ ድረስ በዓለም ያለን ክርስቲያኖች በክርስቶስ ስምለክርስቶስ የምናቀርበው ቅዱስ ዕጣን ነው፡፡ንጹሕ ቁርባን የሚለውንም በማቴ 26፥26፤ ጌታ ኅብስቱንአንሥቶ ነገ የሚቆረሰው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ወይኑንም አንሥቶነገ ስለብዙዎች ሀጢአት የሚፈሰው ደሜ ይህ ነው ብሎለሐዋርያት የሰጣቸው የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው፡፡ ንጹሕየተባለው እርሱ በባሕርዩ ንጹሕ ሆኖ የእኛን የኃጢአት እድፍስለሚያነጻ ነው፡፡በብሉይ ኪዳን በኢየሩሳሌም ብቻ መሆን የሚገባቸው ቤተመቅደሱ፤ ዕጣኑ፣ ቁርባኑ፣ በክርስቶስ ደም በአዲስ ሕይወት፣በአዲስ ተፈጥሮ፤ በአዲስ ሥርዓት፣ ክርስቲያኖች ለሆንንለዓለም ሕዝቦች በየሥፍራው (በያለንበት)እንድንጠቀምባቸው ከተፈቀዱልን በኢየሩሳሌም ይኖሩየነበሩት ሁለቱ ጽላቶች ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያተባዝተው በዓለም ያለን ክርስቲያኖች በያለንበት በየቤተመቅደሳችን ለሥጋውና ለደሙ የክብር ዙፋንነትብንገለገልባቸውና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስምብናከብርባቸው ምን የሚጎዳ ነገር ተገኘ? የሚያስደነግጠውስምኑ ነው? ስህተቱስ የቱ ላይ ነው?እንዲሁም ዐሠርቱ ትእዛዛት የተጻፉባቸው ሁለቱ ጽላቶችመባዛት መራባት የለባቸውም ከተባለ በጽላቶቹ ላይ የተጻፉትዐሠርቱ ትእዛዛት መባዛት የለባቸውም፡፡ ከኢየሩሳሌምምመውጣት የለባቸውም ማለት አይደለም? ትእዛዛቱምተከለከሉ ማለት ነውና፡፡በጽላቶች ላይ የተጻፉት ትእዛዛት በእግዚአብሔር ፈቃድበፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ በሚገኙክርስቲያኖች እጅ ገብተዋል፡፡ ይህም ያስደስታል እንጂአያሳዝንም፡፡ ይህ ከሆነ ለሥጋውና ለደሙ (ለክርስቶስ) ክብርሲባል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥየሚገኙ ጽላቶች ምን በደል አስከተሉ፥ እግዚአብሔርለቀደሙ አባቶቻችን በታቦቱ አድሮ የሠራላቸውን ድንቅ ሥራእያስታወስን እግዚአብሔርን ከማመስገን ውጭ ደግሞምጌታ ስለ ጸሎት ሲያስተምረን ‹‹አባታችን ሆይ በሚለውጸሎት ውስጥ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድርትሁን›› በሉ ብሏል፡፡ በዚህ መሠረት በዮሐንስ ራዕይ 11፥19ላይ ታቦቱን በሰማይ አሳይቶናል፡፡ ስለዚህ የሙሴ የቃል ኪዳኑታቦት በሰማይ እንዲገኝ፤ በሰማይ እንዲሆን፤ በሰማይእንዲታይ ፈቃዱ ከሆነ፤ በምድርም እንዲሆን ፈቃድህ ይሁንብለን ብንጠቀምበት ስህተቱ ምን ይሆን?

    ጥያቄ3፡- የሰሎሞን ቤተ መቅደስ እስኪሠራ ድረስ በእርግጥ ታቦቱ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘዋወር ነበር፤ ቤተ መቅደሱ ተሠርቶ ታቦቱ ወደ ቤተ መቅደሱ ከገባ በኋላ ግን ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው ስለመውጣታቸው መጽሐፍ ቅዱስ አይናገርም፡፡ ታዲያ ዛሬ ክርስቶስ ደሙን ካፈሰሰ በኋላ፤ በብሉይም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መመሪያ ሳይኖር፤ ከየት አምጥታችሁ ነው ታቦትን በየጊዜው በማውጣት የክርስቲያኖች ህሊና ሁሉ ወደተሰቀለው ክርስቶስ መሆኑ ቀርቶ ወደ ታቦቱ የሆነው? መልስ፡- በብሉይ ኪዳን እንኳን አይወጣም ነበር ማለት አንችልም ምክንያቱም በችግራቸው ጊዜ ለችግራቸው መፍትሔ ያገኙ ዘንድ ከነበረበት ከድንኳኑም ቢሆን ያወጡት ነበርና ለምሳሌ፦ 1. በሙሴ ምትክ የተመረጠ ኢያሱ ሕዝበ እስራኤልን እየመራ ወደ ምድረ ርስት ሲሄድ ድንገት የዮርዳኖስ ወንዝ ሞልቶ ባገኘው ጊዜ ወንዙን ከፍሎ አሕዛብን ለማሻገር ከእግዚአብሔር በተነገረው መሠረት ካህናቱ ታቦቱን ከነበረበት ቦታ ተሸክመው ወደ ወንዙ በመሄድ ታቦቱን የተሸከሙት ካህናት እግር ወንዙን ሲረግጥ ወንዙ ተከፍሎ ሕዝቡ ሁሉ በሰላም መሻገራቸውን እናገኛለን፡፡ ኢያሱ 3፥1-17፡፡ 2. እስራኤል ምድረ ርስት በደረሱ ጊዜ ምድረ ርስት (ኢያሪካ) በጠላት እጅ በጽኑዕ ግንብ ታጥራ አገኟት፡፡ በዚህም ጊዜ ይህን የጠላት የግንብ አጥር ለማፍረስና ርስታቸውን በእጃቸው ለማድረግ እግዚአብሔር የገለጠላቸው ጥበብ ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው ሕዝቡም እየተከተሉ ሰባት ጊዜ ግንቡን እንዲዞሩት ነው፡፡ የታዘዙትን አደረጉ ግንቡም ፈረሰላቸው፡፡ ኢያሱ 6፥1-17፡፡ 3. እስራኤል ጠላት በበረታባቸው ጊዜ ጠላትን ለማሸነፍ ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው ይወጡ ነበር፡፡ 1ሳሙ 5፥1-ፍ፡፡ ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ካህናቱ ታቦቱን ከቦታ ወደ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ካልሆነ በቀር ለሚፈልጉት ዓላማ ታቦቱን ካለት ቦታ ተሸክመው አያወጡትም ነበር ማለት አንችልም፡፡ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ካስገባው በኋላ ቢሆንም ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው እንዳያወጡ የሚል ሕግም የለም፡፡ እግዚአብሔር የሠራው ሥራ በብሉይ ኪዳን የተፈጸመው አገልግሎት ሁሉ ሙሉ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አልተጻፈም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስም ያልተጻፈ ብዙ ነገር እንዳለ እናምናለን ከዚህ በመነሳት ነው እኛ በሐዲስ ኪዳን ታቦትን ተሸክመን የምናወጣው፤ በብሉይ ኪዳን በእግዚአብሔር ቸርነት (ትእዛዝ) ካህናቱ ታቦታቱን ተሸክመው እንዲወጡ ተደርጎ ካህናቱም ታቦታቱን ተሸክመው በመውጣት በታቦቱ ያደረ ኃይለ እግዚአብሔር ለሕዝበ እስራኤል ያደረገው ድንቅ ሥራ ለማሰብና እግዚአብሔርን ለማመስገን ነው፡፡ዛሬም ለሥጋና ለደሙ የክብር ዙፋን የሆነውን ቅዱስ ስሙም የተጻፈበትን ቅዱስ ታቦት በምናወጣበት ጊዜ በደሙ የባረከን መድኅነ ዓለም ክርስቶስ አሁንም የሥጋውና የደሙ ዙፋን በሆነው በታቦቱ ረቂቅ ኃይሎች በማስተላለፍ በረከቱን ያበዛልናል ብለን በማመን ነው፡፡ የተሰቀለው አምላክ መክበሩና መንገሡ ቀርቶ በየጊዜው ታቦት ወጣ እየተባለ ታቦቱ ብቻ ነገሠ ከበረ ሕዝቡም ወደ አምልኮ ባዕድ ኮበለለ ስለሚለው ግን አንድ ሕዝብ የንጉሡን ዙፋን ሲያከብርና ሲፈራ ንጉሡን ማክበሩና መፍራቱ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም፡፡ እኛ የምናምነው ቅዱስ ስሙ የተጻፈበትን የክርስቶስ ሥጋና ደም የክብር ዙፋን የሆነውን ታቦት ማክበራችን በኪሩቤል ዙፋን የሚቀመጥ መድኅነ ዓለም ክርስቶስን ማክበራችን መሆኑን ነው፡፡ በታቦቱ ፊት መስገዳችንም በታቦቱ ለተጻፈው ለቅዱስ ስሙ ነው፡፡ በታቦት ፊት ለእግዚአብሔር ስም ይሰግዱ የነበሩ ኢያሱና የእስራኤል ሽማግሌዎች በረከት አገኙበት እንጂ አልተጎዱበትምና ነው፡፡ ኢያ 7፥6፣ ዘዳ 33፥10፡፡ በሐዲስ ኪዳንም ‹‹ድል ለነሣው ስውር መናን እሰጠዋለሁ፤ የብርሃን መጽሐፍንም እሰጠዋለሁ፤ በዚያ መጽሐፍ ውስጥ ላይ ከተቀበለው በቀር ማንም የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎበታል›› ራእ 217፡፡ ለዚህ ስም ደግሞ ጉልበት ሁሉ መንበርከክ እንደሚገባ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ ‹‹ይህም በሰማይና በምድር በቀላያትና ከምድርም በታች ያለ ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰግድ ዘንድ ነው። አንደበትም ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር አብ ክብር ጌታ እንደሆነ ያምን ዘንድ ነው›› ፊልጵ 2፥10-11፡፡ በዚህ መሠረት ቅዱስ ስሙ በተጻፈበት ከነጭ ድንጋይ (ከዕምነ በረድ፣ከእንጨት) በተሠራው በጽላቱ ፊት ለቅዱስ ስሙ መስገድ ታላቅ የመንፈስ ጥበብ እንጂ ሞኝነት አይደለም፡፡ ምናልባት ስለታቦት፣ ስለጽላት ባለማወቅ ባጠቃቀሙ በኩል የሚሳሳቱ አባቶችን፤ እናቶችን ወንድሞችንና እህቶችን በተገቢው መንገድ ማስተማር ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ስለ ታቦት ከቤተ መቅደስ መውጣትና አለመውጣት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ከመሆኑም በተጨማሪ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡

  • ብዙዎች በሐዲስ ኪዳን ታቦትን ለመቃወም በኤር 3፥16፡፡የተጻፈውን ጠቅሰው “በዚያ ዘመን ፦የ እስራኤል ቅዱስእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት እነኋት እያሉም በአፋቸውምአይጠሯትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሿትም።” ተብሏልና ታቦትአያስፈልግም በማለት ያስተምራሉ፡፡እንደተባለው ታቦት ብሎ መጥራት ካላስፈለገ በኤርምያስ31፥34፤ ደግሞ “እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፣እያንዳንዱም ወንድሙን፦ እግዚአብሔርን ዕወቅ ብሎአያስተምርም” ተብሎ ስለተጻፈ እንግዲህ ሰው ሁሉ በየዘመኑእግዚአብሔርን እንዲያውቅ ማስተማር አያስፈልግም ማለትነዋ! ደግሞም ጌታችን በማቴ 28፥19 “እንግዲህ ሂዱና በአብበወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው አሕዛብንሁሉ አስተምሩ” ብሎ መናገሩ ስህተት መሆኑ ነዋ!በአጠቃላይ እንዲህ ነው ብሎ ከመናገር አስቀድሞ በመጽሐፍየተጻፈው ነገር ለምንና እንዴት ባለ ሁኔታና ጊዜ መጻፉንማጥናትና መልእክቱን (ምስጢሩን) መመርመር ይገባልእንላለን፡፡በመጨረሻ ግን በኢትዮጵያ ኦርቶኮክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማርያም፣ የቅዱሳን፣የሰማዕታት፣ የመላዕክትወዘተ…. ታቦት እየተባለ የተሰየመበት ምክንያቱና የዚህ ስያሜከየት ነው የመጣው ምንድን ነው የሚሉ ጥያቄዎች ሊኖሩእንደሚችሉ እርግጥ ነው፡፡እንዲህ ተብሎ መሠየሙ በትንቢተ ኢሳይያስ 56፥46በተገለጸው መሠረት የእግዚአብሔርን ሰንበቱን ለሚጠብቁደስ የሚያሰኘውንም ለሚመርጡ ቃል ኪዳኑንም ለሚይዙጃንደረቦች (ስለእግዚአብሔር መንግሥት ራሳቸውን ጃንደረባያደረጉ ቅዱሳን) ማቴ 19፥12 በእግዚአብሔር ቤትና በቅጥሩየዘለዓለም መታሰቢያ እንደሚደረግላቸው የተገለጠ በመሆኑይህን አብነት በማድረግ ጌታ ሥጋው፣ ደሙ የሚከብርበት ሆኖለቅዱሳኑም መታሰቢያ ለማድረግ ነው፡፡ /መዝ 111፥7/እንዲሁም የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነውና ምሳ 10፥7፡፡በዚህ ምክንያት እንጂ በታቦታቱ የሚከብረው መድኃኒተ ዓለምክርስቶስ መሆኑ ግልጽ ሊሆን ያስፈልጋል፡፡

No comments: