Sunday 1 September 2013

ከሞተ አንበሳ ያልሞተ ውሻ ይሻላል

መጽሃፈ መክብብ ምእራፍ 9:4_6 ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና ሰው ከሕያዋን ሁሉ ጋር በአንድነት ቢኖር ተስፋ አለው። ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን አንዳች አያውቁም፤ መታሰቢያቸውም ተረስቶአልና ከዚያ በኋላ ዋጋ የላቸውም። ፍቅራቸውና ጥላቸው ቅንዓታቸውም በአንድነት ጠፍቶአል፥ ከፀሐይ በታችም በሚሠራው ነገር ለዘላለም እድል ፈንታ ከእንግዲህ ወዲህ የላቸውም።ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችንይህንን ጥቅስ በመጥቀስ ፃድቃን ከሞቱ በሇላ የማያማልዱና መታሰቢያቸው የተረሳ መሆኑን ይናገራሉ ነገር ግን ቅዱሳን መታሰቢያቸው ለዘላለም ነው መዝ.111-6 የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል።ይላል ይረሳል አላለም ጌታ እግዚአብሔር ለዘላለም የመታሰቢያ ስማቸው እንደማይጠፋ ተናግሯል ኢሳ.56:4-54፤ እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና።በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።እግዚአብሔር በቤቱ በቅድስት ቤተክርስቲያን በእኛ በእያንዳንዳችን የማይጠፋ ስም ሰጥቷቸዋል ዳዊትም የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል ያለው ለዚህ ነው:: መታሰቢያነቱ ለዘላለም ስለሆነ ጊዜያዊ ስላልሆነ የማይጠፋ ስም አላቸው ሀጢአን ግን የላቸውም ክፍዎች ግን የላቸውም ቅዱሳን ስማቸው ብቻ ሳይሆን በፅዋ እነሱን ያሰበ ዋጋው አይጠፋበትም:የማቴዎስ ወንጌል 10:42"ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።"ይህ ቃል የእግዚአብሔር ነው:: እንዲሁም በምሳሌ 10-7 የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፤ የኅጥኣን ስም ግን ይጠፋል። ይላል መታሰቢያቸውን ማድረግ በረከት እንዳለው መፅሀፍ ቅዱስ ያስረዳናል ስለዚህ መታሰቢያቸው የተረሳው የሀጢአን እንጂ የቅዱሳን አይደለም ይህ ለቅዱሳን የተነገረ ቢሆን ኖሮ ዳዊት መታሰቢያቸው ለዘለአለም ይኖራል ባላለን ኢሳያስም የዘላለም መታሰቢያ ስም እሰጣቸዋለሁ ብሎ እግዚአብሔር መናገሩን ባልፃፈልን ነበር::ከሞተ ዘመናት ያለፉት ሙሴ ከኤልያስ ጋር በደብረ ታቦር በተገለጸ ጊዜ ኤልያስና ሙሴ ከጌታ ጋር ይነጋገሩ ነበር። ስለ ኢየሩሳሌምም ትንቢት ተናገሩ እንዲል ሉቃስ [9:30] “ሙሴ መናገር መቻሉና ትንቢት መተንበዩ ሕያው መሆኑን ያስረዳናል” ከላይ የተመለከትነው መታሰቢያ ስም እንዳላቸው እነጂ የቅዱሳን መታሰቢያ የሚረሳ አለመሆኑን ነው ሀጢአን ግን መታሰቢያ የላቸውም ተረስተዋል::እንዲሁም ቅዱሳን ከሞቱም በሇላ እንኩዋን ከፈጣሪያችን ጋር ያማልዱናል:: ሰማዕታት በታላቅ ድምጽ እየጮሁ “ደማችንን በከንቱ ያፈሰሱትን የማትበቀለው እስከመቼ ድረስ ነው?” አሉ [ራዕ 6:9] “በታላቅ ድምጽ መጮህ መቻላቸው” ሕያዋን መሆናቸውን ያስረዳናል። ደማችንን በከንቱ ያፈሰሱትን የማትበቀለው እስከመቼ ድረስ ነው? ማለታቸው ደማቸውን በከንቱ ያፈሰሱት እነ ዲዮቅልጥያኖስና ሌሎችም ገና እንዳልተቀጡ ስለሚያውቁ ነው። ጌታም ሌሎች ሰማዕታት ስላሉ እንዲታገሱ ነግሯቸው የንጽህና ምልክት የሆነውን ነጭ ልብስ ሰጣቸው። “ሰማዕታት ደማቸውን በከንቱ ስላፈሰሱት ፍርድን ሲጠይቁ ስለ እኛ ደግሞ ይለምናሉ” በሞት ጊዜ ነፍስ ወደ እግዚአብሔር እንደምትሄድ በነፍሱ እግዚአብሔርን ማየት እንደሚችል መጸሀፍ ቅዱስ ይነግረናል: ኢዩብ 19:26-27 ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ። እኔ ራሴ አየዋለሁ፥ዓይኖቼም ይመለከቱታል፥ከእኔም ሌላ አይደለም።ልቤ በመናፈቅ ዝሎአል።በአጸደ ነፍስ ያሉትን ቅዱሳን በድል አድራጊነት ያሉ በመሆናቸዉ ምልጃቸዉን አጥብቀን እንለምናለን።እንዲህ በምናደርግበት ጊዜ በሰማይም ሆነ በምድር ያሉ አማኞች በአንድ አካል ላይ ያሉ ብልቶች መሆናቸዉን መናገራችንና ማመናችን ነው::ከድል ነሺ ቅዱሳን ጋር ያለን ግንኙነት ሥራህ ያውጣህ በሚል መርህ የተተበተበ አይደለም።ይህ ማለት ጭንቀታችንን ምኞታችንን ይረዳሉ ይጋራሉ ማለት ነው።ለዚህ ነው "አንድም ብልት ቢሣቀይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።" 1ቆሮ 12-26 ተብሎ ስለ አማኞች አንድነት የተነገረው።ይህ ስለሆነ ነው ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ አጸደ ነፍስ ከወጣ ብኃላ በአጸደ ሥጋ ላሉ ልጆቹ እንደሚተጋላቸዉ የነገራቸዉ:: ምክንንያቱም በየትም ቦታ ቢኖሩም አንድ አካል ላይ ያሉ ብልቶች ስለሆኑ ነው።"ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ ማደሪያዬ መለየቴ ፈጥኖ እንዲሆን አውቃለሁና።ከመውጣቴም በኋላ(ወደ ኣጸደ ነፍስ) እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ(በጸሎት)።" 2ጴጥ 1-14

3 comments:

enaseb.blogspot.com said...

http://enaseb.blogspot.com/

enaseb.blogspot.com said...

I have tried to give a response to 3 posts presented in this blog. Please visit, the blog:

http://enaseb.blogspot.com/

Thank you.

enaseb.blogspot.com said...

I have tried to give a response to three posts in this blog; and posted them in the blog:

http://enaseb.blogspot.com/

Thank you.