Wednesday 11 April 2012

ኦርሙዝድ”
በቀድሞ ፋርስ በዛሬዋ ኢራን ኦርሙዝድ” ተብሎ የሚመለክ የመሬት አምላክ ነበር።  በሕብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ወንጀል ፈጽመው የሞት ፍርድ ሲፈረድባቸው ለመሬት አምላክ ክብር ለመጠንቀቅ ሲባል ወንጀለኞቹን ከምድር ከፍ ባለ መስቀል ተሰቅለው እንዲሞቱ ያደርጉ ነበር። ምክንያቱም ወንጀለኞቹ ቅጣታቸውን በመሬት ላይ ከተቀበሉ ኦርሙዝድ የተባለው አምላካቸው እንደሚረክስ ያስቡ ነበርና ነው።

ከዚህ በመቀጠል የመስቀል ቅጣት በግሪክ ፣ በሮም ፣ በአሦር ፣ በግብጽና በጀርመን ተስፋፍቶ ይሰራበት ነበር። ስቅላት በግብጽ የተለመደ ነበር። በዘፍ 40:19 እንደ ተጻፈው የስቅላት ፍርድ የተፈረደባቸው ሰዎች ተሰቅለው ከመሞታቸው በፊት ቅጣቱን ለማክበድ የሚደርስባቸው ተጨማሪ ስቃይ ነበረባቸው። በገመድ መታሰርና በጅራፍ መገረፍ፣ በጥፊ መደብደብ ፣ የሚሰቀሉበትን ግንድ /እንጨት/ ተሸክሞ ወደ ሞት መነዳት ፣ ልብስን ገፎ እርቃንን መስቀል ፣ በመስቀል ላይ ሐሞት መጋት ፣ ጎንን በጦር መውጋትና አጥንትን መስበር የተለመዱ ቅጣቶች ነበሩ።

የአይሁድ መጽሐፍት እንደነገሩኝ የሞት ቅጣት የተወሰነበት ሰው እጆቹን ከራሱ በላይ ቀጥ ካለ እንጨት ጋር አስሮ እስከ ፀሐይ ግባት ማዋል የተለመደ ነበር፤ ዘኁ [25:4] በመስቀል ላይ ማሳደር ግን የተከለከለ ነበር፤ ዘዳ [21: 23] በመስቀል ተሰቅሎ የሚሞት የተረገመ ነው ከተባለ ንጹሐ ባህርይ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ የሞተው ለምንድን ነው? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ጌታችን በመስቀል ተሰቅሎ በፈቃዱ የሞተው በቤዛነቱ የሰውን ልጅ ከእርግማን ለመዋጀት ነው።

“የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል
ቀነወኒ እደውየ ወእገርየ እጄንና እግሬን ቸነከሩኝ
መዝ [21:161] የሚለው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችን በመልዕልተ መስቀል ላይ ከተሰቀለ ወዲህ መስቀል የመርገም ምልክት መሆኑ ቀርቶ በማዕከለ ምድር የቆመ የኃጢአት ጨለማ የተወገደበት የብርኃን አምድ ኾኗል።

“መስቀልና ምሳሌዎቹ”

/1/ የእንጨት መስቀል፦ ጌታ ከ፯ ዕጽዋት በተዘጋጀ ዕጸ መስቀል የመሰቀሉ ምሳሌ ነው።

/2/ የብረት መስቀል፦ በ፭ ቅንዋት ሳዶር ፣ አላዶር፣ ዳናት ፣አዴራ እና ሮዳስ የመቸንከሩ ምሳሌ ነው።

/3/ የወርቅ መስቀል፦ ንጹሐ ባህርይ ነውና

/4/ የብር መስቀል፦ ይሁዳ ለሰላሳ ብር ብሎ አሳልፎ ሰጥቶታልና

/5/ የመዳብ መስቀል፦ መዳብ ቀይ ነውና የክቡር ደሙ ምሳሌ ነው።

በአንድ ወቅት ቅ/ዲዮስቆሮስና ነብዩ ኢሳይያስ በመንፈስ ተገናኙና የጌታን የቀራንዮ የጎሎጎታ ውሎውን እንዲህ ተነጋገሩ፦



አይሁድ ያዙት የመላእክት ሠራዊት በመንቀጥቀጥና በፍርሃት የሚቆሙለትን እርሱን በአደባባይ አቆሙት፤ በመስቀል ላይ ሰቅለው በቀኖት ቸነከሩት፤ ራሱንም በዘንግ መቱት ጎኑን በጦር ወጉት። ለጉበኞች እስራኤል ከአንድ ድንጋይ ያጠጣቸውን ለጥሙ ከከርቤ ጋር የተቀላቀለ ሐሞትን አጠጡት፤

የማይሞተው እርሱ ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ በቃል ኪዳን ተስፋው እንደ ነገራቸው።

ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው፤

እስከ ሞትም አደረሰው።

የሚስቡትን ሰዎች በቀንዱ የማይበረታታ ለሚያርዱትም ሰዎች አንገቱን የሚያዘነብል ላም ምን ይደንቃል!

በሚሸልተው ፊት የማይናገር በግ እንደምን ያለ ነው!

በመከራ ግዜ በሚወጉት ፊት አፉን ያልገለጸ ምን ትዕግሥት ነው!


ኦ በግዕ ዘኢይነብብ በቅድመ ዘይቀርጾ!

O sheep dump before your shearers!

በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን፤

በሸላቾቹ ፍት ዝም እንደሚል በግ አፉን አልከፈተም!

ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ ወአናፎራ /ኢሳ 53:1/

No comments: