Saturday 24 December 2011

አሣን በጾም ለምን አንበላም?

   አሳን በተመለከተ ብዙ ግዜ ጥያቄ ይነሳል፤ በፆም አሳ ለምን አንበላም? ጌታ ለሐዋርያቱ አሳን አበርክቶ ሰቷቸዋል፤ ሐዋርያቱም አሳ በልተዋል፤ ደግሞም እኮ በድሮ ግዜ አሳ ይበላ ነበር ይህ አሁን የመጣ ታሪክ ነው ይሉና ለምን አሳን በጾም አንበላም ብለው ብዙ ግዜ ይጠይቁናል; እናንተም ተጠይቃቹ ወይም ሲባል ሰምታቹ ይሆናል። ለመሆኑ አሳን በጾም ለምን አንበላም?

የበረከት ጌታ 12ቱን እንጀራ ሁለቱን አሳና አበርክቶ 19 መሶብ ተርፎ እንደተነሳ በመጽሐፍ ተጽፎልናል። ወንጌል ዘማቴዎስ ምዕ 14/19፤ 15/34።

+++ ሐዋርያቱ አሳ በልተዋል ነገር ግን ሐዋርያቱ አሳ የበሉት መቼ ነበር? በጾም ወቅት ነበር እንዴ? አይደለም፤
ጌታ ከሐዋርያቱ ጋር እያለ መቼ ጾሙ? ሙሽራው ከነሱ ጋር እያለ አይጾሙም ሙሽራው ከነሱ የሚወሰድበት ቀን አለ ያኔ ይጾማሉ አላቸው። ማቴ 9/15 ፤ ስለዚህም ሐዋርያቱ ጾምን አልሻሩም በጾምም አሳ ስላልበሉ እኛም በጾም አሳ አንበላም ማለት ነው።

+++ ኢትብልሁ ሥጋ ዘእንበለ አሳ ይለናል በቀኖና ቤ/ተ/ክ ይህም ሥጋ አትብሉ አሳን ጭምር ማለት ነው።
ሌሎች ግን ሥጋ አትብሉ ከአሳ በቀር ብለው ተርጉመውታል ይህ ግን ልክ አይደለም። ዘእንበለ የሚለው ግዕዝ ጭምር ወይም በቀር ተብሎ ይተረጎማል። ምሳሌ እናቅርብ፦ እግዚአብሔር ፈጠረ ኩሉ አለም ዘእንበለ ትል” ሲል እግዚአብሔር አለምን ሁሉ ፈጠረ ትልን ጭምር ይባላል እንጂ ከትል በቀር አይባልም። ስለዚህም አሳን ጭምር አትብሉ ማለት ይሆናል ማለት ነው።

+++ 318ቱ ርቱሃነ ሐይማኖት አበው አባቶቻችን በጾም ክርክር ቢነሳ ለጾም አድሉ ከመብል አለመብላት እጅግ ይሻላልና ብለው አልፈዋል።

+++ በድሮ ግዜ አሳ ይበላ ነበርና አሁንም እንብላ ለሚሉ ሰዎች ድሮ አሳ ለምን እንደሚበላ ምክንያቱንም መጠየቅ አለባቸው እንጂ እንዲሁ ባጭር አረፍተ ነገር ለመብላት መዘጋጀት የለባቸውም።  በድሮ ግዜ ለኢትዮጲያ ጳጳስ የሚላከው ከግብጽ ነበር። ጳጳሳቱም ለነገስታቱ እንዲመቻቸው ብለው አሳ በጾም እንዳይበሉ ብዙም አይከለክሏቸውም ነበር፤ አንድም የግብጽ ጳጳሳት ከሃገሬው ህዝብ ጋር በሰላም ለመኖር ብቻ ስለሚያስቡ በቀኖና ላይ አልጻፉትም ነበር; ስለዚህም አሳ ይበላ ነበር፤ አሁን ግን በቅርቡ በቀኖና ቤ/ተ/ክ ስለጸደቀ አሳና ጾም ምሥራቅና ምዕራብ ናቸው; አሳ በጾም አይገባም።

+++ በጣም በቀላሉ ስናየው አሳ ሥጋ ነው ታዲያ እንዴት በጾም ይበላል? የሃገራችን ጅብ ቀን ሙሉ ይጾምና ማታ ያገኘውን ይበላል; ዋና የጾም አላማው ከጥሉላት ምግቦች በመለየት ራስን ለእግዚአብሔር ለማስገዛት ነው። ሥጋም ሆነ የወይን ጠጅ ወደ አፌ አልገባም ዳንኤል 10:3

Our Sunday School /O.S.S/
Pls Do Visit this Blog:  http:// yonas-zekarias.blogspot.com/
Our Sunday School /O.S.S/
Pls Do Visit this Blog:  http:// yonas-zekarias.blogspot.com/


አሣማ ለምን አይበላም?

+++ ሰዎች ለምን አሳማን አንበላም; በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥስ መቼ ተጻፈ እያሉ ይጠይቃሉ።
እስቲ እንጠያየቅ፤ ባስ ይዛቹ መንገድ እየሄዳቹ ነው እንበል; ከአጠገባቹ ካለው አንድ አውሮፓዊ ጋር በውይይታቹ መሃል እንዲህ ብሎ ጥያቄ ጠየቃቹ፦ ሃይማኖታቹ እጅግ ያስቀናል ግን ለምን አሳማ አትበሉም? ብሎ ጠየቀ፤ መልሳችን ምን ይሆን? ዐሳማ ርኩስ ነው ብለን ካለፍን ነጮቹ እነዚህ እኮ ኦሪታዊ ብቻ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስን አያነቡም፤ አባቶቻቸው በታሪክ ነግሯቸው እንዲሁ በዘልማድ ያመልካሉ ብለው እንደሞኝ  ይቆጥሩናል። ወርቅ የሆኑ አበው አባቶቻችን ያወረሱን ግን አንገት የማያስደፋ እውነታን ነው።

ስንመልስ እንዲህ ብለን ብንጀምር መልካም ነው፦ እኛ አሳማን የማንበልው እርኩስ ነው ብለን አይደለም። በምድር አንድም ርኩስ ነገር የለም፤ በክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ ክቡር ደም ሁሉ ተቀድሷልና። ነገር ግን አሳማን የማንበላው በቀኖና ቤተክርስቲያን ስለተደነገገ እኛም የቤ/ተ/ክ ልጆች ስለሆንን ህጓን ለመጠበቅ ታዛዥ መሆናችንን ለመግለጽ አዎ አሳማን አንበላም እንበል። እግዚአብሔር ለአዳም በለስ አትብላ ያለውኮ በለሱ ርኩስ ስለሆነ ሳይሆን ታዛዥ የመሆኑ ምልክት ነበር።
                                     
መጽሐፍ ቅዱስስ ምን አለ

+++ አንድ ቀን ቅ/ጴጥሮስ ለመጸለይ ሰገነት ላይ ወቶ ነበር; ያኔ ከሰማይ ጴጥሮስ ሆይ ተነሳ እነዚህን አርደህ ብላ የሚል ድምጽ ሰማ፤ ጴጥሮስም ጌታ ሆይ እርኩስ ነገር በልቼ አላውቅም አለ; ያም ድምጽ እግዚአብሔር ንጹህ ያደረገውን አንተ እንደ ርኩስ አትቁጠር አለው። የሐዋ.10/9
  
ዐሳማ ሰኮናው የተሰነጠቀ ቢሆንም ስለማያመሰኳ በናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን። ዘሌዋውያን 11:7

ርኩስ ይሁን የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅ/ሥጋውንና ክቡር ደሙን ከማፍሰሱ በፊት በኦሪት ነው። በአዲስ ኪዳን ግን ሁሉ ቅዱስ ነው; ነገር ግን ዐሳማ መብላት አለብን ማለት አይደለም። ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ ሁሉ ተፈቅዶልኛል ነገር ግን ሁሉም ነገር አይጠቅምም እንዳለ። 1ኛ ቆሮ 10:23

+++
ታንቆ የተገኘውን ወይም አውሬ የዘነጠለውን መብላት የእንስሳት ደም መጠጣት እጅግ የተከለከለ ነው ዘሌዋውያን ምዕ 17፤ በደም ውስጥ ነፍስ ስላለ የእንስሳትን ደም መጠጣት የተከለከለ ነው።
ከመ ነፍስ ዘይሃድር በደም እንደሚል

ለሚጠይቃቹ ጥያቄ ሁሉ እንዴት መልስ መመለስ እንዳለባቹ ታውቁ ዘንድ ንግግራቹ ሁል ግዜ
በጨው እንደተቀመመ በፀጋ ይሁን; ቆላስይስ 4:6

ማጠቃለያ ፦

  • አሣ በጾም አይበላም ሐዋርያቱ አሣ የበሉት በጾም ወቅት አልነበረምና

  • አሣማ የማንበላው ርኩስ ነው ብለን ሳይሆን ለቤ/ተ/ክ የፍቅር ታዛዥ መሆናችንን ለመግለጽና በቀኖና ስለተደነገገ ነው።

                                              

/ተክለ መድህን/
Our Sunday School /O.S.S/
Pls Do Visit this Blog:  http:// yonas-zekarias.blogspot.com/

4 comments:

Mehari Berhe said...

KALE HIWET YASEMALIN Wendim Yonas Yemaytegebe Migb kenbeken Tedegagimo Binebeb Yemayselech Kalu n LIUL EGZIABHER Mistrun Ygiletsln+++

Mehari Berhe said...

KALE HIWET YASEMALIN Wendim Yonas Yemaytegebe Migb kenbeken Tedegagimo Binebeb Yemayselech Kalu n LIUL EGZIABHER Mistrun Ygiletsln+++
5 hours ago via mobile · UnlikeLike · 1

Anonymous said...

10q bro its fanos

Wondim Bekele said...

Betam tiru timehirt new! Emebatey yasebkewn tamulale! Erekechialew!