Friday 31 August 2012

“የራሔል ዕንባ በራማ ተሰማ”


«እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የኀዘን የልቅሶና የጩኸት ድምጽ በራማ ተሰማ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች [ኤር. 3115] የእንባ ሰውራሔልሮቤልም ስምዖንም የሚባል ባል ሞቶባት ሐዘንተኛ ነበረች። እርሱ ሲሞት ነፍሰ ጡር ብትሆንም « በእርሱ ምትክ ኖራ ውቀጪ ጭቃ ርገጪ፤ » ተባለች። 
መንታ ፀንሳ ነበርና ደም ፈሰሳት ሕፃናቱም ወጥተው ወጥተው ከጭቃው ወደቁ። ደንግጣ ብትቆምምን ያስደነግጥሻል? የሰው ደም የሰው ሥጋ ጭቃውን ያጸናዋል እንጂ ምን ይለዋል ብለሽ ነው? ርገጪውአሏት። በዚህን ጊዜ ነው « ኢሀሎኑ በዝ ሰማይ አምላከ እሥራኤል በውኑ በዚህ ሰማይ የእስራኤል አምላክ የለምንብላ እንባዋን ያፈሰሰችው። ይኽንንም እንባ በእፍኟ እየሰፈረች ወደ ላይ ረጨችው። እንባዋ ወደ ምድር አልተመለሰም ከመንበረ ጸባዖት ደረሰ እንጂ « ወዐበየት ተናዝዞ ወነጊፈ ላህ ልቅሶ መተውን መጽናናትን እንቢ አለች።» ምክንያቱም ግፉ ያሳዝናልና የሕፃናቱ ሞት የፃር ነውና ሐዘን በየደጁ ኹኗልና፡፡ « እስመ ኢኮንዋ ውሉዳ ውሉደ ልጆቿ ልጆች አልሆኗትምና » ሙተዋልና ባሌ ቢሞት በልጆቼ እጽናናለሁያለችው ከንቱ ኹኖባታልና። ይኽንን ነው ነቢዩ ኤርምያስየኀዘን የልቅሶና የጩኸት ድምፅ በራማ ተሰማ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰችያለው። ቅዱሳን ነቢያት የሚናገሩት ስለ ዘመናቸው ብቻ አይደለም ከዘመናቸው ጋር በማገናዘብ ስላለፈው ይናገራሉ ስለሚመጣውም ይተነብያሉ። ዓረፍተ ዘመን ሳይገታቸው ኃላፊያትንም መጻእያትንም ይተረጉማሉ። 

የራሔል እንባ በራማ ተሰማ

እስራኤል በባዕድ ሀገር በግብፅ በዮሴፍ ስም ተወደው ተከብረው ይኖሩ ነበር፡፡ በኋላ ግን ዮሴፍን የማያውቅ አንድም ደግነቱን ጥበቡን የማያውቅለት ንጉሥ ተነሥቶ ቀንበር አጠበቀባቸው። ይኸውም፦ የእሥራኤል ልጆች ፈጽመው በዝተዋል ከእኛም እነሱ ይጸናሉ ወደፊት ጠላት ቢነሣብን ከእነርሱ ወገን ተሰልፈው ይወጉናል አንድም ከበዙ ዘንድ አገራችንን ያስለቅቁናል። ብሎ ገና ለገና ፈርቶ ነው። ፈሪ ሰው ጨካኝ በመሆኑም፦ « ብልሃት እንሥራባቸው ጡብ እናስጥላቸው ኖራ እናስወቅ ጣቸው ጭቃ እናስረግጣቸው ይህን ሲያደርጉ ከዋሉ ልሙዳነ ፀብእ አይሆኑም አንድም ከድካም ብዛት ከሚስቶቻቸው አይደርሱም ካልደረሱም አይባዙም ካልበዙም አኛን አያጠፉም» አለ። ይኽንንም ብሎ አልቀረም። በብዙ ማስጨነቅ ፌቶም፣ ራምሴንና ዖን የተባሉ ጽኑ ከተሞችን በግንብ አሠራቸው። 


ንጉሥ ዓቀብተ መወልዳትን ( አዋላጆችን ) ሾሞባቸዋል፡፡ እነርሱንም « ዕብራውያትን ሴቶች ስታዋልዱ ለመውለድ እንደደረሱ በአያችሁ ጊዜ ወንድ ቢሆን ግደሉት ሴት ብትሆን ግን አትግደሏት » አላቸው። እነርሱ ግን እግዚአ ብሔርን ፈርተው እንዳዘዛቸው አላደረጉም። ንጉሡም ጠርጥሮ አንድም ከነገረ ሰሪ ሰምቶ « ለምን ያዘዝኳችሁን አልፈጸ ማችሁም ? » ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ምክንያቱም ወንድ ልጅ ተወልዶ ከሦስት ወር በኋላ ሲያለቅስ ሲያነጥስ በድምጹ ይታወቃልና ነው። ሴቶች ምክንያት አያጡምና ( ብልሆች ናቸውና ) « የዕብራ ውያን ሴቶች እንደ ግብፃውያን ሴቶች አይደሉም አዋላጅቱ ሳትመጣ ወልደው ይቆያሉ » ብለው መለሱለት። እነርሱ ለእስራኤል በጐ ነገር በማድረጋቸው እግዚአብሔር ለእነርሱም በጐ አደረገላቸው ንጉሡ እንዳይገድላቸው አደረገ።የንጉሥ ትእዛዝ መተላለፍ ያስገድላልና። ከፍ ብሎ በእግዚአብሔር ቸርነት ዝቅ ብሎ በአዋላጆች ደግነት እሥራኤል እጅግ በዝተው በረቱ። ያንጊዜም ፈርዖን ተቆጥቶ « ከዕብራውያን የሚወለደውን ወንድ ወንዱን ከፈሳሽ ውኃ ጣሏቸው ሴት ሴቱን ግን በሕይወት ተዉአቸው » የሚል አዋጅ አናገረባቸው። የእንባ ሰውራሔልየነበረችው በዚህ ዘመን ነበር። 

የራሔል እንባ እግዚአብሔር እንዲናገር በረድኤትም እንዲወርድ አድርጐታል።ከግብጻውያን እጅ አድናቸው ወደ ተወደደችም ሰፊ ወደምትሆን ወደ ከነዓንም እወስዳቸው ዘንድ ወረድኩ። ከግብፅም አውጥቼ ማርና ወተት ወደሚጐርፍባት ተድላ ደስታ ወደማይታጣባት አገር እወስዳቸዋለሁ » አለ። ማር ያለው ሕገ ኦሪትን ነው ማር የነካው ጨርቅ በውኃ ቢያጥቡት ፈጥኖ እንዲለቅ ሕገ ኦሪትም የሚለቅ ሕግ ነበርና። ወተት ያለው ደግሞ ሕገ ወንጌልን ነው። ወተት (ቅቤ) የነካው ጨርቅ በውኃ ቢያጥቡት እንደማይለቅ ሕገ ወንጌልም የማትለቅ ( ጸንታ የምትኖር ) ሕግ ናትና ዘጸ ፡፡

በአዲስ ኪዳን ደግሞ የሩቆቹ ወርቅ ዕጣንና ከርቤ ይዘው በኮከብ እየተመሩ ሁለት ዓመት ተጉዘው ሲመጡ የቅርቡ ሄሮድስ ግን ዜና ልደቱ አስደነገጠው ጥያቄያቸው « አይቴ ሀሎ ንጉሥ ዘተወልደ የተወለደው ንጉሥ ወዴት ነው ? » የሚል ነበርና ዓለም የሥልጣን ነገር ያሳስበዋል የደነገጠ አውሬም ያደርገዋል የደነገጠ አውሬ ማንንም እንደማይምር ዓለምም እንዲሁ ነው።

ሄሮድስ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከሰብአ ሰገል በጥንቃቄ ከተረዳ በኋላ በልቡ «ለካ ብላቴና ሁለት ዓመት ሆኖታል » አለ። ካህናቱን በስውር ጠርቶ በተረዳውም መሠረት « ቤተልሔም ነው፤ » ብሎ ሰደዳቸው። ከዚህም ጋር « ሄዳችሁ የብላቴናውን ነገር ጠይቃችሁ እርሱን ያገኛችሁት እንደሆነ እኔም እንድሰግድለት በእኔ በኲል ተመልሳችሁ ንገሩኝ፤ » አላቸው፡፡ እርሱ በሽንገላ ቢናገረውም ነገሩ ጥበበ እግዚአብሔር ነው። ሰብአ ሰገል፦ « ለካስ የሀገሩም ነገሥታት ያምኑበታልሳ » በሚል ሃይማኖታቸው እንዲጸናላቸው ነው  

ሰብአ ሰገል ግን ሳጥኖቻቸውን ከፍተው ወርቅ እጣን ከርቤ ለሕፃኑ ከገበሩለት በኋላ መልአኩ እንደነገራቸው በሌላ ጐዳና በሌላ ኃይለ ቃል በሌላ ሃይማኖት ተመልሰዋል በሌላ ጐዳና ሁለት ዓመት የተጓዙትን በአርባ ቀን ገብተዋል። በሌላ ኃይለ ቃል « ወዴት ነውእያሉ መጥተው ነበር « አገኘነው » እያሉ ተመልሰዋል፡፡ በሌላ ሃይማኖት « ምድራዊ ንጉሥ » እያሉ መጥተው ነበር ሰማያዊ ንጉሥ የባሕርይ አምላክ » እያሉ ተመልሰዋል።


ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደዘበቱበት ( ባንተ በኩል እንመለሳለን ብለው በሌላ ጐዳና እንደሄዱ ) በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ተበሳጨ። ጭፍራዎቹን ልኮ ከሰበአ ሰገል እንደተረዳው ዘመን ልክ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን በቤተልሔምና በአውራጃዎችዋ ሁሉ የነበሩትን አሥራ አራት እልፍ ሕፃናት አስገደለ። ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ « ራሔል ስለ ልጆችዋ ስታለቅስ ብዙ ልቅሶና ዋይታ ተሰማ መጽናናትንም እንቢ አለች ልጆቿ የሉምና። » የተባለው ተፈጸመ ይላል። 

እናቶች ልጆቻቸውን ታቅፈው ከመቃብረ ራሔል ገብተዋል ወታደሮች ከዚያም ተከትለው ገብተው ልጆቻቸውን ከእቅፋቸዋ ነጥቀው አንገታቸውን ጠምዘው አርደውባቸዋል። በዚህን ጊዜ አፅመ ራሔል አንብቷል። የራሔል መቃብር ከቤተልሔም አንድ .. ይርቃል።

ሄሮድስ እነዚህን ሁሉ ሕፃናት እንዴት አድርጎ ሰበሰባቸው?

ሄሮድስ አሥራ አራት እልፍ ሕፃናት የሰበሰበው « ንጉሡ ቄሣር ሕፃናትን ሰብስበህ ልብስ ምግብ እየሰጠህ በማር በወተት አሳድገህ ለወላጆቻቸው ርስት ጉልት እየሰጠህ ጭፍራ ሥራልኝ ብሎኛል፤ » የሚል አዋጅ አናግሮ በጥበብ ነው። ያላቸው ልጆቻቸውን፥ የሌላቸው ደግሞ ልብስ ምግብ ልቀበልበት ብለው እየተዋሱ ሄደዋል። እንዲህ አድርጎ ሰብስቦ ፈጅቷቸዋል። ለሁለቱም የግፍ ታሪኮች «የኀዘን የልቅሶና የጩኸት ድምፅ በራማ ተሰማ፤» የተባለው በመላእክት ዘንድ ተሰማ ማለት ነው። ምክንያቱም ኢዮር ራማ ኤረር ዓለመ መላእክት ናቸውና። አንድም በመላእክት ፈጣሪ በእግዚአብሔር ዘንድ ተሰማ ማለት ነው። ምክንያቱም መላእክት ባሉበት እግዚአብሔር አለ። አንድም ራማ የተባለች መንግሥተ ሰማያት ናት። ምሥጢራዊ ትርጉሙም ሃይማኖት ይዞ ምግባር ሠርቶ የሚገባባት አጥታ ታዝናለች ታለቅሳለች ማለት ነው። 

በዚህ ዘመን የሚያስፈልገው ሌላ ነገር ሳይሆን ይህ የራሔል እንባ ነው። ዓለም በግፍ ተከድናለችና ነፃ ሰው የለምና። «ረከሱ በበደላቸውም ጐሰቈሉ በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም። እግዚአብሔርን የሚፈልግ አስተዋይ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ ሁሉ ተካክሎ በአንድነት በደለ አንድ ስንኳ በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም፡፡ ሕዝቤን እንጀራን እንደ መብላት የሚበሉ ግፍ አድራጊዎች ሁሉ አያውቁም እግዚአብሔርን አይጠሩትም።» እንዲል፡፡ መዝ ፶፪ - ስለዚህ


ለራሳችን እናልቅስ ለትዳራችን እናልቅስ ለሀገራችን እናልቅስ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን አንድነት እናልቅስ። 

ዘመን ቢነጉድ እንዲኹ ለሁለት የተከፈለች ቤተክርስቲያን ለትውልድ እናስረክብ ይኾን? ይህስ አይኹንብን። አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ ወነዓ አድኃነነ መዝ [80: 2] ለእንዲህ ዓይነቱ ልቅሶ ከንቱ ልቅሶ እንዳልሆነ እንወቅ። የጭንቀት ልቅሶ አለ ለከንቱ ዓለም የሚለቀስ ልቅሶ አለ፤ ለንስኃ የሚለቀስ ልቅሶ ግን ዜግነቱ ምድራዊ ሳይኾን ሰማያዊ ነው!

አሁን እናት ሀገሬ ኢትዮጵያ እንባ አውጥታ ማልቀስ ያለባት ጊዜ ላይ ነች። እናት ሀገሬ የራሔልን እንባ ተበድራ መልካም እረኛ እና መልካም መሪ ስጠኝ ብላ እያነባች ነው። ለትዳር ለሀገር ለቤተክርስቲያን የሚለቀስ ልቅሶ ዜግነቱ ምድራዊ ሳይኾን ሰማያዊ አየር ላይ የሚበተን ሳይኾን እንደ ራሔል ዕንባ በራማ የሚሰማ ነው! 


     “የራሔል ዕንባ በራማ ተሰማ 


       ~ // ~   




22 ·   · Share
·                                

Emnet Abreham, Meaza Tekaye and 33 others like this.
·                                  
o                                                       
Bethlehem Dessalegn BE EWINET BEZI SEAT GETA YE ETHIOPIAWIYAN LEKISO YISIMA YE MITEKIMIM MERI YAMITALAT!!
o                                                       
Abate Bekele Kale heywotn yasemalene
o                                                       
amen amen kalyweten yasm len
o                                                       
Mulugeta Abrarie Amen kale hiwot yasemaln tebarek wodme "ye rahel eba tesema berama"
August 24 at 8:03pm ·  · 1
o                                                       

No comments: