Thursday 16 August 2012

==>ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ዛሬ ሌሊት ዐረፉ<==





ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ዐርፈዋል፡፡ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር።

የግብጹ ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ካረፉ በኋላ እሳቸውን የመሰሉ ደገኛ አባት ፍለጋ ግብጽ በጸሎት ተጠምዳለች። ዳዊት በትንቢቱኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለችእንዳለ ደገኛ አባት ስጠን ብለን እጃችንን ወደ እግዚአብሔር መዘርጋት ያለብን ዛሬ ነው። በአሜሪካና በሀገር ቤት የተራራቀችውን ቤተክርስቲያን በፍቅርና በብስለት አንድ የሚያደርጉ አባት ይሰጠን ዘንድ የጸሎት ጊዜው አሁን ነው። ሐዋርያውእለት እለት የሚያስጨንቀኝ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ነውእንዳለ እንደ /ጳውሎስ ያለ ለቤተክርስቲያን ቀናተኛ ለመንጋው መልካም እረኛ እግዚአብሔር ያዘጋጅልን



ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ “Apostolic Succession” 

ከሐዋርያት አለቃ ከቅ/ጴጥሮስ እስከ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ድረስ ኢትዮጵያ ያሳለፈችውን ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ እንዲህ እናገኘዋለን፦

የሐዋርያት አለቃ /ጴጥሮስ ነው።

ከቅዱስ ጴጥሮስ ቀጥሎ /ማርቆስ።

/ማርቆስ ግብጽ ሄዶ መንበሩን በግብጽ አደረገ።

ከቅ/ማርቆስ ቀጥሎ አንያኖስ ነው።

ከአንያኖስ ቀጥሎ 20 ፓትርያርክ አሉ። 20ኛው አትናቴዎስ ነው። 

ከአትናቴዎስ ቀጥሎ ከሳቴ ብርኅን አባ ሰላማ /ፍሬምናጦስ/ ይህን ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ወደ ሀገራችን አመጣልን።

ፍሬምናጦስ ኢትዮጲያዊ አይደለም። አንድ ነጋዴ ሲድራኮስና ፍሬምናጦስ የሚባሉ ሁለት ልጆቹን ይዞ አንድ ነጋዴ ቤት ገብቶ መኖር ጀመረ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነጋዴው ሞተ። ልጆቹም በገበሬው ቤት መኖር ጀመሩ። ፍሬምናጦስም የኢትዮጵያዊያንንn እምነትና ባህል አደንቃለሁ። ለምን ሥጋ ወደሙን አትቀበሉም? ብሎ ገበሬውን ጠየቀው። ገበሬውም ካህናት ስለሌሉን ነው አለው። ፍሬምናጦስም በኢዛና እና ሳይዛና ፈቃድ ግብጽ ሄዶ ፕትርክናን ከአትናቶዎስ ተቀበለ።


የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ፍሬምናጦስ ነው።

ከዚህ ጊዜ በኋላ ለብዙ ዘመናት ኢትዮጵያ በግብጽ ፓትርያርኮች ስትመራ ቆይታለች።

የመጀመሪያው አራቱ ኢትዮጲያዊያን ጳጳሳት 1921 ተሾሙ! 

አቡነ ሚካኤል
አቡነ ጴጥሮስ
አቡነ አብርሐም
አቡነ ይሥሐቅ ናቸው።

ከዚህ ጊዜ በኋላ በግብጽና በኢትዮጲያ መካከል ለሃያ አመታት ያክል ሀገራችን ኢትዮጵያዊ ጳጳስ ያስፈልጋታል አያስፈልጋትም በሚል ሽኩቻ ውስጥ ነበሩ። 

ይህ እልህ አስጨራሽ ሽኩቻ አለፈና 1940 ሌሎች አራት ጳጳሳት በግብጻዊው ፓትርያርክ በአቡነ ዮሳብ ተሾሙ።

አቡነ ሚካኤል
አቡነ ያዕቆብ
አቡነ ባስልዮስ
አቡነ ጢሞቴዎስ ናቸው።

ከእነዚህ ጳጳሳት አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ ሊቀ ጳጳስ ኾነው ተሾሙ!! በዚህች እለት 21 ጊዜ መድፍ ተተኮሰ! ታላቅ ደስታ ነበርና! ጊዜውም 1943 . ሲኾን ለአቡነ ባስልዮስ ሊቀ ጵጵስናውን የሰጡት የግብጹ ፓትርያርክ አቡነ ዮሳብ ነበሩ። 

1951-1963 ዓም ድረስ የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ ፓትርያር ኾኑ!!


በርግጥ ከአቡነ ባስልዮስ በፊት አቡነ አብርሐምና አቡነ ዮሐንስ የሚባሉ ሌሎች ሁለት ፓትርያርክ ነበሩ። ነገር ግን የኢጣልያው መንግስት ስለሾማቸው ቤተክርስቲያናችን ሕጋዊ ፓትርያርክ አድርጋ አትቀበላቸውም። የመጀመሪያው ሕጋዊ ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ናቸው።



ከአቡነ ባስልዮስ ቀጥሎ ፓትርያር አቡነ ቴዎፍሎስ ናቸው።

ከአቡነ ቴዎፍሎስ ቀጥሎ አቡነ ተክለሐይማኖት ናቸው። 

ከአቡነ ተክለሐይማኖት ቀጥሎ አቡነ መርቆርዮስ ናቸው።

ከአቡነ መርቆርዮስ ቀጥሎ አቡነ ጳውሎስ ናቸው።


ከአቡነ ጳውሎስ ቀጥሎ ማን ይሆን?

ለቤተክርስቲያን ቀናተኛ ለመንጋው መልካም እረኛ እግዚአብሔር ያዘጋጅልን።

No comments: