Sunday, 7 July 2013

ይድረስ ገዳማዊ ሕይወትትን ለሚቃወሙ!

ነገር ግን ስለዚህ ነገር ፊቱ ጠቆረ፥ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነም ሄደ። " ማር 10:17-22 

ሐዋርያ ጳውሎስ ዓለም በኔ ዘንድ የሞተ ነው፡ እኔም በዓለም ዘንድ የሞትኩ ነኝ ብሏል፡፡ ገላ 6፡ ፡14

ጴጥሮስም አሁን እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ምን እናገኛለን? ብሏል። ጌታችንም "ቤቱን ንብረቱን ወንድሞቹን እኅቶቹን እናት አባቱን ሚስቱን ልጆቹን ርስቱንና ጉልቱን በኔ ስም የተው ሁሉ በሚመጣው ዓለም ዕጥፍ ድርብ ያገኛል ብሎ መለሰለት ማቴ፡ 19:16-27፡፡

«ስለ መንግሥተ ሰማያት ሰውነታቸውን ጃንደረባ ያደረጉ አሉና፤ መፈጸም የሚችል ግን ይፈጽም» ማቴ. 19፡12 ስለዚህ የሰብአ ዓለምና የመነኮሳት ልዩነት ይህ ብቻ ነው እንጂ ለመነኮሳት ሌላ መንግሥተ ሰማይ ለሰብአ ዓለም ሌላ መንግሥተ ሰማይ አለ ማለት አይደለም፡፡

በዘመነ ብሉይ በዚሁ ዓይነት መንኩሰው ከዓለማዊ ግበር ተለይተው ፍጹማን የሆኑ እነ መልከ ጼዴቅ ኤርምያስ ኤልያስና እነ ዮሐንስን የመሳሰሉ ነበሩ::

አቅማችን ስለማይፈቅድ ፍጹም መሆን ብትፈልግ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ተከተለኝ የተባለው ለእኛ አይደለም። ጌታ እንዳለው መፈጸም የሚችል ግን ይፈጽም» ማቴ. 19፡12 እንደ ቅ/ጴጥሮስ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ምን እናገኛለን? የሚል ማን ነው?
10:28am
«ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መስፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም፤» ብሏል። ማቴ ፰፥፳። ጌታችን እስከ ዕርገቱ ድረስ በደብረ ዘይት ተራራ ለምን አደረ? ጌታ በገዳመ ቆሮንጦስ ይጸልይ ነበር አባቶችም በየገዳሙ ይጸልያሉ። ባልጠፋ ቤት በደብረ ዘይት ተራራ ኖረ አባቶችም በገዳም ኖሩ። ነገር ግን ስለዚህ ነገር ፊቱ ጠቆረ፥ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነም ሄደ። " ማር 10:17-22 ሐዋርያ ጳውሎስ ዓለም በኔ ዘንድ የሞተ ነው፡ እኔም በዓለም ዘንድ የሞትኩ ነኝ ብሏል፡፡ ገላ 6፡ ፡14

ጴጥሮስም አሁን እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ምን እናገኛለን? ብሏል። ጌታችንም "ቤቱን ንብረቱን ወንድሞቹን እኅቶቹን እናት አባቱን ሚስቱን ልጆቹን ርስቱንና ጉልቱን በኔ ስም የተው ሁሉ በሚመጣው ዓለም ዕጥፍ ድርብ ያገኛል ብሎ መለሰለት ማቴ፡ 19:16-27፡፡

«ስለ መንግሥተ ሰማያት ሰውነታቸውን ጃንደረባ ያደረጉ አሉና፤ መፈጸም የሚችል ግን ይፈጽም» ማቴ. 19፡12 ስለዚህ የሰብአ ዓለምና የመነኮሳት ልዩነት ይህ ብቻ ነው እንጂ ለመነኮሳት ሌላ መንግሥተ ሰማይ ለሰብአ ዓለም ሌላ መንግሥተ ሰማይ አለ ማለት አይደለም፡፡

በዘመነ ብሉይ በዚሁ ዓይነት መንኩሰው ከዓለማዊ ግበር ተለይተው ፍጹማን የሆኑ እነ መልከ ጼዴቅ ኤርምያስ ኤልያስና እነ ዮሐንስን የመሳሰሉ ነበሩ::

አቅማችን ስለማይፈቅድ ፍጹም መሆን ብትፈልግ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ተከተለኝ የተባለው ለእኛ አይደለም። ጌታ እንዳለው መፈጸም የሚችል ግን ይፈጽም» ማቴ. 19፡12 እንደ ቅ/ጴጥሮስ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ምን እናገኛለን? የሚል ማን ነው?

/፩/ ጴጥሮስ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ያለው ሐዋርያቱ በሞቀ ቤታቸው ከእናት ከአባታቸው ጋ እየኖሩ ነበር ?

/፪/ ያ ጎበዝ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ተከተለኝ ሲባል ንብረቱ ብዙ ስለሆነ ለምን መሸጥ ፈራ?

/፫/ ጌታችንስ ቤቱን ንብረቱን ወንድሞቹን እኅቶቹን እናት አባቱን ሚስቱን ልጆቹን ርስቱንና ጉልቱን በኔ ስም የተው ሁሉ በሚመጣው ዓለም ዕጥፍ ድርብ ያገኛል ብሏልና ምን ማለት ነው?

/፬/ «ስለ መንግሥተ ሰማያት ሰውነታቸውን ጃንደረባ ያደረጉ አሉና፤ መፈጸም የሚችል ግን ይፈጽም» ማለት ምን ማለት ነው? ማቴ. 19፡12

No comments: