/1/ አሁን ድናችኋል? ሁላችሁም በጋራ "አዎ" እንደምትሉ ይታወቃል። የመዳን ቀን ዛሬ ነው ድነናል ትላላችሁ። ከዳናችሁ መልካም። የዳነ ሰው ለምን አማላጅ ያስፈልገዋል?
/2/ አንዷ እህቴ //አቡነ አረጋዊ ባርኩን// የሚል ፖስት ስትለጥፍ ሰከንድ ባልሞላው ጊዜ ከአንድ እህታችን እንዲህ የሚል ተቃውሞ መጣ፦ ማን ናቸውና? በረከት ከእግዚአብሔር ብቻ ነው ተማሪ እሺ ተባረኪ። ብላ መለሰችላት። ራስዋ ባራኪ ሆና ጻድቁ ግን ባራኪ አይደለም ማለትዋ ገረመኝ። ሁል ጊዜ ተባረኩ ትሉናላችሁ ። አንዱን ቅዱስ ባርከን ብንል ስህተት ነው? መፅሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
/3/ ከእኔ አብ ይበልጣልና፡፡ ዮሃ14፡28 አብ ከክርስቶስ ይበልጣል ማለት ነው? ካልተበላለጡ ከእኔ አብ ይበልጣል ለምን ተባለ?
/4/ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያቱ ወረደ ማለት ምን ማለት ነው? በአካል ለሐዋርያቱ ወረደ ማለት ነው?
No comments:
Post a Comment