Sunday, 7 July 2013

ይድረስ ለፕሮቴስታንት ዘመዶቻችን!፮


ሰላም ለሁላችን ይሁን! ከመልስ በኋላ ማብራሪያና ጥያቄ የመጠየቅ መብታችሁ እጅግ የተጠበቀች ናት!! እነሆ ጥያቄው ተጀመረ፦
/፩/ አንዳንዶች እንደሚሉን ወልድ በብሉይ ጊዜ መልአክ ነበር! እስራኤላዊያንን በበረሃ የመራው መልአክ ክርስቶስ ነበር ብላችሁ ልባችንን አስደንግጣችኋል። ክርስቶስ መልአክ ነበር? ካልሆነ ራዕይ 8 ላይ መልአኩ ፀሎት አሳርጓልና መላዕክት ፀሎታችሁን እንደሚያሳርጉ ታምናላችሁ?
/፪/ እስራኤላዊያን ከግብፅ ባርነት የወጡት ለአብርሐም ለይስሐቅ ለያዕቆብ በገባላቸው ቃል ኪዳን ነው ብዬ አስባለሁ። ደጋጎቹ አባቶች ቢሞቱም ለነሱ በገባው ቃል ኪዳን ምክንያት ሕዝቡን ጠላታቸውን ድል አደረገላቸውም ብዬ አምናለሁ። በሐሳቤ ትስማማላችሁ ወይስ የሚቃወም አለ? ዘዳግም 77* ፱
/፫/ ሰው ቤተ መቅደስ እንደሚባል ሁላችንም እናውቃለን!
በ ፱ ሰአት ቅ/ጴጥሮስና ዮሐንስ ለጸሎት ወደ ቤተ መቅደስ ይሄዱ ነበር እኛም እንዲሁ እንሄዳለን። ቅ/ጴጥሮስ ፫ ሺሕ ሕዝብ ካጠመቀ በኋላ ሐዋርያቱ በሙሉ እለት ከእለት በቤተ መቅደስ እየተገኙ በጸሎት ይተጉ ነበር እኛም እንዲሁ እናደርጋለን። ዮሐንስ ባየው ራዕይ ፯ አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ። በታናሽዋ ኢስያ የሚገኙ ቤተ ክርስቲያን ነበሩ። የዘመናችን ሰዎች ከሐዋርያት ጋ ክፉኛ ተጣልተዋልና ማን ይድረስላቸው? ቤተክርስቲያን ወንጌል አልገባትም ትላላችሁ። ልጅ ለእናትዋ ምጥ አስተማረቻት አሉ። እናንተ ከሐዋርያቱ ትበልጣላችሁ? በሰማይ ያለውን ቤተ መቅደስ ምን እናድርገው?

/፬/ አንዳንዶች ገዳማዊ ህይወትን አንወድም ይላሉ። እኛ ለሊቱን ሙሉ እናንኮራፋለን ። እነዚያም ለሊቱን ሙሉ እየጸለዩ ያድራሉ። ፍጹም መሆን ብትወድ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ተከተለኝ ማለት ምን ማለት ነው?

በድንግልና የጸኑ አበው አሉን። የዘመናችን ሰዎች ደሞ ፓስተሮቻቸው ሳይቀሩ ወንድ ከወንድ ይጋባሉ። አበው ግን ለእግዚያብሔር ፍቅር ብለው ስጋዊ ምኞትን ትተው ሩካቤ ስጋን ታግሰው ገዳም ገቡ። አባቶቻችን እንዲህ ናቸው! የእናንተ አባቶችስ እንደ ቅ/ጳውሎስ ድንግል አገልጋይ አላችሁ?

No comments: