Sunday, 7 July 2013

ይድረስ ለፕሮቴስታንት ዘመዶቻችን!


  • ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! ብዙ ጊዜ እንደታዘብነው ጥያቄ ሲጠየቅ ዙሪያ ጥምጥም ባንሄድ ይመረጣል። ከመልስ በኋላ ማብራሪያና ጥያቄ የመጠየቅ መብታችሁ እጅግ የተጠበቀች ናት!!

    /1/ አዳም በበደለ ጊዜ ነፍሳት ሁሉ ወደ ሲዖል በወረዱ ጊዜ በዚያ የጨለማ ጊዜ በዘመነ አዳም ክርስቶስ አዳምንና ሔዋንን እያማለዳቸው ነበር? አሁንስ አዳምንና ሄዋንን እያማለዳቸው ነው?

    /2/ አይበለውና ሰይጣን አሳስቶት አንዱ ተነስቶ ቤት ቢዘርፍ ነፍስ ቢገድል ልዩ ልዩ የሆኑ ኃጢአቶችን ቢሰራ ኢየሱስ ክርስቶስ ያማልደዋል? ካላማለደው ታድያ ከየትኛው ኃጢአት ነው የሚያማልዳችሁ?

    /3/ በዘመነ ኢዮብ ክርስቶስ ኃጢአት የሚሰሩትን ያማልድ ነበር? ካማለደ ኢዮብን ስሙት እሱ ስለ እናንተ ይጸልያል ተብሏልና ((በዘመነ ኢዮብ )) ክርስቶስ ከኢዮብ ሥልጣን በምን ይለያል?

    /4/ ምርጥ ዕቃ የተባለው ንዋየ ኅሩይ ቅ/ጳውሎስ የማስታረቅንም ቃል በኛ ላይ አደረገ ማለት የቱን ማስታረቅ ነው?

    /5/ ከአዳም የመጣው ጥንተ አብሶ /original sin/ አሁንም ገና አልዳንም? ከአዳም የመጣው ጥንተ አብሶ መቼ ነው የቆመው?

    /6/ ዓለም በክርስቶስ ደም ገና አልዳነችም?

    /7/ ደጉ ሰማዕት ቅ/ እስጢፋኖስ //ክርስቶስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል አለ// ነፍስን የሚቀበል አማላጅ ነው አምላክ? እስጢፋኖስ ኢየሱስ ክርስቶስን አየና //ጌታ ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ// ግን ግን ይቅር በላቸው ለምን አለ? እናንተስ ክርስቶስ ሆይ ይቅር በለን ለምን አትሉም?

No comments: