Friday, 12 July 2013

ኃጢአት ተቆጣጣሪዎቹ!



በዘመናችን ብዙ ኃጢአት ተቆጣጣሪ አሉ። ይህን ሥልጣናቸውን ከየትኛው ድርጅት እንዳገኙት ባናውቅም ኃጢአትን ግን ነቅተው ይቆጣጠራሉ። ከዚህ ሥልጣናቸውም መውረድ ከቶ አይታሰብም።

ዘና ብላችሁ ተቀመጡና አንድ ታሪክ ላውጋችሁ።

ሁለት ጳጳሳት ከኢትዮጲያ ወደ ለንደን ቅ/ሥላሴ ቤተክርስቲያን መጡ። እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት የሰንበት ት/ቤቱ ወደ ማረፊያ ቤታቸው ሄድን። ለማስታወሻም ፎቶ ተነሳን። አንዲት እህት ከጳጳሱ ጋ የተነሳችው ፎቶ ከንቱ ክርክርን አመጣ። የጳጳሳቱን መምጣት የማይደግፉ ፖለቲከኞች ነበሩና ከፎቶው ጀርባ አልጋ ነበርና ሰዎቹ ወደ ሥጋዊ አላማቸው ቀየሩት። ይህንኑ ፎቶ በፌስ ቡክ አሰራጩት። ወገኔ በአይናችን ያየነውን ነገር እንዴት ነው ሰማይ ምድር ነበር መሬት ሰማይ ነበር የሚባለው?

ወደ ሌላ ታሪክ እንለፍ

ከቀናት በፊት አንድ ጋቢ የለበሰ ጥምጣም የጠመጠመ ሰው እየጨፈረ የሚያሳይ ቪዲዮ ተለቆ ነበር። ብዙዎች እንደ ጉድ አስተያየት ሰጡ እንደ ጉድም ተከራከሩ። እኔ ግን አስተያየት ከመስጠት ንቄ መተውን መረጥኩ። ። የራሳቸውን ሰው አስመስለው እንዳደረጉት ትንሿ ሚጡም ታውቀዋለችና። አሁን ያ አይገርመኝም። በጣም የሚገርመኝ ከንቱ ክርክሩ ነው። kkkkkkkkk KAKKAKKAKAKAKAKA እያሉ የሚከራከሩ ሰዎች አሉ። እናም እንደነሱ kkkkkk እያልን መከራከር አለብን ማለት ነው? ለምን በከንቱ ሰዓቴን አጠፋለሁ? በገዛ ፈቃዱ ከንቱ መሆን ከፈለገ ሰው ጋ ለምን ከንቱ እሆናለሁ? ሌሎች ኦርቶዶክስ አማኞች እንዳይታለሉ ትክክለኛውን አስተያየት ሰጥቶ ዞር ማለት ያስፈልጋል እንጂ ከንቱ ክርክር ፈልጎ ከመጣው ጋ መከራከሩ ከንቱነት ይመስለኛል።

ለመጥፎ ስራ አእምሯቸው ክፍት የሆኑ ሰዎች አሉ። እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ መባሉን አልሰሙም። የንስኃ አባታችሁ ሰካራም ናቸው ለማለት ደፈሩ። ሲጀመር በራሳቸው ሰው ቪዲዮ መቅረጻቸው የታወቀ ነው። ካህን መደነስ ቢያምረው ትንሽ ሰከር ማለት ቢያምረው ወዲያው ይወገዛል። በቃ ሌላ ተረት ምን ያስፈልገናል። አንድ ካህን ሰክሮ ብናየው የፈለጋችሁትን ኃጢአት መርጣችሁ ቢሰራ ሥጋ ለባሽ ነውና ምን ያስገርማል? አስቀድመን እንደተናገርነው ከክህነቱ ይወገዛል። እንደ ተራ ሰው ይቆጠራል። ነፍሱ ግን የከበረች ናት። እንደ ድሮው የካህን ሥልጣን ባይኖረውም ነፍሱ በዋጋ ተገዝቷልና እጅግ የከበረ ነው!!

አንድ ካህን እንኳን በዝሙት ቢወድቅ ቀርቶ ሌላ ቢያገባ ይወገዛል። ዲያቆኑም ሚስቱ ብትሞት እንኳን ሌላ ሚስት አያገም። ይህ ነው ምሥጢረ ክህነት!! ማንም ሰው ካህን መሆን አይችልም ማንም ሰው ግን ሌላ* መሆን ይችላል የሚባለውም አንዱ ለዚህ ነው!!


ሰክሮ ከመደነስና ክርስቶስን አላውቀውም ከማለት የቱ ይከፋል? ክርስቶስን አላውቀውም ያለው ጴጥሮስ የሐዋርያት አለቃ ሆነ! ይህን ስንል ተቀናብሮ የቀረበውን ቪዲዮ ለማባበል አይደለም። ያ ስራችሁ መሆኑን ስለምናውቅ ማባበል ዓላማችን አይደለምና አሁንም አስተያየት ስትሰጡ እንዳታደክሙን አደራ!

ከአንዷ እህቴ ጋ በዚሁ ግሩፕ ስለ ምሥጢረ ክህነት እየተወያየን ነበር።
ካህናት ጋ ሄደን ኃጢአታችን ይሰረዛል አልኳት።
እኔ ኃጢአት ወደሚሰራ ሰው አልሄድም አንተ ግን ካህኑ ጋ ሂድ አለችኝ።

የታመመ ቢኖር የቤተክርስቲያን ካህናትን ይጥራና ዘይት ቀብተው /ምሥጢረ ቀንዲል/ ይጸልዩለት ኃጢአት ሰርቶም ከሆነ ይሰረይለታል /ምስጢረ ክህነት/ ያዕቆብ 5፦8 ይህን ከነገርኳት በኋላ ውይይታችን በአጭሩ ተቀጨ። ብዙ ጊዜ ብጠይቅም መልስ ግን ጠፋ። የተጻፈውን ለምን እንደማያምኑበት ይገርመኛል። ዋናው ግን ለሕሊና መልስ መስጠቱ ስለሆነ ደስተኛ ነን። ኃጢአታቸውን ይቅር የምትሉ ይቀርላቸዋል የተያዘውም አይቀርለትም እንደተባለ የካህን ክብር ይህ ነው! የሁሉ ጌታ አዘዘ፣ ሐዋርያቱም መስክረዋልና ይህን የሚቃወም ማንን እየተቃወመ ነው?

አዳም የበደለው በደል የዘላለም ሞት አመጣበት!
ልበ አምላክ የተባለው ዳዊትም በሥጋው ተፈትኖ ከሰው ሚስት ጋ ተኛ!
ጴጥሮስም ጌታን አላቅህም ብሎ ካደ!


የዘመናችን ኃጢአት ተቆጣጣሪዎች ሆይ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በሥጋው እንደሚፈተን አታቁምን?


ለዚህ እኮ ነው ነቢዩ "አንተ ኃጢአትን ብትቆጣጠር በፊትህ ማን ይቆማል" ያለው!





Like ·  · 


No comments: