እናንተ ደካሞች ቸክማቹ የከበደ
ወደኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
ማቴ 11/28
ዛሬ እንደጠራኸን
በውጭ ጠፍተን ሳለ ለጠራኸን ዛሬ
ይመስለን ይሆናል እንዲይው ባጋጣሚ
ይመስገን ጌታ ይመስገንልን
በቅዱስ መንፈሱ እርሱ እየረዳን
ከብዙ ምክንያቶች ከልሎ ፤ ከቤቱ ላገባን ።
ማእበሉ ከፋ ወጀቡም አይሏል
ከመርከቡ መግባት አሁን ይሻለናል
መርከብ የተባለች ማእበል ምናልፍባት
የጌታ ቤቱ ቤተክርስቲያን ናት
አለም ብልጭልጭ ናት ሰው ምታዘናጋ
ድካም የበዛባት ፤ ሰላምና ፍቅር የማይገኝባት
ስለዚህ ለኛ ይሻለናል ከመርከብ ብንገባ።
የጌታ ሃዋርያት አሳዎች ሊያጠምዱ
ከጠዋት እስከማታ ነበረ ሲደክሙ
ብዙውን ቢለፉ ብዙውን ቡደክሙ
የዘረጉት መረብ ሆነባቸው ባዶ
የበረከት ጌታ ከነርሱ ሲጠጋ
በ 153 ትላልቆች አሳ
ባዶ የነበረው መረባቸው ሞላ
እኛም በአለም ላይ ብቻችን ስንደክም
መረባችን ሆነ አሳዎች ማይዙ
መረባችሁን በቀኝ ድገሙና ጣሉ
የሚለልን ጌታ ቃሉን ብንሰማ
ጌታችን ሲሆንም ሁሌ ከኛ ጋራ
መረቡ ሲሞላ በትላልቅ አሳ
ቤትህን ታያለህ በረከት ሲሞላ።
ዛሬ እንደጠራኸን ከቤትህ አትለየን
ደሃዎች እንዳንሆን ቃልህ ተለይቶን
ከራብ የሚፀናው የከፋው ርሃብስ
ትልቁ ጥማትስ ቃሉን መጠማት ነው
ቃሉን የመገበን ለኛ ያላስጠማን
ይመስገን እግዚአብሄር ቸሩ አምላካችን።
በቸርነትህ ከቤትህ ያገባኸን
ልትነግረን ነውና የህይወት ቃልህን
ከሰላሙ ቤትህ አንተ አትለየን
ዛሬ እንደጠራኸን ከቤትህ አትለየን።
ወስበሃት ለእግዚአብሄር ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን
ድንቅ ስራውን ካየው
ከጌታ ባርያ
ከአንዱ
/ተክለ መድህን/
No comments:
Post a Comment