ቆይቼ እግዚአብሄርን ደጅ ጠናሁት
እርሱም ዘንበል አለልኝ።
መዝ 39
ከእጅህ አለቀከንም
ወደታች ለማየት እጅግ ከሚያስፈራው
ሆነን ብንደክም ከጅህ አለቀከንም
የማንምች ሲሆን ለእረኝነትም
አንተ ግን ምን ግዜም ከጅህ አለቀከንም።
ቃላት ቢሰካካ ፍቅርህን አይገልፅም
ያንተን ፍቅርማ ፤ ሁሉም የራሱ አለው በየልቡ ጓዳ።
ፍቅር አስገድዶት በመስቀል ላይ ዋለ በማከለ ምድር
እድግ የበዛውን ያን ፍቅሩን ስታየው
ላፍታ ስታስበው ያደረገልህን
ልብህ ይከጅላል ምስጋና ማቅረብን
እስቲ እንመልከት የጌታ ሃዋርያትን
ጳውሎስና ሲላስ በእስር ቤት ሳሉ
ጮክ ብለው መዝሙር ሲዘምሩ
የእጃቸው ሰንሰለት በመበጣጠሱ
የመዝሙርን ፍሬ እንማር ከነርሱ።
ካንተም ሚፈልገው ምስጋና ነውና
በልብህ ያለውን ፍቅርህን መግለጫ
ላደረገልህም ግሩም ድንቅ ውለታ
የዳቢሎስንም ሃይል ማድከሚያ ነውና
ዝማሬን ስትዘምር ድምፅህን አሰማ
ጮክ ብሎ መዘመር ጥቅሙ ይህ ነውና።
በክንፈ ረዴትህ ያልተጠበቀ ሰው
አንተ ግን መልካም እረኛ ነህ
በጎችህን የማትሰጥ ከጅህ አሳልፈህ
ሸክማቹ የከበደ ኑ ወደኔ ብለህ
የምታሳርፍ ነህ በበረታው ክንድህ
ኖላዌ ትጉህ ነህ የማታንቀላፋ
ልጆችህን ሁሉ በለመለመ መስክ የምታሰማራ።
በለንደን ቅ/ሥላሴ ቤተክርስቲያን የተደረገው ታላቁ ጉባኤ ይህን ይመስል ነበር
ይ ቀ ጥ ላ ል
እግዚአብሔር ይሬዕየኒ ወአልቦ ዘየሃጥአኒ።
|
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝም የለም።
|
መዝሙረ ዳዊት 23
|
ከ ጌ ታ ባርያ ከአንዱ
ተክለ መድህን
No comments:
Post a Comment