“Apostolic - church”
v Apostolic Succession [ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ በቅዳሴ]፦
እስቲ በሚመጣው እሁድ ወንጌል ከመነበቡ በፊት ካህናቱን ልብ ብለን እንስማ; እንዲህ ይላሉ፤ ገባሬ ሠናዩ ካህን ወይም ዋናው ካህን አስቀድሞ እንዲህ ይላል፦
His kingdom & his righteousness which he delivers to me I deliver to you
[ዘአወፈየኒ አወፈይኩከ] ወይም የሰጠኸኝን ሰጠሁህ
ካህኑ የሰጠኸኝን ሰጠሁህ ብሎ ወንጌሉን ለንፍቅ ካህን ወይም ለሁለተኛው ካህን ይሰጠዋል ፤ ሁለተኛው ካህንም ለዲያቆኑ ይሰጠዋል; ይህ ነው ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የሚባለው; ዋናው ካህን የጌታ ምሳሌ ሲሆን ሁለተኛው ካህን ደግሞ የቅ/ጴጥሮስ ምሳሌ ነው፤ ዲያቆኑም የምዕመናን ሁሉ ምሳሌ ነው ማለት ነው!! ወርቅ የሆኑ አበው ወርቅ የሆነ ሥርአትን ከተግባር ጋር አወረሱን!
ስለ ቤተክርስቲያን አበው ብዙ ሰርተው አለፈዋል፤ ብርሐነ አለም ቅ/ጳውሎስም ስለ ቤተክርስቲያን ያልሆነው ነገር የለም ነበር። ይህች የቀደመችው እነ ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ የደከሙላት ፤ ይህች ኖህ ከጥፋት ውሃ የዳነባት ከአለም ወጀብ መጠለያ መርከባቻን ፤ ይህች እነ ዳዊት ሊጠለሉባት የመረጧት መልካም ማረፊያችን
ሐዋርያዊቷ ቤተክርስቲያን ናት!!!
“ከቤተመንግስቴ ከአእላፈት ቀን ይልቅ በቤትህ ልጣል ወደድኩ”
መዝ 83(84) ቁጥር 10
v ስለ ሐዋርያዊቷ ቤተክርስቲያን በደንብ ጠንቅቀን እንድናውቅ ግዜው ግድ ይለናል
ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊት ትባላለች ምክንያቱም ከሐዋርያት ተያይዞ የመጣ ሥርዓቷን ጠብቃ ስለምትገኝ ነው። እስቲ በቅዳሴው ስለ ሐዋርያዊቷ ቤተክርስቲያን ዲያቆኑ የሚያዜመውን ውብ ዜማ በማስተዋል እንየው፤ ዲያቆኑ እንዲህ ይላል ፦
“ፀልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት”
[Pray for the peace of the one holy apostolic church orthodox in the Lord]
{ ሐዋርያት ለሰበሰቧት ክብርት ስለምትሆን አንዲት ቤተክርስቲያን ጸልዩ}
ከዜማው እንደምንረዳው አንዲት ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊት ለመሆን 4 ነገሮችን
ማሟላት አለባት፤ የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ላዕለ ኩሉ /ከሁሉ በላይ ናት/ የቤተክርስቲያን ራስ ክርስቶስ ነውና። ኤፌሶን 1:22፤ እስቲ 3ቱን ቀሪዎች ከዜማው በመነሳት አንድ በአንድ እንያቸው፦ [ቀጣዩን ገጽ ይመልከቱ]
v 1) አሐቲ፦ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን አሐቲ ወይም አንዲት
ናት። በከተማ ትሁን በገጠር; ከአፈር ትሰራ ከወርቅ ፤ በአውሮፓ ይሁን በአሜሪካ; ይህች ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊት ከሆነች አሐቲ ናት ወይም አንዲት ናት። በጸሎተ ሐይማኖት ላይም ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን ብለን እንደምንጸልየው ማለት ነው።
“አንድ ጌታ አንዲት ጥምቀት አንዲት ቤተክርስቲያን እንደሚል” ኤፌ 4:4
v 2) ቅድስት፦ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር በደሙ
ያጸናት ቅድስት ናት። “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ጠብቁ እንደሚል” የሐዋ. 20:28 ቤተክርስቲያን ቅድስናዋን ማንም ሊያስቀርባት ወይም ሊያረክስባት አይችልም፤ ለምሳሌ በቤተክርስቲያን የሚቀድሰው ካህን ሰይጣን አስቶት የማይገባ ባሕርይ ቢኖረውና ወደ ቤተክርስቲያን ቢመጣ በካህኑ ምክንያት የሚሰጠው መንፈሳው አገልግሎት ዋጋውን ሊቀንስው አይችልም፤ ያ ካህን ልክ ቤተክርስቲያን ሲገባ አብሮት የነበረው ዲያቢሎስ ከውጭ ሆኖ ይጠብቀዋል እንጂ ወደ ውስጥ አይገባም፤ ልክ አገልግሎቱን ፈጽሞ ሲወጣ በዛ ባሕርይው ከቀጠለ ያም ዲያቢሎስ አብሮት ይቀጥላል ማለት ነው። ካህኑ ልክ እንደ ስልክ አገናኝ (operator) ነው፤ ስልክ የምታገናኘን ሴት ባሕሪዋ መልካም ባይሆን እንደምንም ታግሰን አላማችንን እንደምንፈጽመው ማለት ነው። ካህን ዘር እንደሚዘራ ገበሬ ነው ፤ ገበሬ በተበላሸ እጁ ዘር ቢዘራ የዘራው ዘር መብቀሉ አይቀርምና። ወደ ሃሳባችን ስንመለስ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር በደሙ ያጸናት ቅድስት ናት ብለናል; ልብ ብለን ካስተዋልነው ቅዱስ ደሙን በላዕለ መስቀል ላይ ያፈሰሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቅ/ጳውሎስም ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ መሆኑን ስለሚያውቅ “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ጠብቁ ብሎ በሐዋ. 20:28 ተናግሯል።
v 3) እንተ ሐዋርያት፦ ይህ ክፍል ዋናው የቤተክርስቲያን መሰረት ነው፤ ሐዋርያዊት የሆነች ቅድስት ቤተክርስቲያን ከሐዋርያቱ ጀምሮ እዚህ የደረሰችበት አመጣጧ እነሆ እንዲህ ነው፦
v ጌታ ለሐዋርያት አለቃ እንዲህ አለው; አንተ ጴጥሮስ ነህ በዚህ ዐለት ላይ
ቤተክርስቲያኔን እሰራለሁ…ማቴ 16:18፤ ቅ/ ጴጥሮስም ወንጌላዊው ማርቆስን አስተማረው; ቅ/ማርቆስም በግብፅ መንበሩን መሰረተ። ከማርቆስ ቀጥሎ አንያኖስ ከአንያኖስ 20 ፓትርያርክ ቀጥሎም አትናቴዎስ ተተካ፤ ይህ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ወደ ሃገራችን የመጣው
በፍሬምናጦስ ወይም በከሣቴ ብርሐን አባ ሠላማ አማካኝነት ነበር።
+ የፍሬምናጦስ ታሪክ እነሆ፦ ፍሬምናጦስ ኢትዮጲያዊ አልነበረም ፤ ጌታ ባረገ በ357 ዘመን አንድ ነጋዴ ከኢየሩሳሌም ፍሬምናጦስና ሲድራኮስ የተባሉ ሁለት ልጆችን ይዞ መጣና እንባቆም በተባለ አንድ ገበሬ ቤት ገብተው አደሩ። ከጥቂት ቀናት በሗላ አባታቸው ሞተ፤ ልጆቹም በእንባቆም ቤት መኖር ጀመሩ። ከእለታት በአንድ ቀን ፍሬምናጦስ የኢትዮጲያን ሰዎች ባህልና ሐይማኖታቸውን አደንቃለሁ; ነገር ግን ሥጋ ወደሙን ለምን አትቀበሉም? ብሎ ገበሬውን ጠየቀው; ያም ገበሬ ስንቅ አስይዞ በንጉስ ኢዛና ፈቃድ እስክንድርያ ሄዶ በሊቀጳጳሱ በአትናቴዎስ ተሹሞ ፓፓስ ሆነ። ስሙንም ከሣቴ ብርሃን አባ ሠላማ አለው /ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስታርቅ ማለት ነው/ ፍሬምናጦስም በእንዲህ ባለ መንገድ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽን ወደ ሃገራችን አምጥቷላ ማለት ነው። [ቀጣዩን ገጽ ይመልከቱ]
v [“ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ” // Apostolic Succession”]
ፍሬምናጦስ /ከሣቴ ብርሐን አባ ሠላማ/
ለማየት እንደሞከርነው ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊት የምትባለው ከጌታ ጀምሮ በሐዋርያቱ ቅብብሎሽ ስለምትመራ ነው። ይህም በእንግሊዘኛው Apostolic Succession ወይም ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ በመባል ይታወቃል።
v ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ በቅዳሴ፦ እስቲ በሚመጣው እሁድ ወንጌል ከመነበቡ
በፊት ካህናቱን ልብ ብለን እንስማ; እንዲህ ይላሉ፤ ገባሬ ሠናዩ ካህን ወይም ዋናው ካህን አስቀድሞ እንዲህ ይላል፦
His kingdom & his righteousness which he delivers to me I deliver to you
[ዘአወፈየኒ አወፈይኩከ] ወይም የሰጠኸኝን ሰጠሁህ
ካህኑ የሰጠኸኝን ሰጠሁህ ብሎ ወንጌሉን ለንፍቅ ካህን ወይም ለሁለተኛው ካህን ይሰጠዋል ፤ ሁለተኛው ካህንም ለዲያቆኑ ይሰጠዋል; ይህ ነው ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የሚባለው; ዋናው ካህን የጌታ ምሳሌ ሲሆን ሁለተኛው ካህን ደግሞ የቅ/ጴጥሮስ ምሳሌ ነው፤ ዲያቆኑም የምዕመናን ሁሉ ምሳሌ ነው ማለት ነው!! ወርቅ የሆኑ አበው ወርቅ የሆነ ሥርአትን ከተግባር ጋር አወረሱን!
ርትዕት ይእቲ ሐይማኖቶሙ ለቅዱሳን አበዊነ [የአባቶቻችን ሐይማኖት የቀናች ናት]
በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ; መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ፤ በእርሷም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላቹ [ኤር.6:16]
v ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የቤተክርስቲያን ዋና መሰረቷ ነው።
ለምሳሌ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ይህ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ስለሌላቸው ጥምቀቱም ሆነ ሌላው አገልግሎት ሐዋርያዊ አይደለም ማለት ነው። መንፈሳዊ አገልግሎትን ልንፈጽም የምንችልባቸው ሐዋርያዊት የሆኑ 5 እህትማማቾች ቤ/ተ/ክ ሲኖሩ ከምዕራቡ አለም በሐዋርያዊ ሥርአት ስለሚለዩ
ኦሬንታል ወይም ምስራቃዊ ይባላሉ።
5ቱ ሐዋርያዊት ኦሬንታል ቤተክርስቲያኖች
ሐዋርያዊት “ኢትዮጲያና ኤርትራ”
ሐዋርያዊት ግብፅ
ሐዋርያዊት ሶርያ
ሐዋርያዊት አርመንያ
ሐዋርያዊት ህንድ
(በነዚህ ቤተክርስቲያናት መቁረብና መጠመቅ ይቻላል)
[ቀጣዩን ገጽ ይመልከቱ]
ቤተክርስቲያንና // ፈተናዎቿ
v የመናፍቃኑ ፈተና፦ መናፍቃኑ ቤተክርስቲያን አያስፈልግም የእኛ
ሰውነት ራሱ ቤተክርስቲያን ነው ይላሉ። ነገር ግን ጌታ በወንጌል ላይ እንዲህ አለ፤
ቤትየ ቤተ ጸሎት ትሰመይ // ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል ማቴ 21:13
v የምንደኛ ልጆቿ ፈተና፦ምንደኛ የሚባሉት ለቤተክርስቲያን ታምኝ
ያልሆኑ ልጆቿ ናቸው፤ ሰው እናቱን በገንዘብ ይሸጣል እንዴ? እስከ ዛሬ አልተሰማም; ይሁዳ ብቻ ጌታውን በገንዘብ እንደለወጠ ተጽፏል። ይሁዳ ማለት ታማኝ ማለት ነበር; ነገር ግን እንደስሙ አልታመነም፤ እናቱን ቤተክርስቲያንን በገንዘብ የሚለውጥም ዳግማዊ ይሁዳ ይባላል። አንዳንዶቹ እኛ በሰለጠ አለም ነውና ያለነው ቤተክርስቲያን ትታደስ ይላሉ; በራዕ 15:3 ላይ የሰማይ መላእክት ሱራፌል የዘመሩበት በገና ይቅርና ኦርጋን ይሁን ይላሉ; በውጭው አለም ያሉ አንዳንድ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያንም ግማሹ ባለማወቅ ሌላውም እያወቀ አሜን ብለው ተቀብለዋል፤ መንፈስ ቅዱስ ይታደሳል እንዴ ቤተክርስቲያንን እናድሳት የሚሉት? የተፈጥሮ ሳይንስ dynamic ነው ይሻሻላል; ቤተክርስቲያን ግን ትላንትም ዛሬም ነገም አንዲትና ሐዋርያዊት ናት!!!
v ቤተክርስቲያንን መሳለም፦ አንዳንድ ሰዎች ቤተክርስቲያንን በእጃችን
እያበስን ስንሳለም ሊገርማቸውና ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ እንደሆነ አድርገው ሊቆጥሩ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከድንኳኑ ጀምረህ በውስጡ ያሉትን ንዋያተ ቅድሳትን በሙሉ ቅብዓ ቅዱስ ወይም ሜሮን ቀባና ቀድሳቸው እነሱን የነካም ቅዱስ ይሆናል። ዘጸ 30:22 እኛም የቤተክርስቲያንን ዘርፍ በእምነት የምንዳስሰው በዚህ ምክንያት ነው። 12 አመት ሙሉ ትደክም የነበረችው ሴት እምከመ ገሰስኩ ጽንፈ ልብሱ አሀዩ /በእምነት ሆኜ የልብሱን ዘርፍ ብዳስስ እፈወሳለሁ/ ብላ እንደዳነችው እኛም በእምነት የቤተክርስቲያንን ዘርፍ ብንዳስስ እንፈወሳለን። ጌታ የቤተክርስቲያን ራስ ነውና የልብሱ ዘርፍም ቤተክርስቲያን ናትና!!! ኤፌሶን 1:22
v ቤተክርስቲያን ከሙሴ እስከ አዲስ ኪዳን፦ በነሙሴ ዘመን ህንጻ
ቤ/ተ/ክ ስላልነበረ ህዝቡ ይገናኝ የነበረው በድንኳን ውስጥ ነበርና
የመገናኛ ድንኳን ይባል ነበር። ለመጀመሪያ ግዜ ህንጻ ቤተክርስቲያንን የሰራው ንጉስ ሰለሞን ሲሆን ይህ 46 አመት የፈጀው ቤ/ተ/ክ በአሁኑ ግዜ መስጊድ ተሰርቶበታል!! ከሰለሞን በመቀጠል ዘሩባቤልና ንጉስ ሄሮድስ ሰርተዋል። በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያ ቤተክርስቲያን በሆነችው በማርቆስ እናት በማርያም ባውፍልያ ቤት በላይኛው ፎቅ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያቱ ወረደ።
ከስደት መልስ እነ ሰለሞንንና ዘሩባቤልን ቤቱን እንዲሰሩ የረዳ እኛንም በስደት ሃገር ቤተ መቅደሱን እንድንሰራ የሠራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን ፤ አሜን
የሠራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ወደ ተራራ ውጡ እንጨትም አምጡ ቤቱን ስሩ እኔም በሱ ደስ ይለኛል እከበርበታለሁም ፤ ዘሩባቤል ሆይ በርታ ህዝቤ ሆይ በርታ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና ቤተ መቅደሴን ስሩ” ትንቢተ ሐጌ 1: 7።
[ቀጣዩን ገጽ ይመልከቱ]
እኔ ከዝግባ በተሰሩ ቤተመንግስቴ እየኖርኩ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል። 2ኛ ሳሙኤል 7:2 ፤ ዳዊት ስለእኛ የተናገረው አይመስላችሁም? ምን አልባት እኛ በተመቸ ቤት እንኖር ይሆናል; የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል።
“ህዝቤ ሆይ በርታ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና ቤተ መቅደሴን ስሩ”
ትንቢተ ሐጌ 1: 7
ስሜ ለዘለአለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤተ መቅደስ መርጫለሁ ቀድሻለሁም፤ በቤቴ የሚጸለየውን ጸሎት ዓይኖቼ ያያሉ ጆሮዬም ያደምጣሉ።
|
2ኛ ዜና 7: 15
|
በቅድስናው ስፋራ ለእግዚአብሔር ስገዱ
|
መዝ 28:2
|
አንተን በመፍራት በመቅደስህ እሰግዳለሁ
|
መዝ 5:7
|
ወደ ቤተ እግዚአብሔር እንሂድ ሲሉኝ ደስ አለኝ
|
መዝ 121(122):1
|
እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት
|
መዝ 150:1
|
ከተቀደሰው መቅደስህ በረከትን እንጠግባለን
|
መዝ 64(65):4
|
ለአይኖቼ መኝታ ለሽፋሽፍቴም ረፍት አልሰጥም ለእግዚአብሔር ስፍራ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያ እስካገኝ ብዬ
|
መዝ 131:3
|
የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ መቅደሱ አምጥታቹ ቤተ መቅደሱን ስሩ
|
1ኛ ዜና 22:19
|
እግዚአብሔር ለዘላለም ወደ ቀደሰው መቅደሱ ኑ
|
2ኛ ዜና 30:8
|
አቤቱ በተቀደሰው መቅደስህ የልመናን ከንፈር ስማ የንስሐን እንባንም ተቀበል
|
2ኛ ዜና 6:36
|
ቤቴ ለህዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ይባላል
|
ኢሳ 56:7
|
እለት እለት የሚያስጨንቀኝ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው
|
2ኛ ቆሮ 11:28
|
ዋዕናቅጸ ሲኦል እይሔይልዋ //
የሲኦል ደጆች አይችሏትም
|
ማቴ 16:18
|
ለቤተክርስቲያናችን “ሰላም ክብርና ሞገስ”
ለዘለዓለም ይሁን አሜን!!!
የእግዚአብሔር ቸርነት ከሃገራችን “ከኢትዮጲያና - ኤርትራ” አይለይ አሜን!
[ተክለ መድህን]
No comments:
Post a Comment