የልጅ ዮናስ ቀልድ እና ቁም ነገር!

“ሁለት ቀን ለመኖር አራት ቀን አትጨነቅ” ..... "አሁን ገና በራልኝ አለች እብድ ቤትዋን አቃጥላ!!" ዘና ብላችሁ ተቀመጡና አንድ አሪፍ ታሪክ ላውጋችሁ! (ዘወትር ቅዳሜ ይጎብኙን)

Thursday, 1 August 2013

የህጻናት ጥምቀት

በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት እና በፕሮቴስታንቶች በጥምቀት ላይ ያለ ልዩነት

በጥምቀት ላይ ያለው ልዩነት በአምስት ከፍለን ሊጠቃለል ይችላል እነዚህም ፡-

1. በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት በጥምቀት ድህነትን፣ መንጻትን፣ ፍትህን፣ አዲስ ሕይወትንና በክርስቶስ ክርስቲያን መሆንን ያስገኛልን ወይስ እንደ ፕሮቴስታንት እምነት እነዚህ ሁሉ በማመን ብቻ ይገኛል; በማመን ብቻስ ከሆነ ለምን መጠመቅ ያስፈልጋል ታድያ

2. መጠመቅ የክርስቲየን ምልክት ነው ወይስ ጌታ ስላዘዘ ብቻ ለትዕዛዙ ሲባል ነው፡፡ የምንጠመቀው /ማቴ.28፣19/

3. እኛ ጥምቀትን ከሚሰጥራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ነው ብለን እናምናለን ፕሮቴስታንቶች ግን ይህንን አያምኑም፡፡

4. እኛ ውሀ ውስጥ እናጠምቃን እነርሱ ግን በመርጨት ያጠምቁም፡፡

5. እኛ ህፃናን ስለቤተሰቦቻቸው እምነት እናጠምቃለን፣ ፕሮቴስታንቶች ግን ሕፃናትን በማጥመቅ አያምኑም ምከንያቱም ሲሰጡ ‹‹ከጥምቀት ማመን መቅደም አለበት›› ይላሉ፡፡

የፕሮቴስታቶች የተቃውሞ ነጥቦች

1. ጥምቀት ባይኖር እምነት ብቻውን አይበቃምን?

2. የተሰቀለው ወንበዴ/ፈያታዊ ዘየማን/ሳይጠመቅ እንዴት ዳነ?

3. ውሃ ልጅነት አዲ ሕይወትን ሊሰጥ ይችላልን?

4. ጥምቀት የሕይወት መታደስ ከሆነ ለምን ደግመን እንበድላለን? /ኃጢያት እንሰራለን/

5. አንድ ሕፃን ከተጠመቁና ኃጢያታቸው ይቅር ከተባለላቸው ቤተሰቦች ከተወለደ የቤተሰቦቹን ኃጢያት እንዴት ሊወርስ ይችላል

6. ሐዋያት ስለክርስቶስ እና ስለ ቤተክርስቲያን ግንኙነት ሲገልጽ ባሎች ሆይ ክርስቶስ ደግሞ ቤተክርስቲያን እደወደዳት ሚሰቶቻችሁን ውደዱ በውሃ መታጠብ ከቃሉ ጋር አንፅቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፡፡ /ኤፌ ተ፣26/ ይላል፡፡ ታዲያ በጥምቀት ያው ውሃ የቃል ተምሳት ነውን?

ሕፃናትን ማጥመቅ

የጌታችንን ‹‹ ያመነ የተጠመቀ ይድናል›› የሚለውን ቃል በመንተራስ ፕሮቴስታንቶች ከማጥመቅ ይልቅ እምነት ይቀድማል በማለት ሕፃናጽን አያጠምቁም፡፡ ታዲያ ጥምቀት ያለ እምነት እምነትና እውቀት እንዴት ይከናወናል

እኛ ግን ሕፃናት እንዲጠመቁ እንላለን፡፡ ምክንያም፡-

ሀ. እኛ የምናስበው ስለ ሕፃና ሰማያዊ ሕይወት ነው፡፡ የኸውም ጌታችን ‹‹እውነት እልሃለሁ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡›› /ዩሐ.3.5/ ስላለ ነው፡፡ ታዲያ ስለምን ሕፃናትን አናጠምቅም? ስለምንስ ለእግዚአብሄር ፍርድ አሳልፈን እንሰጣቸዋለን? ጌታችን የላይኛውን ኃይለ ቃል ሲናር ሕፃናትን አልተወም፡፡

ለ. በማጥመቅ ሕፃናት የቤተ ክርስቲያን ሕይወት ይለማመዱታል፡፡ በጥምቀት መንፈሳዊ ጥቅም እና፣ የሰማያዊውን ምስጢር ደስታ ያገኛሉ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ፀጋን የሚያሰጡ ምስጢራትን ውጤታቸውን በሕይወታቸው ይቀምሱታል፡፡ እኛም በዚህ መንገድ ሕፃናን ለክርስትና ሕይወት በተግባር እንዲዘጋጁ እናደርጋቸዋለን፡፡ ከቤተ ክርስቲያ ካገለልናቸው ግን እምነትንና የፀጋ ምክንያቶችንም መከልከላችን ነው፡፡

ሐ. ‹‹ ያመነና የተጠመቀ ይድናል›› የሚለው የጌታ አባባል የጎልማሶችን እምት የሚያመለክት ነው፣ ምንያቱም ጎልማሶች ሊያመዛዝኑ ስለሚችሉ ነው፡፡ ስለዚህም ነው እኛ ጎልማሶችን ካላመኑ የማናጠምቃቸው፣ ለሕፃናት ግን ‹‹ሕፃናትን ተውአቸው ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው፡፡ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና፡፡›› /ማ.19.14/ የሚለው የቤታችን ቃል ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ከእምነት አንፃር ሕፃናት ሁሉንም ነገር ሊቀበሉና ሊያምኑ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ነው ያሉት፣ እምነትን አይቃረኑም ወይም አንቀበልም አይሉም፡፡ በጎልማሶች ነው እንጂ በዓመ ሕፃና መጠየቅና መጠራጠር የለም፡፡ ይህም ከሰማያዊ መንግሥት አያግዳቸውም እነርሱን ማጥመቅ ‹‹ነፃ ድህነት ‹‹ ብለው ከሚያስተጋቡት ከወንድሞችን ከፕሮቴስታንቶች መፈክር ጋር የሚስማማ ነው፡፡

መ. በእምነት ጉደይ ላይ በአነጋገር ጥብቅ ከሆንን፣ የእምነትን ጥልቀትና ምንነት ሊረዱ የማይችሉ እጅግ ብዙ ሰዎችን ለምሳሌ በአእምሮ ያልበሰሉ ጎልማሶችን ያልተማሩ ገበሬዎችን ወዛደሮችን እና ወዘተ . . . ነገረ መለኮታዊ እውነታዎችን ሊያውቁ የማይችሉ ሰዎ የቱ ድረስ ነው የእምነታቸው ሁኔታ ታድያ እንደ ሕፃናት መጠመቅን ልንከለክላቸው ይገባልን? ብለን እንጠይቃን፡፡

ሠ. አንዳዶች ሕፃናት ሲያድጉ እምነቱን ቢተውትስ? ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ያ ሕፃን እንደ ከሃዲ ይቆጠራል ምክያቱም በጥምቀት የተቀበለውን ፀጋ በነፃ ፈቃዱ ክዷል፡፡ እኛ ግን ስለሱ ያብንን ግዴታችንን ተወጥተናል፡፡ ሌላው ጉዳይ ሁሉ ለእርሱ የሚተው ነው፡፡ ‹‹እርሱም በመንፈስ እንደ ጀመረ አሁን ደግሞ በስጋ ሁሉን ለመፈጸም እንደሚሞክር ሆኖአል፡፡ እንግዲህ የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁን? /ገላ.33/እንዳ ሐዋርያው ምናልባትም የተጠመቁና ሕይወታቸው በቤተክርስቲያን የሆነ ትንሽ ሕፃናት የእግዚአብሔር ፀጋ ስለ ቀመሱ፣ እስኪያድጉ ድረስ ትንንሽ ሕፃናት የእግዚብሄር ፀጋ ስለ ቀመሱ፣ እስኪያድጉ ድረስ ካልተጠመቁት ይልቅ ለክህደት ብዙ የተጋጡት አይሆኑም፡፡

ረ. ሕፃናትን ማጥመቅን የማያምኑ፣ በርግጥ በጥምቀት መዳን እንደሚገኝ የሚክዱ ናቸው/ ማር.16.16/ ምክንያቱም ጥምቀት ለመዳ እንደሚያስፈልግ ቢያምኑ ኖሮ ሕፃናትን ከድኅነት ባለከለከሏቸውም ነበር፡፡ ደግሞ እምነት የሌላቸው ስለሆነ ያላመኑትና ያልተጠመቁት ሕፃናት መድረቸው የት ነው? ጥያቄው መልስ የለውም

ሸ. መጽሐፍ ቅዱሰ ይህን ስለሚያመለክት እኛ ሕፃና እናጠምቃለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሙሉ ቤተሰብን መጠመቅ ወይም አንድ ሰው ራሱና ቤተሰቡ ሁሉ ሲጠመቁ ያለክታ፡፡ ታዲያ በነዚህ ቤተሰቦች ውስጥ ሕፃናት እደነበሩ ምም ጥርጥር የለውም፡፡

እነዚህ ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው፡፡

- በፊሊጲያ ለወኀኒ ጠባቂው ቅዱስ ጳውሎስና ሊላስ ‹‹ በጌታ ኢየሱ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተሰቦችህም ትድናላችሁ/ ሐወ.16፣315/ አሉት፡፡ ይህ ማት የጠባቂው እምት የመጀመሪያ እምነት ሆኖ ቤተሰቡን ወደ ድኃነት ይመራ፡፡ ከዚያ በኃላ ነው ‹‹ለእርሱና በቤቱም ላ ሁሉ የእግዚአብሄርን ቃል ተናገሩላቸው፡፡ በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቁስላቸውን አጠበላቸው ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተሰቦቹ ጋር ተጠመቀ፡፡›› /የሐዋ.ሥራ 16፣32/ የተባለው፡፡ መጽሐፍ ቅዱ ከወኀኒ ጠባቂው ቤተሰብ ሕፃናትን ያለጥርጥር ቸምሮ ነው፡፡

• የቀይ ሃር ሻጭዋ የሊዲያ ጥምቀት ‹‹ እርሷ ከቤተሰቦቿ ጋር ከተጠመቀች በኃላ ‹‹/የሐ.ሥራ 16፣15/ተብሎ ተጽፏል፡፡

• ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የእስጢፋስንም ቤተሰቦዎች ደግሞ አጥምቄአለሁ ጨምሬ ሌላ አጥምቄ እንደሆነ አላውቅም›› /1ኛ ቆሮ.1፣16/አለ ታዲያ እነዚህ ሁሉ ቤተሰቦች ያለ ሕፃን ይሆናሉ?

• በእለተ ጴንጤቆስጤ ከተጠመቁት መካከል ህናፃና ያለመኖራቸውን መጽሐፍ ቅዱስ አያመለክትም፡፡

በታሪክም ህፃናትን ማጥመቅ ተጽፎ ይገኛል፡፡ ስዚህም በቅዱስ ወይንስ የተወለደ?/ የተደረገውን ክርክር እንጠቅሳለን፡፡ ቅዱስ አውግስቲን ከሰው የሚወለድ ነው ›› አለ፡፡ ቅዱስ ጀሮም ደግሞ ‹‹የሚፈጠር›› ነው አለ፡፡ ቅዱስ አውግስቲንም የሚፈጠር ከሆነ የአዳምን ኃጢያት አይወርስም፡፡ ስለዚህ ለምን ህፃናትን እናጠምቃን? ሲል ጠይቆታል፡፡ ቅዱስ ጀሮም ለዚህ ሊመልስ አልቻለም፡፡

ሕፃናትን ማጥመቅ የሚከለክል አንድ ጥቅስ እንኳን በመጽሐፍ ቅዱስ የለም፡፡

ከእምነት አንፃር፣ ሕፃናትን ስለቤተሰቦቻቸው እምነት እናጠምቃለን፡፡ ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ምሳሌዎች አሉት ለምሳሌ፡-

ሀ. የኦሪቱ ግዝረት የጥምቀት ምሳለ ነው ቀድሞ እንደገለጽነው የተገረዘው ከእግዚአብሔር ሕዝብ ይቆጠር ነበር ምክንያቱም በእግዚአብሔርና በአብርሃምና መካከል በተደረገው ኪዳ መሰረት ‹‹የሸለፈታችሁንም ሥጋ ትገርዛላችሁ በእኔና በእናነተ መካከል ላለው ቃል ኪዳኔ ምልከት የሆናል፡፡ ተብሎአል፡፡ /ዘፍ.7፣11/ ይህም ግዝረት የሚደረገው ሀፃኑ ከተወለደ በ89 ቀን መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ታዲያ በአብርሃምና በእግዚአብሔር መካከል ስላለው ኪዳ የ80 ቀን ህፃን ም ያውቃልን? ከእግዚአብሔር ህዝብ ጋር አንድነት መደመሩንስ ያውቃልን? ስለተስፋውስ ምን ያውቃል? ያጥርጥ እንዲህ ያለ ነገር አያውቅም፡፡ ነገር ግን ስለቤተሰቦቹ እምነት ተገርዞ የእግዚአብሔር ሕዝብ አባልና እግዚብሔር ለአባታችን ለአብርሃም የሰጠው የተስፋው ቃል ተካፋይ ይሆናል፡፡

ለ. ቀይ ባህርን መሻገር የጥምቀት ምሳሌ ነበር፣ ወይም ደግሞ በራሱ ጥምቀት ነበር ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ ‹‹ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ \ዘንድ በደመናና በባህር ተጠመቁ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ፡፡›› 1ኛ ቁሮ.10፣2/በማለት እንዳስረዳው፡፡ ይኸውም ከሞ ከሰይጣንና ከኃጢያት ባርነት የመውጣት ምሳሌ ነው፡፡ ቀይ ባህርን የተሸገሩ ጎልማሶች ናቸው፡፡ እነርሱም እግዚአብሄር ለሙሴ የሰጠውን ተስፋ ጠንቅቀው ያውቁ ነበር፡፡ ለፈርኦን ባሮች እንደነበሩም፣ ከባነት በኃላ በእግዚአብሄር ኃይል መዳናቸውንም ጭምር ያውቃሉ ሕፃናቱም ቀይ ባህርን በተሻገሩ ጊጊ/ሲጠመቁ/ ድነዋል፣ ከባርነት ነፃ መጥተዋል፣ ተጠምቀዋል፡፡ ታዲያ ይ የተደረገላቸው በራሳቸው እምነት አልነበረም ነገር ግን በቤተሰቦቻቸው እምነት ነው እንጂ፣ ምንያቱም እነዚህ ህፃናት የተፈጸሙትን ሁኔታዎች አያውቋቸውም እነዚህ ህጻናት የተፈጸሙትን ሁኔታዎች አያወቀቋቸውም፡፡

ሐ. ሌላው እጅግ ጠቃሚ ምሳሌ በፋሲካው ጠቦት ደም የህፃናተ መዳን ነበር፡፡ ይኸውም በኩርን ከሚገድለው መልአክ እጅግ ይድኑ ዘንድ እግዚአብሄር ሙሴን የአንድ አመት ነውር የሌለበት ወንድ ፍየል ወይም በግ እንዲያርድና ደሙንም በበሮቻቸው መቃንና ጉበን እንዲቀቡት አዘዛቸው፡፡ ‹‹ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፡፡››/ዘጸ.12፣13/ አላቸው፡፡

- ሐዋርያው የጠቦቱ ደም ድኀነት ያገኘንበት የኢየሱ ክርስቶ ደም ምሳሌ መሆኑ ‹‹ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷልና››/1ቆሮ.5፣5/ በማት አስረዳን፡፡

- ፋሲካው በግ ደም የዳኑት የነዚህ ህፃናት እምነት ምን ነበር? በጌታና በሙሴ መካከል ስለነበረው ኪዳን ወይም ስለፋሲካና በፋሲካው በግ ደም ከሞት ስለመዳን ምንያውቃሉያለጥርጥ ምንም አያውቁም፡፡ ነገር ግን ስለደሙ ጥቅም የፋሲካው በግ ደም ከሞት እንደሚያድን ቤተሶበቻቸው ስላመኑ ህፃነቱ ከሞት ድነዋል፡፡ በመገረዝ በፋሲካው ደምና ታላቁን ባህር በመሻገር የዳኑ ህጻናት እንዚህ ሁሉ ም መሆናቸውን ካደጉ በኃላ አውቀዋቸዋል በመሆኑም ድኅነትን ያለዋጋ ቀድመው አግኝተዋል፡፡

- ቤተሰቦቻቸው በእግዚአብሔር እና በሰዎች መካል በተደረጉ ተስፋዎችና ቃልኪዳኖች ስላመኑ ልጆቹም ሲያድጉ ወደ እምነቱ በተግባር ገብተዋል፡፡

(አንጻራዊ ትምህርተ መለኮት)
Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 03:53 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Wednesday, 31 July 2013

ፕሮቴስታንት ሆይ ከ0-18 ዓመታችሁ አህዛብ ናችሁ?





አህዛብ ማለት እንደ አብርሐም አባት እንደ ጣዖት አምላኪው ናኮር ፈጣሪውን የማያውቅ ማለት ነው። አህዛብ ማለት ጣዖት የማያምን ፈጣሪውንም የማያምን እምነት የለሽ ማለት ነው። ፕሮቴስታንት ህጻናት ጌታን ያውቁታል ግን አያምኑትም! አህዛብ ናቸውና! አንድ በሽተኛ መድኃኒቱን እያወቀ መድኃኒቱን እስካልተቀበለው ድረስ በሽተኛ ነው። መድኃኒቱን ማወቁ ብቻ አያድነውምና! አንድ ጴንጤ መድኃኒት የተባለውን ኢየሱስን አውቆ ነገር ግን አያምንበትም። በሽተኛው መድኃኒቱን እስከሚቀበል ድረስ በሽተኛ እንደሚባል ሁሉ ኢየሱስን እስከሚቀበሉ ድረስ እንደ በሽተኛው ተቆጥረው አህዛብ ናቸው ማለት ነው። መድኃኒቱን አውቀዋለሁ ግን አድጌ ወንጌል ካላነበብኩ ሰው ካልሰበከኝ አላምነውም ይላሉ። ፕሮቴስታንት ልጆች ሲታመሙ ነፍስ አውቀው ስለ መድኃኒቱ አንብበው ሰምተው ነው መድኃኒቱን የሚቀበሉት? እኔ የምለው 2 ዓመት የሆናቸው ፕሮቴስታንት ህጻን ሳያምኑ የሚሞቱት እጣ ፋንታቸው ምን ይሆን? ሄሮድስ የገደላቸው 2 ዓመት የሞላቸው ህጻናት ደማቸው ደመ ጥምቀት ሆኖ ድነዋል። እነዚህ ህጻናት ፕሮቴስታንት ቢሆኑ ክርስቶስን አያምኑምና እጣ ፈንታቸው ምንድን ነው? ክቡራን ሆይ ነፍስ እስከምታውቁ ድረስ አህዛብ ናችሁ እንዴ? ፕሮቴስታንት ልጆች እንዳሉ የማያምኑ አህዛብ ናቸው ለካ? ከልጅነት ጀምሮ ሁሉም ያውቁኛል ያለ ፈጣሪ የህጻናትም አምላክ ነው! እባካችሁ ሰውን ሳይሆን የገዛ ሕሊናችሁን ስሙ። ከልጅነት ጀምሮ ሁሉም ያውቁኛል ብሏልና ህጻናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው እንዳለ እነሆ ህጻናቱ ሆሳዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ። የዘመናችን ሰዎች ደግሞ እነዚህ ሁሉ ህጻናት ጌታን አያምኑም አሉን። እንግዲያውስ ክርስቶስን ካላመኑ ልጆቻችሁ አህዛብ ናቸው አይደል? ፕሮቴስታንት ሆይ ከ0-18 ዓመታችሁ አህዛብ ናችሁ?

http://yonas-zekarias.blogspot.co.uk/
Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 03:15 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

ሞኝና ውኃ እንደወሰዱት ይሄዳል አሉ!



በመጽሐፍ ቅዱስ ልቤን የሚነካ አንድ ታሪክ አለ። በሉቃስ ወንጌል የጠፋው ልጅ ታሪክ ደስ ይላል። ሞኝና ውኃ እንደወሰዱት ይሄዳል እንዲሉ ጓደኞቹን ሰምቶ ከአባቱ ቤት ወጣ። ጠፍቶ አልቀረም አባቱ ቤት ገባ! ጠፍተን ያገኘን በቤቱም ያስገባን ቸር አባታችን ክብር ለእርሱ ይሁን! 

ወደ ጥያቄ እንግባ፦

ሉቃስ ወንጌል 15

4 መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?
5 ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፤
6 ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ። የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል።
7 እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።
8 ወይም አሥር ድሪም ያላት አንድ ድሪም ቢጠፋባት፥ መብራት አብርታ ቤትዋንም ጠርጋ እስክታገኘው ድረስ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት?
9 ባገኘችውም ጊዜ ወዳጆችዋንና ጐረቤቶችዋን በአንድነት ጠርታ። የጠፋውን ድሪሜን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ትላቸዋለች።
10 እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።

ፕሮቴስታንት ዘመዶቻችንን ጥያቄ እንጠይቅ፦

/1/ ኢየሱስ ክርስቶስ ((ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን)) ንስሐ በሚገባ ((በአንድ ኃጢአተኛ)) በሰማይ ደስታ ይሆናል ብሏል። ፕሮቴስታንት ዘመዶቻችን ደግሞ ሁላችንም ጻድቃን ነን ትላላችሁ፤ ጌታ እንዳለው ከመካከላችሁ ንስሐ የማያስፈልገው ጻድቅ ማን ነው?

/2/ ሁላችንም ጻድቃን ከሆንን ((ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ)) ንስሐ በሚገባ ((በአንድ ኃጢአተኛ)) በሰማይ ደስታ ይሆናል ማለት ምን ማለት ነው?

/3/ ክርስቶስ እንዳለው ንስሐ የማያስፈልጋቸው 99 ጻድቃን እነማን ናቸው? ንስኃ የማያስፈልጋቸው ለምንድን ነው? ንስኃ የሚያስፈልገው አንድ ኃጥዕ ማን ነው?
Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 03:12 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

ዘንዶ

http://yonas-zekarias.blogspot.co.uk/

የዮሐንስ ራእይ 12
1 ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።
2 እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች።
3 ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥
4 ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።
5 አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።
6 ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች።

13 ((ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።))
14 ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።

ከመልስ በኋላ ሐሳብና ጥያቄ እንቀበላለን።

((ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።))

/1/ ወንድ ልጅ የተባለው ማን ነው?

/2/ ወንድ ልጅ የወለደችው ሴት ማን ናት?

/3/ ሴቲቱን ያሳደደው ዘንዶ ማን ነው?

http://yonas-zekarias.blogspot.co.uk/

Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 03:10 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Tuesday, 30 July 2013

ለገንዘብ የተጋደሉ

ለሀብት ንብረት ለገንዘብ የተጋደሉ ሰዎች ነበሩ። ለጌታቸው ፍቅር የተጋደሉ ሰዎችም ነበሩ። ለገንዘብ የተጋደሉት ለክርስቶስ የተጋደሉትን ሲሳደቡ አየሁ። ይህ ተጋድሎ ዛሬም ወደ ፊትም ይቀጥላል አሉ። ጌታ ሆይ ገንዘብ የመንግሥተ ሰማይን በር አይከፍትምና ለእነዚያ ሰዎች ነፍስ እጅጉን ፈራሁ። አቤቱ ሆይ ለገንዘብ ያይደ ለ ለፍቅርህ ከተጋደሉት ጋር ደምረን ፤አሜን!
Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 05:25 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

//ኦርቶዶክስ ተዋህዶ//



ሐዋርያው ደም ሳይፈስ ስርየት የለም ይላል! የክርስቶስ ደም የአምላክ ብቻ ነው ከቶ አንልም። ከእመቤታችን የነሳው እንደሆነ እናውቃለንና መለኮትም ደም የለውምና። ድህረ ተዋህዶ የክርስቶስ ደም የሰው ብቻ ደም ነው አንልም። ይህ የከበደ ክህደት ነውና! የሰው ደም አዳነኝ ማለት ነውና፣ የሰው ደም ሲዖልን ከፍቶ ፍጥረት ሁሉ የዘላለም ሕይወት አገኘ የሚል ማን ነው? በአጭሩ ቃል ሥጋ ሆነ ማለት ቃል ወደ ስጋ ተለወጠ ማለት ነውን? በተዋህዶ ቃል ሥጋ ሆነ ! እንግዲያውስ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም የአምላክ ነው ወይስ የሰው? ብዙዎች መመለስ አልቻሉም። ተዋህዶን ስለማይቀበሉ በእርግጥ መልስ የላቸውም። በተዋህዶ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ደም አዳነን!

ፕሮቴስታንት ዘመዶቻችን ቃልና ሥጋ አልተዋሃደም ብለው ያምናሉ። ቃል ራሱን ጠብቆ ቃል ነው፣ ሥጋም ራሱን ጠብቆ ሥጋ ነው ይላሉ። ከክርስቶስ ልደት በፊት ቃል ነበረ፣ ክርስቶስ ሲወለድ ቃል ነው እንጂ ሥጋን አልተዋሃደም ይላሉ፣ ከክርስቶስ ዕርገት በኋላም ቃል ነው ብለው ያምናሉ። ታድያ ቃል ሥጋ የሆነው መቼ ነው?
Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 05:23 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

ሹርባ ልትሰራ ሄዳ ፀጉሯን ተላጭታ መጣች



1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11

10 በዚህ ምክንያት፣ በመላዕክት ምክንያት ፣ ሴት በሥልጣን ስር መሆንዋን የሚያሳይ ምልክት በራስዋ ላይ ታድርግ። (መላዕክት ሥርዓትን ነቅተው ስለሚጠብቁ በቅዳሴ ላይ ሴቶች ፀጉራቸውን ይከናነባሉ) 

በእስራኤል ባህል አንዲት ልጅ ጸጉርዋን ካሳየች ድንግል አይደለሁም ማለትዋ ነው። የዘመናችን ሴቶች ፀጉራቸውን ፈርዘው ሲሰብኩ አይተናልና ምን እንበል? ኢስላም እንኳን ጸጉሩን ተከናንቦ ሲሄድ ኢየሱስን እንሰብካለን የሚሉ ዘመዶቻችን ምነው ልታይ ማለት ወደዱ? እንግዲህ ማንም በዚህ ጉዳይ ላይ //መከራከር// የሚፈልግ እኛም ሆነ ቤተክርስቲያን እንዲህ ያለ ልማድ የለንም። (1ኛ ቆሮንቶስ 11፦16)

ሐዋርያው ሴት ልጅ ጸጉርዋን የማትሸፍን ከሆነ ትቆረጥ ይላል። ለሴት ልጅ ፀጉርዋ ክብሯ ነው ሽልማትዋ ነው ውበትዋ ነው! ይህን የከበረ ፀጉሯን ሹርባ ልትሰራ ሄዳ ፀጉሯን ተላጭታ ከመጣች ግን ክብሯን ሽጣ መጣች ይባላል። መላጣ ሴት ከጸጉራም ሴት በክብር ትለያለች። እስኪ የሰው ክብር ልዩነቱን እንይ፦

/1/ ሁላችንም በኢየሱስ ስላመንን ቅዱሳን ነን ብላችኋል። እንግዲያውስ እኔም ከጴጥሮስ እኩል ቅዱስ ከሆንኩ እንደ ጴጥሮስ ጥላዬ በሽተኛ መፈወስ ለምን አቃተው? ዮናስ = ጴጥሮስ ለምን አልተባለም?

/2/ ወንጌላዊው ሉቃስ ስለ ማርያም ሲናገር እንዲህ አለ፦ ሁሉን በልብዋ ትጠብቀው ነበር። በልብዋ መጠበቅዋን ማን ነግሮት ይሆን? በልብዋ ትጠብቀው አትጠብቀው እንዴት አወቀ?

/3/ ጴጥሮስ ጥላው ድውይ ፈወሰ ለጳውሎስ የልብስ ቁጨት ተዓምር ሰራ ሲባል ሰምተናል። እኛስ ለምን በጥላችን በሽተኛ አንፈውስም? ባህር መክፈል ሰማይ መዝጋት ፀሐይ ማቆም ሙት ማስነሳት ለምን አቃተን?

Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 05:22 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Friday, 26 July 2013

ሚካኤል

‹ያዳናቸውን እግዚአብሔርን ረሱ፡፡ እንዳያጠፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ፡፡›› የተሰመረበትንና ደምቆ የተጻፈውን ኃይለ ቃል ልብ ብለህ ተመልከት፡፡ (መዝ015.23) ባይቆም ኖሮ ሲል ባያማልዳቸው፣ ባይለምንላቸው፣ ባይጸልይላቸው ኖሮ ማለቱ ነው፡፡ ስለዚህ መቆም የሚለው ቃል ማማለድ የሚል ትርጉም እንደሚኖረው እንረዳለን፡፡

ዳግመኛም መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች (መላእክት) በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ፡፡ ሰይጣንም ደግሞ በመካከላቸው መጣ›› ይለናል፡፡ ‹‹ለመቆም›› ሲል ለመለመን፣ ለማማለድ ማለት ነው፡፡ አብሮአቸውም ሰይጣን መምጣቱን ልብ በል፡፡ ሰይጣን የመጣው ለምን ነበር? ጻድቁ ኢዮብን ለመፈተን ፈቃድ ያገኝ ዘንድ ፈጣሪውን ለመለመን አልነበረምን? የመላእክትም አመጣጥ ፈጣሪቸውን ስለሰው ለመለመን እንጂ ለሌላ አልነበረም፡፡ ይህን ሲገልጥ ‹‹ለመቆም መጡ›› ይለናል፡፡ መቆም መለመን፣ ማማለድ ማለት ነውና፡፡ (ኢዮ1.6)

መቆም ማለት መጸለይ፣ ማማለድ የሚል ፍቺ እንዳለው ካስጨበጡ በኋላ ይህንን ቃል በመጠቀም የመላእክትን አማላጅነት ማስረዳት ቀላል ይሆናል፡፡

ቃላት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እኛ ከምናውቀው ውጭ አንዳንድ ጊዜ በተቃራኒ አቅጣጫም እንኳን ፍቺ ይዘው ይገኛሉ፡፡ አገባባቸውን እንደመጽሐፍ ቅዱስ ዘይቤና ምሥጢር መማር የሚያስፈልገው ከዚህ የተነሣ ነው፡፡ ለብዙ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ የተቀመጡ ቃላትን ትክክለኛ መንፈስ አለመረዳት የመላእክትን አማላጅነት እንዳይረዱ አድርጓቸዋልና፡፡

ለምሳሌ፡- ቅዱስ ገብርኤል ራሱ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መልአኩ ገብርኤል ነኝ፡፡›› በማለት ተናግሯል፡፡ ይህም በቅዱስ ወንጌል የተጻፈ ኃይለ ቃል ሲሆን አብዛኞቻንን እናውቀዋለን፡፡ ልዩ የሚሆነው ግን የቃሉን ትክክለኛ አገባባዊ ትርጉም ባለማወቃችን ምክንያት መልአኩ ይህን ባለ ጊዜ ‹‹እኔ አማላጅ ነኝ›› እንዳለን አድርገን አለመረዳታችን ነው፡፡ መቆም ማለት ማማለድ የሚል ትርጉም ካለው ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የምቆም›› ማለት ደግሞ ‹‹የማማልድ›› ማለት መሆኑ አይጠረጠርም፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ገብርኤል አማላጅነቱን ራሱ ግልጽ በሆነ መንገድ ነግሮናል ማለት ነው፡፡

እስኪ እናንተ ፍረዱ! በዚህ ስፍራ ቅዱስ ገብርኤል አማላጅ ነኝ ማለቱን ካላመንን ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው›› ማለቱን ምን ብለን እንረዳዋለን? የእግዚአብሔር ፊቱ ወደ ሁሉም አቅጣጫ ነው እንጂ እንደፍጡር ወደ አንድ ገጽ የተወሰነ አይደለም፡፡ መላእክት ደግሞ በተፍጥሯቸው እንደ ሰው ልጅ የሚታጠፍና የሚዘረጋ እግረ ሥጋ ስለሌላቸው አይቀመጡም፤ አይተኙምም፡፡ ታዲያ አማላጃችሁ ነኝ ማለቱ ካልሆነ በቀር መልአኩ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው›› ሲል ምን ማለቱ ነው? መልአኩ እግዚአብሔርን እንደ ምድራዊ ንጉሥ ራሱን ደግሞ እንደ ንጉሥ ወታደር ቆጥሮ በንጉሡ ፊት ቀጥ ብዬ የምውል ዘበኛ ነኝ ማለቱ ነውን? በፍጹም አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ቤት ደጅ አፍ መቆምና በእግዚአብሔር ፊት መቆም ሁለት የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ምሥጢራቸውም እንዲሁ የተለያየ ነው፡፡ (ራእ21.12፤ ዘፍ3.24) ይልቅ ሊሆን የሚችለው እኔ በፊቱ ባለሟልነት ያለኝ ሁሉ ጊዜ ስለ እናንተ የማማልድ ነኝ የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

መልአኩ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ለምንድን ነው? ለማመስገን ነው እንዳንል ይህንን ሐሳብ ለካህኑ ለዘካርያስ መንገር ለምን አስፈለገው? የሚል ጥያቄ ያስነሣል፡፡ ትርጉሙ እንዲህ ቢሆን ወደ ካህኑ ወደ ዘካርያስ ከመጣበት ጉዳይ ጋር ንግግሩ ምንም ግንኙነት አይኖረውምና ይህን መናገር አያስፈልገውም፡፡ ከዚህ ይልቅ እኔ ሰዎችን ሁሉ ለማማለድ በእግዚአብሔር የምቆም ባለሟልነት ያለኝ መልአክ በመሆኔ የለመንከው ልመና መድረሱን የምሥራች ልነግርህ ብመጣ ቃሌን እንዴት ትጠራጠራለህ? ለማለት ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መልአኩ ገብርኤል ነኝ›› በማለት መልአኩ ይህን ተናገረ ብንል ከሁሉ በላይ የሚያስኬድና ለአእምሮ የሚመች ትክክለኛ ትርጓሜ ነው፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ስለ ቅዱስ ሚካኤልም በትንቢተ ዳንኤል ላይ እንዲህ ተጽፏል፡፡ ‹‹በዚያ ወራት ስለ ሕዝብ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል›› ይላል፡፡ (ዳን12.1) በዚህ ጥቅስ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹ስለ ሕዝብ ልጆች የሚቆመው›› ተብሏል፡፡ እረ ለመሆኑ ቅዱስ ሚካኤል ስለ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ‹‹የሚቆመው›› ለምንድር ነው? ለማማለድ አይደለምን? ይህን ካልተቀበልን ቃሉን ምን ብለን እንተረጉመዋለን? ለማመስገን ይቆማል እንዳንል ቃሉ የሚለው ‹‹ስለ ሕዝብ ልጆች የሚቆመው›› ነው፡፡ ስለ እኛ ጥብቅና ይቆማል እንዳንል ወደ ባሰ ስሕተት ይወስደናል፡፡ ሚካኤል በእግዚአብሔር ፊት ጥብቅና አይቆምምና፡፡ እግዚአብሔርም በጠበቃ የሚሟገቱት አምላክ አይደለምና፡፡ ጥብቅና ይቆማል ከማለት ይልቅ ትክክለኛውና የሚስማማው ወደ ፈጣሪ ሊለምንልን ወይም እኛን ለማማለድ ይቆማል የሚለው ትርጓሜ ነው፡፡ አስቀድሞ እንደተመለከትነው ‹‹መቆም›› የሚለው ቃል ማማለድ የሚል ትርጉም አለውና፡፡
Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 04:49 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

ሕሊና እና ምክንያት





በጎ ሕሊና ያለው ሰው እንዴት የታደለ ነው? ብዙዎች ግን ሕሊናቸውን በምክንያት ያታልሉታል። ድሮ ድሮ ኢየሱስ ጾሞልኛል ብለው ለሕሊናቸው ምክንያት ነግረውት ነበር። ነበር ካልኩ ነገር አለ ማለት ነው፤ ዛሬ ግን መጾም ተጀምሯልና ተመስገን ነው። ግን ግን ምስጢር መደበቁ ነው? መጾማችሁን ሳትነግሩን ድንገት መጾም ጀመራችሁሳ፤ ሆኖም ሁል ጊዜ ወቀሳ ብቻ ሳይሆን ማበረታታትም ይገባልና በርቱ።

በጅብ ሆዳምነት በእህል ጣፋጭነት ሳይተዋወቁ ይኖራሉ አሉ! የሀገራችን ጅብ ቀን ሙሉ ጾሞ ማታ ያገኘውን ሁሉ ግጥም አድርጎ ይጠልፋል አሉ። ጅብ በእኛ ጊዜ ቀረ!! መቼስ የዘንድሮ ጅብ አይረባም ፤ ሲዖል ይዘጋላችሁና ጅቦቹ እንደ ድሮ ከመጥለፍ አፕታይታችን ተዘግቷል አሉ። መቼስ የመርካቶ አራዳ ምግብ ሲበላ እንደ ጉድ ጠለፍን ነው የሚለው አሉ። የዛሬ ዘመዶቻችን ጾማችን ከጅብ ጾም መለየት አለበት አትሉም? ዳንኤልና ሰልስቱ ደቂቅ ጮማ ቁረጡ ጠጁንም ገልብጡ ሲባሉ አትክልትና ውኃ ይበቃናል አሉ።

መዝሙረ ዳዊት

109፥24 ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ።

አሁን ማን ይሙት ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ቅቤ ጠፋ? ታድያ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ ለምን አለ?

እንግዲያውስ ምን እንላለን? ኢየሱስ አድኖኛልና ሁሉ ተፈጸመ ካላችሁ ጾም ለምን አስፈለጋችሁ? ይህን በእጅጉ አስቡበት። ሐዋርያው በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ አለን። ያለመከራ አይገኝም እንጀራ እንዲሉ በመከራችን ብዛት የዘላለም ሕይወትን ባንወርስም ዘላለማዊ ሕይወት በቀላሉ አትገኝም። በጠባብዋ በር ተመላለሱም የተባለው ለዚህ ነው። ጮማ መቁረጥ ቢራ መገልበት ሲቻል አባቶች በበረሃ አትክልት መብላታቸው ዳዊትና ዳንኤል የጾሙትን አይተው ነው። እናንተም ትጾማላችሁ ፤ ገዳማዊያኑም ከእናንተ አስበልጠው ይጾማሉ። ታድያ ከእናንተና ከአባቶች የተሻለውን ማን አደረገ?? በስራና ያለ ስራ መንግስተ ሰማይ አንገባም! በሌላ አነጋገር ስራ የግድ ያስፈልጋል።

አንዳንዶቹም ምክንያት ፍለጋ ይደክማሉ። በየአይነቱ እየበላችሁ ቢራ እየገጠማችሁ ለምን ትጾማላችሁ እያሉ ለሕሊናቸው ምቹ ምክንያት ይነግሩታል። ይህ ግን ምክንያት እንጂ ትክክለኛነትን አያስረዳም። ቢራ ለሚደረግመው ስጋን የሚተኩ ምርጣምርጥ ምግቦች ለሚበላው ጾም ይህ አይደለም ብለን እንነግረዋለን እንጂ ሕሊናዬ ሆይ ደስ ይበልህ ምክንያት አለልህና አትረበሽ አንለውም!

ሕሊና እና ምክንያት

አንድ ኦርቶዶክስ ወንድሜ እንዲህ ብሎ ጠየቀ፦ ሴቶች ራሳቸውን ሳይከናነቡ ለምን ይጸልያሉ? አንዱ ፕሮቴስታንት ደግሞ ተከናንቦ የሚጸልይ ወንድ ራሱን ያዋርዳል ይላልና ካህናቱ ለምን ይጠመጥማሉ ብሎ ጠየቀ። ወዲያው አንዷ እህቴ አሁንማ የነብርን ጭራ ያዝን ብላ እጅግ ስትደሰት አየሁና ተገረምኩ። ለዘመናት የሕሊናዋ ጥያቄ ነበር ማለት ነው። እንግዲያውስ ስለምን ከህሊናዋ ጋ ስትጣላ ኖረች? በመሰረቱ ካህናቱ ከተሳሳቱ እኛን አትናገሩን እንደፈለግን እንሁን እንዴት ይባላል? ሁለታችንም ወደ እውነት እንምጣ ይባላል እንጂ ለሕሊና ምክንያት መደርደር ሕሊና ራሱ ይታዘባል! የዳዊት በገና ይደረደራል እንጂ የሕሊና ምክንያት አይደረደርም!

ተከናንቦ የሚጸልይ ወንድ ራሱን ያዋርዳል ካህናቱ ለምን ይጠመጥማሉ? ካህኑ ኢያሱ በራሱ ላይ ይጠመጥም ነበር። እነሆ መልአኩም አዲስ ጥምጣም ጠመጠመለት እንዲል ካህናት የሚጠመጥሙት ለዚህ ነው።

ዘፀ28:40 ቆቦችንም ለክብር ታደርግላቸዋለሀ...41 በክሀነት እንዲያገለግሉ
ዘሌ8:9 እግዚአብሄርም ሙሴን እንዳዘዘው በራሱ ላይ መጠምጠሚያዉን አደረገ...የተቀደሰዉንም አክሊል
ዘካ6:11 አክሊሎችንም ስራ በታላቁም ካሀን ...ራስ ላይ ደፋ 1ነገ21...

እንግዲያውስ ምን እንላለን? ካህናቱ የሚጠመጥሙት በዚህ ምክንያት ከሆነ እህቶቻችን ፍሪዝ አድርገው የሚጸልዩት ለምን ይሆን? ዘመዶቼ ሆይ ለሥጋችሁ ምኞት ስለምን ምክንያት ፈለጋችሁ? እህቶች ሆይ ኢስላም እህቶች ሲከናነቡ ጌታን ተከታይ መንፈሳዊያኑ ምክንያት ከምትፈልጉ ሥጋዊ ምኞታችሁን መቆጣጠር እንዴት አቃታችሁ? ቅ/ጳውሎስ ሰውን ከማሰናከል ከቶ ሥጋ አልበላም አለ። አስቡት ስጋ መብላት ኃጢአት ባይሆንም ሰውን ላለማሰናከል ብቻ ስጋ አልበላም አለ። ዘመዶቼ ሰውን ላለማሰናከል ይህን ያህል ባታስቡ ትንሿን ነገር መፈጸም እንዴት ተሳናችሁ? በመላዕክት ምክንያት ሴት ራስዋን ትከናነብ ይላል። መላዕክት ሥርዓትን ነቅተው ስለሚጠብቁ በቅድስት ቤተክርስቲያን ሴቶች ራሳቸውን ተከናንበው እንዳማረባቸው ውብ ሆነው ያመሰግናሉ።

አንዳንዶቹም ቅ/ጳውሎስ የጻፈበት ባህል እንጂ ግዴታ አይደለም እያሉ በባህል እያማካኙ እንደተለመደው ለሕሊናቸው ምክንያት ይሰጣሉ። ሕሊና ምክንያት ካላገኘ ደጋግሞ ይጠይቃልና ምክንያት ማቅረባቸው የግድ ነው። ከዚህ ውጪ የሆኑ ብዙ ምክንያቶችም እንደሚደረደሩ እናውቃለንና ሰው በገና ይደረድራል እንጂ ምክንያት አይደረድርም እንላቸዋለን።

ሴቶች ፓስተር ለምን አይሆኑም የሚሉም አሉ። ክርስቶስ 12 ሐዋርያትን ሲመርጥ 6 ወንድ 6 ሴት አድርጎ መምረጥ ይችል ነበር። ከየት እንደመጣ አይታወቅም በድፍረት ይፈጽሙታል። ፕሮቴስታንት ዘመዶቻችንን የሚመሩ አውሮፓዊያን በድፍረት ሁሉን ያከናውናሉ። የሰውን ልጅ ፍቅር እግዚአብሔር ይወዳልና ወንድ ከወንድ ሴት ከሴት ቢጋቡ የፍቅር አምላክ ቅር አይለውም የሚል መፅሐፍ ቅዱስ በቅርቡ ይወጣልና ጠብቁ።

እንግዲህ ለዚህም ክፉ ነገር የሕሊና ምክንያት ይደረደር ይሆን? እንግዲያውስ ምን እንላለን? ለሁሉ ምክንያት ቀረበ፤ ለጾም ምክንያት ....ጅብ በጎቹን ጠብቅ ቢባል ይጠፉብኛል አለ አሉ! ምን አለ ምክንያት ከሚሰጥ እውነቱን ነግሮን ልበላቸው ፈልጌ ነው ቢል? ምክንያት ለሰው ብቻ ሳይሆን ለጅብም ይሰራል ለካ።
Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 02:05 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Thursday, 25 July 2013

ጥንተ አብሶ


በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ 
**የሰው ዘር ናት ማለት በራሱ ጥንተ አብሶ አለባት አያሰኝም፡፡
**ድንግል ማርያም የሞተችው ልጇ ጥንተ አብሶን ካስወገደ በኋላ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡ 
**እኛን እንዳዳነንና እንደቀደሰን ተሰቅሎ፣ ሞቶ፣ ደሙን አፍስሶ ሥጋውን ቆርሶ አዳናት ቢባል ካልዳነችና ካልነጻች ሴት ተወለደ ማለት ነውና ሁሉን ነገር ከንቱ ያሰኛል፡፡ አስቀድሞ ካነጻት በኋላ ከእርሷ ተወለደ የሚባል ከሆነ ደግሞ ያው ዓለሙ ሁሉ ከመዳኑ በፊት ድኅነት በልዩ መንገድ ለእርሷ እንደተደረገ ማመን ግድ ነው፡፡
**‹‹ይህማ ካቶሊኮች ትምህርት ነው›› ፖለቲከኛነት እንጂ መንፈሳዊነት አይደለም፡፡
**የክርስትና እምነታችን ከግብጽ እንዳልመጣልን የታመነ ነው፡፡ 
**‹‹አቡነ እገሌ እንዲህ ያምኑ ነበር፤ አባ እገሌ እንዲህ ብለው ጽፈዋል፤ እንዲህ አስተምረዋል›› ኢየሱስ ክርሰቶስ የመሠረታትን ቤተ ክርስቲያን ክብር የሚነካና በግለሰብእ የተመሠረች ሃይማኖት አድርጎ መቁጠር ነው፡፡ 

ከሁሉ አስቀድሞ ‹‹ጥንተ አብሶ›› ማለት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት ይኖርብናል፡፡ በአጭሩ ‹‹ጥንት›› ማለት መነሻ፣መጀመሪያ ማለት ሲሆን ‹‹አብሶ›› ማለት ደግሞ በደል ማለት ነው፡፡ ሁለቱ ቃላት ተናበው የሚፈጥሩት ሐረግ ‹‹ጥንተ አብሶ›› ሲሆን የበደል መጀመሪያ የሆነ በደልን ያመለክታል፡፡በነጻ ፈቃዳቸው አስበው መበደል የሚችሉ የፍጥረት ወገኖች ሰዎችና መላእክት ናቸው፡፡ በሰማይ በደል የተጀመረው በዓለመ መላእክት ሲሆን በደለኞቹም ሰይጣንና ሠራዊቱ ናቸው፡፡ የሰዎች ልጆች ስለፈጸሙት በደል የምንነጋገር ከሆነ ግን በመጀመሪያ የበደሉ አዳምና ሔዋን ናቸው፡፡ የአዳምንና የሔዋንን በደል የውርስ ኃጢአት ከማለት ይልቅ ጥንተ አብሶ ማለት የበለጠ ይገልጠዋል፡፡ ያ የቀደመ በደል ተወግዷል፡፡ የሰው ልጆች በሙሉ በወልደ ማርያም በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ቤዛነት
ከቀደመው በደል ነጻ ወጥተዋል፤፡፡ ይህን ማስተዋል ስለተሣነው ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ‹‹እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል።›› በጥቅሱ መሠረት ዓይነ ልቡናው የታወረ ካልሆነ በቀር ማንም ቢሆን ከቀደመው ኃጢአት የነጻ መሆኑን መዘንጋት የለበትም፡፡ ይህን መርሳት አምላካችን የከፈለልንን ዋጋ እንደ ከንቱ መቁጠር ነውና፡፡ (2ጴጥ 1፥9)

ጥንተ አብሶ አለባት የሚሉ ሰዎች የሚያቀርቧቸው መከራከሪያዎች 

1.ኛ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከኢያቄምና ከሃና በሩካቤ በዘር የተወለደች የባሕርያችን መመኪያ ፍጽምት ሰው ናት፡፡ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያን የቀደሙትን አበው ቃል እና መጽሐፍ ቅዱስን ዋቢ በማድረግ ‹‹ቅድስት ድንግል ሰማያዊት ናት/ የሰው ዘር አይደለችም/ የሚል ቢኖር ውጉዝ ይሁን›› እያለች አጥብቃ ታስተምራለች፡፡ (ሃይ.አበ 123፥8) ይሁን እንጂ የሰው ዘር ናት ማለት በራሱ ጥንተ አብሶ አለባት አያሰኝም፡፡ አንዳንዶች ሰው ከሆነች ጥንተ አብሶ እንዴት አልኖረባትም እያሉ ይሞግታሉ፡፡ ይህም የጥንተ አብሶን ምንነት ካለማወቅ የሚመጣ ሙግት ነው፡፡ ጥንተ አብሶ በደልና የበደል ውጤት እንጂ ራሱን የቻለ ፍጥረት አይደለም፡፡ ማለትም ሰው እንደተፈጠረባቸው እንደ አራቱ ባሕርያተ ሥጋ እንደ እሳት፣ ነፋስ፣ ውኃና አፈር አይደለም፡፡ አዳም ሳይበድል በፊት ሰው ነው፡፡ መተላለፍ ካገኘውም በኋላ ሰው ነው፡፡ ጥንተ አብሶ የሌለበት ሰው ሊኖር አይችልም አይባልም፡፡ ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ አልደረሰባትም ነገር ግን ሰው ናት፡፡ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስም ጥንተ አብሶን ያጠፋ ፍጹም ሰውና አምላክ ነው፡፡ እኛም ክርስቲያኖች ጥንተ አብሶ ጠፍቶልናል፡፡ ነገር ግን አሁንም ሰዎች ነን፡፡ ስለዚህ ድንግል ማርያም ሰው እስከሆነች ድረስ ግድ ጥንተ አብሶ ነበረባት ማለት ጥንተ አብሶን ተፈጥሮአዊ ማድረግ ነውና ስሕተት ነው፡፡ ጥንተ አብሶ በሰው አለመታዘዝ ምክንያት የመጣ በደል እንጂ ከሰው ልጆች ጋር አብሮ የተፈጠረ ተፈጥሮአዊ ባሕርይ አይደለም፡፡ አዳምም ራሱ በጥንተ አብሶ ከመገኘቱ በፊት ሰው መሆኑን መርሳት አይገባም፡፡

2.ኛ ድንግል ማርያም በ64 ዘመኗ ሞታ በልጇ ሥልጣን ተነሥታለች፡፡ በሦስተኛውም ቀን አሳርጓታል፡፡ ይኸውም ሲሰላ ሞትን ይገድል ዘንድ የሞተው ልጇ በሥልጣኑ ተነሥቶ ካረገ ከ15 ዓመታት በኋላ ይሆናል፡፡ የእርሷ ሞት ‹‹ሁሉን የሚያስደንቅና›› ምክንያት ያለው ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ እንደተናገረው ልጇ በፍርድ እንደማያዳላ የሚያስተምር እና እርሷ የሰው ዘር እንጂ የመላእክት ዘር አለመሆኗን የሚያረጋግጥ ክንውን ነው፡፡ መላእክት እንደ ሰው አይሞቱምና፡፡ ይሁን እንጂ በመሞቷ ምክንያት ብቻ ጥንተ አብሶ ስለነበረባት ነው እያሉ የሚጽፉ አሉ፡፡ ድንግል ማርያም መሞቷ ከላይ የጠቀስነውን እውነታ እንጂ ጥንተ አብሶ ነበረባት አያሰኝም፡፡ የሞተችው ልጇ ጥንተ አብሶን ካስወገደ በኋላ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡ በጥንተ አብሶ ምክንያት ሞተች ማለት ጥንተ አብሶ አልተወገደም ማለት ነውና ከባድ ክህደት ነው፡፡ መሞት ብቻውን ጥንተ አብሶ መኖሩን ያሳያል የሚባል ከሆነ ክብር ይግባውና ኢየሱስ ክርስቶስም ሞቶ ስለተነሣ ጥንተ አብሶ ነበረበት እንደማለት ይቆጠራል፡፡ ይህ ደግሞ አይሁድ ከፈጸሙት የሚከፋ ኃጢአት ነው፡፡ እንኳን ድንግል ማርያም እኛም የምንሞተው ሞት በጥንተ አብሶ ተይዘን አለመሆኑን መረዳት አለብን፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ ሞትን በሃይማኖተ አበው ወደ መንግሥተ ሰማያት እንገባበት ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ መርቆና ከፍቶ ያዘጋጀልን ‹‹አዲስ መንገድ›› ይለዋል፡፡ (ሃይ.አበ 80፥17) ቅዱስ ባስልዮስም በጸሎቱ ስለ ሞት ሲናገር ‹‹ለባሪያዎችህ ሞት የለባቸውም ፍልሰት እንጂ›› በማለት ሞትን ‹‹ፍልሰት›› ሲል ሰይሞታል፡፡ (እግዚአ ሕያዋን) ለሚያምኑ ሁሉ ‹‹ሞት ጥቅም›› ነው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ (ፊል፥121) ስለዚህ ድንግል ማርያም ሞታ መነሣቷ የታመነ ቢሆንም ይህን እየጠቀሱ ጥንተ አብሶ አግኝቷት ነበር ማለት ስሕተት ነው፡፡

3.ኛ እመቤታች በጸሎቷ መሃል ‹‹መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች›› ማለቷን ቅዱስ ሉቃስ በወንጌል መዝግቦልናል፡፡ (ሉቃ1፥47) ‹‹መድኃኒቴ›› ማለቷን በመጥቀስ እንደማንኛውም ሰው ከጥንተ አብሶ መዳን የሚያስፈልጋት ስለነበረችና ስላዳናት ‹‹መድኃኒቴ›› አለች በማለት የሚከራከሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ይህ ቃል እመቤታችን በሃይማኖት የተናገረችው ነው፡፡ አምላክ የሌለው የለምና ሁሉም አምላኬ ሊል ይችላል፡፡ ‹‹መድኃኔቴ›› የሚል ግን የወደደና ፈቅዶ የተቀበለ፤ የተደረገለትንም ያወቀ ሰው ነው፡፡ ስለዚህ እመቤታችን ጥበቃውን እና ያደረገላትን በማድነቅ ፈጣሪዋን ያመሰገነችበት የደስታ ቃል ነው፡፡ ጥንተ አብሶ ነበረባት ግን አያሰኝም፡፡

ምክንያቱም ሰው ዳነ የሚባለው ከደረሰበት ነገር ሲድን ብቻ አይደለም፡፡ ሊደርስበት ከነበረ ነገር የተሰወረ ሰው ተረፈ ወይም ዳነ ይባላል፡፡ መድኃኒትም መድኃኒት የሚባለው የታመመውን ሲፈውስ ብቻ አይደለም፡፡ ገና ያልታመሙ እንዳይታመሙ የሚከላከልም እንዲሁ መድኃኒት ይባላል፡፡ በዚህ ማብራሪያ መሠረት ድንግል ማርያም ‹‹መድኃኒቴ›› ያለችው ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ስለሰወራትና ስላዳናት እንጂ እንደማንኛውም የሰው ዘር ጥንተ አብሶ ካገኛት በኋላ አድኗት አይደለም፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ያለው ጥቅስ ከላይ ያብራራሁትን ሐሳብ የሚደግፍ ቃል ይገኝበታል፡፡ የግብጹ ፈርዖን የእስራኤል ሴቶች ሲወልዱ ወንዶች ከተወለዱ ወዲያው እንዲገድሏቸው አዋላጆችን ሁሉ አዝዞ ነበር፡፡ ነገር ግን አዋላጆቹ በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት ሳይገድሉ አንዳንድ ወንዶችን እንዲሁ ተውዋቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ንጉሡ የግብፅም ንጉሥ አዋላጆችን ጠርቶ። ለምን እንዲህ አደረጋችሁ? ‹‹ወንዶቹን ሕፃናትንስ ለምን አዳናችሁ? አላቸው።›› (ዘጸ1፥18) እነዚህ ሕጻናት በሌሎች ሕጻናት የተፈረደው ፍርድ ተፈጻሚ ስላለሆነባቸው ‹‹ዳኑ›› ተባለ፡፡ ልብ በሉ ‹‹ዳኑ›› የተባለው ከበሽታ ቢሆን ሕመም አግኝቷቸው ነበር ለማለት እንከጅል
ይሆናል፡፡ እነዚህ ሰዎች የዳኑት ፈርዖን አውጆት ከነበረው የሞት ፍርድ ነበር፡፡ ታዲያ እነዚህ ሕጻናት ከሞት ዳኑ ማለት ሞተው ተነሡ ማለት ነው ወይስ ሳይሞቱ ቀሩ?

በተመሳሳይ ሁኔታ እመቤታችንም መድኃኒቴ ማለቷ በዕደ እግዚአብሔር ከጥንተ አብሶና በአዳም ከተፈረደው ፍርድ ስለተጠበቀች እንጂ ረክሳ ስለተቀደሰች አይደለም፡፡ ሎቱ ስብሐት! እንዲሁ በዘሮቹ ሁሉ ላይ በአዳም ምክንያት ፍርድ የተፈረደባቸው ሆኖ ሳለ እርሷ ግን የአዳም ዘር ብትሆንም ቅሉ ያ ዕዳ አላገኛትምና ከዚያ ሁሉ የዳነች ናት፡፡ ያዳናትም አምላኳ ነውና ‹‹አምላኬ፣ መድኃኒቴ›› አለች፡፡ ሊደርስብን ካለ ወይም ከተቃጣ ነገር ወይም እንደሚደርስ ከሚገመት ነገር ነጻ መሆን ራሱ መዳን ይባላል፡፡ ለምሳሌ ሕጻናት ገደል እንዳይገቡ እሳት እንዳያቃጥላቸው ነጠቅ ብታደርጓቸው ዳኑ አይባልምን? ሐዋርያው ጴጥሮስ የሞት ፍርድ ሳይፈረድበት ከእስር ቤት መልአኩን ልኮ ስላዳነው ‹‹አዳነኝ›› ማለቱ ተጽፎአል፡፡(የሐዋ12፥11)

ድንግል ማርያምን ዓለም በዳነበት መንገድ ዳነች፣ ነጻች እያሉ መናገር እናትነቷን መካድ ነው፡፡ እኛን እንዳዳነንና እንደቀደሰን ተሰቅሎ፣ ሞቶ፣ ደሙን አፍስሶ ሥጋውን ቆርሶ አዳናት ቢባል ካልዳነችና ካልነጻች ሴት ተወለደ ማለት ነውና ሁሉን ነገር ከንቱ ያሰኛል፡፡ አስቀድሞ ካነጻት በኋላ ከእርሷ ተወለደ የሚባል ከሆነ ደግሞ ያው ዓለሙ ሁሉ ከመዳኑ በፊት ድኅነት በልዩ መንገድ ለእርሷ እንደተደረገ ማመን ግድ ነው፡፡ እዚህ ድረስ መምጣት ግድ ከሆነ እንደ ኦርቶዶክሳዊያኑ አስቀድሞ ጠበቃት ማለት ክፋቱ ምን ላይ ነው? የበለጠ ፍጹምና መንፈሳዊው የእምነት መንገድ ይልቅ እንዲህ ማመን ነው፡፡ ምክንያቱም ሊወለድባት ሲልም ቢሆን ለብቻዋ ማንጻቱ ላይቀር ከእርሷ ለመጸነስ እስኪመጣ ድረስ ሁሉን እያወቀ ከጥንተ አብሶ ጋር እንድትቆይ አደረገ ከማለት አስቀድሞ በንጽሕና ጠብቆ አኖራት ማለት የበለጠ የቀና ነውና፡፡ ሰው እንኳን ቆይቶ የሚመገብበትን ቁስ ወድቆ ቢያይ ልበላበት ስል አጥበዋለሁና እስከዚያ ይንከባለል ብሎ ችላ እንደማይል የታመነ ነው፡፡ አምላክ እስክወለድባት በጥንተ አብሶ አድፋ ትቆይ ብሎ እናቱን ተዋት ማለት የማይመስል ነገር ነው፡፡

4.ኛ አንዳንዶች ‹‹ድንግል ማርያምን ጥንተ አብሶ ከቶ አላገኛትም›› የሚለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲሰሙ ‹‹ይህማ ካቶሊኮች ትምህርት ነው›› በማለት ለማስተባበል ይሞክራሉ፡፡ ይህንኑ ሐሳብ በጽሑፍ ያቀረቡ ሰዎች አሉ፡፡ ካቶሊኮች ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም ስላሉ ከእነርሱ ለመለየት ስንል እኛ የሌለባትን ጥንተ አብሶ አለባት ብንል ተገቢ አይደለም፡፡ ልዩነቶቻችን እንደተጠበቁ ሆነው ከካቶሊኮች ጋር የምንጋራቸው በርካታ ሃይማኖታዊ ጽንሰ ሐሳቦች አሉ፡፡ እነርሱን ላለመምሰል የምንመሳሰልባቸውን ሐሳቦች ሁሉ የኛ አይደሉም የምንል ከሆነ በዚህ መንገድ ስንቱን ልንጥል ነው? እውነትን መያዝ እንጂ እነ እገሌ ስለያዙት ብሎ መጣል ምክንያታዊ አያሰኝም፡፡ ከእነርሱ ጋር ለመመሳሰል ብለን እንዳልያዝነው ሁሉ ላለመመሳሰል ብለንም እውነቱን አንጥልም፡፡ በሌላ ስውር አላማ፣ ወይም መጠን አልባ የካቶሊክ ግላዊ ጥላቻ ይዞ፣ ወይም ደግሞ እነርሱን የሚቃወም ሁሉ ሐሳቤን ይቀበልልኛል በሚል ይህን የመሰለውን ሁሉ ምክንያት እያደረጉ ማቅረብ ፖለቲከኛነት እንጂ መንፈሳዊነት አይደለም፡፡

5.ኛ ሌላው ነጥብ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያት ከእኅት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ ናት፡፡ ለበርካታ መቶ አመታት ለቡራኬና ለክህነት አባቶችን ከግብጽ ስናገኝ ኖረናል፡፡ ይሁን እንጂ የክርስትና እምነታችን ከግብጽ እንዳልመጣልን የታመነ ነው፡፡ ስለሃይማኖት ትምህርት የራሳችን ሊቃውንት ነበሩን፤ አሉንም፡፡ በረጅም ታሪኳ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን በርካታ ሀብቷን የሚያሳጣና የሚለውጥ ፈተና አጋጥሟታል፡፡ ዋና ዋናዎቹ ተግዳሮቶቿ በፕሮቴስታን አገር ለበርካታ ዘመናት ቅኝ መገዛቷ፣ እስካለንበት ዘመን በሙስሊሞች የበላይነት መመራቷ፣ እና አዎንታዊውን ትተን በራሷ ልጆች የተደረጉ አሉታዊ ለውጦች ናቸው፡፡ ከዚህ ሁሉ ፈተና በኋላ የቤተ ክርስቲያኒቱ እስካሁን መኖር በራሱ በጎ ዕድል ነው፡፡ ስለዚህ አሁን ያሉት የሃይማኖት ተወካዮቿ እንደ ቀድሞዎቹ እንደ አትናቴዎስና እንደ ቄርሎስ ያለ አቋም ባይኖራቸው መደነቅ የለብንም፡፡ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን የወደደችውን ማመንና ማምለክ መብቷ መሆኑን መርሳት የለብም፡፡ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያላት እኅትማማችነት በጠና ቢታመምም ሞተ የሚባል አለመሆኑም እጅግ በጣም መልካም ነው፡፡ በአንድ ርእሰ ጉዳይ ዙሪያ የሁለቱን
እኅት አብያተ ክርስቲያናት አቋም ስንተነትን እነዚህን ሁሉ ጉዳዮች ከግምት ሳናስገባ ከሆነ የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ እንደርሳልን፡፡ ጥንተ አብሶን በተመለከተ ሁለቱን አኀት አብያተ ክርስቲያናት በማስተያየት ወደተሳሳተ መደምደሚያ የሚደርሱ ሰዎችም ይህንን ማስተዋል ያልቻሉ ናቸው፡፡

6.ኛ ‹‹አቡነ እገሌ እንዲህ ያምኑ ነበር፤ አባ እገሌ እንዲህ ብለው ጽፈዋል፤ እንዲህ አስተምረዋል›› እያሉ የግለሰቦችን ቃልና ጽሑፍ ለሃይማኖታዊ ጉዳይ በማስረጃነት የሚያቀርቡ አሉ፡፡ ይህ አካሄድ በራሱ የግለሰብእ ተጠቂ መሆንን ያሳያል፡፡ በተቃራኒዉም ተመሳሳይ ማስረጃ ማቅረብ ቢቻልም ሁለቱም መንገድ ከንቱነት ያለበት በመሆኑ ከዋና ዋና ምንጮች በመነሣት ሐሳብን መግለጥ የበለጠ መልካም ነው፡፡ የራሳቸውን ገድል ያልፈጸሙ መዋቲያንን ዋቢ ማድረግ ኢየሱስ ክርሰቶስ የመሠረታትን ቤተ ክርስቲያን ክብር የሚነካና በግለሰብእ የተመሠረች ሃይማኖት አድርጎ መቁጠር ነው፡፡ ሰው ከዚህ ቀደም የተናገረውን ዛሬ የማይደግም ተለዋዋጭ መሆኑንም መርሳት አይገባም፡፡ ስለዚህ ይህን መሰሉን ምክንያት በቁሙ ውድቅ ማድረግ እንጂ ምላሽ መስጠት አያስፈልገውም፡፡

ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ ነበረባት የሚሉ ሰዎች ሁሉ ከላይ የተጠቀሱትን ክብደት የሌላቸው ምክንያቶች ሁሉ እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ከተነሡበት አጀንዳ ጋር የሚያቀርቡት መከራከሪያ ዝምድና እንደሌለው ሳይረዱ ቀርተው ብቻ አይደለም፡፡ እንዲያው በግምት ብዙ ብንወረውር አንዱ ሳይመታልን አይቀርም ብለው እንጂ፡፡ በተጨማሪም ማስተላለፍ ለፈለጉት መልእክት ድጋፍ የሚሆን ሌላ አሳማኝ ማስረጃ ማቅረብ እንደተቸገሩም ያሳያል፡፡ ሌሎች ይመኑላቸው እንጂ ስለሚናገሩት ነገር እውነትነት ስላቀረቡትም ማስረጃ ተአማኒነት ደንታ የሌላቸው ሰዎች ከዚህ የተለየ መንገድ የላቸውምና አቀራረባቸው ድንቅ አይደለም፡፡
Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 04:40 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

እናት ለልጅዋ ነቢይ ናት!


የነቢዩ ዮናስ እናት ያቺ ሱናማዊት የኤልሳዕን በረከት አግኝታለች። ያልሰማ ካለ ይሂድና እንስራዋን ይይ። በዘይት መሞላቱን ይይ። ዕዳዋ መከፈሉን ይይ። ነቢዩ ኤልሳዕ ምን ላድርግልሽ አላት። ልጅ አልነበራትምና ልጅ እንድትወልድ አበሰራት። ልጇ ሲሞት አስነሳላት። እንግዲያውስ ይህን ህይወት እኛም ብንኖር እንዴት መታደል ነበር? ዕዳ እየከፈሉልን የሞተብንን እያስነሱ መኖር አይ መታደል ነበር!!

ቆይ ግን ሱናማዊቷ እግዚአብሔርን አታውቅም እንዴ?? ደግሞ ኤልሳዕን አገልጋይህ ነኝ ትላለች። የሰው አገልጋይ ነን እንዴ? ይህ ሁሉ አምልኮት ሲደረግ እግዚአብሔርስ እንዴት ዝም አለ?

ሱናማዊቷ ኤልሳዕን ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው ብላ ጠርታዋለች። እግዚአብሔር ማን ኤልሳዕም ማን እንደሆነ በሚገባ ታውቃለች። እነሆ የኤልሳዕን በረከት አፍሳለች፤ አምላክዋ እግዚአብሔርም ማድጋዋን ሞልቶ ልጅ አግኝታ ኖራለች። ደም ከደም ስር ጋ እንደማይጋጭ ሁሉ የእግዚአብሔር ስራ ከቅዱሳኑ ስራ ጋ አይጋጭምና!

የነቢያት ማህበር ለነቢዩ ኤልሳዕ ሰገዱ 2ኛ ነገሥት 2 ፦15 እነዚህ ነቢያት ሁል ጊዜ ይገርሙኛል። እኔ ብሆን ግን እኔም ነቢይ ኤልሳዕም ነቢይ ብዬ የማልሰግድለት ይመስለኛል። ግን ግን እኛም ነቢይ ኤልያስም ነቢይ ምን ያመጣል ብለው እንዴት አልተከራከሩም? ደግሞ እኮ ነቢይ ስለሆኑ ያለፈውንና የሚመጣውን ያውቃሉ። ታድያ ለጌታ ብቻ እንሰግዳለን ለምን አላሉም? የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ ላይ ሆኗል ብለው ነቢያቱ ሰገዱ። ለሰው ሲሰገድ ይህ ሁሉ ባዕድ አምልኮ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ እንዴት ተጻፈ? ይባስ ብለው ነቢያቱ ለኤልሳዕ "እነሆ እኛ አገልጋዮችህ ነን" አሉ። አሁን ማን ይሙት ሁሉም ነቢይ ከሆኑ ለምን አገልጋዩ ሆኑ? ደግሞ የሰው አገልጋይ አለ? ለማየት የሚፈልግ አይኑን ይገልጣል አሉ!

በዮሴፍ ምክንያት ግብጽ ጠገበች። በሙሴ ባህር ተከፈለ ፤ በኢያሱ ፀሐይ ቆመ፣ በኤልያስ ሰማይ ተለጎመ፣ በዳንኤል ምስጢር ተፈታ፤ ስለ ማን እንጨምር ? ለመተረክ ጊዜ የለንም ። እነዚህ ሁሉ እንደ ደመና በዙሪያችን ከበውን አይደለምን? እንግዲያውስ ካላየሁ አላምንም ማለት ዳግማዊ ቶማስ መሆን አይደለምን? ቶማስማ አምኖ አምላኬ ብሏል። ሁሉም ነቢይ አይደለም ሁሉም ጻድቅ አይደለም፤ ሁሉም ካህን ሁሉም ሐዋርያ አይደለም። እንግዲያውስ ሐዋርያቱን ለምን መረጣቸው? አስቀድሞ የወሰናቸውን ጠራቸው። ሁሉን ጥለው ተከተሉት። የጠራቸውን አጸደቃቸው አከበራቸውም። ወደ ቀደመው እንመለስ ፦ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ማለት ምን ማለት ነው? ጌታችን ይህን ቃል ለምን ተናገረ? ትርጉም የሌለው ቃል ነው?

Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 02:29 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Wednesday, 24 July 2013

የኢየሱስ ክርስቶስ ደም የአምላክ ነው ወይስ የሰው?


//ቃል ሥጋ ሆነ//


ቃል እንደ ረጅም ፈትል ከሰማየ ሰማያት ወረደ። ከድልግል ማርያም ተወለደ። ቃልም ሥጋ ሆነ። 

ስለ ፍቅር ብሎ እጆቹን በችንካር ተመታ። በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ አብዝቶ ዝም አለ! በእርሱ ቁስል ጉልበታችን ፀናች ነፍሳችን ተማረች ፤ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን። ስለ ፍጹም ፍቅር እጆቹን ዘረጋ። ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ አዳነን!

የኢየሱስ ክርስቶስ ደም የአምላክ ነው ወይስ የሰው?

የአምላክ ደም እንዳንል መለኮት ደም የለውም። የሰው ደም እንዳንል የሰው ደም ዓለምን እንዴት አዳነ? ሲዖልን እንዴት ከፈተ እንላለን። ፕሮቴስታንት ዘመዶቻችን ሆይ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም የአምላክ ነው ወይስ የሰው?
Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 04:05 5 comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

//ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ//


ማርያም ርኩስ ነበረች የምትል ምላስ ክርስቶስን ለማርከስ የምትቅለበለብ ምላስ ትመስላለች። የክርስቶስ ሥጋና ደም ማን አረከሰው? የእናቱን ሥጋ ተዋህዶ ተወለደ። ታድያ ክርስቶስ የለበሰው ሥጋ ርኩስ ነው የሚል እርሱ ማን ነው?

የሉቃስ ወንጌል 2

22-24 እንደ ሙሴም ሕግ የ((መንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ፥ በጌታ ሕግ።)) የእናቱን ማኅፀን የሚከፍት ወንድ ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይባላል ((ተብሎ እንደ ተጻፈ በጌታ ፊት ሊያቆሙት፥ በጌታም ሕግ።)) ሁለት ዋሊያ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ((እንደ ተባለ))፥ መሥዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት። // ሉቃስ የሚያወራው ሕጉን ስለመፈጸማቸው ነው። ኢይምስልክሙ ዘመጻእኩ እስአሮሙ ለኦሪት /ሕግን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ እንዳለ ሕጉን ፈጽመዋል/ ለዚህ ነው ወንጌላዊው ሕጉ እንደተጻፈና እንደተፈፀመ የሚነግረን። ስለ ሕጉ እየነገረን እንደሆነ ቃላቱን ይመልከቱ፦ ((መንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ፥)) ((እንደ ተባለ))፥ ((ተብሎ እንደ ተጻፈ በጌታ ፊት ሊያቆሙት፥ በጌታም ሕግ።))

ሉቃስ ለኃጢአት መስዋዕት አቀረበች ሊላ አልደፈረም አላማው  ከመንፈስ ቅዱስ ነውና የነገረን ሕጉ ስለመፈጸሙ ነው። የኦሪቱ ሕግ ግን መስዋዕቱ ለኃጢአት መሆኑን በግልጽ ይናገራል፦
ኦሪት ዘሌዋውያን 12

6 የመንጻትዋ ወራትም በተፈጸመ ጊዜ፥ ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአንድ ዓመት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ የርግብም ግልገል ወይም ዋኖስ ((ለኃጢአት መሥዋዕት)) ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታምጣለት።

8 ጠቦት ለማምጣት ገንዘብዋ ያልበቃት እንደ ሆነ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ሌላውንም ((ለኃጢአት መሥዋዕት ታቀርባለች)) ካህኑም ያስተሰርይላታል፥ እርስዋም ትነጻለች።

በዚህ አጋጣሚ የኦሪቱ ሕግ ሴት በረከሰች ጊዜ ቅዱስ ነገር አትንካ ይላል። ይህን ይዘው የጸሎት መጽሐፍ መንካት መስቀል መሳለም የሚፈሩ ሴቶች አሉ። ይህ ግን ልክ አይደለም። ሴት ልጅ በወር ተፈጥሮዋ ጊዜ ቅዱሳን መጻህፍትን ይዛ መጸለይ ትችላለች። ሌላው ሴት ልጅ በወር ተፈጥሮዋ ጊዜ ቤተ መቅደስ አትገባም። ወንድ ሲነስረው እጁ ቢደማ ቤተመቅደስ አይገባም። ምክንያም ስለረከስን ሳይሆን በቤተመቅደስ የሚፈሰው የክርስቶስ ደም ብቻ ስለሆነ ነው።

//ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ//

ኦሪት ዘሌዋውያን 12
1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።
2 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። ((ሴት ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ፥ ሰባት ቀን ያህል የረከሰች ናት እንደ ሕመምዋ መርገም ወራት ትረክሳለች።)) // ማርያም ጌታን ስለወለደች ርኩስ ሆነች የሚል ከቶ ማን ነው? ቅ/ገብርኤል ፀጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ አላት እንጂ መርገመ ሥጋሽ ቀረልሽ እንኳን ደስ አለሽ አላላትም! ማርያም የረከሰች ከሆነች ይህ ሁሉ የመላኩ ምስጋና ስለረከሰች የተነገረ ነውን? ኢሳይያስን ጠይቁት ጽድቃችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው እያለ ያለቅሳልና! እዚህ ደግሞ ፀጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ሲላት ተገረምን! ሰው ሁሉ ጽድቅ በጎደለበት በጨለማ ዘመን ማርያም ግን ፀጋን የተመላሽ ሆይ ተባለች! እነሆ ኤልሳቤትም ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አለቻት! በኦሪቱ ሴት ሁሉ ወንድ ሲወልድ የረከሰ ነው ሲባል ማርያም ግን ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች ናት! መርገመ ሥጋ ወዴት ነበርክ? ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች ማርያምን ታረክሳት ዘንድ እንዴት አቅም አጣህ?

3 በስምንተኛውም ቀን ልጁ ከሥጋው ሸለፈት ይገረዝ።
4 ከደምዋም እስክትነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቀመጥ ((የመንጻትዋ ቀንም እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰን ነገር አትንካ)) ማርያምን ረከሰች የሚል ማን ነው? እስክትነጻ የተቀደሰን ነገር አትንካ እያለ ጌታን በማህፀንዋ ታቅፋ በደረትዋ አመቻችታ በጀርባዋ እንዴት አዘለች? እስኪ መልሱልን? የተቀደሰን ነገር አትንካ እያለ ልጅዋን ስታቅፍ ርኩስ ነበረን? እስኪ መልሳችሁ ይሰማ?

Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 04:01 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Tuesday, 23 July 2013

//የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ//



  • //የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ// ይህችን አባባል ያስቀደምነው ዛሬ ያነበቡትን ነገ ደግመው ለሚጠይቁ ሰዎች የሚስማማ በመሆኑ ነው። ጥያቄ፦ ለመላዕክት የክብር ስግደት ይገባል ?ይህስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?


    መልስ :- 
    ቆርኔሌዎስ "ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል። ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው።እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ።ጌታ ሆይ ምንድር ነው? አለ። መልአኩም አለው። ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።"ሐዋ.10፡3-4

    መላእክት ክብራቸዉ አንዳንዶች እንደሚያስቡት አይደለም።መላእክት ግርማቸዉ እጅግ ድንቅ እና የሚያስፈራ ነዉ።ምክንያቱም የአምላክን ስም ይዘዋልና አምላካቸዉን ለብሰዋልና።"በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ።በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።"ዘጸ.23:20 እንዲል መጽሃፍ።ነገር ግን ሁሌም ሲያረጋጉ አየዞዋችሁ አትፍሩ ነው፡፡እኛም የተዋህዶ ልጆች የአምላክነት ሳይሆን የጸጋ( ከእግዚአብሔር የተሰጠ) ክብር ስለምንሰጣቸው አይዞዋችሁ ይሉናል፡፡የጸጋም ስግደት መጽሃፍ ስለሚያዝ እንሰግድላቸዋልን።

    ሆኖም አንዳንዶች ስህተት ነዉ ይሉናል።ለመልአክ ይሰገዳል ወይስ አሰግደም? በእርግጥ ብዙ ቦታ እግዚአብሔር የመረጣቸዉ የቀደሙ አባቶች ለመላእክት ሰገዱ ተብሎ ተጽፋል። እንዚህ አባቶች ሲያመልኩ የነበረዉ እግዚአብሔርን ነዉ ነገር ግን ለመላእክት የአክብሮት የጸጋ ስግደት ሰግደዋል ታድያ እነዚህ አባቶች ተሳስተዋል? እግዚአብሔርን አላመለኩም? ያመለኩት መላእክትን ነዉ ይባል ይሆን?።አልተሳሳቱም ምክንያቱም መረጃዉ የተገኝዉ በመንፈስ ቅዱስ ከተደርሰዉ መጽሃፍ ቅዱስ ነዉና ሁሌም እዉነት ነዉ።ሰማይና ምድር ያልፋሉ እንጂ ቃሌ ግን አያልፍም ብሎናልና።ማቴ.24:35።ነገር ግን አንዳንዶች በራእይ 22:8 ያለዉን የእግዚአብሄር ቃል በመያዝ ትከከለኛ ሚስጥሩን ባለማዎቅ ለመላእክት አይሰገድም ይሉናል።ግልጽ ለማድረግ እስቲ ለእያሱ የተገለጠ መልአክ እና ለዮሃንስ የተገለጠዉን መልአክ በማነጸጸር አብረን እንመልከት።

    ኢያ. 5 ፡14 “ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ” ለመልአኩ።ራእ.22:8 “በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ” እርሱም፦ እንዳታደርገው አለዉ።ካንተ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ አለዉ ::ለምን? አንዳንድ ወንድሞች ራእ.22:8ን ይዘው ለመልአክት አይሰግደም ይሉናል።ምስጥሩ ምንድን ነው? ለኢያሱ የተገለጠ መልአክ ስህተተኛ ነበር? ለምን አትስገድልኝ አላለውም? ለዮሐንስ የተገለጠውስ ለምን አትስገድልኝ አለ? ሁለቱም ጋ መላዕክት ናቸው ሁለቱም ሰዎች ሰግደዋል አንዱ መልአክ ኢያሱ ሲሰግድለት ምንም አላለም ሌላኛው መልአክ ግን ዮሐንስ ሲሰግድለት አትስገድልኝ አለው።

    እስኪ ይህን ተቃዋሚ ወንድሞች በምን ያስማሙታል? የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ 
    አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ ማለት ይህ ነው። ለመሆኑ ቅዱስ ዮሐንስ እና ኢያሱ ዛሬ እኛ ካለን እውቀት ያነሰ እውቀት ስላላቸው ነው የሰገዱት? እዉነት ለመናገር ኢያሱ እና ቅዱስ ዮሐንስ በዚያን ጊዜም ቢሆን ለማን መስገድ እንዳለባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ።”እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን"።ኢያ.24:15 ያለ ኢያሱ ሆነ ፍቁረ እግዚእ (የጌታ ወዳጅ የተባለ) የስላሴ ሚስጥ አስፋፍቶ የጽፈ(ዮሐ.1:1) ሰማያዊዉን ህይዎት በራእይ መልእክቱ ይሳየን።ምድራዊ ሞትን ያልሞተ።ክብሩ እጅግ የበዛ ዮሐንስ ፈጽሞ የአምላክን ክብር ለመልአክ አሳልፈዉ አይሰጡም።ዮሐንስስ መልአክ መሆኑ ጠፍቶት ነው? እንዲህ እንዳንል ከፍ ብሎ ባሳየኝ በመልአኩ እግር.. ይላል።ዮሐንስ አንድ ግዜ ብቻ አይደለም ለመልአኩ የሰገደለት ቀደም ብሎ በራእ.19:10 ሰግዶለታል።እንዴት ሁለት ገዜ ተሳስቱአል ይባላል? ለነገሩ አልኩ እንጂ ሶስተኛም ቢያገኝዉ ይስግድለታል ምክንያቱም ዮሐንስ ክርስትያናዊ ግዴታዉን እየተዎጣ ነዉና።ዕብ.13:7 "የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው"።የቀደሙት እነማን ናቸው?? ዳዊት ሎጥ ዳንኤል ጌዲዮን ወዘተ...የእነዚህን ፍሬ መመልከት መልካም ነው ፍሬያቸው ያማረ ነው።ዮሐንስ እነሱን መስሎ ሰገደ።ምክንያቱም ቅዱስ ዮሐንስ ለመላእክት እንደሚሰገድ ያውቃል ከቀደሙት አባቶች ተምራልና [ኢያ.5:13_15... ዳን.8:15_17....ዘኁ.22:31]።መልአኩም የጌታን ምሳሌ ተከትሎ እራሱን ዝቅ አደረገ።ዕብ.2:9 ።

    ትምህቱ ይህ ነው እራስን ዚቅ ማድረግ እንጂ ስግደት ይፈቀዳል ወይም አይፈቀድም ለሚል መልስ አይደለም።ለምሳሌ አንድ ትልቅ ሰው ቤታችን ሲመጣ ከወንበር ብድግ ስንል አይገባም ተቀመጡ ቢለን ሌላ ጊዜ ቢመጡ አይገባም ብለውናል ብለን ከወንበራችን አንነሳም? ዮሐንስም ያደረገዉ ይህንኑ ነዉ።ስለዚህ ለመልአክ የሚሰገደው የአክብሮት ስግደት መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል።ነገር ግን ዮሐንስ በክብሩ ታላቅ ስለሆነ መልአኩ እኔም እኮ ባርያ ነኝ አትስገድልኝ ብሏል።እንደዉ ለማስረዳት ያህል እንጅ ስግደት እንኳን ለመልአክ ለሰውም ይሰገዳል።ዘፍ.23፡12 “አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ ...”ዘፍ.23፡ 7 “አብርሃምም ተነሣ፥ ለምድሩ ሕዝብም ለኬጢ ልጆች ሰገደ።”ዘጸ.18፡7 “ሙሴም አማቱን ሊገናኝ ወጣ ሰገደም ሳመውም...”ይልብሃል። አብርሃም ለኬጢ ልጆች የአክብሮት ለእግዚአብሔር የአምልኮ ስግደት እንደሚያስፈልግ ጠንቅቆ ያዉቃልና ።አብርሃም የአምላክን ክብር ለሰው አሳልፎ የሚሰጥ አይነት ደካማ ሰው አይደለም(እነደዚህም ዓይነት ስህተት አይሰራም)።እነደዚህስ ተብሎ አልተጽፈም “ራእይ.3:9 እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ”።በዚህ ጥቅስ አምልኩ ነው ያላቸው ወይም አክብሩት ???

    እንዲሁም 1ኛ.ዜና መዋ.29:20 "ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ።አምላካችሁን እግዚአብሔርን ባርኩ አላቸው።ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔርና ለንጉሡ ሰገዱ"።ለእግዚአብሄር የአምልኮ ለንጉሱ የአክብሮት ስግደት እንደሚገባ ዳዊት አበክሮ ይናገራል።ታዲያ የዘመኑ ሰዎች ምን ነካቸዉ ትህትና ምነዉ ከንሱ ጠፋ??? እንግዲህ ምን እንላልን በመንፈስ ቅዱስ የተደርሰዉ የእግዚአብሄር ቃል መጽሃፍ ቅዱስ ለቅዱሳኑ ስግደት እንደሚገባ ስላስተማረን እንሰግድላቸዋለን።የአምልኮ ስግድት ግን አልፋና ኦሜጋ ለሚባል ይህን አለም ካለመኖር ወደ መኖር ላመጣ በፍጥርት ሁሉ ላይ ስልጣን ላለዉ የዘለአለም ንጉስ የጌቶች ጌታ የአማልክት አምላክ የነገስታት ንጉስ ለሚሆን ለአንድ እግዚአብሔር ብቻ!!!

    ==>የቅዱሳን መላእክት ምልጃ እና እረዳትነት አይለየን።
    ፍጥረታት ሲፈጠሩ የአምላክ ልጆች  መላዕክቱ እልል አሉ። ቃል ሥጋ ሆነ  አሁንም የአምላክ ልጆች መላዕክቱም በደስታ ዘመሩ። ቃል ሥጋ ሆነ ማለት ምን ማለት ይሆን? ፕሮቴስታንት ዘመዶቼ እስኪመልሱት እጠብቃለሁ። 

//የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ  አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ//

ይህችን አባባል ያስቀደምነው ዛሬ ያነበቡትን ነገ ደግመው ለሚጠይቁ ሰዎች የሚስማማ በመሆኑ ነው። ጥያቄ፦ ለመላዕክት የክብር ስግደት ይገባል ?ይህስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?

መልስ :- 
ቆርኔሌዎስ "ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል። ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው።እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ።ጌታ ሆይ ምንድር ነው? አለ። መልአኩም አለው። ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።"ሐዋ.10፡3-4

መላእክት ክብራቸዉ አንዳንዶች እንደሚያስቡት አይደለም።መላእክት ግርማቸዉ እጅግ ድንቅ እና የሚያስፈራ ነዉ።ምክንያቱም የአምላክን ስም ይዘዋልና አምላካቸዉን ለብሰዋልና።"በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ።በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።"ዘጸ.23:20 እንዲል መጽሃፍ።ነገር ግን ሁሌም ሲያረጋጉ አየዞዋችሁ አትፍሩ ነው፡፡እኛም የተዋህዶ ልጆች የአምላክነት ሳይሆን የጸጋ( ከእግዚአብሔር የተሰጠ) ክብር ስለምንሰጣቸው አይዞዋችሁ ይሉናል፡፡የጸጋም ስግደት መጽሃፍ ስለሚያዝ እንሰግድላቸዋልን።

ሆኖም አንዳንዶች ስህተት ነዉ ይሉናል።ለመልአክ ይሰገዳል ወይስ አሰግደም? በእርግጥ ብዙ ቦታ እግዚአብሔር የመረጣቸዉ የቀደሙ አባቶች ለመላእክት ሰገዱ ተብሎ ተጽፋል። እንዚህ አባቶች ሲያመልኩ የነበረዉ እግዚአብሔርን ነዉ ነገር ግን ለመላእክት የአክብሮት የጸጋ ስግደት ሰግደዋል ታድያ እነዚህ አባቶች ተሳስተዋል? እግዚአብሔርን አላመለኩም? ያመለኩት መላእክትን ነዉ ይባል ይሆን?።አልተሳሳቱም ምክንያቱም መረጃዉ የተገኝዉ በመንፈስ ቅዱስ ከተደርሰዉ መጽሃፍ ቅዱስ ነዉና ሁሌም እዉነት ነዉ።ሰማይና ምድር ያልፋሉ እንጂ ቃሌ ግን አያልፍም ብሎናልና።ማቴ.24:35።ነገር ግን አንዳንዶች በራእይ 22:8 ያለዉን የእግዚአብሄር ቃል በመያዝ ትከከለኛ ሚስጥሩን ባለማዎቅ ለመላእክት አይሰገድም ይሉናል።ግልጽ ለማድረግ እስቲ ለእያሱ የተገለጠ መልአክ እና ለዮሃንስ የተገለጠዉን መልአክ በማነጸጸር አብረን እንመልከት።

ኢያ. 5 ፡14 “ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ” ለመልአኩ።ራእ.22:8 “በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ” እርሱም፦ እንዳታደርገው አለዉ።ካንተ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ አለዉ ::ለምን? አንዳንድ ወንድሞች ራእ.22:8ን ይዘው ለመልአክት አይሰግደም ይሉናል።ምስጥሩ ምንድን ነው? ለኢያሱ የተገለጠ መልአክ ስህተተኛ ነበር? ለምን አትስገድልኝ አላለውም? ለዮሐንስ የተገለጠውስ ለምን አትስገድልኝ አለ? ሁለቱም ጋ መላዕክት ናቸው ሁለቱም ሰዎች ሰግደዋል አንዱ መልአክ ኢያሱ ሲሰግድለት ምንም አላለም ሌላኛው መልአክ ግን ዮሐንስ ሲሰግድለት አትስገድልኝ አለው።

እስኪ ይህን ተቃዋሚ ወንድሞች በምን ያስማሙታል? የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ 
አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ ማለት ይህ ነው። ለመሆኑ ቅዱስ ዮሐንስ እና ኢያሱ ዛሬ እኛ ካለን እውቀት ያነሰ እውቀት ስላላቸው ነው የሰገዱት? እዉነት ለመናገር ኢያሱ እና ቅዱስ ዮሐንስ በዚያን ጊዜም ቢሆን ለማን መስገድ እንዳለባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ።”እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን"።ኢያ.24:15 ያለ ኢያሱ ሆነ ፍቁረ እግዚእ (የጌታ ወዳጅ የተባለ) የስላሴ ሚስጥ አስፋፍቶ የጽፈ(ዮሐ.1:1) ሰማያዊዉን ህይዎት በራእይ መልእክቱ ይሳየን።ምድራዊ ሞትን ያልሞተ።ክብሩ እጅግ የበዛ ዮሐንስ ፈጽሞ የአምላክን ክብር ለመልአክ አሳልፈዉ አይሰጡም።ዮሐንስስ መልአክ መሆኑ ጠፍቶት ነው? እንዲህ እንዳንል ከፍ ብሎ ባሳየኝ በመልአኩ እግር.. ይላል።ዮሐንስ አንድ ግዜ ብቻ አይደለም ለመልአኩ የሰገደለት ቀደም ብሎ በራእ.19:10 ሰግዶለታል።እንዴት ሁለት ገዜ ተሳስቱአል ይባላል? ለነገሩ አልኩ እንጂ ሶስተኛም ቢያገኝዉ ይስግድለታል ምክንያቱም ዮሐንስ ክርስትያናዊ ግዴታዉን እየተዎጣ ነዉና።ዕብ.13:7 "የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው"።የቀደሙት እነማን ናቸው?? ዳዊት ሎጥ ዳንኤል ጌዲዮን ወዘተ...የእነዚህን ፍሬ መመልከት መልካም ነው ፍሬያቸው ያማረ ነው።ዮሐንስ እነሱን መስሎ ሰገደ።ምክንያቱም ቅዱስ ዮሐንስ ለመላእክት እንደሚሰገድ ያውቃል ከቀደሙት አባቶች ተምራልና [ኢያ.5:13_15... ዳን.8:15_17....ዘኁ.22:31]።መልአኩም የጌታን ምሳሌ ተከትሎ እራሱን ዝቅ አደረገ።ዕብ.2:9 ።

ትምህቱ ይህ ነው እራስን ዚቅ ማድረግ እንጂ ስግደት ይፈቀዳል ወይም አይፈቀድም ለሚል መልስ አይደለም።ለምሳሌ አንድ ትልቅ ሰው ቤታችን ሲመጣ ከወንበር ብድግ ስንል አይገባም ተቀመጡ ቢለን ሌላ ጊዜ ቢመጡ አይገባም ብለውናል ብለን ከወንበራችን አንነሳም? ዮሐንስም ያደረገዉ ይህንኑ ነዉ።ስለዚህ ለመልአክ የሚሰገደው የአክብሮት ስግደት መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል።ነገር ግን ዮሐንስ በክብሩ ታላቅ ስለሆነ መልአኩ እኔም እኮ ባርያ ነኝ አትስገድልኝ ብሏል።እንደዉ ለማስረዳት ያህል እንጅ ስግደት እንኳን ለመልአክ ለሰውም ይሰገዳል።ዘፍ.23፡12 “አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ ...”ዘፍ.23፡ 7 “አብርሃምም ተነሣ፥ ለምድሩ ሕዝብም ለኬጢ ልጆች ሰገደ።”ዘጸ.18፡7 “ሙሴም አማቱን ሊገናኝ ወጣ ሰገደም ሳመውም...”ይልብሃል። አብርሃም ለኬጢ ልጆች የአክብሮት ለእግዚአብሔር የአምልኮ ስግደት እንደሚያስፈልግ ጠንቅቆ ያዉቃልና ።አብርሃም የአምላክን ክብር ለሰው አሳልፎ የሚሰጥ አይነት ደካማ ሰው አይደለም(እነደዚህም ዓይነት ስህተት አይሰራም)።እነደዚህስ ተብሎ አልተጽፈም “ራእይ.3:9 እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ”።በዚህ ጥቅስ አምልኩ ነው ያላቸው ወይም አክብሩት ???

እንዲሁም 1ኛ.ዜና መዋ.29:20 "ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ።አምላካችሁን እግዚአብሔርን ባርኩ አላቸው።ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔርና ለንጉሡ ሰገዱ"።ለእግዚአብሄር የአምልኮ ለንጉሱ የአክብሮት ስግደት እንደሚገባ ዳዊት አበክሮ ይናገራል።ታዲያ የዘመኑ ሰዎች ምን ነካቸዉ ትህትና ምነዉ ከንሱ ጠፋ??? እንግዲህ ምን እንላልን በመንፈስ ቅዱስ የተደርሰዉ የእግዚአብሄር ቃል መጽሃፍ ቅዱስ ለቅዱሳኑ ስግደት እንደሚገባ ስላስተማረን እንሰግድላቸዋለን።የአምልኮ ስግድት ግን አልፋና ኦሜጋ ለሚባል ይህን አለም ካለመኖር ወደ መኖር ላመጣ በፍጥርት ሁሉ ላይ ስልጣን ላለዉ የዘለአለም ንጉስ የጌቶች ጌታ የአማልክት አምላክ የነገስታት ንጉስ ለሚሆን ለአንድ እግዚአብሔር ብቻ!!!

==>የቅዱሳን መላእክት ምልጃ እና እረዳትነት አይለየን።
    Like ·  · Unfollow Post · 3 hours ago
    • Meazi Habeshawit, Moges Abeje, Bright Destiny and 9 others like this.
    • Biruk Feleke 3 amet geta bewalebet wilo baderebet adiro yekalun timihirt yadamete yohannes endet yisasatal? Raeyun yetsafew eko 96 ametemiret gedema new 60'win amet mimenanin min bilo astemare?
      3 hours ago via mobile · Unlike · 1
    • Mezgebe Alem Lisanework kalehiwot yasemalen
      2 hours ago · Like
    • ዲያቆን ዮናስ ዘካርያስ 1ኛ.ዜና መዋ.29:20 "ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ።አምላካችሁን እግዚአብሔርን ባርኩ አላቸው።ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔርና ለንጉሡ ሰገዱ"።ለእግዚአብሄር የአምልኮ ለንጉሱ የአክብሮት ስግደት እንደሚገባ ዳዊት አበክሮ ይናገራል።
      2 hours ago · Like · 4
    • Feker Tsige dn yonas egziabihear abzito yibarkih betam yemifeligewin neger new yagegnehut.kalehiwet yasemalin
      41 minutes ago via mobile · Like
    Options

Posted by ዮናስ ዘካርያስ at 05:13 No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest
Newer Posts Older Posts Home
Subscribe to: Posts (Atom)

እነሆ የአንባቢዎች ቁጥር 115,762 ደረሰ! /አሜሪካ እንግሊዝና ኢትዮጲያ ከ1ኛ - 3ኛ ያለውን ቦታ ይዘዋል/

ከልብ ለምወዳት ሰ/ት/ቤቴ

Promote Your Page Too

ተጨማሪ ማንበብ ይቻላል!

  • ▼  2014 (4)
    • ▼  03/30 - 04/06 (1)
      • ከቀልድ ዓለም!
    • ►  03/02 - 03/09 (1)
    • ►  02/09 - 02/16 (1)
    • ►  02/02 - 02/09 (1)
  • ►  2013 (57)
    • ►  12/29 - 01/05 (1)
    • ►  12/22 - 12/29 (1)
    • ►  11/10 - 11/17 (1)
    • ►  09/01 - 09/08 (1)
    • ►  08/25 - 09/01 (5)
    • ►  08/18 - 08/25 (3)
    • ►  08/11 - 08/18 (3)
    • ►  08/04 - 08/11 (4)
    • ►  07/28 - 08/04 (8)
    • ►  07/21 - 07/28 (9)
    • ►  07/14 - 07/21 (3)
    • ►  07/07 - 07/14 (14)
    • ►  04/07 - 04/14 (1)
    • ►  03/10 - 03/17 (1)
    • ►  03/03 - 03/10 (1)
    • ►  01/06 - 01/13 (1)
  • ►  2012 (89)
    • ►  12/23 - 12/30 (2)
    • ►  12/16 - 12/23 (1)
    • ►  12/09 - 12/16 (1)
    • ►  11/25 - 12/02 (1)
    • ►  09/16 - 09/23 (1)
    • ►  09/09 - 09/16 (1)
    • ►  09/02 - 09/09 (2)
    • ►  08/26 - 09/02 (2)
    • ►  08/19 - 08/26 (37)
    • ►  08/12 - 08/19 (2)
    • ►  08/05 - 08/12 (1)
    • ►  07/29 - 08/05 (2)
    • ►  07/22 - 07/29 (1)
    • ►  07/08 - 07/15 (1)
    • ►  07/01 - 07/08 (2)
    • ►  06/24 - 07/01 (1)
    • ►  06/17 - 06/24 (2)
    • ►  06/10 - 06/17 (1)
    • ►  06/03 - 06/10 (1)
    • ►  05/27 - 06/03 (2)
    • ►  05/20 - 05/27 (1)
    • ►  05/13 - 05/20 (1)
    • ►  05/06 - 05/13 (2)
    • ►  04/22 - 04/29 (1)
    • ►  04/15 - 04/22 (1)
    • ►  04/08 - 04/15 (2)
    • ►  04/01 - 04/08 (1)
    • ►  03/25 - 04/01 (2)
    • ►  03/18 - 03/25 (1)
    • ►  03/11 - 03/18 (1)
    • ►  03/04 - 03/11 (1)
    • ►  02/26 - 03/04 (2)
    • ►  02/19 - 02/26 (1)
    • ►  02/12 - 02/19 (1)
    • ►  02/05 - 02/12 (1)
    • ►  01/29 - 02/05 (1)
    • ►  01/22 - 01/29 (1)
    • ►  01/15 - 01/22 (2)
    • ►  01/08 - 01/15 (1)
    • ►  01/01 - 01/08 (1)
  • ►  2011 (27)
    • ►  12/25 - 01/01 (2)
    • ►  12/18 - 12/25 (3)
    • ►  12/11 - 12/18 (2)
    • ►  12/04 - 12/11 (2)
    • ►  11/27 - 12/04 (7)
    • ►  11/20 - 11/27 (11)

የልጅ ዮናስ ብሎግ አባል ይሁኑ!

በባህላችን ምግብ ለብቻ አይበላምና ይህን ምግበ ነፍስ ለጓደኛዎ ያስተዋውቁ!. Ethereal theme. Theme images by MichaelJay. Powered by Blogger.