Wednesday, 31 July 2013

ፕሮቴስታንት ሆይ ከ0-18 ዓመታችሁ አህዛብ ናችሁ?





አህዛብ ማለት እንደ አብርሐም አባት እንደ ጣዖት አምላኪው ናኮር ፈጣሪውን የማያውቅ ማለት ነው። አህዛብ ማለት ጣዖት የማያምን ፈጣሪውንም የማያምን እምነት የለሽ ማለት ነው። ፕሮቴስታንት ህጻናት ጌታን ያውቁታል ግን አያምኑትም! አህዛብ ናቸውና! አንድ በሽተኛ መድኃኒቱን እያወቀ መድኃኒቱን እስካልተቀበለው ድረስ በሽተኛ ነው። መድኃኒቱን ማወቁ ብቻ አያድነውምና! አንድ ጴንጤ መድኃኒት የተባለውን ኢየሱስን አውቆ ነገር ግን አያምንበትም። በሽተኛው መድኃኒቱን እስከሚቀበል ድረስ በሽተኛ እንደሚባል ሁሉ ኢየሱስን እስከሚቀበሉ ድረስ እንደ በሽተኛው ተቆጥረው አህዛብ ናቸው ማለት ነው። መድኃኒቱን አውቀዋለሁ ግን አድጌ ወንጌል ካላነበብኩ ሰው ካልሰበከኝ አላምነውም ይላሉ። ፕሮቴስታንት ልጆች ሲታመሙ ነፍስ አውቀው ስለ መድኃኒቱ አንብበው ሰምተው ነው መድኃኒቱን የሚቀበሉት? እኔ የምለው 2 ዓመት የሆናቸው ፕሮቴስታንት ህጻን ሳያምኑ የሚሞቱት እጣ ፋንታቸው ምን ይሆን? ሄሮድስ የገደላቸው 2 ዓመት የሞላቸው ህጻናት ደማቸው ደመ ጥምቀት ሆኖ ድነዋል። እነዚህ ህጻናት ፕሮቴስታንት ቢሆኑ ክርስቶስን አያምኑምና እጣ ፈንታቸው ምንድን ነው? ክቡራን ሆይ ነፍስ እስከምታውቁ ድረስ አህዛብ ናችሁ እንዴ? ፕሮቴስታንት ልጆች እንዳሉ የማያምኑ አህዛብ ናቸው ለካ? ከልጅነት ጀምሮ ሁሉም ያውቁኛል ያለ ፈጣሪ የህጻናትም አምላክ ነው! እባካችሁ ሰውን ሳይሆን የገዛ ሕሊናችሁን ስሙ። ከልጅነት ጀምሮ ሁሉም ያውቁኛል ብሏልና ህጻናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው እንዳለ እነሆ ህጻናቱ ሆሳዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ። የዘመናችን ሰዎች ደግሞ እነዚህ ሁሉ ህጻናት ጌታን አያምኑም አሉን። እንግዲያውስ ክርስቶስን ካላመኑ ልጆቻችሁ አህዛብ ናቸው አይደል? ፕሮቴስታንት ሆይ ከ0-18 ዓመታችሁ አህዛብ ናችሁ?

http://yonas-zekarias.blogspot.co.uk/

No comments: